TGStat
TGStat
Qidiruv uchun matnni kiriting
Ilg‘or kanal qidiruvi
Uzbek
Sayt tili
Russian
English
Uzbek
Saytga kirish
Katalog
Kanal va guruhlar katalogi
Kanallar qidiruvi
Kanal/guruh qo‘shish
Reytinglar
Kanallar reytingi
Guruhlar reytingi
Postlar reytingi
Brendlar va shaxslar reytingi
Analitika
Postlarda qidiruv
Telegram'ni kuzatish
TGAlertsBot
Каналингиз репостлари ва эсловлари ҳақида хабар беради.
Ботга ўтиш
reklama
TGStat Bot
Telegram'дан чиқмай туриб каналлар статистикасини олиш
Ботга ўтиш
reklama
SearcheeBot
Telegram-каналлар оламидаги сизнинг йўлбошчингиз.
Ботга ўтиш
reklama
Telegram Analytics
TGStat хизмати янгиликларидан бохабар бўлиш учун обуна бўл!
Каналга ўтиш
reklama
Statistika
Saralanganlar
Yederaw - የደራው
@yederaw
Kanal geosi va tili:
Efiopiya, Amharcha
Toifa:
Yangiliklar va OAV
የደራው መጽሔት "ፀሐይ አትጠልቅም!"
visit | www.yederaw.com
ያግኙን
@YederawSupport
Bog‘liq kanallar
|
O‘xshash kanallar
Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Yangiliklar va OAV
Statistika
Saralanganlar
Kanal siznikimi?
Tasdiqlash
Kanal tarixi
Postlar filtri
Oyni tanlash
O‘chirilganlarni yashirish
Repostlarni yashirish
Yederaw - የደራው
3 Sep, 23:00
Telegram'da ochish
Ulashish
Shikoyat qilish
Prev
Next
876
0
4
6
Yederaw - የደራው
3 Sep, 22:59
Telegram'da ochish
Ulashish
Shikoyat qilish
"My Seed" የተሰኘ የሞባይል ስልክ መተግበሪያ ይፋ ተደረገ!
በማህበራዊ ሚዲያ «ቲቸር ዳኒ» በሚል ስሙ የሚታወቀው መምህር ዳኛቸው ሻምበል፣ ተማሪዎች ባሉበት ቦታ ሆነው በስልካቸው በቀላሉ ትምህርት የሚከታተሉበትን "My Seed" የተሰኘ አዲስ የሞባይል መተግበሪያ ይፋ ማድረጉን ገለጸ።
መተግበሪያው በተለይም ከአምስተኛ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የተዘጋጀ ሲሆን በገጠርም ሆነ በከተማ የሚገኙ ተማሪዎችን በቴክኖሎጂ ታግዞ እኩል የትምህርት እድል ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ገልጿል።
በላይ የተጫነው ይህ መተግበሪያ ተማሪዎች የሀገሪቱን የትምህርት ካሪኩለም መሰረት ያደረጉ ትምህርቶችን አሰልቺ ባልሆነና ልክ እንደ ፊልም የተቃኙ ማራኪ ቪዲዮዎች አማካኝነት እንጅ በማድረግ እንዲማሩ ተደርጎ የተቃኘ ነው።
ከተለመዱት የትምህርት አይነቶች በተጨማሪ የመንፈስ ጥንካሬና አስተሳሰብን የሚያጎለብቱ የማይንደሴት ስልጠናዎችን እንዲሁም ተማሪዎች ወደፊት መሆን የሚፈልጉትን ሙያ እንደ ዶክተር ኢንጂነርና ፓይለት የመሳሰሉትን እንዲረዱ የሚያስችሉ ትምህርቶችን አካቷል።
አፕሊኬሽኑ በአሁኑ ወቅት በአማርኛ ቋንቋ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን ወደፊትም እያንዳንዱ ተማሪ በአፍ መፈቻ ቋንቋው እንዲማር ለማስቻል በሌሎች አራት የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች ተደራሽ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።
አፕሊኬሽኑን ተጠቃሚ ለማድረግ በቀረበው እቅድ መሰረት ተማሪዎች በወር 399 ብር ክፍያ በመፈፀም ሁሉንም የትምህርት አይነቶች ማስታወሻዎችንና የልምምድ ጥያቄዎችን ማግኘት ይችላሉ።
በተጨማሪም በኔትወርክ ችግር ምክንያት የዳታ እጥረት እንዳይገጥማቸው ቪዲዮዎችን አንድ ጊዜ ዳውንሎድ በማድረግ ያለ ኢንተርኔት ኮኔክሽን መከታተል የሚችሉበት አሰራር የተዘረጋ ሲሆን በቅርቡም ሙሉ በሙሉ ዳታ በማይስፈልግበት መልኩ አገልግሎቱን ለማስፋፋት እየሰራ መሆኑን መምህር ዳኛቸው አስታውቋል።
ተማሪዎችን ለማበረታታትም በአመቱ መጨረሻ የተሻለ ውጤት የሚያስመዘግቡ ተጠቃሚዎችን በልዩ መስፈርት በመምረጥ የመኪና ሽልማት የሚያበረክት "መማር ያሸልማል" የተሰኘ ፕሮግራም ማዘጋጀቱ ተገልጿል።
860
0
3
4
Yederaw - የደራው
3 Sep, 22:59
Telegram'da ochish
Ulashish
Shikoyat qilish
Prev
Next
569
0
1
Yederaw - የደራው
3 Sep, 22:58
Telegram'da ochish
Ulashish
Shikoyat qilish
ኦርቢክስ ቴክኖሎጂስ የኢትዮጵያን ከተሞች የሚያዘምኑ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን ይፋ አደረገ
በኢትዮጵያ ከተሞች እየታየ ያለውን ፈጣን እድገትና የመሰረተ ልማት ስፋት ተከትሎ፣ የዜጎችን የእለት ተእለት ህይወት እና የአገልግሎት አሰጣጥን የሚያቀልሉ አዳዲስ የቴክኖሎጂ መፍትሄዎችን ይዞ መውጣቱን ኦርቢክስ ቴክኖሎጂስ አስታወቀ።
የኦርቢክስ ቴክኖሎጂስ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ስዩም ተስፋዬ እንደገለጹት፣ ድርጅታቸው እንደ ስታርትአፕ ካምፓኒ የዜጎችን እለታዊ እንግልት የሚቀንሱ እና ከተሞችን ዘመናዊ የሚያደርጉ አራት ዋና ዋና የቴክኖሎጂ አሰራሮችን አስተዋውቋል።
እንደ አቶ ስዩም ማብራሪያ፣ የመጀመሪያው የቴክኖሎጂ መፍትሄ የመኪና ማቆሚያ ወይም የፓርኪንግ ችግርን የሚያቃልል ነው። በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባም ሆነ በሌሎች ዋና ዋና ከተሞች የተገነቡ የፓርኪንግ ቦታዎች ቢኖሩም፣ አሽከርካሪዎች በቅጽበት ትክክለኛውን መረጃ ለማግኘት እንደሚቸገሩ ጠቁመዋል።
ኦርቢክስ የሰራው ስርዓት ግን የግል እና የመንግስት የፓርኪንግ ቦታዎችን ወደ አንድ ማዕከላዊ የመረጃ ቋት በማምጣት አሽከርካሪዎች ባሉበት ሆነው ክፍት ቦታዎችን በስልካቸው እንዲያዩ፣ እንዲይዙ እና ያለምንም ሰው ንክኪ በራሳቸው አገልግሎት አግኝተው እንዲወጡ ያስችላቸዋል ብለዋል።
ሌላው ሁለተኛው ስራ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የኃይል መሙያ ወይም የቻርጂንግ ስርዓትን ማዕከላዊ ማድረግ ሲሆን ኢትዮጵያ እስከ 2030 ድረስ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ወደ ስራ ለማስገባት እና በርካታ የኃይል መሙያ ጣቢያዎችን ለመገንባት ባስቀመጠችው እቅድ መሰረት፣ አገልግሎቱ በተበታተነ መልኩ እንዳይሰጥ "ኦርቢክስ ኢቪ "የተሰኘ የተቀናጀ መተግበሪያ አልምቷል።
አቶ ስዩም አክለውም፣ ይህ ስርዓት ተጠቃሚዎች በአንድ መተግበሪያ ብቻ የትኛውም ቦታ የሚገኝ የኃይል መሙያ ጣቢያን እንዲጠቀሙ ከማድረጉም በላይ፣ የአገሪቱን የኢነርጂ መረጃ ደህንነት በአገር ውስጥ የመረጃ ቋት ውስጥ ጠብቆ ለማቆየት እና የመንግስት አካላት የኃይል ፍጆታውን በአንድ ማዕከል እንዲከታተሉ የሚያስችል እንደሆነ ገልጸዋል።
በሶስተኛ ደረጃ የቀረበው «አይ ሀብ» የተሰኘው የዜጎችና የመንግስት ግንኙነት ማጠናከሪያ መድረክ ሲሆን፣ ነዋሪዎች በመንገድ፣ በኤሌክትሪክ፣ በትራፊክ በድንገተኛ አደጋዎች ላይ የሚያዩአቸውን ችግሮች እና መረጃዎች በስልካቸው ለሚመለከተው የመንግስት አካል በቀጥታ እንዲያደርሱ ያደርጋል።
ስርዓቱ መረጃዎችን በየአካባቢው ክልል በመለየት እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት በመተንተን ለአስፈጻሚ አካላት የሚልክ በመሆኑ፣ ለቀረቡት ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እና በህዝብና በመንግስት መካከል ያለውን እምነት ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
«ኢትዮ ፓርክስ» የተሰኘው አራተኛው የቴክኖሎጂ ማዕቀፍ፣ በከተሞችና ከከተሞች ውጭ ያሉ የተፈጥሮ፣ የባህል እና የቪዲዮ መዝናኛ ቦታዎችን ዲጂታላይዝ በማድረግ ለአገር ውስጥ እና ለውጭ ሀገር ጎብኚዎች የሚያቀርብ ነው።
ተጠቃሚዎች የፓርኮችን መረጃ፣ የሚሰጡትን አገልግሎት እና የመግቢያ ክፍያዎችን አስቀድመው በመተግበሪያው በማጠናቀቅ የሚፈልጉትን መዝናኛ በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ።
አቶ ስዩም ተስፋዬ ሲደመድሙ፣ ኦርቢክስ ተራ መተግበሪያ ሳይሆን አጠቃላይ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን የሚደግፍ እና ወደፊት ወደ ሌሎች የአፍሪካ አገራት ለማስፋፋት የታቀደ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ምህዳር መሆኑን አብራርተዋል።
📸 ከበደ መክብብ
672
0
0
2
Yederaw - የደራው
27 Aug, 07:54
Telegram'da ochish
Ulashish
Shikoyat qilish
Prev
Next
827
0
2
Yederaw - የደራው
27 Aug, 07:52
Telegram'da ochish
Ulashish
Shikoyat qilish
"ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ" እስከ 30 በመቶ የሚደርስ ልዩ የበዓል ቅናሽ ይፋ አደረገ
#Ethiopia | በቀድሞ ስያሜው ያሥሚን ጀማል ኮንስትራክሽን በመባል የሚታወቀውና በግንባታው ዘርፍ አዲስ የጥራትና የፍጥነት መለኪያ ያስቀመጠው ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ መጪውን የ2019 አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለደንበኞቹ እስከ 30 በመቶ የሚደርስ ልዩ የበዓል ቅናሽ ማዘጋጀቱን ገልጿል።
የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኑረዲን መሐመድ በሰጡት መግለጫ በቦሌ አትላስ ሳይት የመሬት ደጋፊ (ሾሪንግ) ሥራ መጠናቀቁን እና በካዛንቺስ ሳይት አምስት የቤዝመንት ደረጃዎች አልቀው ህንፃው ግራውንድ ወለል ላይ መድረሱን ተክቶ አዳዲስ የመኖሪያና የንግድ ፕሮጀክቶችን ለገበያ ማቅረባቸውን አሳውቀዋል።
በዚህም መሠረት ከ55 ካሬ ሜትር ስቱዲዮ እስከ 165 ካሬ ሜትር ባለ 3 መኝታ አፓርትመንቶች እንዲሁም የንግድ ሱቆች በካሬ ሜትር ከብር 80,500 ጀምሮ ለሽያጭ የቀረቡ ሲሆን ይህ ልዩ ቅናሽ እስከ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ብቻ የሚቆይ ይሆናል።
ድርጅቱ ደንበኞቹን ከገበያ የዋጋ ንረት ለመጠበቅ የ"ዋጋ ዋስትና" አሰራር መዘርጋቱን የገለጸ ሲሆን በዚህም መሠረት በግንባታ ወቅት የውጭ ምንዛሬ ጭማሪም ሆነ የቁሳቁስ ዋጋ መወደድ ቢከሰት ደንበኞች በተዋዋሉበት የኢትዮጵያ ብር መጠን ብቻ ክፍያቸውን ፈጽመው በወቅቱ ቤታቸውን የሚያረከቡ ይሆናል።
የሀገር ውስጥ እና የቻይና ባለሙያዎችን በማጣመር አያት፣ ልደታ፣ ቦሌ እና ወዳጅነት ፓርክ ፊትለፊት በርካታ ህንፃዎችን በመገንባት ላይ የሚገኘው ተቋሙ፣ በቀጣዮቹ 10 ዓመታት በሀገሪቱ የሪል ስቴት ዘርፍ ቀዳሚ ከሆኑ ተቋማት ተርታ ለመሰለፍ አልሞ እየሰራ ይገኛል።
በተጨማሪም ድርጅቱ የማኅበረሰብ ተሳትፎ ኃላፊነቱን ለመወጣት በአንድ የበጎ አድራጎት ተቋም እና ለሁለት ትምህርት ቤቶች ለሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
📸 ከበደ መክብብ
#HolidayDiscount #EthiopianNewYear #DiscountsEthiopia #EthiopianNewYear2019 #HouseForSaleAddis #ApartmentForSale
910
0
2
3
Yederaw - የደራው
16 Jun, 15:09
Telegram'da ochish
Ulashish
Shikoyat qilish
Prev
Next
1.1k
0
0
4
Yederaw - የደራው
16 Jun, 15:09
Telegram'da ochish
Ulashish
Shikoyat qilish
ዴልታ ኤስፒኤምዩ አካዳሚ ይፋዊ የምረቃ እና የምስረታ ስነ-ስርዓቱን አካሄደ
#Yederaw I በመዋቢያ እና የውበት ጥበብ (Aesthetics) ዘርፍ ላይ ያተኮረው የዴልታ ኤስፒኤምዩ አካዳሚ (DELTA SPMU ACADEMY) ይፋዊ የምረቃ እና ጋዜጣዊ መግለጫ ተካሄደ።
የዴልታ ኤስቴቲክስ ትሬይኒንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ ኤደን ካሳሁን በሰጡት ይፋዊ መግለጫ፣ ተቋሙ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ወጣቶች በተለይም ከዋና ከተማው ውጪ በየክልሎቹና በየገጠራማው አካባቢ ለሚኖሩ ዜጎች ተደራሽ የሚሆን ተግባራዊ እና ዘመናዊ የሙያ ስልጠናዎችን ለመስጠት ራዕይ ሰንቆ ስራ መጀመሩን ገልጸዋል።
በፕሮግራሙ ላይ እንደተገለጸው፣ ተቋሙ በውበት ጥበብ ዘርፍ የሚስተዋለውን የሰለጠነ የሰው ኃይል እጥረት ለመቅረፍ እና ወጣቶች የራሳቸውን የስራ እድል እንዲፈጥሩ ለማስቻል ያለመ ነው።
ዋና ስራ አስፈጻሚዋ በማብራሪያቸው “ስራን ለመፈለግ ብቻ ሳይሆን ስራን ለመፍጠር፣ ገቢን ለማግኘት ብቻ ሳይሆን ነጻነትን ለመቀናጀት፣ ክህሎትን ለመማር ብቻ ሳይሆን ህይወትን ለመለወጥ” በሚል መርህ ተቋሙ ወደ ስራ መግባቱን ጠቁመው፣ ዴልታ አካዳሚ ፍጹም ባይሆንም ስህተቶችን እየታረመ እና የአሰራር መንገዶችን እያሻሻለ ከማህበረሰቡ ጋር በቅንነት ለመስራት ቃል መግባቱን አስረድተዋል።
የዴልታ ኤስቴቲክስ ትምህርቱን 80 ፐርሰንት በኦንላይን ሲሆን 20 ፐርሰንት በተግባር ይሰጣል ተብሏል።
በመግለጫው ማጠቃለያ ላይ ተቋሙ ለወደፊት ተማሪዎቹ፣ ለደጋፊዎቹ እና ለሽርክና አጋሮቹ ምስጋናውን ያቀረበ ሲሆን፣ ይህ የምስረታ ታሪክ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ወጣቶች አዲስ የስራ እድል እና የክህሎት በር የሚከፍት መሆኑም ተመልክቷል። በፕሮግራሙ ላይ ላይ የክብር እንግዳ በመሆን የሜሪጆይ መስራች ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፏል።
1.1k
0
0
2
8
ta oxirgi post ko‘rsatilgan.
Yana ko‘rsatilsin
16 725
obunachilar
Kanal statistikasi
Kanalda mashhur
#5383 post: Rasm
"ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ" እስከ 30 በመቶ የሚደርስ ልዩ የበዓል ቅናሽ ይፋ አደረገ #Ethiopia | በቀድሞ ስያሜው ያሥሚን ጀማል ኮንስትራክሽን በመባል...
#5398 post: Rasm
"My Seed" የተሰኘ የሞባይል ስልክ መተግበሪያ ይፋ ተደረገ! በማህበራዊ ሚዲያ «ቲቸር ዳኒ» በሚል ስሙ የሚታወቀው መምህር ዳኛቸው ሻምበል፣ ተማሪ...
ኦርቢክስ ቴክኖሎጂስ የኢትዮጵያን ከተሞች የሚያዘምኑ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን ይፋ አደረገ በኢትዮጵያ ከተሞች እየታየ ያለውን ፈጣን እድገትና የመሰረተ ...