ጭለማ ውሃ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Bloglar


በ እንቅልፍ ስካር በሌሊት ወደ ተከፈተው ቻናሌ እንኳን ደህና መጣችሁ ( ለጥ ብዬ እጅ ነሳሁ)
ያለውን የሰጠ ንፉግ አይባልም... ይኸው።
ሃሳብ እና አስተያየታችሁን በዚህ በኩል
👇👇👇
@wuhachilemabot

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Bloglar
Statistika
Postlar filtri


ስለት ሲወጋህም ሲወጣልህም እኩል ይቆርጥ የለ?

እና ስትወጋ ነው ይበልጥ ያመመህ ወይስ የተወጋህበት ሲወጣ?... ስትመጣ ያኔ የተወጋሁ ጊዜ እኔም ከዚህ በላይ አያምም ብዬ ነበር መች የፈጠነ እንደምትሄድ አወቅኩና

ማጣት ከማግኘት እኩል ሲያመኝ የመጀመሪያ ነው በምን አይነት አመክንዮ ላስረዳ ይሄንን?

የሄደች ሰሞን ተንቦጃቦጅኩ መልኬ ሰፋኝ... የመጣች ሰሞን አፌን ከፍቼ እሷን ሳስብ እውል ነበር ሁሉም ነገር እያለፈኝ ፣ ከሃሳቧ ውጪ ገለባ ሆኖብኝ

የሄደች ጊዜ ድጋሚ አፌን ከፈትኩ ከህመሙ ውጪ ምንም አልታይህ አለኝ ፤ ለሰው አካላዊ ህመም እና ስሜታዊ ህመም አንድ ናቸው አሉ... ኮቪድ ከተረሳ በኋላ የሚገርም ጉንፋን እሽት አድርጎኝ ነበር ይሄ ከሱ አይብስም ግን ያስናፍቃል ፤ ጭንቅላቴ ደንዝዞ አስር ጊዜ እንዳትመላለስበት... ይመኛል

ራሱን ገርፎ ራሱ አለቀስ አለች

መች የሷ ጥፋት ሆነና እኔው ነኝ እንጂ ቅዠታሙ ሳታውቀኝ አግብቼ ወልጄ ከብጄ የኖርኩ ሚስቴ ያልኳት እኔ ነኝ እንጂ ሳትመጣ እንደመጣች አብራኝ ሳትሆን እንደተወቺኝ ነገር ራሴን የጣልኩ እንጂ

እሷ ምን አጠፋች ፤ ይሄ ለየት ያደርገኛል ብዬ ስለማስቦ ራሴ ላይ በግድ የጫንኩት ሸክም መሰለኝ።



ውሃ

https://t.me/wuhachilema


ልቤ የተሰበረ ይመስለኛል ፣ እርቦኝም ሊሆን ይችላል... አንዱን ከአንዱ በምንስ ይለያል.. ማጣት ማጣት ነው... ነገር አታወሳስቡ


ያኔ ፈላ እያለሁ ጉልቤው የሰፈሬ ልጅ እየኮረኮመ የገዛሁትን ብስኩት ተቀብሎኝ አይኔ እያየ ሲበላ፣ ሌላ ቀን ደሞ ስንት ጊዜ ፈጅቶብኝ የሰፋሁትን ኳስ አልሰጥም ብዬ ሲገግም... life bully ማድረጓን ጀመረች እላችኋለሁ ፤ ከዛ ቀድሞ እሪሪሪሪሪሪ እያልኩ ሄጄ ታላቅ እህቴን ምን እንደሆንኩ ብነግራት የታል አሳየኝ እያለች በአንድ እጇ አንጠልጥላ ሰፈር ለሰፈር ታዞረኝ ነበራ... ልጁ ሲገኝ ወይ ተቆጥታው ወይ መትታው ( እንደ እድሜውና አቅሙ ይወሰናል) የተቀበለኝን ታስመልስልኝ ነበር


ማን ያስመልስልኛል?



እኮ ፣ ሲርብህ ማለቴ በጣም ሲርብህ እጅህ መንቀጥቀጥ ሰውነትህ በላብ መዘፈቅ ይጀምራል ሙቀት ሙቀት ይልሃል ልብህ ከደረትህ ልትወጣ ትር ትር ስትል ይሰማሃል... ያቅለሸልሽሃል... ልብህም ሲሰበር እንደዛው ነው

እርቦኝ በሆነና በበላሁበት... መፍትሄ ያለው ነገር ደስ ይላል በራስ ጎትትተው ያመጡት ኮተት ማለቂያ የለለው ቅራቅምቦ ምን ይደረጋል?... ምንም

ያም ሄደ ያም ተወሰደ... ያኛውንም ተነጠቅክ... ተደባድበህ የማታስመልሰው አውርተው የማታሳምነው ሲሆን ምን ትያለሽ?... ለምነሽ ጠብ ሳይል ሲቀር... ምን ይባላል?... እኮ ፨

#ውሃ

@wuhachilema


ልብስህ ያንተ አይደለችም... ከሆነ ቦታ ከሆነሰው የተገፈፈ ከሆነ ነገር የተወሰደ ከዛም በፊት የተፈጠረ ነው... ተፈጥሯል ብለህ ምታምን ከሆነ
ስጋህ ያንተ አይደለችም... ነብስህ ያንተ አይደለችምና በሷ ላይ የማዘዝ ስልጣን የለህም ፤ ፅድቅህ ያንተ አይደለም የፅድቅ ባለቤት የፈጣሪህ እንጂ
ምግብ ብትል ሃሳብ ምንጫቸው ቢጣራ ካንተ አይደሉም

ይሄ ሁላ ያንተ ሳይሆን ካንተ ሳይሆን ሃጢአትህ ያንተ ብቻ መሆኑ ምንሼ

ከሌላው ቀን በተለየ ፈጣሪ ጨካኝ መስሎ የተሰማኝ ለምንድነው ደሞ በቤቱ ተቀምጬ ይሄም የኔ ቤት አደለም የሱ እንጂ... ከሱ ውጪ ያሉትም የባሱ ነጣቂዎች ሆነው ታዩኝ... ሞት ህይወትህን መጥጦ ነብስና ስጋህን ሊለይ ያሰፈስፋል... እንቅልፍ አንተን ዘርሮ አዕምሮህን በህልምና ቅዠት ሊጫወትበት ሲንጥህ ይውላል

ዞር ብትል እሳት ዞር ብትህ እሾህ ይታይሃል ነጣቂ የበዛባት ሰጪም የሱ ያልሆነውን ሊሰጥ የሚቋምጥበት ባለቤት የምትለውም አምላክህ ተደብቆ እንደፈለግን እንድንሆን ትቶናል እንዴ እስክትል ድረስ ብዙ ነገር የተተራመሰበት ዘመን ላይ ቀን ላይ ራስህን ታገኘዋለህ

#ውሃ


@wuhachilema


።።።።።።።፡።።።።።።።።።።።።


A question... የ ፓርቲ አባል መሆን ከሞት ያስጥላል እንዴ? ፣ ተው ፣ ምናልባት የሆነ ከለላ ስንፈልግ የሚጋርደን

ጥግ ብቻ ይሆን እንዴ ይሄ ሁሉ ኮተት? ፣ ምናልባት ልጅነት ይሆናል እንዳልኖረ እንዳላሰለፈ ሰው ይሄን እንዴ ፣ ቢሆንስ ምናምን እያልኩ የሚያፅፈኝ። ምናልባት ይቺን ምናልባት ሙጥኝ ያልኩበት የምሸሸግበት ጥግ ይሆናል ከራሴ ጋኔኖች

እና ስትደበቅ የንጉሱ ልጅ ነኝ አለቺን በሷ ሚዛን ራሴን ልመዝን ቃጣኝ የ... የማን ልጅ ነኝ ልበላት የመገበኝ የቆሻሻ ገንዳ? ያሞቀኝ አፈር የተንተራስኩት ድንጋይ ልጅ ነኝ ልበላት? ግን ይሄ ምኑ ያኮራል? እንደማያኮራ እንዳያኮራ አድርገው ነው የነገሩን ወርቅ ውድ ነዋ

ልብሷ ያምር ነበር... የኔ ተበርጥቆ ፣ ሚገርመኝ ያየኋት መስሎኝ ራሴን ስገመግምባት ፍትህ የሌለው ለመሰለኝ አለም ማብራሪያ ስጠብቅባት ነበር... አላየኋትም።

ቁርስ ምን እንደበላች ስትነግረኝ ፣ የማላውቀው አይነት የምግብ ዝርዝር ስትጠራ ጊዜ... ሆዴ ጮኋል ባይጣፍጡስ ብዬ አላሰብኩም... ፋፍታለቻ እንዴት የማይጣፍጥ ምግብ ሊያፋፋ ይችላል ደሞ ምግብ ምግብ ነው... ይጣፍላል

ለምን... ምግብ ነዋ።

ማታ ለ እራት እሳቱን ከበን ስንደረደር ከሰማሁት መሃል የሃብታም ቤት ምግብ አይጣፍጥም። ለምን? ሃብታም ስለሆኑ 😂😂😂 የደሃ ምግብ ይጣፍጣል

ለምን? እንጃ... ግን ከረሃብ በላይ ምግብ የሚያጣፍጥ ቅመም ከየት ይመጣል? ፤ ኧረ ደሞ ሌላ... ሃብታም ተኝቶ አያድርም አሉ... ስለሃብቱ ሲያስብ ሲጨነቅ ሲገላበጥ ይነጋበታል አሉ ፤ እኔ እዚ አፈሩ ሲቆረቁረኝ ብርዱ ሲገሸልጠኝ ሳልተኛ የማድረው እንዴት ያለ ሞጃ ብሆን ነው እእ።

ደሞ የሃብታም ልጅ ገገማ ነው አሉ ፣ ድህነት ነቃ ያደርጋል እንዴ እእ? ያልበላ እና ያልተማረvs የበላ እና የተማረ

እሰይይ... አሁን ማን ይሙት ቁራጭ ድንች ካለው ሾርባ እና ከጥሩ ስጋ የቱ ይጣፍጣል? ፣ ስጋ ባቄላን ይተካል 😂😂😂 no shit


ውሃ


@wuhachilema


አርጅቻለሁ

ስለ ነገ ምን ታስባለህ?... የ አጭር ጊዜ እቅድ? ( አይ ይቺስ ቀልድ ናት)... ግን በዚህ አመት ምን ለማድረግ አሰብክ?... ብዙ ጥያቄ... ሰው እንኳ ባይጠይቅ ሊጠይቁ ይችላሉ ብሎ የሚያስበው ጭንቅላቴ ቃፊርነት ቆሞ ይሞግተኛል... አሁን ስለ እነርሱ ጥያቄ ምን አገባውና ነው እ?... ስለማናውቀው ነገ ፣ ነገ ላይ ከዛሬው እኛነታችን ለምንሻል ነገር... ዛሬ ላይ እናቅዳለን

በጊዜ ክፍተት ያለውን የኛን እድገት እና ለውጥ አንፈልገውም መሰል... ዛሬ ላይ የነገን እናቅዳለን... ጠዋት ስነሳ አራት እጅ ኖሮኝ እንደማልነሳ በምን አውቅና ነው... ወይም አህዮች ቅኝ ግዛት ገዝተውን ለ ጠዋት የወፍጮ ቤት ጭነት በ ዱላ ተነርቼ እንደማልነሳ በምን አውቄ ነውና ነው?

ወይስ ያለፈ ልምድ ለነገ ዋስትና ይሆናልና ነው?... እርጅና ሲመጣ አዕምሮ ይላሽቃል እና የኔውም ሊወድቅ እንዳለ ዛኒጋቢ ግጣሞቹ ላይ ያቃስታል... እንደዚህ።

ግን አርጅቻለሁ... በማይታወቅ ነገ ከ ነገው ባልበረታሁ እኔ አስልቼው እንዳልኖር ደብሮኝ... ዛሬ የሚባለው ጊዜ ደሞ አልጨበጥ ብሎኝ በ ትላንት ውስጥ በምቾት ከተንፈላሰስኩ ስለቆየሁ አረጀሁ...
ባለፈው ነገር ውስጥ ከሚኖር በላይ ያረጀ ሰው አለ?

ጥያቄ ነው

ውሃ

https://t.me/wuhachilema


-

ያንተ ጀግና ማነው?... እንጃ ብዬ ለጠየቀቺኝ ጥያቄ አንድ ሰው አንስቼ ጀግና አደረኩት not my hero, but a hero

ምናልባት አጉል ሃቅ ጠልፎ ይጥል ይሆናል... ባንተ ነጭ ነጠላ አልፈው ቆሻሻ እድፍ ካለብህ ሊያዩ ይቻኮላሉና
ባንተ እውነት ግላጭ ሾልከው ገብተው ውሸትን ያነፈንፋሉና

ግትርነታችን ጥሎን የጠፋ ቀን ግን እንጃ...
ወደ ቀድሞ ነገር ስመለስ... ያንተ ጀግና ማነው ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄዎች ብዙ አይነት ሰው የጠቀሱ ገፋ ሲል ደሞ እኔው ራሴ ያሉ... ሲራቀቁ( በነሱ ቤት) my future self ያሉ አሉ።

የኔ ጀግና ማነው?

የቻለ ያሸነፈ ያልተረታ የመሰለኝን ሰው ጀግና ብዬ ብጠራ ብዙ ስም ይመጣልኛል ግን ሁሉም ወድቀው የተረገጡበት ታሪክ አላቸው... ሁሉም ሌላ ቦታ ቁስለኛ የሆኑበት ገፅ አላቸው
እና ማን ጀግና ይባል

ወይ እንደ ጀለስ እናት ጊዜ ነው ጀግና ብዬ ለሱ ላሸክመው ይሄን ሁሉ ክብር?... ወይስ ተስፋ የማይቆርጡ ናቸው ብዬ motivational speech ላድርገው?

ግን ጀግና ጀግና ነው.... በቃ
ወተት ነጭ አይደለም ነጭ መልክ አለው እንጂ

ስሜት ይሰጥ ይሆን?

ንፋስ

https://t.me/wuhachilema


Maybe it's comforting to be around people that need u

Maybe that's why people bore children
maybe that's why

እንግዳ ሃሳብ ነው ሸክም መውደድ ፣ መሄጃ የሌለው ሸክም ይዞኝ ነው ብሎ ለማሳበብ
እኔ ጠንካራ ደሞም ሸክሜ ብዙ ብሎ brag ለማድረግ
ደሞ
ደሞ
ለለሌላ
ሌላ

ደሞ ለጡንቻ ነው... ሸክም ህም ያጠነክር ይመስል... ልብ ጡንቻ ያወጣል እንዴ?... ለምን ይሆን?... ጥጋብ


፨ንፋስ


@wuhachilema


ርዕስ ነበረው

አታውቅም ፣ አያውቅም ላለመባል ያክል የሚዋልሉ የመልስ ጥላዎች በጭንቅላቴ ውስጥ አሉ... ግን መሬት ላይ አንጥፎ የመተኛትን ያክል ምቾት አይሰጡም

መልሶች... የቆጥ አልጋ ከፍ ብለው የተሰቀሉ... በ እንቅልፍ ልቤ ብንቆራጠጥ የምወድቅ የምወድቅበት የሚመስለኝን ሆኑብኝ... የመልስ ጥላ።

ምን መሆን ትፈልጋለህ ሲባል የምንመልሰው አራዳ የሚያስመስለን መልስ አዘጋጅተን አስቀምጠናል.. ጥፍጥ ካለ backstory ጋር ግን ያም ጥላ ነው... ጉም የማይጨበጥ

ግን እየኖርን ነው... ለምን እንደሆነ እንጃ ምናልባት ጥላውን ተከትለን ባለ ጥላውን አካል አልፎ ብርሃኑን አልፎ የብርሃኑን ምንጭ እንድናገኘው ይሆን ይሆናል

ግን የኛ ህይወት ጠዋት ተፈጥረው ማታ እንደሚሞቱ ነብሳት አለመሆኑን በምን እናውቃለን?... ፈጣሪ? ሃይማኖት? ጉንዳኖች የተቸነከረላቸው ክርስቶስ ፣ ቁርዐን የወረደለት መሐመድ ቢኖራቸውስ?

የጠየቀ አለ?

እንቅልፍ ቆንጆ ነገር ነው ለማንኛቸውም

፨ አለቀ፨
ውሃ
@wuhachilema


፨ ይፈንዳ ፨



እስር... እግረ ሙቅ

አው ፣ እየነጠረ እየጠገ ቢያስቸግር ይታሰራል ሃሳብ ነዋ ከዛ እሱ ሃሳብ እንዳይወጣ ስንጠብቅ እንውላለን እናድራለን... እኛ እስር ቤት ጠባቂ አሳሪ

ያ ደግሞ ታሳሪ ፣ ቀን የጠመመበት
አቤት ያሰርን መስሎኝ ያሰርኩ መስሎኝ ባሰርኩት አስተሳሰር ሃሳብ የተተበተብኩ በያመልጣል ቅዠት ራሴው የታሰርኩ እስረኛ... የ እስርቤት ጠባቂ
አሳሪ 😁

ከ ታሳሪ መሃል ካቦ ይመረጣል... ካኪ ነው የሚለብሱት የወየበ ቢጫ እንበል ፣ አልን ( የስብሃት ስታይል ናት ፣ ይሜ ማን ከ መሞትህ በፊት) እና ካቦው ወይ ኮት ይደርባል ወይ ሱሪ ይቀይራል..
ይሄ ጨቋኝ አሳብ ሌሎቹን መስመር የሚያሲዘው ነው ፣ አጭር ዱላ ( ቆመጥ ነው የሚባለው ወገን?... አማርኛ ከዳን እኮ ፣ ስንከዳው ጊዜ አትልም?)
ይሰጡታል..
እኛ ደሞ ለ ካቦ ሃሳባችን ምን አይነት ዱላ ሰጥተነው ይሆን?

እና የኔ ነጥብማ ፣ አስረህ ያስቀመጥከው አሳሪህን ፍታው ነው

ያበጠው ከፈነዳ ከ አሁን አሁን ፈነዳ አልፈነዳ እያሉ ሚፈሩት ምን እበጥ አይኖራል?
እ.በ.ጥ.
ፈንዳ ያለው ቀን ሊፈነዳ ነገር ፣ ጠብቀን ምናድነው ይመስል... እንደው ግሩም እኮ ነው ወገን

ከ ራስህ ጠጉር አንዲቷን ነጭ ወይም ጥቁር ልታደርግ አትችልም ተብለን...( እዚ ጋር ስለ ፀጉር ቀለም አይነት የሚያወራ እኮ አይጠፋም) እኛ ያንን የሚያክል እበጥ ከ መፈንዳት የምናስቀር ይመስለናል

ይፈንዳ ኣ

ውሃ

@wuhachilema


እነሆ ድጋሚ ተጀመረ

፨ የ እለት ሃሳብ ፨


ከሆነ ነገር አመልጥብ ብዬ ጭልጥ የምልበት እንቅልፍ ነበረኝ

ከ ድብርት ንዴት ጭንቀት ረሃብ... ሲርብህ እየቀሰቀሰህም ባልሰማ ትተኛበታለህ... ከ ፍርሃት ከ ሃላፊነት ከ እውነት ያስመልጠኝ ይመስል የምሸሸግበት ጥግ ነበረኝ


እንቅልፍ


አገኘሁ ብዬ ስለጥጠው እሱም እንደ እውነተኛው አለም ትክክለኛ መልኩ መገለጥ ተጀመረአ... ፈላ እያለሁ ላይፍ ቀላል ነበር... ሆዴ ከሞላ እና ጭንቅላቴ ላይ የመጣውን ካደረግኩ እንደኔ አይነት ስኬታማ ና ደስተኛ ሰው አልነበረም... ሃሳቤ ትንሽ ነበርና ለደስታ ቀረብኩ

ቀረብን እንጂ... ተጠጋጋን።

ከዛ መማር ይመጣል ከዛ እኚ ድሪቶ የሆኑ የፍላጎት የምኞት ዘባተሎዎች ጫንቃችን ላይ ይወድቃሉ... የሆነ ቀን የሚያናድደንን አስተማሪ ልክ ለማስገባት እንደምንችል ለማሳየት ስንጣደፍ እንገኛለን
እኛው ነና

ማን የዚህን ያክል ውስብስብ ይሆናል ብሎ አሰበ?... ግን ሆነም... ተተበተበና ድሪቶ ሲበዛ ነጠላ ፍለጋ ወደ እንቅልፍ የሚባል ሃገር ስደት... ኧረ አገር አቋራጭ ጉብኝት ጀመርና

ጉብኝቱ ሲበዛበት...
ምን ሆነ? አው እንቅልፍ እንቅልፍ መሆኑ ጠፋ ( እዚህ ጋር የሚገርም እንቅልፍ ይዞኝ ሄደ)

* በሌላ ቀን *

እንቅልፍ ሲጥለኝ ህልም ቀና አድርጎ ይለጋኛል... አናቴን ነዋ ሊያውም ፣ ቀን ቀን ስሰራ ሳስብ የዋልኩትን በእንቅልፌ መድገም... እኔን ብሎ ባለ እንቅልፍ ደሞ ህእ... በኔ ቤት እኮ አረፍኩ ብዬ መተኛቴ ነው... ጭራሽ የማይፈለጉ ሰዎች አጉል ጣልቃ እየገቡ የመድረክ ድራማ ይሰሩብኝ ጀመር... በዛው በ ኑሮው ላይ ነውኮ ደሞ

እና በንዴት እየራገምኩ ከ እንቅልፌ... ማነው ከሌላኛው ላይፌ እነቃለሁ... ቲሽ
ለዚህ ለዚህማ ቆሞ ማደር በስንት ጣዕሙ ፣ እንቅልፍ ግን ጥጋበኛ ነው አልተኛም ስትል ከዚህ አለም ያሰናብትሃል... ይኸው አሁን ራሱ አይኔ ላይ ተቀምጦ አፍንጫህን ሳልሰብረው ይሄንን ችክቸካ ትተት ተጋደም ይለኛል

ይመቸው

ለጥጥጥጥጥ

፨ውሃ

@wuhachilema


ከተረት መፅሐፍ ነው




ወንዙን ተከትለው ብዙ ዛፎች በቅለዋል ምቾት አሞቅሙቋቸው

ሰፍተው

እና እንደተወለዱት ሁሉ አንድ ፊላ ተወለደ... አጥንት የሌለው ልፍስፍስ ብለው የፈረጠሙቱ ሳቁ... ( ዛፍ ሲስቅ ይታይሽ እንግዲ) ያ ፊላ የቀጠነው ቀስ እያለ ማደጉን ተያያዘ... ልደግ ብሎም ባይሆን ለቅጠል ሌላ ምን ግብር አለውና? ፣ ግን ወቅት ተቀየረ... ያዘናፈሉትን ቅጠላቸውን የሚያውለበልቡበት የነበረው ንፋስ ጉልበት ጨምሮ ከስራቸው ሊነቅላቸው መታገል ጀመረ... አጥንት የሚሰብር መጣ ፤ ምቾት ከውስጥ በልቷቸው ኖሮ የሰባው አካላቸው ከ ትንሽ ስር እንደቆመ ከማየታቸው ንፋሱ ይዟቸው ሄደ

ፊላ ቀረ... ንፋሲ ሲመጣ እየሰገደ እየተጋደመ ፣ የ አጥንት ዘመን ያለፈበት ይመስላል።

ውሃ

@wuhachilema


፨ የአለም ምፀት ፨


(ሃሳብ በ እኔ አይደለም)
ምፅ የተባለበት... ደሞ ምናገናኛቸው... እዛ ጋር እዝን ብሎ እዚህ ጋር ታዝኖለት... የውሸት? ደሞ አለሁ ብሎ ወልዶ
አለሁ ብላ አልምዳ
አለሁ ብሎ ተላምዶ ሲያበቃ ምፅ ሃዘኔ ብርቱ ነው ግን አፍንጫሽን ላሺ
....አዝናለሁ ግን ገደል ግባ
ሃሳብ ከኔ አደለም... የሰው ወርቅ አያደምቅ ሆኖ ( እንደ ቀለም ቢፃፍበት መሰለኝ... ስለ ወርቃማ ብዕር ሊያወሩ ፈልገው ይሆን? እንጃ) ሃሳቡ በምላሴ ላይ ሲፈረካከስ በ ጣቴ ውስጥ ሲንሸራተት ይታወቀኛል... አለው ብሎ እልም ታይቶ እንደሚጠፋ የወቅት አካል ነኝ ብሎ የገገመ ደሞ አዘንኩ ብሎ ሙድ የሚይዝ እያለ በምኑ ሃሳቤ ይረጋጋ

እሱም አለሁ ብሎ ረግቻለሁ ብሎ አሁን ሊለሰልስ አሁን ሊዘናጋ አሁን ቋሚና ተራማጅን ሊለይ መስሎ የተሰናዳ... አዝናለሁ ብሎ እልም አላለም? በ እውነት ሃሳብም ይከዳል እኮ... እሷን አምኖ መሰለኝ... ከ መቀመጥ መራመድ ይሻላል ብላ ልቡን አሮጠችው... በሳሩ ሜዳ ላይ እየቦረቀች ሲያያት... ከአድማስ ደርሼ በፈጣን እግሮቼ ፀሐይን እነካለሁ ስትለው ጊዜ... የምድር ጥግ ደርሼ ምርጡን ሳር አጣጥማለሁ ስትለው ቅጠል ባይበላም አፉ በምራቅ ሲሞላ ታውቆታል... አሳመነችው... ከዛ እንሂድ ብላ መጣች አንድ ቀን

ከ ስሩ ተገንጥሎ እወጣ ሲል ተፈጥሮ ሳቀችበት... ዛፍ እና ፍየል አብረው ሊሸፍቱ ብላ ምፅ አለች... ከዛ ከት ብላ መሳቅ
ተታለለ... የሱ እግር ከተተከለበት ቆፋፍሮ ከ ስሩ እርጥበት አዝሎ ካረሰረሰው መሬት የወጣውን ሳር የጋጠችው ፍየል አንድ ህብረት እንደሌላቸው ሲያውቅ
የተተከለው እሱ በአለም ምፀት ሳቀ

ሌላ ምን ይባላል?... እ?
ከት... ደሞ አሁንም ፈገግ አለች በዥልጥ ሃሳቡ ውስጥ ስትንፈላሰስ ቆይታ ኋላ ይሄ ገጀራ ተጃጅሎ አጃጃለኝ እኮ ምፅ ብላ መጽሐፉን አጠፈች...

ውሃ

@wuhachilema


፨ ብጣሽ፨

ብጣሽ ቃል ብጣሽ ጨርቅ ብጣሽ እንጀራ

ብጣሽ ሃሳብ... ብጣሽ... ብጣሻም ፤ ብጣሽ ስንጠላ ደሞ... ካልተቀደደ ሙሉ ጨርቅ የተሰራ ይመስል... እድሜ ልክ አዲስ ማይበጠቅ ይመስል... መጣፊያ የሚሆን ብጣሽ አንፈልግ ይመስል... ባንፀባራቂው በቀለማችን በጥንካሬው ስንመካ

አይቀደድ ይመስል... ስናዳላ
የጉድ ቀን አይመጣ ይመስል ፣ ሰው በተሰበሰበት ከወደመቀመጫው አይተረተር ይመስል... ያ ብጣሽ ጨርቅ አያስፈልግ ይመስል

ከ ክር ያልተሰራ ይመስል... እንደመሰሎቹ... ፤ በክር ይሰፋ ዘንድ የክር ክምር በዛፍ ቅርንጫፍ መሬቱን እየጫረ ተክዞ አንዴ በልቡ እንደው ፈጣሪዬ መች ነው እኔም ከጨርቅ እኩል ምሆነው መች ነው እኔም ብጥቅ የምሸፍን መች ነው ሰው( ጨርቅ) የምሆነው ብሎ እየፀለየ... ስራ ፈቱ እንዲጣፍ ተመኘ... በሌላ ጨርቅ መቀደድ ላይ የህይወቱ ትርጉም ተንጠልጥላ እያያት ነይ ውረጅ ክር ሁሉ እኩል ነው አላላትም... መንጠልጠል መቀጠል ይቀላላ

ስወጣ አስፍቶ ሞልቶ ነው የሰጠኝ ቀለሜም ሚወይብ አይመስል ሲል ሲመካ ይቆይና... እህም የቅዱ ቀን ሲመጣ... ኪሮሽ ቅድ ሲያደርጉት ይተርፍና... ሸሚዝ ሊሰሩበት ይተርፍና... በ አጋጣሚ መጣፊያ ሆኖ ይቀራል... ከልባሽነት መደ መጠገኛ ሲዞር ትምክህቱ ውሃ ሲበላው( ጨርቁ ሲታጠብ በሉ ከተመቻችሁ) እንደ አዲስ መፈጠር እንዳ... እንዳዲስ... ሌላ ምኞት ይወለዳል... ክር

ክር ክርን ልትሰፋ በመርፌ አይን አልፋ
ክር እኔ እሻል ብላ ተደርባ ከ ወደታች ተጠምጥማ ታስራ ሌላ የክር ክምር ልታገናኝ... ሰብ(ፍ) ብላ ትመጣለች... ባለ ተራ እድለኛ ከ ኩራት ከፍታ የወደቀ ቀኑን ጠብቆ ይቀላቀላል በክር ጉልበት ( እሱም በሆነበት) ምናል ደና ቦታ ቢሆን


ሰፍቶኝ ከተቦተረፈው ከ ወደመቀመጫው ጣፍኩት

እኔ ስለቦታ ስለተፈጥሮ እሷ ስለ ክር ስለ ጥለት ስታወራ የተጋመድንበትን ተፈጥሮ ካድን
( የገባው ገብቶታል)

ውሃ

@wuhachilema


፨ ልጅ ወለዱ ፨

ከተፈጥሮ በተጣላ መንገድ... እንዴት?

የተጣለ ፍሬ ዘር ሆኖ ይበቅላል... ድንጋይ ሆኜ በቀረሁበት የ አረም ሽበት ከወረረኝ... ቦታ ተመላላሽ በዛ ፣ ከጎኔ ሌላ ተሸናፊ ወደቀኣ... በ ትንሽ የ አፈሩ ጉብታ ላይ የተጎነጎነ አበባ በየኑ የሚቀይሩለት በየቀኑ ያልወየበ ልዩ ልዩ ጥቁር ልብስ ( መልኩ ቢመሳሰልም ማስታወቁ መች ይቀራል) እየለበሱ እንባቸውን በ ሶፍት እያበሱ በትልቅ መነጥር ተጋርደው የሚመጡ ብዙ ወዳጆች ያሉት ሬሳ ከጎኔ አረፈ

አዲስ ጫማ... ጥቁሩን፤ የሚቅለጨለጭ ቁልፍ በጃቸው... ባጁ ያልተነቀለ ኮፊያ ካናታቸው ደፍተው በየተራ ይመላለሳሉ .... የሃውልቱን መብቀል በጉጉት ይጠብቁት ይመስል... አንዱማ እየነዳሁ ካልገባሁ ብሎ የተገለገለ ነው አሉ አስር ጊዜ የመኪና ቁልፉን የሚያቅለጨልጨው ፣ ግን የወደቀ ሁሉ ጊዜውን ጠብቆ ይረሳል( ይነሳል ለ ሬሳ አይሰራም)... ወዳቂውን ይዞ መውደቅ የትም አያደርስ ብለው አልፈው ሂያጆች በረከቱ... ጉንጉኑ የ አበባው ፣ ከውሃ ጠገብ ወደ ጠወለገ ተቀየረ... ደረቀ... ከሰመ... ረገፈ.... ተረሳ... ሃውልቱ ብቅ ያለ ጊዜ ግር ብለው መጥተው አዳነቁ ( ውድ ነበራ ፣ እምነ በረድ ውድ ነበራ) ጥበቡን አዩ በነዛ ትላልቅ መነጥሮች የተደበቁት ጥቃቅን አይኖቻቸው በ ቅናት የተንገበገቡ ይመስላል

ሰው እንዴት በሟች ይቀናል? ፣ ሃውልቱ በቶሎ ተረሳ የሟች ታሪክ እንደወደቀ ቀርቶ በ ሆነ ጊዜ የሚያነሳው ሰው ተገኘ... አልለቅም ያለ... አልለቅም ያለች በየቀኑ የምታለቅ ተገኘች...

[ ሰው እንዴት ያለተፈጥሮ ይወልዳል? ፤ ሌላ እንቆቅልሽ... ደሞ እኔ ምን ቤት ነኝ? ]

ጊዜዋን ጠብቃ የማትቀር አንድ እሷ ኖረች ለሟች... አንድ አይነት ጥቁር ልብስ... ትላንት የነካትን አዋራ ዛሬም ለብሳው ምትመጣ... ፈጠን ቸኮል እያለች ደርሳ የወጓን አድርሳ እየተንደረደረች ትኼድ የነበረች ከጊዜ በኋላ ቀስ እያለች እየተራመደች ትመጣ ጀመረቻ

ከፊት በርከክ ብላ ጉልበቷን በመቃብሩ አፈር እንዳላቦካች አሁን ቆማ ሆነ የወጉን ምታደርሰው... እንባዋ ግን አልተቀየረም... በሆዷ ያለው ሃዘን ሁሌ እንደከበዳት ነው ግን ልጇ ባሰ... ተባብረው ከበዷት ሆዷ ገፋ...

በማታ መጣች ያልለመደባትን... ጥድፍ ብላ... እንባዋ ታንቆ ረገፈ... ጉልበቷ መሬት ነካ
... የሃዘን ሳይሆን የጭንቅ እንባ... በ እኩለሌሊት አጋነንንት ለቡና ሲጠራሩ የሷ ልጅ እያለቀሰ ፈልቅቋት ወጣ... በሙሉ ጨረቃ

ቀጥቁር ሻርፗን ጠቅልላ ታቀፈችው... አይን አይኑን አየችው... ጨረቃ ይቺ አሽቃባጭ ጉድ አልደብቅ ብላ ታበራባታለች... ልጅቷ ልጇ ላይ አመነታችና... ለመወሰን አንገራግራ ከነጨርቁ ሸፋፍና ከ መቃብሩ ላይ አኖረችው

ከኔ መቃብር ላይ... ሽበታም ድንጋይ እንዴት ካለቀሰችለት አፈር በላይ ይታመናል?... ድንጋይ እንዴት ለዚህ ሃላፍትና ይበቃል?... አላየችም እንዴ ምንም እንደሆንኩ?... አይታ የለም እንዴ?

ሌላ ቀዝቃዛ ደሞ የጨቅላ ሬሳ በላዬ ላይ ሲደረብ ተሰማኝ... ቸኮለች... አውቃ ይሆን?... ሊኖር የወጣ ገና አንዴ በማገው አየር ድፍት ይላል?... ደሞ የሷ እየፈገጉ መሄድ?
መረጋጋቷስ እ?

ሄደቻ... እኔ ባለ አደራ ህእ? ማን እንዲወስደው ማን እንዲበላው? በምኔ ላሞቀው ከብርዱ ላስጥለው እ?... ጨነቀኝ ፤ ሟች እንደሚጨንቀው ነዋሪ ሆኜ አለማወቄ

ማን አወቀ?

አይነጋ የለ... አነጋሁት

መሞት አያምም... ይሄ ግን ያማል... ነግቶ ጠሃይዋ አየሩን ማሞቅ ጀመረች... ያረፈደ... ለሃውልቱ ምርቃት

የተራውን ቅራቅንቦ እያቅለጨለጨ መጣ... አይኑን ወደላይ አንጋጦ ሃውልቱ ጋር ሲደርስ መለስ አለ... መነጥሩን አውልቆ ከላይ እስከታች ቃኘው... ፊቱን አጣሞ

ከዛ... መለስ አለ... ማየት ባንፈልግም የምናያቸው ነገሮች አሉ አደል?... የተጠቀለለ ከፊቱ በቀር፣ የተደገፈ በኔ መቃብር አፈር ህፃን ልጅ አየ...

ድንጋጤ ፣ ወድቆ ያገኘው ወርቅ ይመስል ዞሮ መቃኘት ፣ ድጋሚ ድንጋጤ... ቀረብ፣ ራቅ ፣ሄድ ፣መጠት ማለት
ተጠግቶ ትንፋሽ ካለው ማየት... ልብ ምቱን ለማዳመጥ ከመሬት አንስቶ መደ ጆሮው ማስጠጋት... አቀፍ እንደማድረግ ማለት... የልጁ ነብስ መዝራት... ከ እንቅልፉ ተቀስቅሶ እንደነቃ ህፃኖ ከ እናቱ ሆድ የወጣ ጊዜ የጀመረውን ለቅሶ ካቋረጠበት ቀጥሎ እሪሪሪሪሪሪ አለ

ልጅ ወለዱ... እንደዚህ


ውሃ

https://t.me/wuhachilema


ጥፍር



ምኔ ነው ብለን ስለምንጠይቃቸው ቆርጠን ስለጣልናቸው ባዶ ቀኖች

ወደኋላ መለስ ብሎ ለማየት ያክል ብዙ ዘመን የኖርኩ ሲመስለኝ ቆምኩና... አው በትክክል ወደኋላ ለማየት ሞከርኩ... ከዛ ከማስታውሳቸው እልፍ ቀኖች ውስጥ ብዙ ነገሮች ፈልጌ አጣሁ ያ ነገር የት ገባ እያልኩ

ጥፍር... የሰውነት ቆሻሻ የቀን ጉማጅ ደባሪ ዘባተሎ ፣ ደሞ ቆንጆ ቆንጆ ቀኖችን ያያይዝ ነበራ... ቀረጣጥፌ በላሁት ( ጾም ያስፈርሳል እንዴ ጥፍር?... እንጃ) መለስ ብሎ ለማየት ያክል የዞርኩት አዟዟር አንገቴን በዛው ጠምዝዞ እንደሚያስቀረው መች አወቅኩ... በዚህ እድሜዬ የምን ትዝታ ነው ብዬ ደረቴን ነፍቼ ነበር

ምን ያደርጋል... የቀረጠፍኩት ጥርስ ትዝ ብሎኝ አሁን ለሱም ንሰሃ ልገባ ነውንዴ አልኩ?... ሃ ስጋ እንደበላ... ግን ጥፍር እንደ ቀንድና ጥርስ ነው ተብሎ አልነበር እንዴ የሚል ሃሳብ ብልጭ ይላል ደሞ የክብር ልብስን ከመብላት በላይ ፆም መግደፍ አለ እንዴ የሚል ሌላ ውሃ ብልጭታውን ያዳፍነዋል

ችልስ

ለጥጋብ ማረጋገጫ የቸለስኩት ቀዝቃዛ ውሃ ከ ደስታ ማረፊያ ያሳለፍኩትን ደባሪ ቀን ያክል እንደሆነ... ውሃ ዋጋ ቢስ ነው እላለሁንዴ?
ከፀጋ ተራቁተን ከ አካላችን ተገፎ በጣታችን ላይ ልክ እንደ በአድ ተለጥፎ ስለተቀመጠ ተበልቶ ይለቅ ብሎ መፍረድ ይከብዳል... ይሄንን ኢ ፍትሃዊነት የሚያስተውል ጭንቅላት ስለሌለኝ ረዣዥሞቹን ደባሪዎቹን ቀናት ቀረጣጥፌ በላኋቸው

ታሪክ ወደኋላ ሲባል ትዝ የሚሉኝን ቀኖችን በጣት ቆጥሬ ጨረስኳቸው... ስጋ በልቶ ፆም ላፈረሰ ንሰሃ ሲሰጠው የራሱን ቀን ቀርጥፎ ለበላ ምን ይደርሰዋል?... ፍርዱ ፈጠነሳ

( ጥፍር ለመቁረጥ ይሄንን ሁሉ ማሰብ አይከብድም?)

@wuhachilema


የፎቶ ፍሬም ውድ ነው
እንጉርጉሮ የሚከፈትበት ቴፕ ውድ ነው

🖋 ንፋስ


፨ ከ ሽበታም ድንጋይ ምን ይጠበቃል? ፨


ከሞትኩ በኋላ ምን እንደምንሆን ፣ የምንሄድበት ቦታ ይኑር አይኑር አስባለሁ ፤... ለመኖር የተፈጠረ ኑረቱን የሚቃረንን ነገር እየፈራ ወይ እየተጠነቀቀ ይኖራል
እንደዛ ነበር ስናደርግ የነበረው ፤ ሞት የሚባል ባላንጣነት ከመኖር ሊነጥለን እየመጣ ነው እያልን ሁሉንም ቀን እስከ ሽራፊ ሰከንዱ ድረስ ልንኖረው እንወዳለን ፣ መኖር በብዙ ነዋ።

ደሞ ማደግ ሲመጣ ከሞት በላይ፣ ከዚህ አለም የነጥሎ ከመቅረት በላይ ፤ እዚሁ ሆኖ ስለአለመኖር እናስባለን... አሁንም ሃሳባችን መኖር ነዋ!
እድሜያችን ሲገፋ አካላችን ሲገድበን በትዝታዎቻችን ውስጥ እንኖራለን ፣ በትንላንት ውስጥ በደስታ እንፈነጫለን... የህልም ገነታችን ውስጥና ጭልጥ እንላለን። የሚደብረው ነገር ትላንት የተባለው ጊዜ ውስጥ የእውነት መቆየት አለመቻላችን ነው... ሁሌ ትላንት እንደሆነ እናውቃለን ሁሌም ቢሆን... ምንም ያክል ሰላማዊ ቦታ ቢሆን ትላንት እውነት አሁን አለመሆኑን እናውቃለን።

አካል ይደክማል ለለውጥ እጁን ይሰጣል ከዛ... እንሞታለን ፤ አንከብክበው ይቀብሩናል።

ሳረጅ አንከብክበው ቀበሩኝ እንዳልሸት እንዳልገማ ብለው ፣ ከነ ትዝታ ቋቴ ከነ ማንነቴ ከነ ህልሜ ስለተሸነፍኩ ቀበሩኝ... ለ አርባዬ ትልቅ ድንጋይ ተክለው ስሜን ቀረፁበት ፣ የወለዱኝን ፣ መች እንደተወለድኩ በ ጥቅስ አጅበው ፃፉት
ከሞት በኋላ ምን እንደምሆን ለማወቅ ስጓጓ የነበርኩት እኔ በሞትኩበት ቅፅበት ከነበርኩበት ጨለማ በ አርባዬ ማግስት የብርሃን ፍንጣቂ ሲገባብኝ አየሁ፣ ድንጋይ የድንጋይ ሽበት ሆኜ በቀልኩ

የተቀረፀ ድንጋዬ... ሽበት የበለሰ ድንጋይ ሆኜ አረፍኩታ ፤ ሟቾቻቸውን ሊጠይቁ የሚመጡ ሁሉ ባጠገቤ ሲያልፉ ቆይ እንተዋወቅ ስል ህይወቴ ልንገራችሁ ስል አልፈውኝ ይሄዳሉ... መች ይሰሙኝና... ሽበት የወረረው ድንጋይ ምን ቁም ነገር አለውና


🖋ውሃ


https://t.me/wuhachilema


ከዛ ደሞ ፈልጎ ማግኘት የሚባል ነገር አለ ፤

እንትን ትፈልጋለህ... ወይ የጠፋ ወይ የተደበቀ ወይ ልታውቀው የምትፈልገው ነገር እንትን ይኖራል... የሆነ እንትን አለ አደል ?... አው እሱን... ቀድሞ ግን ያንን እንትንን መፈለግን ትፈልጋለህ ያንን መፈለግም ትማራለህ...

ከዛ ቀድሞ ስትፈልጋቸው የነበሩትን እንትኖች እንዴት እንዳገኘህ እና እንዴት እንዳላገኘሃቸውም ታስባለህ... እንትን ሲሄድ ሌላ እንትን ሲተካ... ፈልገህ ደክመህ ሳታርፍ ታሸልባለህ ... የእንትኖች ፍለጋ ህይወትህን ከወዲያ ወዲህ ሲያላጉት አምሽተው በቃው ስትባል ያለ መልስ ያለ ቃል ጥለውህ ይጠፋሉ

እነሱ ምን አለባቸው

የምትፈልገውን ነገር መፈለግ እንዳለብህ ትማራለህ ከዛ ትፈልገውና ታገኘዋለህ... ያው እሱን ሳይሆን ሌላ እንትን እንደምትፈልግ ትረዳለህ... ከዛ ያ እንትን ቀድሞ ነገር ያለህ ወይም የነበረህ ነገር እንደሆነ ይነግሩሃል 😂... እንዳይደክምህ ብለው መሰለኝ... እንዳልኩት እንትን ፍለጋ ማብቂያ የለውም

እንትን እንትን እንዳልክ መሞት እንደሌለብህ ሊያስረዱህ ይሞክራሉ... ማንም የሚፈልገውን እንትን አግኝቶ ደስ ያለው ያረፈ የለም... ሌሎች ተፈላጊ እንትኖች አሉዋ

መፍትሄው አለመፈለግ ነው ብሎ መገገም አይቻልም ግን እንትኖችን ስለመፈለግ የተማርንበት መንገድ ልክ አይመስለኝም

አለም ስለ መፈለግ እና ስለ ማግኘት ብቻ ነች ያለው ማነው ?

አስታወስኩ











ሁሉም ሰው ነው

🖋 ንፋስ

https://t.me/wuhachilema


አንድ አመት


#ሳንሱር ያልተደረገ

ሌሎቹን እብዶች ምን እንደሚያስቃቸው አላውቅም... እኔ ግን የሆነውን ሳብራራ ውሸቴን ይመስላቸዋል ይሄኔ የሚለው ሃሳብ ይኮረኩረኛል... ከዛ ፈገግ... ፈገግ... ፈገግ... ፈ ገ ግ

የ ዘፈን ዳር ዳሩ እስክስታ ነው አላሉም... የቱ እንደሚቀድም እንጃ... ዘፈኑ ያስጨፍራቸው ወይስ ጭፈራው ያዘፍናቸው?... የ ኪነት ክበብ ያደረገኝ ማነው.... ይሄንን ሳስብ ደሞ.... ፈገግ ፈገግ አው እንደዛው ነው ፤

ባለፈው ለታ በ ጭንቅ የተያዘውን በ ቀለም ድርብርብ በ ጭቃ ምርግ በ ሲሚንቶ ግርፍ የተጨቆነውን ቋሚ አጠና እና ቤተሰቡን ነፃ አወጣ ብዬ የ አንድ ሰው ትጥቅ ትግል ጀመርኩ... መዶሻም ሌላም ሌላም ሰብስቤ መከርኩ... እኔ ባልችል እንኳ እዳትቆሙ እንዳትሰለቹ... የቋሚው እጣ በ እኛ እጅ ነው ብዬ ሞቅ ያለ ንግግር አደረግኩ... ድንጋይ ፣ መዶሻ ፣ ዘነዘና ቀጥ ብለው ተሰልፈዋል... በፊታቸው እየተንጎራደድኩ የህይወታቸውን ድንቅ ንግግር ሳሰማ ዘነዘና እንባ ሲተናነቀው አይቻለው... በውነት በውነት።

" እነሆ የነፃነት አዋጅ ታውጇል በ ጭለማ አገዛዝ ውስጥ ላሉም ብርሃን ሊበራላቸው ነው!!! " ብዬ ካንባረቅኩ በኋላ ጨቋኙን ግድግዳ እንተገትገው ገባን... "በል አይዞህ!"... "እንዲያ ነው እንጂ! " " እሰይ " እያልን ስቃዩን እናበላው ገባና... አንዱ ነፃ ሊወጣ ጨቋኙ ይቀጣ ዘንድ ግድ ነው

ቀስ በቀስ እያደግን በድል ላይ ድል እየደረብን አላፈገፍግ ያለውን ግድግዳ እየደመሰስን ፣ እጅ የሰጠውን እየማረክን... ጥቂት ማገሮችን እና ለመቁጠር የሚታክቱ ሳጋዎችን አስለቀቅን...

የውጭው በር ተከፍቶ ስዞር በ እጇ የያዘችውን እቃ ጥላ ፈዛ ታየኛለች... ሳያት ታየኛለች... ይቺ የማናት ፈዛዛ አልኩና በ ጀነራል ዲጂኖ እየተመራን የምናካሂደውን ትግል ላስቀጥል ዞርኩ... አንድ ሁለት እንዳልኩ እጄን ይዛ " ኡኡኡኡኡ " አለች

" ኧረ ቤቴን አፈረሰው.... ኡኡኡኡኡኡኡ " ጓረቤት ተሯሩጦ ገባ ፣ ጓሮ የነበሩትም እየተላላጡ ወጡ ... ሰው ግቢውን ሞላው... የያዝኩትን አስጣሉኝ... ፣ የትግል ጓደኞቼ አንድ በ አንድ እየተለቀሙ ተያዙ...

ከዳር ቆማ ስታየኝ የነበረች ፈልፈላ ደሞ " መዶሻዎቹን ሰብስቦ ሲያናግራቸው ነበር ብላ አቃጠረች "... ሰው እንዴት በመዶሻ እና ዘነዘና መሃል ያለውን ልዩነት ሳይለይ የሃገር ምሥጢር ለማፍሰስ ያስሮጠዋል? እ... አሁን አፍ መፍታት አይቀድምም?

የከበቡኝን ገረመምኳቸው... አሁን ደሞ ይሄንን እንዴት ነው ምታብራራላቸው? የሚል ጥያቄ ከ ህሊናዬ ጓዳ ብቅ አለ... ፈገግ ፈገግ

ፈገገገገግ... ከት ብሎ መሳቅ ነውንጂ


* * *

https://t.me/wuhachilema

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

96

obunachilar
Kanal statistikasi