ጥምቀተ ክርስቶስ
በሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ
ጥር ፲ ቀን፳፻፱
ክፍል ሦስት (፫)
ጌታችን ጥምቀቱን በውኀ ያደረገው በሌላ ያላደረገው ስለምንድን ነው ቢሉ ትንቢቱ፣ ምሳሌው ሊፈጸም፤
ትንቢት፦"ወእነዝኃክሙ በማይ ወትነጽሑ፤ ጥሩ ውኃንም እረጭባችኋለሁ፤ እናንተም ትጠራላችሁ፤"ተብሎ ተነግሯል ሕዝ.፳፮፥፳፭፡፡
ምሳሌ፦ ውኀ ለዅሉ አስፈላጊ ነው፡፡ ያለ ውኀ መኖር የሚችል የለም፡፡ ጥምቀትም ለዅሉም የሚገባ ሥርዓት ነው፡፡ ያለ ጥምቀት ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት አይቻልምና፡፡ ውኀ መልክ ያሳያል፤ መልክ ያለመልማል (ያጠራል)፡፡ ጥምቀትም መልክዐ ነፍስን ያሳያል፤ መልክዐ ነፍስን ያለመልማልና (ያጠራልና)፡፡
መንፈስ ቅዱስ በአምሳለ ርግብ ወርዶ በራሱ ላይ ሲቀመጥበት አየ፡፡ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል መውረዱም ምሥጢር አለው
ርግብ ኃዳጊተ በቀል ናት፤ መንፈስ ቅዱስም ኃዳጌ በቀል ነውና፡፡ ርግብ በኖኅ ጊዜ 'ሐጸ ማየ አይኅ ነትገ ማየ አይኅ፤ የጥፋት ውኀ ጎደለ' ስትል ቆጽለ ዕፀ ዘይት ይዛ ተገኝታለች፡፡ መንፈስ ቅዱስም ተስፋ መስቀልን ያበሥራልና፡፡
ጥምቀቱን በቀን ያላደረገው በሌሊት ያደረገው ስለ ምን ነው ቢሉ
በቀን አድርጎት ቢኾን መንፈስ ቅዱስ በቁሙ ርግብ ነው በተባለ ነበርና፤ አሁንስ ርግብ አለመኾኑ መንፈስ ቅዱስ መኾኑ በምን ይታወቃል ቢሉ ጌታ የተጠመቀው ከሌሊቱ በዐሥረኛው ሰዓት ነው፡፡ በዚያን ጊዜ ተሐዋስያን ወፎች (ርግቦች) ከየቦታቸው አይወጡምና መንፈስ ቅዱስ መኾኑ በዚህ ይታወቃል፡፡
መንፈስ ቅዱስም መውረዱ ከውኀው ከወጣ፣ ከዮሐንስ ከተለየ በኋላ ነው፡፡
ከውኀው ውስጥ ሳለ ወርዶ ቢኾን ለቀድሶተ ማያት ነው የወረደው ባሉት ነበርና፡፡ ከዮሐንስ ጋርም ሳለ ወርዶ ቢኾን ለክብረ ዮሐንስ ወረደ ባሉት ነበርና፡፡
ረቦ ወርዷል ያሉ እንደ ኾነ አብ ምሉዕ ነው፤ አንተም ምሉዕ ነህ፤ እኔም ምሉዕ ነኝ ሲል፡፡ አሰይፎ ወርዷል ያሉ እንደ ኾነ የብሉየ መዋዕል የአብ ሕይወት ነኝ፤ የአንተም ሕይወት ነኝ፤ እኔም ብሉየ መዋዕል ነኝ ሲል፡፡
ወርዶ ራሱን ቆንጠጥ አድርጎ ይዞታል ቢሉ አብ አኃዜ ዓለም ነው፤ አንተም አኃዜ ዓለም ነህ፤ እኔም አኃዜ ዓለም ነኝ ሲል፡፡ ምሥጢሩም እናንተም ብትጠመቁ መንፈስ ቅዱስ ይወርድላችኋል ለማለት፣ አብነት ለመኾን ነው፡፡
"ወናሁ መጽአ ቃል እምሰማይ ዘይብል ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር ዘቦቱ ሠመርኩ፤" ለተዋሕዶ የመረጥኩት በእርሱ ህልው ኾኜ ልገለጥበት የወደድኩት የባሕርይ ልጄ ይህ ነው፤ የሚል ቃል ከወደ ሰማይ ተሰማ፡፡
ይህም አብ የተናገረበት ቃል ያው የሚጠመቀው አካላዊ ቃል ነው እንጂ ሌላ ቃል አይደለም፡፡ የሥላሴ ልብ፣ ቃል፣ እስትንፋስ አንድ ነውና፡፡ አብ ልብ፤ ወልድ ቃል፤ መንፈስቅዱስ እስትንፋስ በመኾን አንድ አምላክ ነውና፡፡ "አብኒ ልቡናሆሙ ለወልድ ወለመንፈስ ቅዱስ ወልድኒ ቃሎሙ ለአብ ወለመንፈስቅዱስ ወመንፈስቅዱስኒ እስትንፋሶሙ ለአብ ወለወልድ፤ አብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ልቡናቸው ነው፡፡ ወልድም ለአብ ለመንፈስ ቅዱስ ቃላቸው ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስም ለአብ ለወልድ ሕይወታቸው ነው፤"በማለት ጎርጎርዮስ ነባቤ መለኮት እንደ ተናገረው፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀውም በሠላሳ ዓመቱ ነው" ሉቃ. ፫፥፳፫፡፡
በሠላሳ ዓመቱ የተጠመቀበት ምሥጢርም
አዳም የሠላሳ ዓመት፤ ሔዋን የዐሥራ አምስት ዓመት ሰው ኾነው ተፈጥረው አዳም በዐርባ ቀን፣ ሔዋን በሰማንያ ቀን ከሥላሴ የተቀበሉትን ልጅነት በምክረ ከይሲ ዕፀ በለስን በልተው አስወስደው ነበረና በሠላሳ ዓመቱ ተጠምቆ መልሶላቸዋል፡፡
በሠላሳ ዓመት የመጠመቁ ምሥጢር ይህ ሲኾን እኛ ዛሬ ወንዶች በዐርባ ቀን፣ ሴቶች በሰማንያ ቀን በዕለተ ዓርብ ከቀኝ ጎኑ በፈሰሰው ማየ ገቦ ተጠምቀን ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ ሁለተኛ የምንወለድበት ምክንያትም አዳም በዐርባ ቀኑ፣ ሔዋን በሰማንያ ቀኗ ከሥላሴ ያገኙትን ልጅነት መሠረት በማድረግ ነው።
ኩፋ. ፬፥፱
የምንጠመቀውም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነው፡፡ "ወእንዘ ታጠምቅዎሙ በሉ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ ስታጠምቋቸውም በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቋቸው፤"እንዲል ማቴ. ፳፰፥፲፱
ዛሬም ታቦታቱን ወደ ጥምቀተ ባሕር በማውረድ በዓለ ጥምቀቱን ለሚያከብሩ ክርስቲያኖች በሙሉ ከታቦታቱ ሁለት ሺሕ ክንድ ርቀው መከተል እንዲገባቸው በመጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ተብሎ ተገልጿል፤ "ሕዝቡን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ ከሰፈራችሁ ተነሥታችሁ ተከተሉት፡፡ በእናንተና በታቦቱ መካከል ያለውርቀት በስፍር ሁለት ሺሕ ክንድ ይኹን፡፡ በዚህ መንገድ በፊት አልሔዳችሁበትምና፤ የምትሔዱበትን መንገድ እንድታውቁ ወደ ታቦቱ አትቅረቡ፤።"
ኢያ.፫፥፩–፲፯
ይህ ኃይለ ቃል ዛሬ ታቦታቱ ወደ ጥምቀተ ባሕር ወርደው ለማደራቸው መነሻ ትምህርት ነው፡፡ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀትም ጌታችን ከተጠመቀበት ከ፴ ዓመተ ምሕረት ጀምሮ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ በየዓመቱ ጥር ፲፩ ቀን ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ ሲከበር ይኖራል፡፡
"ጌትነቱን ገለጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ፤"
ዮሐ. ፪፥፲፩
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የበዐላት አከባበር ቀመር ከበዓለ ልደት፣ ግዝረት እና ጥምቀት ቀጥሎ ቃና ዘገሊላ ይከበራል፡፡
ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ለማዳን ወደዚህ ዓለም በመጣበት ወቅት ልዩ ልዩ ድንቅ ተአምራትን አድርጓል፡፡ ከእነዚህ መካከልም....
ክፍል አራት ይቀጥላል...
🙏 ይቆየን 🙏
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@yemezmur_gexem