ታላቁ የበድር ዘመቻ
ክፍል 1
ታላቁ የበድር ጦርነት በአምስተኛው አመተ ሂጅራ በተቀደሰው ወርሃ ረመዳን 17 ላይ የተካሄደ እውነት ከሐሰት የተለየበት ታላቅ ክስተት ነው።
የሥልጠና ቅኝትና ዝግጅት
የአላህ መልእክተኛ ሰላሁ ዐለይህ ወሠለም ሰሃቦቻቸውን ማሠልጠን ያዙ። ሥልጠናውንም ወደ ተግበር ለመለወጥ በመዲና ዙሪያም ተዋጊ፣ ቃኚና አሣሽ ቡድን ላኩ። ከነኚህም መካከል እራሣቸው የመሯቸው ቡድኖች ሲኖሩ አንዳንዶቹንም ከሰሃቦቻቸው መካከል መርጠው እንዲመሩ አድርገዋል። ከቡድኖቹም መካከል
1:በሀምዛ ኢብኑ ዐብዱልሙጦሊብ የምትመራና ሠላሣ የሙሃጅር /ከመካ የተሠደዱ/ ፈረሠኞችን በመያዝ ወደ ዒስ የባህር ዳርቻ የተላከ ቡድን
2: በዑበይዳ ኢብኑ አል-ሃሪስ የምትመራና ስልሣ የሙሃጅር ፈረሠኞችን በመያዝ ወደ ራብግ የተላከች።
3: በሰዕድ ኢብኑ አቢወቃስ መሪነት በመካና መዲና መንገድ ለቅኝት ተልእኮ የተላከች ሰማኒያ ሰዎችን የያዘች ቡድን
4: የወዳን ዘመቻ (ገዝዋ)፡- በአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይህ ወሠለም የተመራችና ሁለት መቶ ፈረሠኞችንና እግረኞችን በመያዝ ለውጊያ ተልእኮ ወደ ውዳን የሄደች ጦር። የአላህ መልእክተኛ በዚህ ዘመቻ ከበኒ ደምረህ ጋር ስምምነት የፈጠሩ ሲሆን የዚህ ዘመቻ ዋና ዓላማ የነበረውም የመካ- ሻም /ሶሪያ/ መንገድን ይቆጣጠሩ ከነበሩ ጎሣዎች ጋር ስምምነትና ግንባር ለመፍጠር ነበር።
5: የዑሺራ ዘመቻ፡- የውጊያ ተልእኮ የነበራት ሲሆን ሁለት መቶ ፈረሠኞችና እግረኞች የተካተቱባት በአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) የምትመራ ጠንካራ ሀይል ነበረች። ዋና ዓላማዋ የነበረውም ለሙሽሪኮች የሙስሊሙን ሀይል ለማሣየትና በየንቡዕ አካባቢ በቁረይሽ የንግድ መንገድ ላይ በመካና መዲና መካከል ከሚገኙ ጎሣዎች ጋር የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስ ነበር።
6: የቡዋጥ ዘመቻ፡- የመዋጋት ተልእኮ የተሠጣት ሁለት መቶ ፈረሠኞችና እግረኞች የተካተቱባት በአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) የምትመራ ሀይል ነበረች። ዓላማውም በረድዋ ተራራ በኩል አድርጎ ቡዋጥ በመድረስ በመካና መዲና መካከል የቁረይሾች የንግድ መስመር የሆነውን ጎዳና ለመቆጣጠርና ቁረይሾችን ስጋት ላይ ለመጣል ነበር።
7: በዐብደላህ ኢብኑ ጀህሽ የተመራች እና ሰማኒያ ጠንካራ ሙሃጂሮች የተካተቱበት የቅኝት ተልእኮ የተሠጣት ሀይል ስትሆን መሪዋም ከሁለት ቀን ጉዞ በኋላ እንጂ ደብዳቤውን እንዳይከፍት ነቢዩ ያዘዙት የተፃፈ መልእክት የያዘ ነበር። የጦሩ መሪ ከሁለት ቀን በኋላ ደብዳቤውን ሲከፍት “ይህን መልእክት እንዳየህ በአንዲት በመካና ጧኢፍ መካከል ከምትገኝ የተምር ዛፍ እስክትደርስ ድረስ ተጓዝ። እዚያም ሁንና የቁረይሾችን ሁኔታ ተከታተል ስለሁኔታቸውም ለማወቅ ሞክር።” ዐብዱላህ ከተምር ዛፏ እስኪደርስ ድረስ ተጓዘ። የቁረይሽ ቅፍለት በዚያ በኩል ስታልፍም ሙስሊሞቹ ጥቃት ከፈቱባት። ከሙሽሪኮችም ወገን ዐምር ኢብኑ አል-ሀድረሚ ተገደለ። ሁለት የቁረይሽ ሰዎችም የተማረኩ ሲሆን አራተኛው ሸሽቶ አመለጠ።
☆የመጀመሪያው የበድር ዘመቻ
የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይህ ወሠለም እና ሰሃቦቻቸው ከሙሽሪኮች አንፃር የጠበቁትና የገመቱት ነገር መከሠቱ እውን ሆነ። ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይህ ወሠለም መዲና ገብተው ብዙም ሣይረጋጉ በከርዝ ኢብኑ ጃቢር አል-ፍህሪይ የተመራ የሙሽሪኮች ጦር በመዲና ዳርቻ በሚገኙ የግጦሽ ማሣዎች ላይ ወረራ በማካሄድ የሙስሊሞች የሆኑ የተወሰኑ ግመሎችንና ፍየሎችን ነድቶ ወሰደ።
የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይህ ወሠለም የተዘረፉ የሙስሊም ግመሎችንና ፍየሎችን ለማስመለስ ሙሽሪኮቹን ለማሣደድ ወጡ። በአላህ መልእክተኛ የተመራው የሙስሊሙ ጦር ለበድር ቅርብ ከሆነው የሰፍዋን ሸለቆ ድረስ ተጓዘ። ነገርግን የሙሽሪኮቹ ሀይል ላይ መድረስ ባለመቻላቸው ያለ አንዳች ውጊያ ወደኋላ ተመለሱ።
♧የታላቁ የበድር ጦርነት ምክኒያቶች
1.በመካ ይኖሩ የነበሩ ሙስሊሞች ሀብት ንብረታቸውን ተዘርፈው ከአገራቸው እንዲወጡ በመደረጋቸው።
የመካ ቁረይሾች በሙስሊሞች ላይ ጦርነት ያወጁት የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይህ ወሠለም ኢስላማዊ ጥሪያቸውን በይፋ ማድረግ ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ነበር። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ግፉ ቀጠለ። የሙስሊሞችን ደም ማፍሠስ በድብቅም ይሁን በይፋ ያመኑትን የመካ ሙስሊሞች ቤቶቻቸውን መቀማትና ሀብት ንብረቶቻቸውን በሀይል የግላቸው ማድረግ ጀመሩ። ሙስሊሞችም የአላህን ውዴታ አስበልጠው ከተወለዱባትና ካደጉባት ቀዬ ነፍሦቻቸውን ይዘው ኮበለሉ። ጥለው የኮበለሉት ሀብት ንብረትም በቁረይሾች ቁጥጥር ሥር ዋለ። በስደታቸው ወቅትም ሱሀይብን የመሣሰሉ ሰሃቦች ወደ መዲና መሠደድ ፈልገው በመታገዳቸው ሙሉ ንብረታቸውን አሣልፈው በመስጠት እንዲለቋቸው እስከመደራደር ደርሰዋል።
2.ሙሽሪኮች መዲና ድረስ በመምጣት ሙስሊሞችን ማሣደዳቸው
ቁረይሾች መካ ሣሉ በሙስሊሞች ላይ ባደረሱት ግፍና ጭቆና ብቻ በቃን አላሉም። ከስደት በኋላም ቢሆን በነሱ ላይ ማሴርና ማነሣሣትን ሥራዬ ብለው ተያያዙ። በመዲና የሚገኙ ሙስሊሞችን በማጥቃት ንብረቶቻቸውን እንዲዘርፉ እንዲያሸብሯቸውም ጭምር ከሌሎች ሙሽሪኮች ጋር በመተባበር በኩረዝ ኢብኑ ሀባብ አል-ፍህሪ የሚመራ ጦር ላኩ። ይህ ጥቃት የመጀመሪው የበድር ጦርነት በመባል ይታወቃል። ስለሆነም ቁረይሾች ለሙስሊሞች ላሣዩት የከፋ ጥላቻና ሙስሊሞችንና ኢስላምን ለማጥቃት ባደረጉት እንቀስቃሴ ምክኒያት የእጃቸውን ዋጋ ማግኘትና መራራ ውጤቱንም መጎንጨት ነበረባቸው። ጥቅሞቻቸውንና የንግድ መስመሮቻቸውን ሙስሊሞች አደጋ ላይ ሊጥሉ እንደሚችሉ ማሣወቁ የሚያስፈልግበት ጊዜ ደረሠ። እስልምና መጠናከሩን፤ መንግስት ያለው መሆኑን እና ጥቃትንና ክፋትን ሁሉ መመለስ እንደሚችል እንዲሁም ሀቅን የማስፈን ውሸትን የመደምሰስ ሀይል ያለው እጅ እንዳለው ማሣየቱ ግድ ሆነ።
3.ቁረይሾችን ሥርዓት ማስያዝና የሙስሊሞችን ሀብት ንብረት ማስመለስ
በሺህ ግመሎች የምትገመትና አርባ ሰዎችን የያዘች በአቡ ሱፍያን ኢብኑ ሀርብ እና ዐምር ኢብኑ አል-ዓስ የምትመራ የቁረይሾች ቅፍለት የንግድ እቃዎች ይዛ ከሻም ሀገር ወደ መካ መንቀሣቀሷን የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይህ ወሠለም በሰሙ ጊዜ ሙስሊሞች ለመውጣት አሰቡ። ነቢዩም “ይህች የቁረይሾች የንግድ ቅፍለት እንዳታመልጣችሁ።” አሏቸው። የተወሰኑ ሰዎች በፍጠነት ለጥሪው ምላሽ ተዘጋጁ። ከፊሎቹ ደግሞ የአላህ መልእክተኛ ለጦርነት አላዘዙንም በሚል መልኩ ተረዱ። ነቢዩ በማስከተል “የሚሣፈር እንሠሣ በቅርብ ያለው ሰው ይሣፈርና አብረን እንሂድ።” አሉ። ወዲያውም የሚሳፈሩትን እንሰሣ በቅርብ የሌላቸውን ሰዎች ሣይጠብቁ በአፋጣኝ ቅፍለቷን አስበው ወጡ።
በወቅቱ የሙስሊሞች ቁጥር ሦስት መቶ አሥራ ሦስት ሰዎች ነበር። መቶ አርባ ምናምን የሚሆኑ ሰዎች ከአንሷር /የመዲና ሰዎች/ ነበሩ፤ የተቀረው ቁጥር ከሙሃጅሮች /ከመካ ወደ መዲና የተሠደዱ ሰዎች/ ነበር። ሙስሊሞቹ ሁለት ፈረስ እና ሰባ ግመሎች ነበሯቸው።
https://t.me/youthmission
https://t.me/youthmission
በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል