💓 ትርታዬ 💓 dan repost
#ፍቅሬ
በልጅነት ዘመን፥በጨቅላነት እድሜ፣
ሳይሽ ደነገጥኩኝ፥አፍቅሬሽ ቀድሜ፤
ሳይገባኝ ሚስጥሩ፥የአዳምነቴ፣
ሄዋኔ አደረኩሽ፥ወዶሽ እኔነቴ፤
ገና ሀሁን ሳልቆጥር፥ቀለም ፊደላቴን፣
ልቤ ላይ ተፅፈሽ፥አጠፋሺው ቀልቤን።
ገና አንቺን ሳይሽ፥መንፈሴ ይረካል፤
የልጅነት መልክሽ፥በፍቅር ማርኮኛል።
የጥርሶችሽ ማማር፥የፊትሽ ገፅታ፣
ውበትሽ ድንቅ ነው፥ቅኔ ማይፈታ፤
ሳይገባኝ ሳልውቀው፥የሂወትን ጣእም፣
በተፈጥሮሽ ታምር፥ተክዤ ስደመም፣
ማንስ አስተዋለኝ፥ተደብቄ ሳይሽ፤
በናፍቆት ህመሜ፥እንደወደኩልሽ፤
ለፍቅርሽ መኖሬን፥በተስፋ ፅናቴ፣
አብሬሽ እንዳለሁ፥የፍቅር ንግስቴ!!!
✍ አዲሶ
@lib_mit
@robina2721
ከተመቻቹ 👍 like
በልጅነት ዘመን፥በጨቅላነት እድሜ፣
ሳይሽ ደነገጥኩኝ፥አፍቅሬሽ ቀድሜ፤
ሳይገባኝ ሚስጥሩ፥የአዳምነቴ፣
ሄዋኔ አደረኩሽ፥ወዶሽ እኔነቴ፤
ገና ሀሁን ሳልቆጥር፥ቀለም ፊደላቴን፣
ልቤ ላይ ተፅፈሽ፥አጠፋሺው ቀልቤን።
ገና አንቺን ሳይሽ፥መንፈሴ ይረካል፤
የልጅነት መልክሽ፥በፍቅር ማርኮኛል።
የጥርሶችሽ ማማር፥የፊትሽ ገፅታ፣
ውበትሽ ድንቅ ነው፥ቅኔ ማይፈታ፤
ሳይገባኝ ሳልውቀው፥የሂወትን ጣእም፣
በተፈጥሮሽ ታምር፥ተክዤ ስደመም፣
ማንስ አስተዋለኝ፥ተደብቄ ሳይሽ፤
በናፍቆት ህመሜ፥እንደወደኩልሽ፤
ለፍቅርሽ መኖሬን፥በተስፋ ፅናቴ፣
አብሬሽ እንዳለሁ፥የፍቅር ንግስቴ!!!
✍ አዲሶ
@lib_mit
@robina2721
ከተመቻቹ 👍 like