Yidnek kasim ይድነቅ ቃሲም


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Ta’lim


Our beloved family welcome

Bog‘liq kanallar

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሆነው ተሰየሙ‼️

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ወ/ሮ አዳነች አቤቤን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አድርጎ ሰይሟል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማ አስተዳደር መንግሥት ምስረታና 4ኛ ዙር የመክፈቻ ጉባኤውን በዓድዋ ድል መታሰቢያ በሚገኘው የምክር ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል።


የኢትዮጵያን ቡና ወደ ዓለም የሚያቀርብ አዲስ የትብብር ምዕራፍ ተጀመረ!

Goldenland Trading PLC ከ Neo Marketing እና Abri Business Group ጋር በመተባበር በቡና ዘርፍ ላይ የጋራ ሥራ ለመስራት የሚያስችል የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ።

የኢትዮጵያ ቡና ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ የሚያሸጋግር ታላቅ የቡና ቅምሻ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ በኦክቶበር 31 በአዳዋ አዳራሽ እንደሚካሄድ ታወቀ። መርሃ ግብሩ የአፍሪካ ኮፊ ካፓስ ዋና ዳይሬክተር እንዲሁም የስፔሻሊቲ ኮፊ አሶሴሽን (Specialty Coffee Association) ዋና ዳይሬክተርና የአለም አቀፍ የገበያ ክፍል ሃላፊ በተገኙበት ይካሄዳል።

በዝግጅቱ ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች፣ የቡና ቀማሾች (ኩፐርስ)፣ እንዲሁም ከቡና ዘርፍ ጋር በተለያየ መልኩ የሚመለከታቸው ሌሎች አካላት እንደሚገኙ ታውቋል።

የመርሃ ግብሩ ዋና አላማ ለቡና አምራቾችና ላኪዎች የአለም አቀፍ ደረጃ የብቃት ሰርተፍኬት ማስገኘት ነው። ለቡና ላኪዎችም አዲስ የአለም አቀፍ የገበያ ትስስር ለመፍጠር ያለመ ነው።በተጨማሪም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች በአለም አቀፍ ደረጃ የተመሰከረላቸው (internationally certified) ባለሙያዎች እንዲሆኑ የሚያግዝ ሲሆን፣። አዘጋጆቹ እንዳስታወቁት፣ ይህ ለአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚቀርብ በአሜሪካና በአውሮፓ ደረጃ እውቅና ያለው የ speciality coffee association campus የዲኘሎማ certification ከ እሜርካን እገር እንደሚያገኙ ተገልፀዎል። የትምህርት ቤቱ የregistration እና ሌሎች ጉዳዮች ዝግጅቱ ላይ ይፉ ይደረጋሉ።

የመርሃ ግብሩ አዘጋጆች እንደሚገልጹት፣ ይህ ክንውን ለሀገሪቱ ቡና አምራች ገበሬዎችና ላኪዎች ሰፊ የገበያ እድል ከመፍጠሩም ባለፈ ለሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ገቢ ያለውን አስተዋጽኦ ከፍ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። መርሃ ግብሩ በስፔሻሊቲ ኮፊ አሶሴሽን ሚዲያዎች አማካኝነት በ170 ሀገራት ለሚገኙ ተሳታፊዎች እንደሚተላለፍም ተገልጿል።

ባለሙያዎች እንደሚያስረዱት፣ ኢትዮጵያ በጣዕም ጥራት ከሌሎች ሀገራት ቀድማ ልትሆን የምትችልበት አቅም ያላት ሲሆን፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ የምርት ጥራት ማሻሻያና የወጣቶች ስልጠና ስራዎች እየተከናወኑ ናቸው። ይህም ኢትዮጵያ በአለም ቡና አምራች ሀገራት ተርታ ጎልታ እንድትታይ የሚያግዝ ስትራቴጂ አካል መሆኑን ምንጮች ጠቁመዋል።

ተያያዥ ዝግጅቶችና ተጨማሪ ዝርዝሮች ወደፊት ይፋ እንደሚደረጉ ይጠበቃል።




ተማሪዎች የምደባ ውጤታቸውን ማይት ይችላሉ

የትምህርት ሚኒስቴር የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን የዩኒቨርሲቲ ምደባ ማጠናቀቁን አስታወቀ።

ምደባው የተማሪዎችን ውጤትና ምርጫ፣ የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የክልል፣ የወረዳ፣ የዞን እና የትምህርት ቤት ስርጭት እንዲሁም የፆታ ሚዛን ታሳቢ በማድረግ መከናወኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በተጨማሪም ከ600 ነጥብ 500 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች በመጀመሪያ ምርጫቸው መመደባቸውን አስታውቋል።

ተማሪዎች የምደባ ውጤታቸውን በተዘጋጀው የኦንላይን ሥርዓት https://student.ethernet.edu.et/view-placement ማየት ይችላሉ ብሏል።

ቅሬታ ያላቸው ምደባው ይፋ ከሆነበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ በኦንላይን፦ https://student.ethernet.edu.et/complaints ብቻ ቅሬታ ማቅረብ እንደሚችሉ ተገልጿል።


አቶ ኢሳይያስ ጂራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን በፕሬዚዳንትነት ለሦስተኛ ዘመን እንዲመሩ ተመረጡ

አዲስ አበባ — የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ላለፉት ስምንት ዓመታት በፕሬዚዳንትነት ሲመሩ የቆዩትን አቶ ኢሳይያስ ጂራን ለተጨማሪ አራት ዓመታት በኃላፊነት እንዲቀጥሉ በይፋ መረጠ።

በዛሬው ዕለት በተካሄደው የፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባዔ እና የፕሬዚዳንትነት ምርጫ ሂደት፣ አቶ ኢሳይያስ ብቸኛ ተወዳዳሪ ሆነው የቀረቡ ሲሆን፣ በተሰጠው ቀጥታ ድምፅ አብላጫ ድጋፍ አግኝተዋል።

የምርጫው ውጤት ዝርዝር፡

• የተሰጠ ጠቅላላ ድምፅ፡ 88
• አቶ ኢሳይያስ ያገኙት ድምፅ፡ 81
• የስልጣን ዘመን፡ ለቀጣይ 4 ዓመታት

በዚህም መሠረት አቶ ኢሳይያስ ጂራ የኢትዮጵያ እግር ኳስን በከፍተኛ ኃላፊነት ለሦስተኛ ዘመን የመምራት አደራ ከጉባዔው ተረክበዋል።


በትግራይ ክልል ይማሩ ለነበሩ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተሰጠ አሰቸኳይ ጥሪ‼️
በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ሲከታተሉት የነበረውን ትምህርት ያቋረጡ ተማሪዎችን በጊዜያዊነት በሌሎች የሀገሪቱ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለመመደብ የሚያስችል የማመልከቻ ሂደት መጀመሩን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት፣ ተማሪዎች ከዚህ ቀደም ይማሩበት የነበረውን ዩኒቨርሲቲ፣ የትምህርት ዘመን፣ የትምህርት ፕሮግራም እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን በማስገባት በይነመረብ (Online) ማመልከት ይችላሉ።

የማመልከቻ ዝርዝር መረጃዎች፦

1.የማመልከቻ ድህረ ገጽ፦ https://student.ethernet.edu.et/university-transfer/

2. የሚያስፈልግ መረጃ፦ የግል የፋይዳ (የመለያ) ቁጥር

3. የማመልከቻ ጊዜ፦ ከዛሬ ጀምሮ እስከ መስከረም 8/2019 ዓ.ም ብቻ

ማሳሰቢያ፦ ቀደም ሲል በወረቀት ማመልከቻ ያስገቡ ተማሪዎችም ቢሆኑ የዝውውር ሂደቱ እንዲካተትላቸው በተጠቀሰው የድህረ ገጽ አድራሻ ገብተው በድጋሚ ማመልከት እንዳለባቸው ትምህርት ሚኒስቴር አሲስቧል።


🌼🌼🌼መልካም አዲስ #የኢትዮጵያ አመት ይሁንልን ቤተሰብ🙏
2019 ደግ ደጉን የምንሰማበት ፣መልካም መልካሙን የምንሰራበት፣ የፍቅር፣የሰላም፣የደስታ በአጠቃላይ የበረከት አመት ይሁንልን🌼🌼🌼

መልካም አዲስ አመት🇪🇹💚💛❤️🇪🇹


ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala dan repost
የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ፤ የ 13 ወራቶች ስያሜና ትርጉማቸው

➺  መስከረም

መስከረም ማለት ክረምቱ አለፈ ማለት ነው።
መስ:-  ማለት አለፈ ሲሆን
ከረመ:- ማለት ደግሞ ክረምት ነው።
መነሻ ቃል፦ መስ እና ከረመ

➺  ጥቅምት

ጥቅምት ማለት ጠቃሚ ጊዜ (ስራ የሚሰራበት ጊዜ) ማለት ነው።
መነሻ ቃል፦ ጠቀመ

➺ ኅዳር

ሕዳር ማለት ማደር ማለት ነው።
ገበሬው ለአስመራ ጊዜ ማሳ ውስጥ ለጥበቃ ማደሩን ያመለክታል።
መነሻ ቃል፦ ኀደረ

➺ ታኅሳስ

ታሕሳስ ማለት መመርመር ማለት ነው።
ገበሬው በመኸር ወቅት ሰብል መመርመሩን ያመለክታል።
መነሻ ቃል፦ ኀሠሠ

➺ ጥር

ጥር ማለት ጠረረ ፣ ነጻ (ብልጭ አለ) ማለት ነው።
የፀሐይን ግለት ወቅት ያሳያል።
መነሻ ቃል፦ ነጠረ

➺ የካቲት

የካቲት ማለት መክተቻ ማለት ነው።
የእህል መክተቻ ወቅት መሆኑን ያመለክታል።
መነሻ ቃል፦ ከቲት

ይቀጥላል...

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala #Ethiopia
youtube.com/@tariknwedehuala11


​ዛሬ የሚደረጉ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች

​01:45 | አቴንስ ከ ላስክ
01:45 | ክለብ ብሩጅ ከ አስቶን ቪላ
04:00 | ዶርትሙንድ ከ ቪያሪያል
04:00 | ፖርቶ ከ ማንቸስተር ሲቲ
04:00 | ሊል ከ ቤቲስ
04:00 | ሪያል ማድሪድ ከ ኢንተር ሚላን

​


ከማረሚያ ቤት ከተፈታ በሦስተኛ ቀኑ የአምቡላንስ ተሽከርካሪ ቁልፍ የሰረቀው ግለሰብ በጽኑ እሥራት ተቀጣ።


ከዚህ ቀደም በተጣለበት የፍርድ ውሳኔ መሠረት በማረሚያ ቤት ቆይታ የእስር ጊዜውን አጠናቆ በወጣ በሦስተኛው ቀን በድጋሚ በስርቆት ወንጀል የተከሰሰው አቶ ያሬድ ገብረሚካኤል የተባለው ግለሰብ መሆኑ የአክሱም ከተማ ፖሊስ  አስታውቋል።


የማዕከላዊ ዞን ዓቃቤ ሕግ ቢሮ እንዳስታወቀው ተከሳሹ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው፣ ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም በዓድዋ ከተማ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ያለችን እህቱን ለመጠየቅ የመጓጓዣ ገንዘብ እንደሌለው በመግለጽ በዓድዋ ከተማ ቀይ መስቀል ማህበር አምቡላንስ ተሳፍሮ በመጓዝ ላይ በነበረበት ወቅት ነው።


ግለሰቡ በተሳፈረበት አምቡላንስ ውስጥ ተቀምጦ የነበረውን የተሽከርካሪውን ቁልፍ ሰርቆ ከተሰወረ በኋላ በጸጥታ አካላት በተደረገ ክትትል በአክሱም ከተማ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል።የአክሱም ከተማ ፖሊስ ወንጀል ፈፃሚዉን እጅ ከፍንጅ ይዞ በቁጥጥር ስር በማዋሉ አስፈላጊውን ማጣራት በማጠናቀቅ መዝገቡን ለዓቃቤ ሕግ አቅርቧል።


ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የአክሱም ከተማ ፍርድ ቤትም ነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት የቀረበበትን የሰነድ እና የሰው ማስረጃ መርምሮ ግለሰቡ በተከሰሰበት የስርቆት ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ6 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እሥራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።


ፖለቲከኛ ልደቱ አያሌው የሙዚቃ አልበም ሊያወጣ ነው‼

ልደቱ እንደገለፀው "እኔ የኪነ-ጥበብ ሰው ባልሆንም፣ ትንሽ አንዳንድ ዝንባሌዎች አሉኝ እና አንድ 'ሀሳብን በዜማ' የሚል አንድ አልበም በ AI ሰርቻለሁ። እና በውስጡ 12 ዘፈኖችን የያዘ ነው። ይሄ አልበም የፖለቲካ ፍልስፍናዬን፣ እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች፣ በሌሎች የሕይወት ዘርፎችም ያለኝን እይታ የምገልጽበት ነው እና ለአዲሱ ዓመት ከመስከረም 1 ጀምሮ ለ12 ተከታታይ ቀናት በየእለቱ ቀን አንድ አንድ ዘፈን እለቃለሁ።" በማለት ገልጿል።ፖለቲከኛው በመጨረሻም እዚህ ላይ በመድረሱ ብዙዎች እየተነጋገሩበት ነው።


አርሰናል በአሸናፊነቱ ቀጥሏል !

በፕሪሚየር ሊግ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አርሰናል ቼልሲን 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

የመድፈኞቹን የማሸነፊያ ግብ ካይ ሀቨርትዝ እና ኦዴጋርድ ሲያስቆጥሩ የቼልሲን ግብ ሞርጋን ሮጀርስ ከመረብ አሳርፏል።

ክሪስቶስ ዞሊስ በዚህ አመት በአራት ጨዋታዎች ሶስተኛ ለግብ የሆነ ኳሱን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

መድፈኞቹ የመጀመሪያ ሶስት ጨዋታዎችን በማሸነፍ ጥሩ የሚባል አጀማመር ማድረግ ችለዋል።

አርሰናል እና ማንችስተር ሲቲ እስካሁን ሁሉንም ጨዋታዎች ያሸነፉ ክለቦች ሆነዋል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

2️⃣ አርሰናል :- 9 ነጥብ
4️⃣ ቼልሲ :- 6 ነጥብ

ቀጣይ መርሐ ግብር ?

ረቡዕ :- ናፖሊ ከ አርሰናል ( ucl )

ረቡዕ :- ቼልሲ ከ ሊድስ ዩናይትድ ( ሊግ ካፕ )


ባርሴሎና መሪነቱን አጠናክሯል !

ባርሴሎና ከቫሌንሽያ ጋር ያደረገውን አራተኛ ሳምንት የሊግ መርሐግብር 5ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

በጨዋታው ላሚን ያማል ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ራፊና ፤ ሎፔዝ እና ፔድሪ ቀሪዎቹን ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል።

ራፊና በውድድር አመቱ ስድስተኛ የላሊጋ ጎሉን ማስቆጠር ችሏል።

ባርሴሎና የመጀመሪያ አራት የሊግ ጨዋታዎችን በማሸነፍ ሊጉን በ 1️⃣2️⃣ ነጥቦች እየመራ ይገኛል።

ባርሴሎና በሊጉ ባደረጋቸው አራት ጨዋታዎች 1️⃣7️⃣ ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።

ባርሴሎና ረቡዕ ከፌይኖርድ ጋር የሻምፒየንስ ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደርጋል።


የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የ 3ተኛ ሳምንት  ጨዋታ ተጠናቀቀ

ኤቨርተን 2-2 ማንችስተር ዩናይትድ
          


የለንደን ደርቢ ጨዋታ

211ኛው ታላቁ የለንደን ደርቢ በአርሰናል እና  ቼልሲ መካከል ዛሬ ምሽት 12:30 ይደረጋል
አርሰናል ወይስ ቼልሲ




የአሜሪካ የዜግነትና የኢሚግሬሽን አገልግሎት፣ አዲስ አበባ ውስጥ ዓለማቀፍ ቢሮውን ሊከፍት ነው። የተቋሙ አዲሱ ቢሮ በቀጣዩ ሳምንት አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር መስሪያ ቤቱ ሰሞኑን ባሠራጨው መረጃ ገልጧል። ቢሮው፣ ወደ አሜሪካ የሚጓዙ የውጭ አገር ዜጎችን ሠነዶች የማረጋገጥ፣ የሠነድ ማጭበርበር ድርጊቶችን የመመርመርና የስጋ ዝምድናን ለማረጋገጥ የሚረዱ የዘረመል መረጃዎችን የማጠናቀር ሃላፊነት ይኖረዋል ተብሏል። እነዚህ ሥራዎች እስካሁን በዋናነት ሲከናወኑ የቆዩት፣ በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ አማካኝነት ነበር።



18 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.