የሸይጣን አምባሳደር አትሁን
የሸይጣን አምባሳደር ማለት ሰዎች በረመዳን አፉው እንዳይባበሉ የሚያነሳሳና በረመዳን ይቅርታ መጠያየቅን የሚያሳንስ ሰው ነው።አንዳንዶች ይቅርታ እንዳንባባል «አመቱን ሙሉ የት ነበራችሁ?» እያሉ አሁን ይቅርታ መጠየቃችንን አላግባብ እንደሆነ ሊያንጓጥጡ ይፈልጋሉ።አንዳንዶችም ቢድዐ ነው ይላሉ።
በዚህ ወር ዐፍው ካልተባባልን መች ልንባባል ነው? እስከዛሬ ሸይጣንና ነፍስያ ይዘውን ይቅርታ ለመጠየቅ ኮርተን ሊሆን ይችላል። አሁን ደግሞ ነፍስያችንን ለማሸነፍ ፈልገን ይቅርታ ጠየቅን። ምንድን ነው ነውራችን? ወይስ በዚያው በነፍስያችን ላይ መቀጠላችን ነበር አግባብ?
አላህ በቂያማ እለት በዳይና ተበዳይን ያገናኝና ተበዳይ አፉው አልልም ይላል። አላህም ግዴለህም ይቅር በለው ይህን ህንፃ እሸልምሀለሁ ብሎ አንድ የጀነት ህንፃን ያሳየዋል። ባሪያውም አፉው ይላል። አላህ ባሮቹን ይቅር ለማባባል እዚህ ድረስ ሽልማት ያዘጋጃል።
የኛዎቹ ደግሞ እዚሁ ዱንያ ላይ አፍው የመባባያ መድረክ ላይም ይቅርታ እንዳንባባል ያሳንፉናል። ይህ የሸይጣን አምባሳደርነት እንጅ ምንድን ነው? ሰዎች ከልባቸው ይቅር እንዳሉህ እያሰብክ ወደ አላህ ለመቃረብ መጓዝ የቀልብ እርጋታን ይሰጣል! እኔ አፍው ብያለሁ አፍው በሉኝ ያ አሕባብ!
አላህ ከእሳት ነፃ የምንባልበት የዒባዳ ወር ያድርግልን!
ረመዳን ሙባረክ!
የቴሌግራም ቻናል ፦ t.me/ismaiilnuru