✞ ጥምቀተ ክርስቶስ ✞
በሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ
ጥር ፲ ቀን፳፻፱
ክፍል አራት (፬)
"ጌትነቱን ገለጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ፤"
ዮሐ. ፪፥፲፩
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የበዐላት አከባበር ቀመር ከበዓለ ልደት፣ ግዝረት እና ጥምቀት ቀጥሎ ቃና ዘገሊላ ይከበራል፡፡
ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ለማዳን ወደዚህ ዓለም በመጣበት ወቅት ልዩ ልዩ ድንቅ ተአምራትን አድርጓል፡፡
ከእነዚህ መካከልም በቃና ዘገሊላ በሰርግ ቤት ተገኝቶ ያደረገው ተአምር ተጠቃሽ ነው፡፡
ይህንንም ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ እንዲህ ጽፎታል፤"በሦስተኛው ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ኾነ፡፡" ምን በተደረገ በሦስተኛው ቀን የሚል ጥያቄ በኹላችንም አእምሮ እንደሚመላለስ አያጠያይቅም፡፡
ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማየ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ ጥር ፲፩ ቀን ተጠምቆ ሳይውል ሳያድር ዕለቱን ገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ ዐርባ መዓልትና ዐርባ ሌሊት ጾሞ፤ ዲያብሎስን ድል ነስቶ፤ መዋዕለ ጾሙን ፈጽሞ፤ ለእኛም ዲያብሎስን ድል የምንነሳበትን መንገድ አሳይቶ ከገዳመ ቆሮንቶስ መልስ ደቀ መዛሙርቱን መረጠ፡፡
ከጥር ፲፩ እስከ የካቲት ፳ ቀን ያለው ጊዜ ፵ ቀን ይኾናል፡፡ ጌታችን መዋዕለ ጾሙን የካቲት ፳ ቀን ፈጽሞ በወጣ በሦስተኛው ቀን በገሊላ አውራጃ ቃና በተባለች መንደር ሰርግ ኾነ፡፡
በዚህ ሰርግ ብዙ ሰዎች መታደማቸውን ወይን ጠጁ ማለቅ ያስረዳናል፡፡ የተጠሩት ሰዎች ብዙ ለመኾናቸው ባሻገር ብዙዎችን መመገብ የሚችል አምላክ በሰርግ ቤት መጠራቱ ልዩ ዕለቱን ያደርገዋል፡፡ በዚህ ሰርግ ከሰዎች በተጨማሪ ሦስት አካላት ተጠርተዋል፡፡
፩.ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
"ወጸውዕዎ ለእግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ጌታ ኢየሱስንም ጠሩት"
ዮሐ.፪፥፪
ተብሎ እንደ ተጻፈ እናትን ጠርቶ ልጅን መተው ተገቢ አይደለምና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ጠርተው ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስንም ጠርተውታል፡፡
ይህም ፍጹም ሰው መኾኑን
ያስረዳል።ጌታችን እንደ ሰውነቱ ወደ ሰርግ ቤት ተጠራ፤ እንደ አምላክነቱ ተአምራቱን በማሳየት ጌትነቱን፣ አምላክነቱን ገለጠ፡፡
ከሚደሰቱት ጋር መደሰት፤ ከሚያዝኑት ጋር ማዘን ተገቢ መኾኑን መድኀኒታችን ክርስቶስ በተግባር አስተማረን፡፡
በቃና ዘገሊላ ከሰርግ ቤት እንደ ሔደው በአልዓዛር ቤት ለለቅሶ መገኘቱን ልብ ይሏል፡፡ ወደ ሰርግ ቤት የሔደው በደስታ ነበር፡፡ "ሖረ ኢየሱስ በትፍሥሕት ውስተ ከብካብ እንዘ ይገብር ተአምረ ወመንክረ በውስተ አሕዛብ፤ ኢየሱስ በአሕዛብ ፊት ተአምራትንና ድንቆችንእያደረገ በደስታ ወደ ሰርግ ሔደ፤"በማለት ቅዱስ ያሬድ እንደ ገለጠው፡፡
ጌታችን ወደ አልዓዛር ቤት ሲሔድ ግን በኀዘን ውስጥ ኾኖ ነበር፡፡"ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እርሷ (ማርታ) ስታለቅስ ባየ ጊዜ በልቡ አዘነ፤ በራሱም ታወከ (ራሱን ነቀነቀ – የኀዘን ነው) ዕንባውን አፈሰሰ፡፡ አይሁድም ‹ምን ያህል ይወደው እንደ ነበር እዩ› አሉ፤"
እንዳለ ወንጌላዊው ዮሐ.፲፩፥፴፫-፴፰
ጌታችን "አምላክ ነኝና ከሰርግ ቤት አልሔድም፤ ከልቅሶም ቤትም አልገኝም፤" አላለም፡፡ ከዚህም ጌታችን ከኀጢአት በቀር የሰውነትን ሥራ እንደ ሠራ፤ የሰውን የተፈጥሮ ሕግ እንዳከበረ እና እንደ ፈጸመ እንረዳለን፡፡
በመደሰት እና በማዘን ፍጹም ሰው መኾኑን፤ በሰርጉ ቤት ውኀውን የወይን ጠጅ በማድረግ፤ እንደዚሁም አልዓዛርን ከአራት ቀናት በኋላ ከሞት በማስነሣት ደግሞ ፍጹም አምላክ መኾኑን አስረዳን፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ነውና በሰርግ ቤት የጎደለውን መላ፡፡ አምላክ ነውና የሞተውን አልዓዛርን "መግነዝ ፍቱልኝ? መቃብር ክፈቱልኝ? ሳይል" ከሞት እንዲነሣ አደረገ፡፡
"ወሶበ ኀልቀ ወይኖሙ ወትቤሎ እሙ ወይንኬ አልቦሙ፤ የወይን ጠጅ ባለቀባቸው ጊዜም እናቱ (እመቤታችን) 'የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም' አለችው።ዮሐ ፫፥፫
እርሱም "አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም፤" አላት፡፡
ይኸውም "ያልሽውን ልፈጽም ነው ሰው የኾንኩት፤ ያልሽኝን እንዳልፈጽም ከአንቺ ጋር ምን ጠብ አለኝ?"ማለት ነው፡፡ ‹ጊዜዬ ገናአልደረሰም› የሚለው ቃልም ጌታችን ሥራውን ያለ ጊዜው እንደማይፈጽመው ያሳያል፡፡
"ለእግዚአብሔር የሥራ ጊዜ አለው፤" እንዲል
መዝ.፻፲፰፥፻፳፮
በሌላ መልኩ "ጊዜዬ ገና አልደረሰም" የሚለው ቃል እግዚአብሔር አምላካችን ይህን አድርግ ብሎ በግድ ማንም ሊያዝዘው የማይቻለውና በራሱ ፈቃድ የወደደውን ዂሉ የሚያደርግ፤ ቢፈልግ የሚያዘገይ፣ ሲፈልግ ደግሞ በዐይን ጥቅሻ በፈጠነ መልኩ መፈጸም የሚችል፤ በራሱ ፈቃድ እንጂ በሰምች ፈቃድ የማይመራ አምላክ መኾኑን ያስተምረናል፡፡
"ፈቃድህ በሰማይ እንደ ኾነችእንዲሁ በምድር ትኹን" ብላችሁ ለምኑኝ ያለውም ለዚህ ነው፡፡
የወይን ጠጁም ሙሉ ለሙሉ አላላቀም ነበር፡፡ ምክንያቱም ጌታችን ያለውን ቢያበረክተው ተአምራቱን አናደንቅም የሚሉ ይኖራሉና ፈጽሞ ጭልጥ ብሎ እስከሚያልቅ ድረስ መጠበቅ እንደሚገባ ሲያስረዳ 'ጊዜዬ ገና አልደረሰም' አለ፡፡
ሰው ቢለምን፣ ቢማልድም እግዚአብሔር በእርሱ ፈቃድ ጊዜው ሲደርስ ነው የሚፈጽመው፡፡ ምልጃው አልተሰማም፤ ተቀባይነት አላገኝም ማለት ግን አይደለም፡፡ ተቀባይነት ያገኘ መኾኑ የሚታወቀው በመደረጉ ነውና፡፡
ተማላጅነት የአምላክ፤ አማላጅነት ደግሞ የፍጡራን መኾኑን ጌታችን በዚህ ሰርግ ቤት አስተምሯል፡፡ ጌታችን በሰርግ ቤት ባይገኝላቸው ኖሮ ሰዎቹ ምን ያህል ኀፍረት ይሰማቸው ይኾን? የእርሱ እንደዚሁም የእናቱ በሰርጉ ቤት መገኘት ለባለ ሰርጉና ለታዳሚዎች ሙላት ነበር፡፡
እርሱ ባይኖር የሰርጉ ቤት ከደስታ ይልቅ በኀዘን ሊሞላ ይችል እንደ ነበር ምንም ጥርጥር የለውም፡፡
አማላጅ ያስፈለገውም እርሱ የማያውቀው ምሥጢር ኖሮ፤ ሥራውን የሚሠራውም በስማ በለው ኾኖ አይደለም፡፡
ለሰው ልጆች ያለው ፍቅር ይታወቅ ዘንድ እና የሰው ልጆችን ከችግር የሚያወጣበት መንገዱ ብዙ መኾኑን ለማስረዳት ነው እንጂ፡፡
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሚዜዎችን 'ኵሎ ዘይቤለክሙ ግበሩ፤ ያዘዛችሁን ዂሉ አድርጉ፤' ማለቷ "አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?" የሚለው የጌታችን መልስ እሺታን (ይኹንታን) የሚገልጽ ቃል መኾኑን ያስረዳል፡፡
ጌታችንም "ውኃ ቅዱና ጋኖችን ምሏቸው"ባላቸው ጊዜ...
ክፍል አምስት ይቀጥላል...
🙏 ይቆየን 🙏
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@yemezmur_gexem