ዘሪሁን ገሠሠ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Siyosat


በመረጃ እንቀራረብ! በመረጃ እንተሳሰር!

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Siyosat
Statistika
Postlar filtri


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
እየሆነ ያለው ይህ ነው!

'' የ7 አመት ልጄን ነጠቁኝ!😭''

ታግለህ ህልውናህን ከማስከበር ውጪ ፥ አንዳችም አማራጭ የለህም!


ሁላችሁም ዝግጁ?

ከዛሬ ምሽት 2:00 ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀን የሚቆየውንና በአማራ ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን ሁሉን አቀፍ ጥቃት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማሳወቅን አላማው ያደረገ የ X ዘመቻ መርሀግብር ተቀላቅለናል! ተዘጋጅተንም ሰአቱን እየጠበቅን ነው!

መልእክቶች በአስተባባሪዎች በኩል ተሰናድተው እንደሚደርሱን ይጠበቃል!

የX አካውንት የሌላችሁ ክፈቱ!

የኔን የX አካውንትም Follow ያላደረጋችሁ እንድንወዳጅ እጠይቃለሁ!👇👇👇

https://x.com/hfTMjjqZIqFe5eL?t=QpcskzOSs0eNtoiztHl37w&s=09


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይህን እንዲፈቅድ የሚያስገድደው አለማቀፋዊ ህግ ይኖር ይሆንን ?

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ማረፊያዎቹን ለወታደራዊ አገልግሎት እንዲውሉ መፍቀዱን ፣ ይህ ዛሬ ከባህርዳር አየር ማረፊያ የተወሰደና ለበረራ ዝግጁ የሆነች Bayraktar TB2 ድሮንን የሚያሳይ ምስል አንድ ማሳያ ነው!

ይህን የሚፈቅድ አለምአቀፋዊ ህግ ካለ ምናልባት ላላውቅ እችላለሁ ፣ ነገርግን ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ የመንገደኛ አውሮፕላኖች ፣ ወታደሮች ሲጓጓዙ የሚያሳዩ መረጃዎችን በተለያዩ ሚዲያዎች ተመልክተናል ፣ የአየር መንገዱ አየር ማረፊያዎች ለወታደራዊ አገልግሎት እየዋሉ መሆኑንም ሰምተናል ፣ ሌላው ቀርቶ የበረራ ህጉ በማይፈቅደው መልኩ እኔን ጨምሮ በርካቶች ከእጃችን ላይ ካቴና እንኳ ሳይፈታ በበርካታ ወታደሮች ታግተን ወደእስር ቤቶች ስንጓጓዝ የነበረውም በዚሁ አየር መንገድ አውሮፕላን ነው!

አገዛዙ ባለፈው አንድ ሳምንት ብቻ በጎንደርና በጎጃም መጠነ ሰፊ የሆነ የድሮን ጥቃት እየፈፀመ ሲሆን ፣ በጎጃም በአንድ ሳምንት ብቻ ከ50 በላይ የድሮን ጥቃት ተሰንዝሯል። በዚህም ህፃናትና ሴቶችን ጨምሮ ከ100 በላይ አርሷደሮች ሲጨፈጨፉ ፣ ከ10 በላይ ትምህርት ቤቶችም መውደማቸውን ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች ያስረዳሉ! በሸዋና በወሎም ተመሳሳይ የድሮን ጥቃት እየተፈፀመና በርካታ ንፁሀንን እየቀጠፈ እንደሚገኝ መረጃዎች ያመለክታሉ!

በንፁሀን ወገኖቻችን ላይ ያለእረፍት ከከባድ መሳሪያዎች በተጨማሪ በድሮን ፣ በጀትና በሄሊኮፕተር የሚፈፀመውን ፍጅት በመረጃና በማስረጃ እያጠናቀሩ መያዝ ተብሎም ለአለማቀፍ ማህበረሰብ ማጋለጥ ያስፈልጋል!

//ምስሉን የወሰድኩት ከጋዜጠኛ በላይ ማናዬ - Belay Manaye የፌስቡክ ገፅ ነው።//


እንደህዝብ አሸናፊ የሚያደርገንን ብቸኛ የአንድነት መንገድ በቶሎ መማተሩ ይበጃል!

በአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ውስጥ ፤ በፍፁማዊ ጥላቻና በበቀለኝነት ስሜት የታወረ ፣ የሆኑ አካባቢዎችን ''ጠላት ፣ ፀረ-እነሱ ፣ መጥፋትና መደምሰስ ያለባቸው ፥ ወዘተረፈ '' ብሎ የፈረጀና ፣ ይህን የተፈረጀ የማህበረሰብ ክፍል ሁለንተናዊ እሱነቱን ለማኮላሸት ፣ በእሱ ላይ ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ ለመታየት ፣...ወዘተ ሲል ፣ ከሰይጣን ጋርም ቢሆን አብሮ ለመቆም የማያመነታ ፣ እኩይ ፍላጎቱን ይዞ በመንደር (ጎጥ) ውስጥ የተወሸቀ ፣ ጥቂት የግለሰቦች ስብስብ እንዳለ የማይካድ ሀቅ ነው!

ይህ ቡድን መሻቱን እውን ለማድረግ የአማራ ህዝብ አሳቢ በመምሰል ለመታየት ቢሞክርም ፣ የአማራ ትግል በአፍጢሙ ቢደፋ ደንታ የሌለው ፣ አሁን ህዝባችን እንደፖለቲካ ማህበረሰብ ይኖርበታል ተብሎ ተሰፍቶ የተሰጠው ክልላዊ መዋቅር እንኳ ''መፍረስና መሸንሸን አለበት' ብሎ የሚያምን ፥ ይህን ለማሳካትም ፣ ይህን አማራውን በጎጣዊ ማንነት የተሸነሸነ የፖለቲካ ማህበረሰብ እንዲሆን ማድረግን የፖለቲካ ግባቸው አድርገው ከሚንቀሳቀሱ አካላት ጋር (መንግስትን ጨምሮ) አብሮ የሚሠራ ፣ ከትህነግ ጋር በተለያዩ የመንግስታዊ መዋቅሮች ውስጥ አብሮ እየሰራና እየተደራደረ እንኳ የአማራን ህዝብ ትግል ''የወያኔ'' እያለ ለመፈረጃነት የሚጠቀም አደገኛ አመለካከት የታጠቀ ቡድን ነው!

ታዲያ! ይህ ቡድንን ከማህበረሰብ ፣ ከተቋምና ከአደረጃጀቶች ውስጥ በጥንቃቄ ነጥሎ ማስቀረት ትልቁ የፖለቲካ ብስለት የሚጠይቅ ስራ ነው! ይህን ቡድን የብዙሀኑ ማህበረሰብ መፈረጃ ካደረክ ፣ ይህን ቡድን ለማጋለጥም ሆነ ለመታገል ስትል አነጣጥረህ የምትወረውረው የሀሳብ ቀስት ፥ ሌላውን ከነካብህና ይህ ቡድን ትግልህን ለመከፋፈል ብሎም ሀይል ለማሰባሰብ እንዲጠቀምበት ካደረግክ ፣ የዋናውን ህዝባዊ ትግልህን የአሸናፊነት መሠረት በቀላሉ እንዲናድ እያደረክ መሆኑን መገንዘብ ያሻሃል! ምክንያቱም የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ በአሸናፊነት ለመጠናቀቅ የቀረው ነገር ህዝባዊ አንድነትን አጠናክሮ አንድ ተቋማዊ ቅርፅ ባለው የሀይል አሰላለፍ በመሰተር ፣ ''የፖለቲካ ኃይል'' ሆኖ ድሉን ወደፍሬ መቀየር ብቻ ስለሆነ ነው!

ከዚያ ውጪ የአማራ ህዝብ ትግል በአውራጃዊና ቡድናዊ መከፋፈል ውስጥ ሆኖ የፈለገ ግዙፍ ሰራዊት ቢኖረው ፣ አውደውጊያዎችን ቢያሸንፍ ፣ የቱንም ያህል የፐርሶኔልና የሎጅስቲክ አቅም ቢያካብት ፣ ''ኃይል'' ሆኖ ለአማራ ህዝብ ጥቅምና ፍላጎት የሚደራደር ፣ ህዝቡ የተቃጣበትን የህልውና አደጋ ቀልብሶ ከጦርነት ማግስት ህዝባዊ አስተዳደር እንዲኖረው የሚያደርግ ሀይል መሆን አይቻለውም! 'እታገላለሁ' የሚለው ሀይል ሳይቀር ፥ ራሱን ወደማይታደግበት ደረጃ እንዲወርድ በራሱ ጊዜ በር ከፋች ይሆናል!

ይህ ደግሞ ከላይ የጠቀስኳቸው ጥቂት ቡድኖች ግብና ፍላጎት ነው! በየትኛውም መመዘኛ የአማራ ህዝብ ትግል አሸናፊ የሚያደርገውን አንድነትን የተላበሰ ተቋማዊ ትግል እውን እንዲሆን የማይሰራ ፣ በየፊናው የሚወራጭና እርስበርሱ የሚፈላለግ አደረጃጀት ሁሉ ፣ በአንደበቱ ''ለአማራ ህዝብ እታገላለሁ!'' ቢልም ፣ ከዚያም አልፎ የህይወት መስዋዕትነት ሁሉ የሚከፍል ቢሆንም ፣ አማራውን ' ተሸናፊ ' በሚያደርገው አሰላለፍ ውስጥ እስከተገኘና ፥ የራሱን ፍላጎትና ስሜት እስካልገራ ድረስ ፣ ከላይ ከጠቀስኳቸው በየመንደሩ ተቧድነው ጥላቻና በቀለኝነትን ታጥቀው ፣ ለአማራ ህዝብ ትግል ተውሳክ ከሆኑ ቡድኖች የተለየ ሊሆን አይችልም!

ስለዚህም መሠል ተውሳክ ቡድኖችን ከትግሉ ነጥሎ ለማስቀረትና ለማጋለጥ የሚደረገው እንቅስቃሴ ፍፁም ፖለቲካዊ ብስለት የታከለበት ሊሆን ይገባል! ብቻቸውን ነጥሎ ራቅታቸውን የሚያስቀር ብሎም መደበቂያ የሚሆን ማህበረሰባዊ ዋሻና ከለላ የሚያሳጣ ፣ በአርቆ አሳቢነት የሚከወን መሆን ካልቻለ ፣ በገዛ ቀስትህ አዙረው እንዲወጉህ ፣ ኃይል ማሰባሰቢያ እንዲያደርጉት ፣ የትግል አደረጃጀትህን ወደብዙ ትናንሽ ህዋስ እንዲከፋፍሉብህ ብሎም ''እንድትታረቅ ሆነህ ተጣላ '' እንዲሉት ብሂል ፣ በእነሱ ሳቢያ ከተከፋፈለው የገዛ ወገንህና የትግል ሀይልህ ጋር እንኳ ፣ ዳግም ተመልሰህ ለመነጋገርና መወያየት እንዳትችል አድርገው እንዲያራርቁህ እድሉን ትሰጣቸዋለህ ማለት ነው! ይህ ሁኔታ አሁንም በጉልህ እየተስተዋለ ነውና ልብ ያለው በቶሎ ልብ ሊለው ይገባል!

ውግንናችንና የምንከተለው ፦ አንዱ በአንዱ ሲስቅና ሲሳለቅ የምንደሰትና የምንከፋበት ፣ ተቋማዊነት ተዘሎ ቡድናዊ (መንደራዊ) አደረጃጀቶችና ግለሰቦች የሚገኑበት ብሎም የትርምስ ማእከል የሚሆኑበት ፣ ማንም ገብቶ እንዲፈተፍትበት ክፍት የተተወውና አሸናፊ የማያደርገን አዋራጅ መንገድ ሳይሆን ፣ እንደህዝብ ከተቃጣብን የህልውና አደጋ ታድጎ ፣ የህዝባችንን ጥቅምና ፍላጎት ተደራድሮ ለማስከበር የሚያስችለውን ፣ እንደህዝብ አሸናፊ የሚያደርገንን የህብረትና የተደራጀ ህዝባዊ ተቋማዊ የትግል መንገድ ሊሆን ይገባል!

አሁንስ ፈጣሪም ፦ ልቦናችንን ክፍት አድርጎ ፣ በሰማይ በምድር ያለእረፍት እሳት እየዘነበበት ላለው ህዝባችን ፣ ዋስትና የሚሆንና አሸናፊ የሚያደርገውን የትግል መስመር እንድንመለከት ይርዳን!

በቅንነት የምታነቡኝ በግርድፉ ያቀረብኳቸውን ነጥቦች ፣ ከነባራዊው አውድ ጋር በማሰናሰን ሰፋ አድርጋችሁ ግንዛቤ ትወስዱበታላችሁ ብዬ አስባለሁ!

ሠላማችሁ ይብዛ!


በአወንታዊም ሆነ በአሉታዊ መልኩ የሚዲያው ተፅዕኖ እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው!

> ብላችሁ በሚዲያው ዘርፍ የተሰማራችሁ አካላት ጥቂትም ሁኑ ብዙ ፣ ሁላችሁም በአንድ ተቋም (ሚዲያ) መስራት የግድ ባይሆንም ፣ ከሚያለያዩአችሁ ጥቃቅን ነገሮች ይልቅ ' የሚያገናኛችሁ ትልቅ የጋራ ህዝባዊ አላማ ይኖራችኃል' ተብሎ ይታመናልና ፣ ቢያንስ እየተገናኛችሁ እርስበርስ ልምድ የምትለዋወጡበት ፣ ክፍተት የምትሞላሉበት ፣ የሀሳብ ፍሰታችሁን የምታስተካክሉበት ፣ የጋራ እቅድ የምታቅዱበትን ፣ የመገናኛ ፕላትፎርም ፈጥራችሁ በሳምንትም ሆነ በወር ለመገናኘት ሞክሩ!

እንደግልም የየራሳችሁን የሚዲያ ተቋም እንቅስቃሴ ከአማራ ህዝብ የህልውና ትግልና መዳረሻ ግብ ብሎም አንድነት ከመገንባት ወዘተ ከመሳሰሉት ነጥቦች አኳያ ስትራቴጂክ የሆነ ግምገማ የማድረግን ልማድ አዳብሩ! ራሳችሁን ፈትሹ! በአወንታዊና በአሉታዊ መልኩ የምታሳርፉትን ተፅዕኖ ገምግማችሁ የራሳችሁን መገኛ በመለየት አወንታዊ አቅማችሁን ይበልጥ አጠንክራችሁ ፣ ክፍተቶችን ደግሞ ሞልታችሁ ስራችሁን የማስቀጠል ልማድ አዳብሩ!

ጨለማውን ለመሻገር - እንተባበር!
እንድንጠነክር - እንከባበር!
እንድንግባባም - እንደማመጥ!


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
#ፋኖ ከመላው ኢትዮጵያ አመታዊውን የግሸን ማሪያም የንግስ በዓል ለማክበር ወደደቡብ ወሎዋ አምባሰል የመጡ ምእመናንን በዚህ መልኩ ተቀብሎ ፣ ኃይማኖታዊ ስነ-ስርአቱ በሰላምና ያለአንዳች የፀጥታ ስጋት እንዲከብር ማድረጉ ትልቅ ትርጉም አለው!


እርግጥ ነው መንግስት ማሸነፍ አይችልም! ነገርግን ....!

መቀመጫውን ዋሽንግተን ያደረገው > የተሰኘው ተቋም ፣ ከቀናት በፊት በኢትዮጵያና በሌሎች ሀገራት ያለውን ሁኔታ አስመልክቶ ባወጣው ስታስቲካዊ መረጃ የታከለበት ረዘም ያለ ሪፖርቱ ውስጥ ፦ 👇

>

በማለት አስተያየቱን ያስቀምጣል።

እውነት ነው! አለመሸነፍ ማለት ማሸነፍ ማለት አይደለም።  አላማና ግብን በማያሳካ መልኩ ተጉዞ ማሸነፍም ከመሸነፍ እኩል ነው። በዚህ አይነቱ መንገድ ስንጓዝ በውጤት ደረጃ የምናገኘውም ሁለት ተሸናፊ ሀይል ነው!

ሙሉ ፅሁፉን ታነቡት ዘንድ ጋበዝኳችሁ!

https://www.understandingwar.org/backgrounder/africa-file-september-26-2024-fano-offensive-ethiopia%E2%80%99s-amhara-egypt-arms-somalia-rebel

ተቋማዊ አንድነትና ህብረት - ለአሸናፊነት!👊




የሚሊሻ አባላት ትጥቅ ለማስፈታት የመጡ ከ12 በላይ የሚሆኑ በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላትን በቁጥጥር ሥር አውለው ለመንግሥት ያስረክባሉ። በዚህ የተበሳጩ የታጠቀ ቡድኑ አባላት በአብተጋሆ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ ሰዎችን፣ ሴቶች እና ሕፃናትን ጨምሮ፣ 23 ሲቪል ሰዎችን አፍነው ወደ ቴዎድሮስ ከተማ በመውሰድ የተወሰኑት ሲመለሱ ሌሎችን ገድለዋል። በዚህ ግጭት ምክንያት በሚሊሻ አባላት እና በአካባቢው በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን አባላት መካከል ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ የተቀሰቀሰው ግጭት ተባብሶ ሐምሌ 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ወደ ማኅበረሰብ ግጭት ተሸጋግሮ ባይካዎ እና አጋም ውሃ ቀበሌዎች ከሁለቱም ብሔር ተወላጆች ብዛታቸው ያልታወቀ ሰዎች ሕይወት አልፏል። ከሟቾች መካከልም ግጭቱን ማምለጥ ያልቻሉ አረጋውያን፣ ሴቶች እና ሕፃናት የሚገኙበት መሆኑን እና በዚሁ ግጭት ቤቶች እና የሰብል ማሳ መቃጠላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

#ሼር


ይነሳ ቀበሌ አማስሬ በተባለ አካባቢ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ አቶ ወርቁ ሞት ባይኖር (የ70 ዓመት አረጋዊና 7 ሰዎች ያሉበት ቤተሰብ አስተዳዳሪ) የጫት ማሳቸውን በማረም ላይ እያሉ በአድማ ብተና ፖሊስ 2 እግራቸውን በጥይት ተመተው ከፍተኛ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን በኢሰመኮ ክትትል ወቅት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበበ ጊዮን ሆስፒታል ሕክምናቸውን በመከታተል ላይ ይገኙ ነበር።

©በአማራ ክልል፣ ማእከላዊ ጎንደር ዞን፣ አለፋ ወረዳ፣ ሻውራ ከተማ ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 7፡30 ሰዓት ድረስ በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት እና በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች መካከል በተደረገው ከባድ ውጊያ ከ10 በላይ ሲቪል ሰዎች ከየትኛው ወገን እንደተተኮሰ ባልታወቀ ተባራሪ ጥይት እንዲሁም ግጭቱ ከቆመና ታጣቂዎች ለቀው ከወጡ በኋላ “ታጣቂዎችን ትደግፋላችሁ”፣ “መረጃ ትሰጣላችሁ” በሚል የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ቤት ለቤት በመሄድና መንገድ ላይ ያገኟቸውን ሰዎች እንደገደሉ ነዋሪዎችና የተጎጂ ቤተሰቦች አስረድተዋል።

©ነሐሴ 22 ቀን 2016 ዓ.ም. ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ላይ በአማራ ክልል፣ ጎንደር ከተማ፣ ማራኪ ክፍለ ከተማ፣ ቀበሌ 16 ልደታ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ማንነታቸው ያልታወቀ የታጠቁ ቡድኖች ወ/ሮ መብራት ኪዳነ ማርያም ወደ ተባሉ ግለሰብ መኖሪያ ቤት በኃይል በመግባት በአምላክ አብርሃም ከተባለች የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመጨረሻ ዓመት ተማሪ ልጃቸው ጋር በጥይት ደብድበው ገድለዋቸዋል። በእናትና ልጅ ላይ የተፈጸመው ግድያ ምን አልባት ጥቃት ፈጻሚዎቹ “የእገታ ሙከራ” ሲያደርጉ ተጎጂዎች ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ራሳቸውን በመከላከላቸው ምክንያት በአጋቾቹ በተወሰደ እርምጃ ሊሆን እንደሚችል የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

©ነሐሴ 24 ቀን 2016 ዓ.ም. በአማራ ክልል፣ ጎንደር ከተማ፣ ቀበሌ 03 ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ሕፃን ኖላዊት ዘገየ የተባለች የ2 ዓመት ታዳጊ በወላጆቿ መኖሪያ ቤት ግቢ ውስጥ በመጫወት ላይ እያለች ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች የታገተች መሆኑን፤ የሕፃኗ ወላጅ አባትም ነሐሴ 25 ቀን 2016 ዓ.ም. ስልክ ተደውሎ ለሕፃኗ ማስለቀቂያ 1 ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ የተጠየቁ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል። ይሁን እንጂ የሕፃኗ ወላጅ አባት በሹፍርና ሙያ ተቀጥረው የሚሠሩ በመሆኑ የተጠየቀውን ገንዝብ ለመክፈል እንደማይችሉ በመግለጽ ከአጋቾች ጋር በስልክ በመደራደር 300,000 ብር ለመክፈል ይስማማሉ። ሆኖም የሕፃኗ ቤተሰቦች ከተለያዩ ሰዎችና ዘመዶቻቸው በመለመን የተጠየቀውን ገንዘብ አሰባስበው ነሐሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ሸዋ ዳቦ ከተባለ አካባቢ በመሄድ በባጃጅ ገንዘቡን ለአጋቾች በመላክ ልጃቸውን እንዲሰጧቸው ሲጠይቁ “መኖሪያ ቤታችሁ ታገኟታላችሁ” የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸው ወደ መኖሪያ ቤታቸው በመመለስ ላይ እያሉ ሕፃኗ መኖሪያ ቤታቸው አካባቢ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድላ ተጥላ ተገኝታለች። ይህንን ተከትሎ የከተማው ነዋሪዎች ወደ አደባባይ በመውጣት ማእከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳደር ጽሕፈት ቤት አካባቢ በመሰባሰብ ድርጊቱን በማውገዝ በጎንደር ከተማ እየተፈፀመ ያለው እገታ እንዲቆም ድምጻቸውን በሰላማዊ ሰልፍ አሰምተዋል። የመንግሥት ጸጥታ አካላት ሰልፈኞቹን ለመበተን በተኮሱት ጥይት ቢያንስ 3 ሰልፈኞችን የገደሉ ሲሆን ከ11 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት የደረሰ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። የጎንደር ከተማ አስተዳደር ጸጥታ ምክር ቤት ነሐሴ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ ነሐሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ሕፃን ኖላዊት ዘገየ እንዲሁም ነሐሴ 22 ቀን 2016 ዓ.ም. ደግሞ ወ/ሮ መብራት ኪዳነ ማርያም እና ልጃቸው በአምላክ አብርሃም ላይ የግድያ ወንጀል በአጋቾች የተፈጸመ መሆኑን አረጋግጧል። መንግሥት በእገታ፣ በግድያና በዘረፋ ወንጀል የተጠረጠሩ 49 ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ያዋለ ሲሆን የሕፃን ኖላዊት ዘገየን ሞት ተከትሎ ነሐሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም. በሲቪል ሰዎች ላይ የደረሰውን ጉዳት በማጣራት እና እርምጃ በመውሰድ ውጤቱን ለሕዝብ እንደሚያሳውቅ ምክር ቤቱ ገልጿል። ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ነሐሴ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. የአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ባወጣው መግለጫ የሥነ-ምግባር ብልሽት ያለባቸው፣ ኃላፊነታቸውን ከመወጣት ይልቅ የእገታው አባሪና ተባባሪ በመሆን የተጠረጠሩ 14 የጸጥታ አካላት ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን ገልጿል።

©ጳጉሜን 2 ቀን 2016 ዓ.ም. በአማራ ክልል፣ ጎንደር ከተማ አስተዳደር፣ አዘዞ ጸዳ ክፍለ ከተማ፣ ጸዳ ቀበሌ ጤና ጣቢያ አካባቢ 1 የመንግሥት የጸጥታ አባል ተገድሎ መገኘቱን ተከትሎ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጸዳ ካምፓስ የነበሩ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከተለያዩ አካባቢዎች ለገበያ ወደ ተሰበሰቡ ሰዎች ጥይት በመተኮስ 3 ሰዎችን እንዲሁም አስፓልት መንገድ ላይ ያገኟቸውን 8 ወጣቶች በአጠቃላይ ቢያንስ 11 ሲቪል ሰዎችን የገደሉ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች አስረድተዋል።

©መስከረም 6 ቀን 2017 ዓ.ም. በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎንደር ዞን፣ ደባርቅ ከተማ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጣቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት መካከል ከጠዋት እስከ እኩለ ቀን ድረስ ከተካሄደው የትጥቅ ግጭት ጋር በተያያዘ ዒላማቸውን ባልጠበቁ ተኩሶች እና በተባራሪ ጥይቶች ቢያንስ 20 ሲቪል ሰዎች እንደተገደሉ ኢሰመኮ ያነጋገራቸው የከተማው ነዋሪዎች እና የዐይን ምስክሮች አስረድተዋል። 9 ሰዎች ደግሞ ከቤታቸው እየተወሰዱ በመንግሥት የጸጥታ አካላት እንደተገደሉ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ከእነዚህ ውስጥ ከገጠር ወደ ደባርቅ ከተማ መጥተው አልጋ ይዘው የነበሩ 5 መምህራን ይገኙበታል። በተጨማሪ ዒላማቸውን ባልጠበቁ ተኩሶች እና በተባራሪ ጥይቶች 36 ሲቪል ሰዎች ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው ደባርቅ አጠቃላይ ሆስፒታል ገብተው የሕክምና አገልግሎት ያገኙ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 1 የ3 ዓመት ሕፃንን ጨምሮ 2 ሰዎች እንደሞቱ ለማወቅ ተችሏል።

©በአማራ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ የኤፍራታና ግድም ወረዳ አስተዳዳሪ ግንቦት 25 ቀን 2016 ዓ.ም. እና የቀወት ወረዳ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት በመኖሪያ ቤታቸው ተገድለዋል።

©በአማራ ክልል፣ ምዕራብ ጎንደር ዞን፣ በቋራ ወረዳ ከግንቦት ወር መጀመሪያ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ የአማራ እና የአገው ብሔረሰብ ተወላጆች በሚኖሩባቸው ቀበሌዎች ማለትም ይካዎ፣ አብተጋሆ፣ አጋም ውሃ፣ ገለሎ፣ ባምባ ውሃ እና ሌሎች ቀበሌዎች ላይ በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት የመንግሥት የሚሊሻ አባላት ትጥቃቸውን እንዲያስረክቧቸው ጥያቄ በማቅረባቸው እና የሚሊሻ አባላቱ የመንግሥትን ትጥቅ እንደማያስረክቡ በመናገራቸው ግጭቶች መነሳት መጀመራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። የግጭቱ መነሻ እና መባባስን በተመለከተ የአካባቢው ሰዎች እንደሚያስረዱት በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም.


በአማራ ክልል፣ ምሥራቅ ጎጃም ዞን፣ እነብሴ ሳር ምድር ወረዳ፣ ዶማ በተባለ አካባቢ የነበረውን ግጭት ተከትሎ ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ∙ም. 1 የ“ፋኖ” ታጣቂ አባል ቆስሎ 2 ወንድሞቹ ሊያነሱት ሲሄዱ 3ቱም ወንድማማቾች በመንግሥት የጸጥታ አባላት መገደላቸውን ኢሰመኮ የደረሰውን አቤቱታ መነሻ በማድረግ ባደረገው ማጣራት ማረጋገጥ ችሏል።

©ነሐሴ 6 ቀን 2016 ዓ.ም. በአማራ ክልል፣ ምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ቋሪት ወረዳ፣ ገነት አቦ ከተማ ሲካሄድ የዋለው ውጊያ ከቆመ በኋላ የመንግሥት ጸጥታ አባላት ቤት ለቤት ፍተሻ እያካሄዱ በነበሩበት ወቅት አቶ ካሳ ምትኩ የተባሉ መስማት የተሳናቸውና የሚጥል በሽታ ተጠቂ የነበሩ ግለሰብን ከቤታቸው በር ላይ ከሕግ ውጭ ግድያ የፈጸሙባቸው መሆኑን ኢሰመኮ ለማረጋገጥ ችሏል። ከዚህ በተጨማሪ የመንግሥት የጸጥታ አባላት በዚሁ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ 2 ቤታቸው ውስጥ የነበሩ ሴቶችን በር እንዲከፍቱ ጠይቀዋቸው በፍርሀት ባለመክፈታቸው በመስኮት በኩል ጥይት ተኩሰው የአካል ጉዳት ያደረሱባቸው ስለመሆኑ ኢሰመኮ ካሰባሰባቸው መረጃዎች መረዳት ችሏል።

በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎጃም ዞን፣ ሰሜን ሜጫ ወረዳ፣ ወተት ዓባይ ቀበሌና በአካባቢው በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት መካከል ከነሐሴ 6 እስከ 7 ቀን 2016 ዓ.ም. ከተካሄደ ውጊያ ጋር በተያያዘ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በመንገድና ቤታቸው ውስጥ ያገኟቸውን በግጭቱ ተሳትፎ ያልነበራቸውን 7 ሰዎች እንደገደሉ ነዋሪዎች አስረድተዋል። ከሟቾች ውስጥ 1 በአካባቢው የማኅበረ ሥነ ልቦና ጉዳት እንዳለበት የሚታወቅ ሰው እና 1 የ17 ዓመት ልጅ ይገኙበታል። በተጨማሪ ነሐሴ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ከንጋቱ 11፡30 ሰዓት አካባቢ ቄስ አወቀ መኮንን የተባሉ አረጋዊ ሃይማኖታዊ ሥርዓት ለማከናወን ወደ አቡነ ዘርዓብሩክ ቤተክርስቲያን በመጓዝ ላይ እያሉ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በጥይት እንደተገደሉ ለማወቅ ተችሏል።
©ነሐሴ 8 ቀን 2016 ዓ.ም. በአማራ ክልል፣ ደቡብ ጎንደር ዞን፣ እስቴ እና አንዳ ቤት ወረዳ አስተዳደር አመራሮች ለስብሰባ ወደ ደብረ ታቦር ከተማ በጉዞ ላይ እንዳሉ በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት ባደረሱት ጥቃት የሞትና የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ለመረዳት ተችሏል።

©ነሐሴ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. በአማራ ክልል፣ ምሥራቅ ጎጃም ዞን፣ ደብረወርቅ ከተማ አካባቢ በመንግሥት ወታደሮች እና በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት መካከል የተደረገውን ውጊያ ተከትሎ አቶ ዘውዴ ጫኔ እና አቶ እንቻለው መኮንን የተባሉ አርሶ አደሮች ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከሚተኮሰው ከባድ መሣሪያ እራሳቸውን ለማዳን ሲሸሹ የመንግሥት የጸጥታ አባላት መንገድ ላይ ከያዟቸው በኋላ የ“ፋኖ ደጋፊ ናችሁ” በሚል በጥይት የገደሏቸው መሆኑን ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን፣ የመንግሥት የጸጥታ አባላት የሟቾችን የእጅ ስልክ በመውሰድና ለቤተሰቦቻቸው በመደወል ጸያፍ ስድቦችን እንደሰደቧቸው እንዲሁም “እናጠፋችኋለን” ብለው እንደዛቱባቸው ምስክሮች ገልጸዋል።

በአማራ ክልል፣ ባሕር ዳር ከተማ፣ አባይ ማዶ ዘንዘልማ በሚባለው አካባቢ በሚገኘው የገበያ ማእከል አካባቢ ሰሳ በረት በሚባል ቦታ 4 ወጣቶች እና አሽራፍ በሚባል አካባቢ 2 ወጣቶች በድምሩ 6 ወጣቶች ለጊዜው ባልታወቁ አካላት እጃቸውን የኋሊት ታስረው በጥይት እና በስለት በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለው ነሐሴ 12 ቀን 2016 ዓ.ም. ተገኝተዋል።

ነሐሴ 14 ቀን 2016 ዓ.ም. ከምሽቱ ከ1፡00 እስከ 1፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ በአማራ ክልል፣ ባሕር ዳር ከተማ፣ በተለምዶ ቀበሌ 5 በግ ተራ አካባቢ “ሜላት ካፌ” በመባል ከሚጠራው ስፍራ ጀምሮ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች (የአድማ ብተና ፖሊስ ዩኒፎርም የለበሱ) በከፈቱት እሩምታ ተኩስ በጎዳና አነስተኛ ሥራ እና በልመና ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሲቪል ሰዎች ላይ 2 የሞት እና 10 የአካል ጉዳት እንደደረሰ ለማረጋገጥ ተችሏል። ሟቾች 1 ዐይነ ሥውር የ11ኛ ክፍል ተማሪ እና ድንች ቅቅል ጎዳና ላይ በመሸጥ የምትተዳደር 1 ሴት ሲሆኑ ከቆሰሉት መካከል ደግሞ 1 ዐይነ ሥውር የ11ኛ ክፍል ተማሪ እና 1 የሟቿ ሴት ሕፃን ልጅ እንደሚገኙበት ለማወቅ ተችሏል።

©ነሐሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም. ጠዋት በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት እና በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች መካከል የነበረውን የትጥቅ ግጭት ተከትሎ በአማራ ክልል፣ ሰሜን ወሎ ዞን፣ ራያ ቆቦ ከተማ ዙሪያ የቆቦ ከተማ እና የዋጃ ከተማ ነዋሪ የሆኑ 4 ወጣቶች ባልታወቁ ሰዎች ተገድለው የተገኙ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

©በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎጃም ዞን፣ ባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ፣ ይነሳ እና ይባብ ቀበሌ የሚገኙ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች (የአድማ ብተና ፖሊስ አባላት እና ሚሊሻ) በአካባቢው ምንም ግጭት ሳይኖር በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ጉዳት አድርሰዋል ሲሉ ነዋሪዎች አስረድተዋል። ለምሳሌ ነሐሴ 8 ቀን 2016 ዓ.ም. ይባብ ቀበሌ ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ላይ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ወ/ሮ መብራቴ መኳንንት (61 ዓመት፣ አርሶ አደር እና 10 ሰዎች ያሉበት ቤተሰብ አስተዳደሪ) እና ወ/ሮ ነጻነት ምትኩ (25 ዓመት፣ አርሶ አደር) ከቤተክርስቲያን ተመልሰው መኖሪያ ቤታቸው ሲደርሱ በጥይት የገደሏቸው ሲሆን፣ የሟች ልጅ የሆኑትን ወ/ሮ ውብእህል ተባባል (25 ዓመት፣ አርሶ አደር) ደግሞ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ የቀኝ እጃቸውን በጥይት በመምታት የአካል ጉዳት አድርሰውባቸዋል። ነሐሴ 12 ቀን 2016 ዓ.ም. ይባብ ቀበሌ ጭንጫር ጎጥ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ አቶ ወርቁ ስሜ የተባሉትን የ74 ዓመት አርሶ አደር በመኖሪያ ቤታቸው ቡና በመጠጣት ላይ እያሉ የአድማ ብተና ፖሊስ አባላት ወደ መኖሪያ ቤታቸው በኃይል በመግባት ግለሰቡና ቤተሰቦቻቸው ላይ ድብደባ ከፈጸሙ በኋላ፣ ግለሰቡን በመኪና ጭነው ወደ ካምፓቸው ወስደው ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ መልሰው ወደ መኖሪያ ቤታቸው አካባቢ በማምጣት ከመኪና ላይ ገፍትረው አስፓልት መንገድ ላይ በመጣል በ3 ጥይቶች ተኩሰው ገድለዋቸዋል። ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም. ይባብ ቀበሌ ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ላይ አቶ ታደለ እውነቴ (42 ዓመት፣ አርሶ አደርና 4 ሰዎች ያሉበት ቤተሰብ አስተዳዳሪ) የበቆሎ ማሳ ለማሳረም የቀን ሠራተኞችን መንገድ ዳር ቆመው በመጠባበቅ ላይ እያሉ የአድማ ብተና ፖሊስ አባላት ጭንቅላታቸውን በ2 ጥይቶች መተው ገድለዋቸዋል። ነሐሴ 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ይነሳ ቀበሌ ድንጅማ በተባለ አካባቢ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ አቶ ላቀ ቢተው (46 ዓመት፣ አርሶ አደር እና 7 ሰዎች ያሉበት ቤተሰብ አስተዳዳሪ) ከብቶቻቸውን ወደ ቤታቸው እየነዱ በመሄድ ላይ እያሉ የአድማ ብተና ፖሊስ አባላት 2 እግራቸውን በጥይት በመምታት የአካል ጉዳት ያደረሱባቸው ሲሆን በኢሰመኮ ክትትል ወቅት ሕክምናቸውን በፈለገ ሕይወት ሆስፒታል በመከታተል ላይ ይገኙ ነበር። ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ.ም.


እጅግ አስደንጋጩና አሳዛኙ የኢሰመኮ ሪፖርት!

የአብይ አህመድ ሰራዊት በአማራ ክልል በሶስት ወራት ብቻ የፈፀመው ጭፍጨፋ በመንግስታዊው ኢሰመኮ ሪፖርት ይፋ ሁኗል።

©ሰኔ 2 ቀን 2016 ዓ.ም. ሌሊት በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት ከክልሉ አዊ ብሔረሰብ ዞን፣ ቲሊሊ ከተማ አሽፋ ቀበሌ እንደወጡ የመንግሥት የጸጥታ አካላት ወደ ቀበሌው በመግባት ሰኔ 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጠዋት ጀምሮ እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ቤት ለቤት በመፈተሽ “ፋኖን ትደግፋላችሁ፤ ትቀልባላችሁ፤ ቤት ታከራያላችሁ” እንዲሁም “የፋኖ አባላት ናችሁ” ብለው የጠረጠሯቸውን 10 ሲቪል ሰዎች በጥይት መግደላቸው ታውቋል።

©ከአማራ ክልል፣ አዊ ብሔረሰብ ዞን፣ ቲሊሊ ከተማ በ8 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ወንጀላ ቀበሌ ሰኔ 5 ለሰኔ 6 ቀን 2016 ዓ.ም. አጥቢያ ሌሊት ላይ በመንግሥት ጸጥታ አካላት እና በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት መካከል የተደረገውን የተኩስ ልውውጥ ተከትሎ የ“ፋኖ” ታጣቂዎች ቀበሌውን ለቀው ከወጡ እና ጦርነቱ ከቆመ በኋላ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ወደ ቀበሌዋ በመግባት ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ቤት ለቤት እየዞሩ “ፋኖን ትደግፋላችሁ፤ ትቀልባላችሁ” በማለት 5 ሰዎችን ከቤታቸው አስወጥተው የገደሉ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች አስረድተዋል። ከሟቾቹ መካከልም 1 የ75 ዓመት አረጋዊ እንደሚገኙበት ተገልጿል።

©ሰኔ 7 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት አካባቢ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከአማራ ክልል ሞጣ ከተማ ወደ ቀራንዮ ከተማ መኪና አጅበው በመጓዝ ላይ እያሉ መንገድ ላይ በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት የደረሰባቸውን የደፈጣ ጥቃት ተከትሎ የሰራዊቱ አባላት ወደ ቀራኒዮ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ በመግባት የዕድራቸው አባል የሆኑ መነኩሴ ሞተው የቀብር ቦታ በመቆፈር ላይ የነበሩ 6 የከተማው ነዋሪዎችን እንዲሁም 1 የአብነት ተማሪን የገደሉ መሆኑን የዐይን ምስክሮች አስረድተዋል።

©ሰኔ 8 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀኑ 8:00 ሰዓት አካባቢ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ደቡብ ሜጫ ወረዳ ተነስተው ወደ ሰሜን ሜጫ ወረዳ ወተት አባይ ቀበሌ አቅጣጫ በመጓዝ ላይ እያሉ መከኒ ዋርካ ቀበሌ አልቃ በተባለ ቦታ ላይ በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ በበቀል ስሜት በጉዟቸው ላይ ያገኟቸውን 10 አርሶ አደሮችን በጥይት የገደሉ፣ሌሎች 2 አርሶ አደሮችን ደግሞ ያቆሰሉ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች አስረድተዋል።

©ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. በግምት ከቀኑ 12፡00 ሰዓት አካባቢ በአማራ ክልል፣ ምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ጅጋ ከተማ አስተዳደር፣ “ጎህ” በተባለ ካፌና ሬስቶራንት ውስጥ የነበሩ ሰዎችን ጨምሮ ቢያንስ 16 ሰዎች በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከሕግ ውጭ መገደላቸውን የሟች ቤተሰቦች፣ የአካባቢው ነዋሪዎችና የመንግሥት አስተዳደር አካላት ገልጸዋል። አንድ የመንግሥት ኃላፊ የግድያውን መነሻ ምክንያት ሲያስረዱ “በዕለቱ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ከከተማ ውጭ ቆይተው ሲመለሱ በተተኮሰባቸው ጥይት 2 አባላት መቁሰላቸውን እና 1 ወታደር ተደብድቦ ጉድጓድ ውስጥ ወድቆ ማግኘታቸውን ተከትሎ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ‘ፋኖ ያለበትን አሳዩን’፤ ‘መረጃ ስጡን’፤ ‘ምን እንደተፈጠረ ተናገሩ’ በሚል በሬስቶራንት ውስጥ የነበሩ ሰዎች እና ተኩሱን ሰምተው በመሮጥ ላይ የነበሩ ሲቪል ሰዎችን ገድለዋል” በማለት ገልጸዋል። ከሟቾች መካከል 2 አእምሮ ሕመም ያለባቸው ሰዎች እንዲሁም በሬስቶራንቱ ሲስተናገዱ የነበሩ የአቢሲኒያ ባንክ እና የአዋሽ ባንክ ሠራተኞች ይገኙበታል።

@በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችና በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት መካከል ሰኔ 17 ቀን 2016 ዓ.ም. በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎጃም ዞን፣ አዴት ከተማ ላይ በተካሄደ የትጥቅ ግጭት አባትና ልጅን ጨምሮ በግጭቱ ተሳትፎ የሌላቸው ሰዎች ተገድለዋል። ከግጭቱ ጋር በተያያዘ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከ3 ወር በፊት ተይዘው ካምፕ ውስጥ ታስረው የነበሩ 3 የ“ፋኖ” አባላት በጸጥታ ኃይሉ ተገድለው አስከሬናቸው ሰኔ 18 ቀን 2016 ዓ.ም. ተጥሎ መገኘቱን ኢሰመኮ ለማወቅ ችሏል።

በተመሳሳይ በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት በበቀል ስሜት በቁጥጥር ሥር አውለዋቸው የነበሩትን የሚሊሻና የአድማ ብተና አባላት ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. እንደገደሏቸው ለማወቅ ተችሏል።

በአማራ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ጣርማ በር ወረዳ፣ ከደብረ ሲና ከተማ ወጣ ብላ በምትገኝ ሾላ ሜዳ በተባለች ቦታ ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላትን ለመክበብ ሲሄዱ ታጣቂዎቹ ቀድመው ይወጣሉ። ይህንን ተከትሎ የመንግሥት የጸጥታ አባላት በመንገድ ያገኟቸውን፣ ቤታቸው በር ላይ ቆመው የነበሩ እና ሻይ ቤቶች አካባቢ የተገኙ በድምሩ 15 ሲቪል ሰዎችን “ለፋኖ መረጃ ትሰጣላችሁ፣ ፋኖን ትደብቃላችሁ” በሚልና በመሰል ምክንያቶች ግድያ እንደፈጸሙባቸው የሟች ቤተሰቦች አስረድተዋል።

©ሰኔ 25 ቀን 2016 ዓ∙ም. በአማራ ክልል፣ ሰሜን ወሎ ዞን፣ ውርጌሳ ከተማ አካባቢ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት መካከል የትጥቅ ግጭት መካሄዱን ተከትሎ በአካባቢው ከነበረው የመንግሥት የጸጥታ ኃይል የተተኮሰ ከባድ መሣሪያ መኖሪያ ቤቶች ላይ ወድቆ በ4 የአንድ ቤተሰብ አባላት እና በሌላ 2 የቤተሰብ አባላት ላይ በድምሩ 6 ሰዎች ላይ 1 የሞት እና 5 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት አድርሷል። ጉዳት ከደረሰባቸው ሰዎች ውስጥ 4ቱ ሕፃናት ሲሆኑ ቀሪ 2ቱ ደግሞ የሕፃናቱ ወላጆች ናቸው።
በአማራ ክልል፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ አህመድ አሊ ሰኔ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀኑ 7፡00 ሰዓት አካባቢ መስጊድ ቆይተው ወደቤታቸው ሲመለሱ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገድለዋል።

©ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት አካባቢ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች አቶ ይመር መስፍን የተባሉትን ሰው “ፋኖ ነህ፤ ልጆችህም ፋኖ ናቸው” በማለት ከአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎጃም ዞን፣ ሰሜን ሜጫ ወረዳ፣ ወተት አባይ ቀበሌ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው አስወጥተው በባዶ እግራቸው ወደ አምቦ መስክ ቀበሌ ከወሰዷቸው በኋላ ገድለው አስከሬናቸውን ጥለውት የሄዱ መሆኑን፣ አስከሬኑም ሲታይ አካላቸው የተለያየ ቦታ ተወግቶና ተበሳስቶ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ መሆኑን እንደሚያሳይ ምስክሮች ገልጸዋል።

ሐምሌ 5 ቀን 2016 ዓ∙ም. በአማራ ክልል፣ ጉባ ላፍቶ ወረዳ፣ ውድመን ቀበሌ ላይ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት መካከል በትጥቅ የታገዘ ግጭት መካሄዱን ተከትሎ በአካባቢው ከነበረው የመንግሥት የጸጥታ ኃይል በተተኮሰ ከባድ መሣሪያ ቢያንስ 7 ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል።


ብዙ ዝርዝር ሳያስፈልገው የሚከተሉት ጉዳዮች የእርምት እርምጃ ቢደረግባቸው መልካም ነው ብዬ አስባለሁ!

✅የፋኖ መሪዎችና አባላት እንዲሁም ታዋቂ የሚዲያ ሰዎች በአንዳንድ ፈፅሞ የማይመለከቱን ወይም ተቀዳሚ አጀንዳችን ባልሆኑ ጉዳዮች ላይ ጭራሹኑ አስተያየት ባይሰጡ ይመረጣል። በተለይም ስሜት በተሞላበትና የፖለቲካውን አውድ በቅጡ ባልተረዳ መልኩ የሚሠጡ አስተያየቶችን ''አንዳንድ ማጣፊያው ያጠራቸው አካላት...'' ላልተገባ ፕሮፓጋንዳ ሲጠቀሙባቸው እያስተዋልን ስለሆነ ቢታሰብበት መልካም ነው!

✅አንዳንድ የፋኖ አባላት ከተማከለው የመረጃ አስተዳደር ውጪ ፣ ወደቲክቶክና መሠል የማህበራዊ ሚዲያዎች እየመጡ የሚሠጧቸውን ፖለቲካሊ አውዳሚና ለፕሮፓጋንዳ ጫጫታ የሚዳርጉ አስተያየቶችና መልእክቶችን ፈፅሞ ባያስተላልፉ መልካም ነው። አመራሮች ይህን ጥብቅ በሆነ ዲስፕሊን እንደሚያርሙት ተስፋ አደርጋለሁ።

✅አሁንም አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ ሀይማኖታዊ የሆኑ መልእክቶችንና በጉልህ በሚታይ መልኩ ሀይማኖታዊ ምልክቶችን እያንፀባረቁ ቪዲዮና ፎቶግራፎችን መልቀቅም ፣ ከመሠረታዊና መሬት ላይ ካለው እውነታ ባሻገር ለሚስተጋቡ አደናጋሪ ፕሮፓጋንዳዎች መጋለጥ ነውና ይህም በመሪዎችና በአሰራር ደምብ ተመስርቶ ቢታረም ጥሩ ነው!

✅መስዋትነት የከፈሉ አርበኞችን ታሪክ ራሱ በጉልህ የሚዘከርበት አምድ አለው። አመቺ ሁኔታ ሲገኝም አልፎ አልፎ ለሞራልና ለማነቃቃት ያህል መሠል ተሰብስበው የሚከበሩ የመታሰቢያ ፕሮግራሞች ሊኖሩ ይችላሉ። አሁን ላይ ግን ፈፅሞ መሠል በዓላት፣ በጀግኖች መታሰቢያና በመሳሰሉት ሰበብ ተሰባስቦ የሚደረግ ድግስም ሆነ ስብሰባ ሊኖር እንደማይገባ መረዳትና መጠንቀቅ ያስፈልጋል!




ለህዝብ እየተከፈለ ያለ ውድ መስዋትነት !

>

....ከብዙ ተማፅኖና ውትወታ በኃላ የጤናው ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ስለነበር ፣ አዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ከሚገኘው የማሰቃያ እስር ቤት ሪፈር ተፅፎለት ወደ አዲስአበባ ( ሚክሲኮ ፌደራል ፖሊስ እስር ቤት ) መጣ። ከህመሙ ጋር ተዳምሮ አካሉ ተጎሳቁሎ ፣ ፀጉርና ፂሙ አድጎ ቢታይም ፣ መንፈሱ ግን ፍፁም ጠንካራ ነበር። ሁላችንም ተቀብለን ወደማረፊያው አስገባነው።

ከቀናት በኃላ ወደተለያዩ ሆስፒታሎች ሄዶ ምርመራውን አደረገ። ከደም ግፊቱና ስኳር በተጨማሪ እግሩ ከውስጥ እየቆሰለ ይፈርጥ ነበር። ሀኪሞችም በሁለት የተለያዩ ኬዞች ምርመራ ካደረጉ በኃላ ህክምናውን ለመቀጠል ፣ የአንድ ሳምንት ቀጠሮ ሰጥተውት ተመለሰ።

ከትንሽ ከትልቁ ጋር ተግባብቶ መኖር የሚችልበት ፣ ጨዋታው ጥርስ የማያስገጥመውና የሁላችንም መካሪ አባት የነበረው ጆን ፣ ከህክምና ቀጠሮ ይዞ በተመለሰ 24 ሰአት ሳይሞላው ፣ ከእስር ቤቱ ክሊኒክ ለህክምና እንደሚፈለግ በተደጋጋሚ ተጠራ። ሁኔታው ቀድሞ ገብቶት ስለነበር ፣ ''ተረጋጉ የሚሆነውን በትእግስት እናያለን!'' ብሎን ወደተባለው ክሊኒክ ሄደ።

ነገርግን እዚያ ሲደርስ ለህክምና አልነበረም። ወታደሮች መንገድ ዘግተው ወደተዘጋጀው መኪና እንዲገባ አመለከቱት። > ቢላቸውም ሊገባቸው አልቻለም። ያለው አማራጭ > ብሎ ወደእኛ መጣ። ወደውስጥ ገብቶም > ብሎን እቃውን ይዞ ወጣ። ከነህመምና ስቃዩም ወደአዋሽ አርባ ኮንሰንትሬሽን ካምፖ ብቻውን ታጅቦ ተመለሰ።

የሚገርመው እኔና በላያ ከመሰል ወንድሞች ጋር ፣ በወርሀ ህዳር/2016 ዓ.ም ''አመፅ በመምራት ...!'' የሚል ታፔላ ተለጥፎልን ወደ አዋሽ አርባ ተጭነን ስንሄድ ፣ በስፍራው ከተቀበሉን መካከል ጆንን ጨምሮ ስንታየሁ ቸኮልና ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ዘርፉን ፣ እኛ በመጣንበት መኪና አፋር ክልል/ሰመራ በግለሰብ መኖሪያ ግቢ የተከፈተ አዲስ እስር ቤት አዘጋጅተው ጭነዋቸው መሄዳቸው ነበር። ይህ እስር ቤት የተከፈተው በ3ቱ ወንድሞቻችን ቢሆንም ከዚያ በኃላ በርካቶች እየታፈኑ ተወስደው እስከሞት የደረሰ መከራን ሲቀበሉ እንደነበር የሚታወስና ሁሉም የሚረዳው የአደባባይ ሀቅ ነው። እነጆንም ወደእኛ የተመለሱት ያለአንዳች ምክንያት ሰመራ በአንዲት ጠባብ ክፍል ለወር ከ15 ቀን ያህል ሲሰቃዩ ከቆዩ በኃላ ነበር።

አስታውሳለሁ! አዋሽ በነበርንበት ሰአት የሆኑ የገዢው ባለስልጣናት ግቢውን ሊጎበኙ መጡና እኛ ለሽንት ተሰልፈን ስንወጣ ፊት ለፊት ተገጣጠምን። አጃቢዎቹ ሹማምንቱ እስኪያልፉ ባለንበት እንድንቆም ቀጭን ትእዛዝ አስተላለፉ። ታዲያ በዚህ መሀል ግቢውን የሚያስጎበኘው ባለማእረግ ሰውዬ በጣቱ የእኛን ማጎሪያ መጋዘን እየጠቆመ > በማለት በአሸናፊነትና በኩራት በሚመስል መልኩ የስላቅ ሳቅ ሲስቅ ፣ የተሰማንን ስሜት ፈፅሞ አልረሳውም። ይህ ሁሉ የሚከፈለው ለህዝባችንና ለህልውናው መከበር ሲባል ነው! ይህ ሁሉ ሰቆቃ እያለፈ ያለው ለግላዊ ፍላጎትና መሻትም አይደለም!

ወንድማችን ዮሐንስ ቧያለውን ጨምሮ ክርስቲያን ታደለ ፣ ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃይለማርያም ፣ ዶ/ር ካሳ ተሻገር ፣ ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱ ፣ ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ንብረት ፣ ዶ/ር ዘሪሁን ፣ ሺበሺ ፣ ወተቱ ፣ መሪጌታ በላይ ፣ ሻምበል አድማሱ ፣ ......ወዘተረፈ ዘርዝሬ የማልጨርሳቸው ወንድም እህቶቻችን ፥ ከህዝባቸው ጎን በመቆማቸውና በማንነታቸው ብቻ ''አሸባሪ'' የሚል ታፔላ ተለጥፎላቸው ፣ ዛሬም በቂሊንጦና ቃሊቲ ማረሚያ ቤቶች ፥ ነግቶ እስከሚመሽ የሰቀቀንና የሰቆቃ ጊዜን እያሳለፉ ይገኛሉ። የአንዳንዶቹ ቤተሰቦቻቸው ተበትነው ፣ ተቸግረውና ልጆቻቸው የለመዱትን አጥተው ፣ በናፍቆት ሰቀቀን እየተቀጡም ናቸው።

ታዲያ እኛ እኚህን ወገኖቻችንን ሂደን መጠየቅና ማበረታታት ፣ ቤተሰቦቻቸውን አለንላችሁ ማለት ይቅርና ስንቶቻችን ነን የምናስታውሳቸው ? ስንቶቻችን ነን አስታውሰንስ ድምፅ እየሆንንላቸው ያለነው ? መልሱን ለእናንተ ለአንባቢያን ተውኩት!

እኔ ግን እላችኃለሁ! ለህዝብ ሲሉ ዋጋ የሚከፍሉትን መደገፍና ከጎናቸው መቆም ፣ እነርሱን ሳይሆን ህዝባዊ ትግሉን መደገፍ ብሎም ብዙ ለመስዋዕትነት የተዘጋጁ ጀግና የህዝብ ልጆችን መፍጠር ነው!

#ፍትህ ማንነታቸው እንደወንጀል ተቆጥሮ ፣ በየወህኒ ቤቱ እየተሰቃዩ ለሚገኙ ወንድም እህቶቻችን!


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ይህ በአማራ ህዝብ ላይ በአደባባይ የተፈፀመ የዘር ፍጅት ቅስቀሳ ነው!

ከዚህ ጀርባ ያለው እቅድና አላማም ግልፅ ነው!


ሰንበሌጥን ማን ሊደገፈው?

አማራ አጋር ማፍራት አለበት ይባላል፡፡ ተደጋግሞ ይጻፋል፣ ተደጋግሞ ይነገራል፡፡ በጣም ትክክለኛ ነገር ነው፡፡ ነገር ግን አጋርም ሆነ አጋሮች ለማግኘት መጀመሪያ ለአጋርነት የሚፈለግ ሆኖ መገኘትን ይጠይቃል፡፡ ጠንካራ soft power/attraction መገንባትን ይጠይቃል፡፡ ከሃይማኖት እኩልነት አንፃር፣ የሃሳብ ልዩነትን በሰለጠነ መንገድ ከማስተናገድ አንፃር፣ የብሄረሰቦችን መብት ከማክበር አንፃር ወዘተ የት ላይ ነው ያለነው ብሎ ራስን መመርመርና ማስተካከል ያስፈልጋል፡፡ ያለንን የሚዲያና የትርክት የበላይነት መገምገም ያስፈልጋል ወዘተ፡፡

ጠንካራ ሆኖ ለመገኘት hard/coercive power መገንባትን ይጠይቃል፡፡ በግል፣ በቡድና እንደ ህዝብ ያለን የኢኮኖሚ አቅም፣ ያሉን ተቋማት፣ ያለን የተዋጊ ሰራዊት አቅም ወዘተ መገምገም አለበት፡፡ በፈተና ውስጥ ሆነንም ቢሆን መጠናከር አለብን፡፡ እንዲያውም ፈተናው ይበልጥ ሊያጠናክረን ይገባል፡፡

እነዚህ ሁለት ወሳኝ ሃይሎች/አቅሞች ሲኖሩን ነው አጋሮችን የምናገኘው፡፡ ያ ካልሆነ በሌሎች ላይ መለጠፍና መጠጋት እንጅ አጋርነት አይሆንም፡፡ ሰንበሌጥን ማን ሊደገፈው? ምናልባት መረማመጃና መጠቀሚያ ሊያደርጉት ይችሉ ይሆናል፡፡ እውነተኛ አጋርነት የሚመጣው ከጥንካሬ ነው፡፡

ጥሩ አጋር ለማግኘት ቢያንስ ቢያንስ የማሸነፍ ተስፋ እንዳለ ማሳየት ያስፈልጋል፡፡ እየጠነከርንና እየደረጀን የምንሄድ መሆናችን ገና ከወዲሁ የሚታይ መሆን ይገባዋል፡፡

አማራ ታሪኩንና ቁጥሩን በሚመጥን ሁኔታ ላይ መገኘት አለበት፡፡ ይህ ደግሞ የግድ መሆን ያለበት ነው፡፡ መሆንም የሚችል ነው፡፡ በእርግጥም የግድ መሆን መቻል አለበት፡፡ የአማራ ህዝብ ታሪኩንና ቁጥሩን በሚመጥን ደረጃ ላይ እንዲገኝ የሚያስችለው ፍቱን መድሃኒት ደግሞ የአማራ ብሄርተኝነት ነው፡፡ የሚኖረው ባሌም ሆነ መተከል፣ ከፋም ሆነ ሃረርጌ፣ ወልቃይትም ሆነ አረርቲ፣ ራያም ሆነ ደራ፣ አሜሪካም ሆነ አውስታሊያ፣ እስራኤልም ሆነ ደቡብ አፍሪካ… ሁሉንም አማራ በወንድማማችነትና እህትማማችነት መንፈስ የሚያስተሳስረው ብሄርተኝነታችን ነው፡፡ እሱን አጥብቀን እንያዝ፡፡ እናንብብ፣ በጥናት ክበብ እየተደራጀን እንወያይ፣ እንደራጅ፣ የትግሉ አካል እንሁን!

የአማራ ብሄርተኝነት ይለምልም!

@Hailu Bitania


ፋኖ እና የአማራ ብሄርተኝነት ምንና ምን ናቸው?

// በሀይሉ ቢታኒያ//

ፋኖ እና የአማራ ብሄርተኝነት አንድና ያው ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ፋኖ ከመዋቅሮች (structures) መካከል አንዱ ነው፡፡ የአማራ ብሄርተኝነት ከሁሉም መዋቅሮች በላይ የሆነ ዣንጥላ መዋቅር (overarching structure) ነው፡፡ “ርእሰ መዋቅር” እንበለው፡፡ በአማራ ብሄርተኝነት ርእዮት የተቃኙ የሚዲያ ተቋማት፣ በአማራ ብሄርተኝነት ርእዮት የተቃኙ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ የጥናትና ምርምር ተቋማት፣ የፖለቲካ ድርጅት/ቶች፣ እንዲሁም በአማራ ብሄርተኝነት ርእዮት የተቃኘ አርበኛ ሰራዊት (ፋኖ) ያስፈልገናል፡፡ ይሁን እንጅ ከእነዚህ ተቋማት መካከል አንዱም ብሄርተኝነቱን አይተካም፡፡ ከብሄርተኝኑ ጋር እኩል ሊሆንም አይችልም፡፡ ብሄርተኝነቱ እስከተጠናከረ ድረስ እንድ ተቋም በተለያየ መንገድ ችግር ውስጥ ቢገባ ራሱን አርሞ ይድናል፡፡ ሳይሆን ቀርቶ ከፈረሰም በሌላ ይተካል፡፡

ስለሆነም የአማራ ብሄርተኞች የሁልጊዜም ታማኝነታችን ለብሄርተኝነቱ፣ ከእሱ ቀጥሎ ለድርጅቶች/ተቋማት መሆን ይገባዋል፡፡ ጠንካራ መሪዎችን የሚፈጥራቸው በጠራ ርእዮት የሚመራ ድርጅት ነው፡፡ የቻይናው አብዮታዊ መሪ ማኦ ሲ ቱንግ ብቻውን ኮምኒስት ፓርቲውን አልገነባውም፡፡ ከሌሎች ጓዶቹ ጋር ሆኖ ነው፡፡ ፓርቲው የእሱ የእጅ ሥራ አይደለም፡፡ በጋራ አመራር የተገነባ ነው፡፡ ማኦን ማኦ ያደረገው ፓርቲው ነው፡፡ ማኦ ከፓርቲው ቢወጣ ማንም እዚህ ግባ የማይለው ተራ ግለሰብ ሆኖ በቀረ ነበር፡፡

ስለዚህ በሶስዮሎጂስቶቹ አባባል methodological collectivist እንሁን፡፡ ዋነኛው ታማኝነታችን ለህዝባችን (ይኸውም ለብሄርተኝነቱ) ይሁን፡፡ ከእሱ ቀጥሎ በብሄርተኝነት ርእዮት ለተገነቡት ድርጅቶች ይሁን፡፡ ግለሰብ መሪዎችን ማክበር ያለብን በመዋቅሩ/በድርጅቱ አሰራር መሰረት ነው፡፡ እሱን ተከትለን እናክብራቸው፡፡ ከዚህ ውጪ ግለሰብ ማምለክ ወይም ግለሰብን ማዋረድና ሲረግሙ መዋል ግን ከብሄርተኛ የሚጠበቅ አይደለም፡፡

የአማራ ብሄርተኝነት ይለምልም!!!


ደራሲ አዜብ ወርቁ ዛሬ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሏ ተሰምቷል!

አዜብ ሰሞኑን በጫካ ፕሮጀክት ምክንያት ስለሚነሱ ነዋሪዎች ''ልማት የሰውን ልጅ ሲያፈርስ አየሁ'' በሚል ርዕስ  አንድ ፅሁፍ በማህበራዊ ሚዲያዎች ካጋራች በኋላ ጽሁፉ በስፋት መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። በኋላም ከማህበራዊ ገጿ ጽሁፉን ማንሳቷን ማስታወቋም አይዘነጋም።

ታዲያ! ''ትችት'' የሚባል ነገር ፈፅሞ እንዲሰነዘርባቸው የማይሹት ፍፁም አምባገነኖቹ ፣ ግለሰቧን አፍነው ወደሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ወስደው እንዳሰሯት ቤተሰቦቿን ዋቢ አድርጎ አንከር ሚዲያ ዘግቧል።

የጉድ ሀገር!


ትግሉ ጠንካራ ውስጣዊ የፋይናንስ ድጋፍ መሠረት ሊገነባ ይገባል!

IMF ለነአብይ ብድርና ድጋፍ ሲያደርግ አመታትን የፈጀ ድርድር አድርጎ ''የብር የመግዛት አቅምን ማዳከምን'' ጨምሮ በርካታ ቅድመ ሁኔታዎች እንዲሟሉ ብሎም ፣ እጅ ጠምዝዘው ከእነሱ ፍላጎትና ጥቅም አንፃር የተቀኘ የኢኮኖሚ ስርአት እንዲገነባ በማድረግ ነው! ያው ምዕራባውያን ድህነትህን ተጠቅመው በእጅ አዙር ባሪያ እንደሚያደርጉህ የሚታመን ነው!

በአማራ ህዝብና ትግል ስም ገንዘብ ሰብስበህ ለመስጠት ፣ ቅድመ ሁኔታ የምታስቀምጥና ተናጠላዊና ቡድናዊ ፍላጎትህን ለማሳካት መደራደሪያ የምታደርግበት ከሆነ ከምእራባውያኑ አበዳሪዎች በምን ትለያለህ ? እነአብይንስ ስለምን ትተቻለህ ?

እንደው ሀተታውን ልተወውና ... የአማራ ህዝብ የህልውናና የነፃነት ተጋድሎ መደገፍና የፋይናንስ ምንጩ መሠረት መሆን ያለበት ፣ በራሱ ሀገር ቤት ባለው ህዝቡ ነው!

ይህን ውስጣዊ የድጋፍ መሠረት መጣል የምትችለው ደግሞ ፣ በጠራ አስተሳሰብና አላማ ላይ ተመርኩዞ የተገነባ የጋራ ተቋማዊ መንገድና አደረጃጀት መስራት ስትችል ብቻ ነው!

በአማራ ኮዝ ላይ ለመታገል ወጥተህ ፣ ርእዮተ-አለማዊና የግብ ልዩነት ሳይኖርህ ፣ ህብረትና አንድነትን ለማምጣት ብሎም የተማከለ ተቋማዊ አስተዳደር ለመገንባት አዳጋች ከሆነብህ ፣ እመነኝ! አንድም እራስህን ፈትሽ ሁለትም ራስህ በፈጠርክላቸው ክፍተት ተጠቅመው ጠላቶችህ ከውስጥ ወደውጭም ፣ ከውጭ ወደውስጥም እየሸረሸሩህ መሆናቸውን አበክረህ ተረዳ!

ተቦርቡረህ ላለመውደቅና ላለመሰባበር ያለህ ብቸኛ አማራጭ ደግሞ ፣ ግለኝነትን (ቡድንተኝነትን) ነቅለህ ፣ በጠራ አስተሳሰብና አላማ ላይ ተመርኩዞ የተገነባ የጋራ ተቋማዊ መንገድ ገንብተህ ተጓዝ!

ከዚያ ውጭ የፈለገ የቀጠናውን ግዙፍ ሰራዊት በየፊናህ ብትገነባ ፣ እርስበርስህ ከመናከስ ፣ በገዛ ልምጭህ ከመገረፍ ፣ የማንም ሀሳብና ፍላጎት መጫኛ ከመሆን ብሎም አይደለም ህዝብን ራስህንም ለመታደግ ከማትችልበት ማጥ ውስጥ መዘፈቅህ ሳይታለም የተፈታ ነው!

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.