የነፃነት ጉዞ!
፨፨///////፨፨
የእውቀት ውሱንነት፣ የመረጃ እጦት፣ የብስለት ማነስ፣ የተነሳሽነት ችግር፣ በእራስ የመቆም ፍራቻ የነፃነታችን ዋነኛ ፀር ናቸው። የወረደ ህይወት እንድንኖር፣ በየጊዜው ለፈተና እንድንጋለጥ፣ ህይወታችን አቅጣጫ እንዲያጣ፣ ከአምናው ከካቻምናው የተሻለ ስፍራ እንዳንገኝ የሚያደርገን ትልቁ ነገር የእውቀት ማነስ ነው። አላዋቂ ይፈራል፣ አላዋቂ በሃሳቡ ብቻ ነገሮች የሚቀየሩ ይመስለዋል፤ አላዋቂ ነገሮች ሁሉ በምኞት እንዲከናወኑለት የሚጠብቅ አይነት ሰው ነው። እውቀትህ የነፃነትህ መሰረት ነው፤ መረዳትህ ትልቁ የስኬትህ በር ነው። አንብብ፣ ተማር፣ ቁጭ ብለህ አስተማሪ ታሪኮችን አዳምጥ፣ ጊዜ ሰተህ የሚገነቡህን ተግባራት ፈፅም። ነፃነት በአንዴ የሚመጣ አይደለም፤ ነፃነት ከተወሰኑ መፅሃፍትና ንግግሮች ቦሃላ የሚከሰት አይደለም። የሚሰሩህን፣ የሚያንፁህን፣ ለምትገነባው ህንፃ መሰረት የሚሆኑህን መፅሐፍት ያለማቋረጥ ልታነብ ይገባል።
አዎ! ጀግናዬ..! የነፃነትህ ጉዞ ለእውቀት ባለህ ጥማት የሚፈፀም ነው፤ የስኬትህ ሚስጥር እራስህ ላይ ለመስራት ቆራጥ የመሆንህ ነው። አዲስ ተዓምር የለውም፤ እያንዳንዱን የምታደርጋቸውን ነገሮች ከለውጥና እድገትህ ጋር አያይዛቸው፤ የከፍታህ፣ የስኬትህ ግብዓት አድርጋቸው። ብዙ ነገር ባወክ ልክ ብዙ በሮች እየተከፈቱልህ ይመጣሉ፣ ማንነትህን በሚገባ ትረዳለህ፣ ቀጣዩ እርምጃህ አያስፈራህም፣ የወደፊት መዳረሻህ አያስጨንቅህም፣ በባዶ ተስፋ የምትኖርበት ምክንያት አይኖርም። ተማር፣ አንብብ፣ እወቅ ካንተም በላይ የብዙዎችን ህይወት መቀየር ጀምር። የለውጥ ፍራቻ ትልቆቹ ምክንያቶች የእውቀት ውሱንነትና ውድቀት ናቸው። ሳታውቀው በምትጀምረው የትኛውም ስራ ስኬታማ የምትሆንበት መንገድ አይኖርም። ጉዞህን ከመጀመርህ በፊት ስለጉዞው ምንነት መጠየቅ፣ ማወቅና መረዳት ይኖርብሃል።
አዎ! የቻይናዎችን አባባል አስታውስ "ስለመንገዱ ማወቅ ከፈለክ የሚመለሱትን ጠይቅ።" አንተ ልትጓዝበት የምትፈልገው መንገድ ቢያስፈራህ፣ ቢያስጨንቅህ፣ ጉዞህን ለመጀመር ደጋግመህ የምታመነታ ከሆነ ያለምንም ቅድመሁኔታ ካንተ በፊት በጉዞው ላይ የተሳተፉ ሰዎችን ጠይቅ፣ ከእነርሱ ተማር፣ የእነርሱን የጉዞ ታሪክ አጥና፣ መውሰድ የሚገባህንም ትምህርት ውሰድ። እወቀት ለተጠማት ሁሌም ቅርብ ነች፤ ጥበብና ብስለት ለሚፈልጋቸው ዘወትር ዝገጁ ናቸው። እራስህን በእራስህ ብቁ ካላደረክ ማንም አንተን ብቁ ሊያደርግህ የሚመጣ አካል አይኖርም። እያንዳንዳችን የገዛ ሃላፊነታችንን የመውሰድ ግዴታ አለብን። ካንተ በላይ እንደሆኑ የምታስባቸው አብዛኞቹ ሰዎች አንተ የማታውቀውን ያውቃሉ፣ አንተ የማታደርገውን ያደርጋሉ፣ አንተ የምትፈራውን እነርሱ ይደፍራሉ። የእውቀት ጥማትህን ጨምር፣ በየጊዜው እራስህን ማደስህን ቀጥል፣ በጥበብ በማስተዋል ወደ ወሳኙ የህይወት ግብህ በልበሙሉነት ተጓዝ።
ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን!