🐄 ጥሩ የሆኑ የወተት ላሞችን ዝርያና አይነት ለርቢ እንዴት እንመርጣለን?
🐄 ከዚህ በታች በዝርዝር የተመለከተው አንድ ግለሰብ የወተት ላሞችን ለመግዛት በሚያቅድበት ወቅት ቅድመ ዝግጅት አድርጎ እንዲዘጋጅ የሚያግዙ የአመራረጥ ዘዴዎች ናቸው፡፡
🐄 ለመግዛት የታሰበውን የወተት ላም የሕይወት ታሪክ(breed record) በመጀመሪያ ማጥናት በዚህ ስር ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ መመዘኛዎች፦ የወተት ምርት መጠን(milk production) ፣ የወተት ቅባት መጠን (milk fat content)፣በተለይ ለርቢ የምንፈልጋቸው የወተት ላሞች ጀርሲ የሚባሉ ዝርያዎች ከሆኑ በየአመቱ ጥጃዎችን ማስገኘታቸው(calving interval and rate) ፣ በሽታን የመከላከል ችሎታ(general health status)፣ የአካባቢን አየር በቀላሉ ተላምዶ ለመኖር መቻልና የመሳሰሉትን ያጠቃልላል።
🐄 የከብትን የውጭ አቋም በመመልከት (general body condition scoring and conformation )፦ የጡት አቀማመጥ እና አወራረድ(udder and teat structure) ፣ ከልብ ወደ ጡት የሚወርደው የደም ስር(milk vein)፣ የወተት ላሞች ቅርጽ ጎንና ሆዳቸው ሰፋ ያለና ቅልጥማቸው ረዘም ያለ ነው፣ ግትና ጡታቸው የተስተካከለ እና የመሳሰሉትን በጥልቀት መመልከት ያስፈልጋል፡፡
🐄 በጸባያቸው/የማያስቸግሩ(docile breed)፦ ባጠቃላይ ለርቢ ስራው ስለማይመቹ በተለይ በወተት አለባ ወቅት የመራገጥና የመዋጋት ጸባይ ያላቸውን የወተት ላሞች መምረጥ የለብንም፡፡
🐄 ጤናማነታቸው የተረጋገጠ ላሞችን መምረጥ፦ የወተት ላሞች ግዢ በሚደረግበት ወቅት ከእንስሳት ሐኪም(trained veterinarian) ወይም ልምድ ካለው የወተት ከብት እርባታ ውስጥ ከሰራ ባለሞያ ጋር ቢሆን ይመረጣል፡፡
🐄 ባጠቃላይ የወተት ከብቶች በሚሰጡት ውጤት/የወተት ምርት ታሪካቸውን በማየት(annual and daily milk production)፦ መዛግብት በመመርመር በሚሰጡት የወተት፣ የጥጃ ምርት እና የመሳሰሉት፡፡
🐄 የውጭ የደም መጠናቸው ላይ በመመርኮዝ መምረጥ፦ እርጉዝ ጊደሮችን ወይንም የመጀመሪያ ጥጃ የወለዱ ጤናማ እርጉዝ ላሞች መርጦ መግዛት፣ ከልብ ወደ ግት የተዘረጋው የደም አስተላላፊ ቦንቧ መጠኑ በሰፋ ቁጥር የወተት ምርታቸውም ይጨምራል፡፡ የወተት ላም ግዢ በሚፈጽሙበት ወቅትም ይህንን ማስተዋሉ ይጠቅማቹሀል።
https://t.me/ye_lamoch_erbata_gebeya