የገዢ ቁጣ ሲነድ በላዬ፤
ፍንክች ላልል ላለቅ ስፍራዬን፤
በትዕግስት ስፋት መቆየት ላደርግ፤
ታላቁን ጥፋት ጸጥ እስክታደርግ፤
እንድኖር በቃልህ ልቤን አስፋልኝ፤
ቀን እስኪመጣ እስክትፈርድልኝ፤
ያደከመኝን እስክታደክመው፤
የበቀል ጣትህን አይኔ እስኪያየው፤
ድቅድቁን ስታዝ አይቀር መንጋቱ፤
ጎህ ሊቀድልኝ ሊያልፍ ለሊቱ፤
የቀረ ይመስላል አንዲት እርምጃ፤
ተራራው ሊናድ ሊሆን መሄጃ።
የወጀቡ አዛዥ የተራራው ሰሪ፤
የሸለቆው ጌታ ለጨለማው መሪ፤
የማዕበሉ አዝማች የመብረቁ ንጉስ፤
አንተ ነህ የእኔ አባት የእስራኤል ቅዱስ።
አሜን - አስቴር አበበ
▸ Albastros.com
@Yedestaye_Elilta
ፍንክች ላልል ላለቅ ስፍራዬን፤
በትዕግስት ስፋት መቆየት ላደርግ፤
ታላቁን ጥፋት ጸጥ እስክታደርግ፤
እንድኖር በቃልህ ልቤን አስፋልኝ፤
ቀን እስኪመጣ እስክትፈርድልኝ፤
ያደከመኝን እስክታደክመው፤
የበቀል ጣትህን አይኔ እስኪያየው፤
ድቅድቁን ስታዝ አይቀር መንጋቱ፤
ጎህ ሊቀድልኝ ሊያልፍ ለሊቱ፤
የቀረ ይመስላል አንዲት እርምጃ፤
ተራራው ሊናድ ሊሆን መሄጃ።
የወጀቡ አዛዥ የተራራው ሰሪ፤
የሸለቆው ጌታ ለጨለማው መሪ፤
የማዕበሉ አዝማች የመብረቁ ንጉስ፤
አንተ ነህ የእኔ አባት የእስራኤል ቅዱስ።
አሜን - አስቴር አበበ
▸ Albastros.com
@Yedestaye_Elilta