አንጋፋው ሙዚቀኛ አለማየሁ እሸቴ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል:: በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈው አንጋፋው ድምፃዊ አለማየሁ እሸቴ ትናንት ምሽት እኩለ ሌሊት በድንገት ህይወቱ ማለፉ ተገልጿል፡፡ አርቲስት አለማየሁ እሸቴ በኢትዮጵያ የግል ሸክላ ሙዚቃ ህትመት ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያ የሆነበትን ሙዚቃ በአምሃ ሬከርድስ አማካኝነት ማሳተም የቻለ አርቲስት ነበር:: "ተማር ልጄ" "አዲስ አበባ ቤቴ "እና በሌሎች በርካታ ተወዳጅ የሙዚቃ ስራዎቹ የሚታወቀው አርቲስት አለማየሁ እሸቴ በልብ ህመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ተ