*የብሔራዊ መታወቂያ (ፍይዳ) ምዝገባን ይመለከታል*
ትምህርት ሚኒስቴ ከሰኔ 2017 ጀምሮ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ለሚወስዱ ዕጩ ተመራቂዎች እና ዳግም ተፈታኞች ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ እንደቅድመ ሁኔታ መቀመጡ ይታወቃል። በመሆኑም በተቋማችሁ እየተማሩ ያሉና ከዚህ ቀደም ተፈትነው ማለፊያ ውጤት ሳያሟሉ የቀሩ የተቋማችሁ ተፈታኞች ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ምዝገባ እንዲያካሂዱ ባሉት አማራጮች በሙሉ በቂ መረጃ እንድታደርሷቸው እናሳስባለን።
*ማሳሰቢያ፡*
1.ለመጀመሪያ ዙር ተፈታኞች መረጃ ማስገቢያ ሲስተም (
https://eap.ethernet.edu.et ) ላይ ማስተካካያ ስልተደረገ በቅርቡ ORIENTATION የምንሰጥ ይሆናል።
2.ዳግም ተፈታኝ አመልካቾች ከሚያዝያ 14/2017 ዓ.ም -- ግንቦት 05/2017 ዓ.ም ድረስ ከላይ የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት በ
https://exam.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ ይችላሉ።
3.ዳግም ተፈታኞች የአገልግሎት ክፍያ የሚከፍሉት በቴሌ ብር በኩል ብቻ ነው።
*የኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር*