መረጃ ‼️
የሱማሊያ መከላከያ ሚንስትር አብዱልቃድር ሞሐመድ ኑር፣ ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር የተፈራረመችውን የባሕር በር የመግባቢያ ስምምነት ካልሰረዘችና የኢትዮጵያ ወታደሮች ከታኅሳስ በኋላ ሱማሊያ ውስጥ ከቆዩ "እንደ ወራሪ" እንቆጥራቸዋለን በማለት መናገራቸውን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።
የአፍሪካ ኅብረት የሽግግር ተልዕኮ በታኅሳስ መጨረሻ ወታደሮቹን ሙሉ በሙሉ ከአገሪቱ ያስወጣል ተብሎ የሚጠበቅ ሲኾን፣ ኢትዮጵያ በኅብረቱ ተልዕኮ ሥርና በኹለትዮሽ ስምምነት በአገሪቱ ያሠፈረቻቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች አሏት።
ሚንስትሩ፣ በጥር ወር በአገሪቱ ለሚሠማራው ተተኪ የኅብረቱ ተልዕኮ 90 በመቶው የገንዘብ ድጋፍ ተገኝቷል ማለታቸውንም ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል።
via:ዋዜማ
@zena_ethiopia24