ዘካቱልፊጥር ምንድን ነው?
ዘካቱልፊጥር የረመዳን ፆም መገባደጃ ላይ የሚሠጥ ሶደቃ (ምፅዋት) ነው። በነፍስ ወከፍ እያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። “ሰደቀቱል-ፊጥር”፣ “ሰደቀቱ ረመዳን” እና “ዘካቱል-በደን” ተብሎም ይጠራል- ዘካቱልፊጥር።
መች ተደነገገ? አስፈላጊነቱስ?
ዘካቱልፊጥር ከሒጅራ በኋላ ሁለተኛው አመት ላይ ተደነገገ። እንደ አብዝሀ ዑለሞች እምነት ዘካቱልፊጥር ግዴታ (ዋጂብ) ነው። ጥቂቶች የጠበቀ ሱና (ሱና ሙአከዳ) እንጂ ግዴታ አይደለም የሚል አቋም አላቸው። ግዴታ ለመሆኑ የሚቀርቡ መረጃዎች በርካታ ናቸው። ከነርሱ መሀል ጥቂቶቹን እናንሳ። በቅድሚያ ከቁርአን፡-
وَالَّذِينَ فِي أَمْوَالِهِمْ حَقٌّ مَّعْلُومٌ
لِّلسَّائِلِ وَالْمَحْرُومِ
“እነዚያም በገንዘቦቻቸው ላይ የታወቀ መብት ያለባቸው የኾኑት። ለለማኝ ከልመና ለሚከለከልም (መብት ያለባቸው የኾኑት)።”(አል-መዓሪጅ 70፤ 24-25)
ከሐዲስ ደግሞ ይኸኛውን እንይ፡- ከዐብዱላህ ኢብኑ ዐባስ እንደተዘገበው።
فَرَضَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم زَكَاةَ الْفِطْرِ؛ طُهْرَةً لِلصَّائِمِ مِنَ اللَّغْوِ وَالرَّفَثِ، وَطُعْمَةً لِلْمَسَاكِينِ، مَنْ أَدَّاهَا قَبْلَ الصَّلاةِ فَهِيَ زَكَاةٌ مَقْبُولَةٌ، وَمَنْ أَدَّاهَا بَعْدَ الصَّلاةِ فَهِيَ صَدَقَةٌ مِنَ الصَّدَقَاتِ
“ዘካቱልፊጥር ፆመኛ ከአልባሌ ንግግርና ከረፈስ (የወሲብ ወሬዎች) እንዲፀዳበትና ለድሆች ምግብ እንዲሆን የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ደንግገውታል። ከሰላት በፊት የሠጠ ሰው ተቀባይነት አለው። ከሰላት በኋላ የሠጠ ሰው ግን እንደማንኛውም ሰደቃ ትሆንለታለች።” (አቡ ዳዉድና ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል፤ ሃኪም ሀዲሱን በቡኻሪ መስፈርት ሶሂህ ብለውታል)
join & share
https://t.me/youthmission