ይድረስ እኔ ትውልድ
(ሳሙኤል በለጠ )
ሰሞኑን የጥያቄ ናዳ አናት አናቴን ሲቀጠቅጠኝ ሰነበተ ፥ ስንቱን መለስኩት? ስንቱን ገፋሁት? ከስንቱ ጩኸት ከስንቱ ዝምታ ጋር ተላፋሁ የሕይወት ሽታዋ እስቲጠፋብኝ ከራሴ ጋር ታገልኩ ብቻ ሁሉም ነገር ጥያቄውም በዘመን ጥላ ሥር ይለፍልኝ ፤ ሌላ ምን እላለሁ ፡ የሰው ልጅ ሟምቶ እኔ ላይ የፈሰሰኝ እስቲመስለኝ ጭጋግ ገላዬ ላይ ሚስጥር ሆኖ እስከሚቋጠርብኝ ድረስ ዳከርኩ ፤ ከእቤቴ ድንኳን ተሸጉጬ አንድ ፊልም ዐየሁ ብቻ ታሪኩ በዓለም አንድ ጥግ አንድ ባይተዋር ተወለደ ፣ ተወልዶ ከሚከረፋ አንድ ጫፍ ተፈጠፈጠ ፣ ተገፋ ይጮኻል ፣ ያለቅሳል ፣ ኋላ ላይ በመከራ ንፋስ ላይ ተንሳፎ ፣ በአበቦች እና በመልካም ጠረን ፍቅር ተነድፎ የአማልክቱ ጉያ እንኳ ፍጹም የሌለ የተመረጠ የሽቱ መዓዛ ቀመረ ይህ ተዓምር አይደል? በእርግጥ ያሳዝናል በመንገዱ ስለሚቀጥፋቸው አበቦች እንኳ ግድያውን ያጸደቀ ብቸኝነቱን የቻለ እንደ እግዜር ያለ የራቀ የረቀቀ ነው። (ፊልሙ Perfume The Story of a Murderer ነው።) ከዚህ ፊልም ብኋላ ብዙ ጥያቄ ተመላለሰብኝ እኛ ለዚህች ውሏ ለጠፋባት አገር እንደ አገር አገር ሆና እንዳትቀጥል መፍትሄ የሚሆን ሰቆቃ ለምን እናባክናለን ?! "የቻይናውያን ውርደት ኮንፊሽየስንና ላዎ ዙን ፡ የራሺያውያን ስቃይ ፑሽኪንንና ዶስቶቮስኪን፡ የዳቶች ሰቆቃ ቫን ግን ፡ የህንዶች ና የደቡብ አፍሪካውያን ዎዮታ ጋንዲንና ማንዴላን ፣ የጥቁር አሜሪካውያን ሕመም የጃዝ ሙዚቃን ሲወልድ ፣ ምነው ያበሻ ረሃብና ድህነት ፣ ውርደትና ሃፍረት እንዲሁ መከነ ?" ብሎ ነበር መልካም ፍጹም ድሃነትን የመሰለ ሃብት ፍጹም ውርደትን የመሰለ ክብር ፣ እንዲሁ ባክኖ ፣ ከንቱ ሆኖ ይቅር!?" ኬክሮስና ኬንትሮስ በስንቅነህ እሸቱ(ኦታም ፑልቶ) ይህ አንድ ሳንቲም ጥያቄ እኔ ላይ ሁለት ገጽታ ፈጥሯል ። አንድም ያን ትውልድ እንዳይ ሁለትም ይህንን ትውልድ እንዳስተውለው እድል ፈጥሮልኛል ። በእርግጥ የያ ትውልድ እና የዚህ ትውልድ የሽግግር መቅደስ ሲሰራ መቅደሱ መቅደስ እንጂ ምሰሶ እንዲኖረው ተደርጎ አልተሰራም ስለዚህ ሽግግሩ ቀናዊ እንጂ መንፈሳዊ ነገር በውስጡ እንዳልያዘ ግልጽ ነው ።
ከ ኀሳብ አንጻር
...የምናየው ፣ የምንሰማውና የምንኖረው ሁሉ ግብዓተ-ኃሳብ እንደሆነ እሙን ነው ። ያም ግብዐተ-ኀሳብ በይደር ሲብላላና ሲውዋሃድ በአመክንዮም ተጠየቅ ሲጎለብት እውቀት ይሆናል። እውቀት ከመሆኑ በፊት የለው የመብላላት ሂደት ነው። #ኀሳብ ...እውቀትም እውቀትነቱ በተግባር ይገለጣል ...እውቀት በተግባር ሥጋ ካለበሰ ብዙን ጊዜ ምውት ነው ...ቋንቋ ሆኖ ይቀራል። የዘመኔ ትውልድ ምንድነው ? የሚሰማው ምንድነው ? የሚኖረው ? ይሄንን መቅጡ መመርመር አለበት ይህ ካልተመረመረ ወይ እዉቀቱ ካልተተገበረ ፤
ልክ የማሽን አሰራር በጽንሰ-እሳቤ ደረጃ እንደ "ማወቅ" ግን ስራውን እንዳለመቻል ይሆናል ።
...እውቀት ከተግባር ብዙም ልዩነቱ አይታየኝም ማለትም ልትኖረው የቻልነውን፣የበቃነውነውን እውቀት አይደል ተግባር የምትለው ? እና ከመግባቢያ ቋንቋነት ባሻገር ያለውን ትክክለኛውን እውቀት ልንተገብረው ፣ ልናስተገብረው ይገባል ። ሁላችንም እንደምንሞት እናውቃለን እንላለን ነገር ግን የምር እናውቃለን ? መሞቱን የምር የሚያውቅ ሰው እንዲህ ተበሳብሶ ነው እንዴ የሚኖረው ? ማለት እውቀት የምርም በአንድ ሰው ውስጥ ካለ እንዴት አይለወጥም ? ወይንም ያ ሰው ሊለወጥበት ይግገባል ። ካልሆነ እውቀቱ ትክክል አይደለም ስለዚህ የዘመኔ ትውልድ እውቀቱን ሊመረምር ይገባል ። ለምሳሌ የዘለለት አሁናዊ ኑሯችንን እንይ እኔ ሳስበው ሰዎች ሲሞቱ ስላየን እንደምንሞት እናስባለን እንጂ የምርም የገባንና ያውቅነው አይመስለኝም... አውቀን ቢሆን ኖሮ እኒህ ሁሉ ጣርነቶች "ምን ሆነን ነው ? ምን ነክቶን ነው? በሚል ማምመልስል ያከትማላቸው ነበር ብዬ አስባለሁ ። ነገር ግን እኛ በአፍ መዋቲ እንደሆንን ብንመሰክርም ! በልባችን ያልለውን ሥውር እምነት(በቋንቋነቱ እውቀት) ዘላለማዊ እንደሆን ነው ...።
(ምሳሌ ሌላ)
አሁን ይህን የምጽፈው ሻይ እያፈላሁ ፣ በበራድ እያንተከተኩ ነው። ... ለመጻፍ ሳስብ ሻይ ደመነፍሴን ሸቶት ነው። ሻይ ላፍላ ብዬ አስሰብኩ ይህን ኀሳቤን ስለ ሻይ አፈላል ባለኝ #እውቀት ደግገፍኩት ከዚያም አደረኩት... ይህ ዑደት ዐፍታ ወስጄ ካስሰቡበት የሶስቱን ነገረ አንድም ሦስትምነት ይገልጠል ብዬ አስባለሁ (ኅሳብ ፣ እውቀት ፣ ተግባር)። ማሰብ ወስሳኝ ነው ...ማሰብ ግን ብችቸኝነትና ለራስ የሚስሰጥ ጎንንና ልብን ማድመጫ ጊዜን ይሻልና በውስጣችን ካለም ረብሻና ጫጫታ ጋር ያገናኛልምና ለብዞዎቻችን ሚቻል አይነት ነገር አልሆነም... ካሰብንም በኋላ በማሰብ ሂደት ውስጥ የሚግገለጠውን እውቀት ለመተግበር ለኀሳቦቻችን ለውጤቶቻቸውም ማለትም ለእውቀቶቻችን ቀና እና ታማኝ መሆን ግድ ይላል ድፍረትንም ይጠይቃል...እንደ እውቀት መኖር ማለት ታላቅ አመጽ ነው። ይህ ትውልድ አመጹን ለምን ፈራው?
(የተሰሰረዘ ምሳሌ)
(የተሰረዘ) እውቀት ማለት ተዓምር ነው። ብርሃን ነው - ፍጹም ይለውጣል ፣ እውቀት ራሱም ፍጹም ነውና በነገራችን ላይ አወቅን ስንል የምርም በንቁውና ንቁ ባልሆነው የአዕምሯችንም ክፍል በደመ-ነፍሳችንም ያንን እውቀት ስናሰለጥን የበላይ ገዥ ስናደርግ ነው። ይህንንም የምናደርገው በኀሳብ ነው ። በእውቀትና በተግባር ልምምድም - ይህ ብርሃንና እውቀትም እርቅ ነው። የአንድ ሰው አለመከፋፈል እዛ ውስጥ ይመስለኛል ። ሁሉው ያለው ሰላሙም ፣ ፍቅሩም ...ግን እንዲህ ስንናገረው 'ሚቀል ። ግን ክቡድ የሆነ ነገር ነው ። መሞከር ግን ይቻላል ።
( እንደገና )
የቻይናውያን ውርደት ኮንፊሽየስንና ላዎ ዙን ፡ የራሺያውያን ስቃይ ፑሽኪንንና ዶስቶቮስኪን፡ የዳቶች ሰቆቃ ቫን ግን ፡ የህንዶች ና የደቡብ አፍሪካውያን ዎዮታ ጋንዲንና ማንዴላን ፣ የጥቁር አሜሪካውያን ሕመም የጃዝ ሙዚቃን ሲወልድ ፣ ምነው ያበሻ ረሃብና ድህነት ፣ ውርደትና ሃፍረት እንዲሁ መከነ ?" ብሎ ነበር መልካም ፍጹም ድሃነትን የመሰለ ሃብት ፍጹም ውርደትን የመሰለ ክብር ፣ እንዲሁ ባክኖ ፣ ከንቱ ሆኖ ይቅር!?" ኬክሮስና ኬንትሮስ በስንቅነህ እሸቱ(ኦታም ፑልቶ) ታላቁ የህንድ ባለቅኔ ራቢንድራናዝ ታንጎ ሊሞት ሲል አንድ ጓደኛው ወደ እርሱ ይመጣል ፤ የሥነ - ጹሁፍ ጓደኛው ነው ። ሰውየው ታላቅ ኀያሲ ነው ። ራቢንድራናዝ ታንጎ "በጥልቅ 'ርካታ መሞት ትችላለሁ ምክንያቱም በጣም ብዙ መዝሙሮችኔ ዘምረሃል ። ከዚህ ቀደም ማንም ይህን ያህል ቁጥር ያላቸው መዝሙሮች ዘምሮ አያውቅም ። አለው ጓደኛው ራቢንድራናዝ ታንጎ ስድስት ሺህ መዝሙኖችን ጽፏል ። እያንዳንዱ ግጥም እጅግ ለስሜት ንክር ፣ ውብ እና የተለየ ነው ። ጓደኛው እንዲህ ሲለው ከራቢንድራናዝ ታንጎ ዐይኖቹ ዕንባ አፈተለኩ ጓደኛው ለምን ታለቅሳለህ ሞትን ፈራህ አለው ራቢንድራናዝ ታንጎም "አይ ! ይህ ሞትን መፍራት አይደለም ። ሞት የሕይወትን ያህል ውብ ነው ።! እያለቀስሁ ያለሁት ውብ መዝሙሮች አዕምሮዬ ጓዳ ውስጥ ልውጣ አልውጣ እያሉ ስላስጨነቁኝ ነው ። ይህ ፍትሕ አይደለም አሁን የምር ለመዝመር ዝግጁ ነበርኩ! አለ!። (Until You Discourse on the sufi way Die by osho) ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን በአጤ ቴዎድሮስ መንፈስ ውስጥ ሆኖ "ያለፈ ጥረታችንን ሳስታምመው ትዝ ሲለኝ ከሞከርነው ነገር ይልቅ ያልሞከርነው ነው