የግል ትምህርት ተቋማት የትምህርት ማህበረሰብ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ የምዝገባ ንቅናቄ መድረክ ተካሄደ::
(ታህሳስ 22/2017 ዓ.ም) መድረኩ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ እና በብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም (National ID Ethiopia) አማካኝንት በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ የግል ትምህርት ተቋማት ላይ የሚገኙ የትምህርት ማህበረሰቡ አካላት የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ እንዲያከናውኑ ለማድረግ እንዲቻል ንቅናቄው መካሄዱ በመድረኩ ላይ ተጠቅሳል::
ዲጂታል መታወቂያ በትምህርት ዘርፉ በተለይም በግል ትምህርት ተቋማት ላይ ያለውን ፋይዳ አስመልክቶ የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት አስተባባሪ አቶ ዮዳሄ አርአያስላሴ ምዝገባው የተማሪዎችንና የትምህርት ማህበረሰቡን ማንነትን በመለየት የተማሪን መረጃ በቀላሉ ለማወቅ ያስችላል ብለዋል::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ በበኩላቸው ከትምህርት ማህበረሰቡ ጋር በጋራ መስራት ለማህበረሰቡ አቅም ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ለስራው ስኬታማነት ጉልበት እንደሚሆን ተናግረዋል ::