የኢዜማ ዋና ጸኃፊ አበበ አካሉ ከፓርቲው በገዛ ፍቃደቸው ለቀቁ፡፡
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) ከምስረታው ጀምሮ በዋና ጸኃፊነት ሲሰሩ የቆዩት አበበ አካሉ ከሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከፓርቲው መልቀቃቸውን ለምርጫ ቦርድ ከፃፉት ይፋዊ ደብዳቤ አሻም ለመረዳት ችላለች፡፡
ዋና ጸኃፊው መልቀቃቸውን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት ‹‹ ባለፉት አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ ውስብስብ የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ የዜግነት ፖለቲካን በማቀንቀን፣ አቅምና ችሎታዬ በፈቀደልኝ መጠን የበኩሌን አስተዋጽኦ ለሰላማዊ ትግሉ ሳበረክቴ መቆየቴ እሙን ነው ›› ሲሉ ያለፉት ዓመታት የፖለቲካ ተሳትፏቸውን አስታውሰዋል፡፡
ይሁንና ‹‹ እያደረ በሚስተዋለው የፓርቲው አቋምና አጠቃላይ እንቅስቃሴ ውስጥ በኃላፊነትም ሆነ በአባልነት መቀጠል ስለማልፈልግ፣ ከሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ›› በይፋ መልቀቃቸውን አስታውቀዋል፡፡
https://t.me/zenacentral