የአእላፋት ዝማሬ | Melody of Myriads, [07/01/25, 2:22 pm]
[🖼 ሁለተኛው የአእላፋት ዝማሬ በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም በድምቀት ተካሔደ::
| ጃንደረባው ሚድያ | ታኅሣሥ 29 2017 ዓ.ም.|
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጠቅላይ ቤተ ክህነት በማኅበራት ምዝገባና ክትትል መምሪያ በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ የተዘጋጀው የአእላፋት ዝማሬ ለሁለተኛ ጊዜ በድምቀት ተካሔደ:: ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክን ጨምሮ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የትግራይ ማይጨውና የማኅበራት መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ቶማስ የአዊ ዞን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ አቡነ መቃሪዮስ የምዕራብ ካናዳ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ አቡነ ኤጲፋንዮስ የምሥራቅ ጉራጌ ሀገረ ስብከት ጳጳስ
የመምሪያ ኃላፊዎችና የአኃት አብያተ ክርስቲያናት ልዑካን ፣ አንጋፋ ዘማርያን በተገኙበት በዚህ የአእላፋት ዝማሬ ላይ ከአምናው በቁጥር እጅግ የበዛና ቅጽረ ቤተ ክርስቲያኑን አልፎ መንገዱን እስከ መዝጋት የደረሰ ሕዝበ ክርስቲያን በዝማሬው ላይ ታድሞ አምሽቶአል::
በመምህር ጳውሎስ መልክዓ ሥላሴ መሪነት በተካሔደው በዚህ ጉባኤ በተያዘው መርሐ ግብር መሠረት ከቀኑ ዐሥር ሰዓት ላይ ስለ ሀገራችን ሰላምና የተፈጥሮ አደጋዎች ጸሎተ ምሕላ በማድረግ የተጀመረ ሲሆን በቅዱስነታቸው መሪነት ጸሎተ ወንጌልና ኪዳን ደርሶ ተጀምሮአል:: በማስከተል የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አቅርበዋል:: በማስከተል የአእላፋት ዝማሬ የማብሠሪያ መዝሙር በቅዱስነታቸው ፊት ከተዘመረ በኋላ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የልደት በዓልን አስመልክቶ ትምህርተ ወንጌል ሠጥተው የአእላፋት ዝማሬን ማኅቶት ባርከው በመለኮስ አስጀምረው ዝማሬውን ባርከው ወደ መንበራቸው ተመልሰዋል:: የአእላፋት ዝማሬ ከአምናው በተለየ ዝግጅት የመድረኩን ቅርጽ በጥንታዊ ኢትዮጵያዊ ሥዕላት ያጌጡ ሲሆን ከመድረኩ ግርጌም ኢትዮጵያ ሁለቱን ኪዳናት እንደተቀበለች በሚያሳይ መንገድ ታቦተ ጽዮንና የጃንደረባው ሠረገላ ለእይታ ቀርበዋል::
የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ጃን አጋፋሪ የሴኪውሪቲ ኃላፊ ወ/ሪት ትዕሲት "ከተጠበቀው በላይ የምእመናን ቁጥር በዝማሬው ላይ በመገኘታቸው ምክንያት የፍተሻና የመስተንግዶ ሒደቱን ከአቅም በላይ ያደረገው ቢሆንም ምእመናን በትዕግሥትና በታዛዥነት የአእላፋት ዝማሬን ያማረ እንዲሆን ስላደረጉ ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርባለን" ያሉ ሲሆን "በቀጣይ ዓመት ከዘንድሮው በተሻለ መንገድ ለማካሔድ ከወዲሁ ዝግጅት እንደምንጀምር ቃል እንገባለን" ብለዋል::
የአእላፋት ዝማሬን በአካልና በኦንላይን ሚልዮኖች የታደሙበት ሲሆን የዘንድሮው አእላፋት ከአምናው በተለየ በርካታ ምእመናን በቦሌ ደብረ ሳሌም ቆይተው በማስቀደስ በቅዳሴ እንዲያጠናቅቁ መመሪያ የተሠጠበት ነበረ:: በዚህም መሠረት በርካታ ምእመናን እዚያው ቆይተው ያስቀደሱ ሲሆን ቤተ መቅደሱ ከሞላ የደረሱ ምእመናን ደግሞ በስክሪን ቅዳሴውን ተከታትለዋል:: የኢጃት ጃን ቅዳሴ ሰብሳቢ መምህር ኃይለ ኢየሱስ "ለ2018 ዓ.ም. የአእላፋት ዝማሬን ሙሉ በሙሉ ወደ አእላፋት ቅዳሴ ለማሸጋጋር በቅርብ ቀን የቅዳሴ ተሰጥኦ ትምህርት በጃንደረባው ሚድያ ስለምንጀምር ምእመናን ለመማር ዝግጁ ሆነው ይጠብቁን" ብለዋል:: የአእላፋት ዝማሬ በበርካታ ሀገር በቀልና ዓለም አቀፍ ሚድያዎች ሽፋን አግኝቶአል::]
ሁለተኛው የአእላፋት ዝማሬ በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም በድምቀት ተካሔደ::

የአእላፋት ዝማሬን በአካልና በኦንላይን ሚልዮኖች የታደሙበት ሲሆን የዘንድሮው አእላፋት ከአምናው በተለየ በርካታ ምእመናን በቦሌ ደብረ ሳሌም ቆይተው በማስቀደስ በቅዳሴ እንዲያጠናቅቁ መመሪያ የተሠጠበት ነበረ:: በዚህም መሠረት በርካታ ምእመናን እዚያው ቆይተው ያስቀደሱ ሲሆን ቤተ መቅደሱ ከሞላ የደረሱ ምእመናን ደግሞ በስክሪን ቅዳሴውን ተከታትለዋል:: የኢጃት ጃን ቅዳሴ ሰብሳቢ መምህር ኃይለ ኢየሱስ "ለ2018 ዓ.ም. የአእላፋት ዝማሬን ሙሉ በሙሉ ወደ አእላፋት ቅዳሴ ለማሸጋጋር በቅርብ ቀን የቅዳሴ ተሰጥኦ ትምህርት በጃንደረባው ሚድያ ስለምንጀምር ምእመናን ለመማር ዝግጁ ሆነው ይጠብቁን" ብለዋል:: የአእላፋት ዝማሬ በበርካታ ሀገር በቀልና ዓለም አቀፍ ሚድያዎች ሽፋን አግኝቶአል::