ነብዩሏህ ሷሊህ_(ዐ,ሰ)
ክፍል2⃣
ዘጠኝ ሁነው ግመሏ ውሀ
የምትጠጣበት ስፍራ ደረሱ።
ውሀው ዘንድም ደረሱ'ና በያዙት ሰይፍ ገደሏት።ከአጠገቧ ግልገሏ ነበር'ና
ግልገሏንም አሳድደው በትልቅ ተራራ ላይ ይዘውት ገደሉት።ከሙጅሪምነታቸው
የተነሳ የግመሊቱን ስጋ ቀኑኑ ተከፋፈሉት።
ሳሊህም ዐ ሰ ይህን በተመለከተ ግዜ፦"አሁን የጌታችሁን ቅጣት
ተጠባበቁ።የጌታችሁ ቅጣት ከመውረዱም በፊት ስጋውን ተሎ ተሎ በልታችሁ
ጨርሱ" አላቸው።
ህዝቡም፦"አንተ ምን ዝም ብለህ ቅጣት ቅጣት እያልክ ትዝትብናለህ! እስቲ
አምጣ ቅጣት ምትለውን" ሲሉት
ሳሊህም፦"በዚህ 3 ቀን ውስጥ የጌታችሁ ቅጣት እናንተ ላይ ተፈፃሚ
ይሆናል።ለዚህም ማረጋገጫ ዛሬ ፊታችሁ ብጫ ይሆናል።ነገ ደሞ ቀይ
ይሆናል።ከነገ ወዲያ ደግሞ ጥቁር ይሆንና ትጠፋላችሁ ይህም ሀሰት የሌለው
ዛቻ ነው" አላቸው።
እነዚህ የሀፅያትን ፅዋ ጠጥተው የማይጠግቡ ህዝቦችም ሳሊህን ዐ ሰ
ለመግደል ወስነው ዝግጅታቸውን አጠናቀው ሳለ በመጀመርያ ግመሏን
በገደሉት ዘጠኙ ሰዎች ላይ እቤት ተደረመሰባቸው
ሳሊህም ዐ ሰ የእምነት ወንድም እህቶቹን ይዞ ወደ ፊለስጢን ምድር እንዲሸሸ
በአላህ ታዘዘ።
ሳሊህ እና ተከታዮቹ ተወልደው ያደጉበትን ምድር ትተው ወደ ፊለስጢን ምድር
መትመም ጀመሩ።
አሁን የአመፀኞቹ ህዝቦች ፊታቸው መቀያየር ጀምሯል።ሀሉም የፊቱ ብጫ
መሆን አስፈርቶት እርስ በርስ ይተያያል።
ሁለተኛው ቀን ደርሶ በነጋታው ሰዉ ሲነቃ ሁሉም ፊቱ ደም መስሏል።በድንጋጤ
የሞቱትም ብዙ ነበሩ።ያን ቀን በትካዜ እና በፍራቻ ካሳለፉ በኋላ የማይደርስ
የለም'ና ሶስተኛዋ ቀን መጣች።
ፊቶቻቸውን ጥቁረት ወረረው፣ተስፋም ቆረጡ ሁሉም በመሰባሰብ ከፈናቸውን
ለብሰው ሽቶ ተቀብተው ሞታቸውን መጠባበቅ ጀመሩ።
ልክ ፀሀይ ጀንበሯን ተሻግራ ብቅ ማለት ስትጀመር ከወደ ሰማይ በኩል
እንደመብረቅ ያለ ከፍተኛ ድምፅ ያለው ነገር መጣ።ምድርም በሀል
መንቀጥቀጥ ጀመረች...ጂብሪልም በከፍተኛ ድምፁ ጮኸባቸው።
ያን ግዜ ልቦቻቸው ከደረታቸው መበጣጠስ ጀመረ።አይኖቻቸውን ወደ ሰማይ
ያፈጣሉ...መቅሰፍቱ ከየት በኩል እንኳን እንደመጣ ማወቅ እየተሳናቸው
ነፍሶቻቸው ወደ ሰውነታቸው ዳግም ላትመለስ ተነጠለቻቸው።
የከተማይቱ ህዝብ ሁሉም በያሉበት በድን ሁነው ሲሞቱ አንዲት ሴት ብቻ
ቀረች ስሟም ከልባ ቢንት ሰለቅ ይባላል።ለሳሊህ ዐ ሰ ከፍተኛ ጥላቻ ሲኖታት
የክህደትን ዘውድ ከራሷ አኑራለች።
ይህን ስትመለከት እግሬ አውጭኝ ብላ ከሀገሩ ሸሸች። ብዙ ከተጓዘችም
በኋላ አንድ የዐረብ ነገድ የሚኖሩበትን መንደር ደረሰችና የሆነውን ሁሉ
ነገረቻቸው።በመጨረሻም ውሀ እንዲያጠጧት ጠይቃ ልክ ውሀውን
ስትቀምሰው ነፍሷ የሙታንን መንደር ተቀላቀለች።
ሳሊህ ደግሞ በፊለስጢን ምድር ትንሽ ካሳለፉ በኋላ ወደ መካ ሄደው እዛው
ጌታቸውን ማምለክ ጀመሩ። በመጨረሻም በ58 አመታቸው የዚህችን አለም
ጣጣ አጠናቅቀው ነፍሳቸውን ለጌታቸው አስረከቡ።
.....❀━┅┉┈ተፈፀመ┈┉┅━❀
በነገራችን ላይ ረሱላችን (ሰዐወ) አንድ ቀን ለተቡክ ዘመቻ ባልደረቦቻቸውን
ይዘው በመሄድ ላይ ሳሉ የሳሊህ ህዝቦች የጠፉበትን ከተማ ደረሱ።ማንም
አይኖርበትም...ከዚያም ነቢያችን ሰ ዐ ሰ፦"ይህችን ከተማ ስትገቡ
እያለቀሳችሁ እንጂ ዝም ብላችሁ እንዳትገቡ።እኔ በነሱ የወረደው በላእ
እናንተን እንዲያገኝብኝ አልፈልግም" አሏቸው።ፊዳከ አቢ ወ ኡም ወነፍሲ
ወደሚ ወዒርዲ ያ ረሱሉላህ
በዚያ አከባቢም ያሉ ነገሮችን ሁሉ ለባልደረቦቻቸው አሳይዋቸው።ግመሏም
የወጣችበትን እና የተገደለችበትንም ቦታ ወስደው አሳይዋቸው።
___________________________________
ምንጮቻችን፦
ﺍﻟﻘﺮﺀﺍﻥ ﺍﻟﻜﺮﻳﻢ
ﺍﻟﺒﺪﺍﻳﺔ ﻭﺍﻟﻨﻬﺎﻳﺔ / ﺍﻟﺠﺰﺀ ﺍﻷﻭﻝ /
ﺻﺤﻴﺢ ﻣﺴﻠﻢ
ﺻﺤﻴﺢ ﺍﻟﺒﺨﺎﺭﻱ
ኢንሽአላህ ምርጥ የአላህ ወዳጅ የሆኑት የ'ኢብራሂም(ዐ,ሰ)ታሪክ
ይ.......ቀ....ጥ......ላ.....ል፡፡
ሌሎች የነብያት፣ የሰሃቦች ታሪክ ና የተለያዪ ትምህርታዊ ፅሁፉች ቶሎ ቶሎ
እንዲደርሶ ከስር ሊንኩን በመክፈት ግሩፑን ይቀላቀሉ እርሶ ጋር እንዲቀመጥ
አይፍቀዱ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ።
👉🏻@yenebiyattaric
@yenebiyattaric