"... ትገርመኛለህ..."
የሚያባራ ሳቋን ፍሬን እየያዘች... ከእዝነት ይሁን ከሳቅ ብዛት ከሚያባብሉ አይኖቿ ዳር ኮለል ያሉ እንባዎቿን እያበሰች ... በትኩስ እንባ ሰበብ ቀልተው እንጆሪ የመሰሉ ጉንጮቿን እያደራረቀች... ደም ያጋተ የታች ከንፈሯን ላመል እየነከሰች... ባይኖቿ የሚሸሻትን ገፄን እያሳደደች...
(... ይህን ተተንትኖ የማያልቅ የገፅዋን ጣዕም... ሳያት ባፌ ሃምራዊ ሳቅ የሚሞላኝን... እዚህ አልፃፍኩትም... )
..."ምኔ ይገርማል" አልኳት በዓይኗ እየተሳደድኩ...
"... ከደስታ ቀኖችህ የሃዘን ወይን ትቀዳለህ..."
"... ጥሩ ወይን ነው?..."
"... ሚገርመኝ እሱ አይደል..."
"ምኑ?"
"... ሃዘን መጣፈጡ... "
... ዝም...
እንዳዘነች ነገር ... አንገቷን ትከሻዬ ላይ ሰበረች... ፀጉሯ አንገቴ ስር መዓዛውን ይነሰንሳል... ገርበብ ያሉ አይኖቿን አያለውሁ... የረሳችው የታች ከንፈሯን አያለሁ... ገላዬ ታርሶ እንደለሰለሰ የሃምሌ መሬት ዘር ሆና እንድትበተን ይጎመጃታል... የእግዜር ሞፈር ባበጀው ተረተር ወዟን እንድትዘራ... ሁለመናዋን ሁለመናዬው ውስጥ አቀፍኩት... መለኮታዊ መልዕክት እንደማደርስ ሁሉ... ክብርና ፍርሃት የሞላው መውደድ አዋስኳት...
... በለሆሳስ እንዲህ አለቺኝ...
"እኔ ምልህ..."
"እ..."
"... ይሄ ምኑ ያሳዝናል?...”
|ዘካሪያስ|
°•.• @yenie_kal •.•°
@yenie_kal
○○○○○○○