ኬቨን ሃርት የተባለው ኮሜዲያን እዚህ የስኬት ጫፍ ላይ ከመድረሱ በፊት ብዙ መከራ ያሳለፈና አትችልም ተብሎ የተገፋ ሰው ሲሆን፣ ከሲንግል እናቱ ቤት ሥራ ፍለጋ ሲወጣ እናቱ የሰጡት ስጦታ መጽሐፍ ቅዱስ ነበር።
ኬቨን አንድ ቀን የሚመገበው አጥቶ በጣም ቸግሮት ለእናቱ ይደውላል፣ ''ማሚ ስራ ማግኘት አልቻልኩም እባክሽ እርጂኝ" አላቸው።
እናቱም "የሰጠውህን መጽሐፍ ቅዱስ አነበብክ ወይ?" ነበር መልሳቸው።
እርሱም "ራበኝ እያልኩሽ የምን መጻሕፍ ነው የምትይው" አላቸው።
"ልጄ! የሰጠሁህን መጻሕፍ ቅዱስን አንብበህ ቢሆን ኖሮ እኮ አይርብህም ነበር" አሉት።
ኬቨን አንብብ ያሉትን መጻሕፍ ቅዱስ ሳያነብ እናቱ በማኅፀን በር ካንሰር ያርፋሉ፣ እርሱም በዓለም ምርጡ ኮሜዲያን ውዱ አከተርም ከሆነ በኋላ አንድ ቀን የልጅነት ፎቶግራፎቹን ለፊልም ፈልጎ ሲበረብር ያንን እናቱ የሰጡትን መጻሕፍ ቅዱስንም ገለጠው፣ ውስጡ እናቱ ለስራ መፈለጊያና መጠነኛ ቤት መከራያ እንዲሆነው የተውለትን 1ሺ ዶላር አገኘ።
ገንዘቡ ለአሁኑ ኬቨን ምንም ብትሆንም እናቱ ግን ንብረታቸውን ሸጠው ነበር ለልጃቸው የሰጡት።
መጻሕፍት ውስጥ ብዙ መልሶች አሉና መጻሕፍትን እናንብብ። ቀና ብሎ በዕውቀት ለማውራት ብዙ አጎንብሶ ማንበብን ይጠይቃል።
(ፍፁም አብርሃም)