🌺ሴና🌺
#ክፍል 2⃣
#ተከታታይ ልቦለድ መልካም ንባብ
ቀናት ተቆጠሩ ትምህርት ተጀመረ በጥዋቱ ወንድሜ የዩኒቨርስቲው በር ላይ አድርሶኝ ሄደ፡፡ የዩኒቨርስቲው በር ላይ ቆሜያለው ፡፡
ግራና ቀኙን መመልከት ጀመርኩኝ ተማሪዎች ፣ መምህራን፣ ተሽከርካሪዎች ይገባሉ ይወጣሉ፡፡ ከዚህ ሁሉ ሰው መሀል አንድ የማውቀውን ሰው ባገኝ ስል በውስጤ እየተመኘው ወደ ገቢው ገብቼ ወደ ዶርሜ ማቅናት ጀመርኩ፡፡ ወደ ዶርሜ አካባቢ ስደርስ ሴት ተማሪዎች ሁለት ፣ሶስት እየሆኑ እየተሳሳቁና እየተጨዋወቱ በእጃቸው ማስታወሻ ደብተር ይዘው ወዲያ ወዲ ሲተራመሱ አየሁ፡፡ 'መቼ ተዋዉቀው እንደዚ ተግባቡ?' ስል ራሴን እየተየኩ ወደ ዶርሜ ህንፃ ገባሁ፡፡ ዶርሜ ሁለተኛ ፎቅ ላይ ዶ.ቁ21ነው፡፡ ደረጃውን ወጥቼ ወደ ዶርሜ ስቃረብ እኔ ከተመደብኩበት ዶርም 3ሴቶች እየተሳሳቁ ሲወጡ ተመለከትኩ ቀርቤ ሰላምታ አቅርቤላቸው እዚህ ዶርም እንደሆንኩ ነገርኳቸው፡፡ልጆቹም በቅንነት የያዝኩትን ሻንጣ ተቀብለውኝ ወደ ዶርም አብረውኝ ተመለሱ፡፡
ገና ዶርሙን ከፍተው ስንገባ የተለያየ የቅባት ፣ዶድራንት እና የሽቶ ሽታ በመደባለቅ ለዶርሙ ልዩ ጠረን ሰጥተዉታል፡፡ ዶርሙ ዉስጥ አራት ተደራራቢ አልጋዎች ግራና ቀኝ ተቀምጠው በመሃላቸው አንድ ባለ አራት በር ቁምሳጥን አለ፡፡ በተጨማሪም ከመግቢያ በሩ በስተቀኝ እና በስተግራ ባለ ሁለት በር ቁምሳጥኖች አሉ፡፡የተደራራቢ አልጋዎች የታችኞቹ በሙሉ በጨርቅ ተጋርደዋል፡፡ በዉጭ በኩል ያለው መስኮቱ በመጋረጃ ስለተሸፈነ ክፍሉ ጨለም ብሎአል፡፡ በከልጋዎቹ መሀል መሬት ላይ ሁለት ትንንሽ ጠረቤዛዎች ተቀምጠዋል፡፡ሁሉም አልጋዎች ተነጥፈዋል፡፡ መሬቱም በአግባቡ ስለመፀዳቱ ራሱ ይመሰክራል፡፡ ደስ የሚል ስሜት ተሰማኝ፡፡
ሻንጣዬን የተቀበለችን ልጅ ጥግ ካለው አልጋ ላይ እያስቀመጠች "ሴና አልጋሽ ይሄ ነው፡፡ ያው ባዶ ከሚሆን ብለን ነው ያነጠፍነው፡፡" አለችኝ ፈገግ እያለች፡፡ሁለቱ ሴቶች ከወደበሩ ቆመዋል፡፡ስሜን እንዴት እንዳወቀች ገርሞኛል፡፡ ግን መጠየቅ አልፈለኩም፡፡ ልጅቷ ቀጠለች "ይሄ ደሞ ሎከርሽ ነው፡፡"አለች ከባለ አራት በሩ ቁም ሳጥን የአንዱን በር ከፍታ እያሳየችኝ፡፡አንድ ነገር አወኩ እኔ ቁምሳጥን ብዬ የጠራውት የዶርም ስሙ ሎከር መሆኑን፡፡
"የክላስ ሰአት አልደረሰም?" ስል ጠየኳቸው፡፡ "ባክሽ ዛሬ ዝም ብሎ ነው አይጀመርም ነገ እንገባለን፡፡" አለችኝ ሎከሩን መልሳ እየዘጋች፡፡ከሁዋላዬ የቆሙትም በአውንታ ራሳቸውን ነቀነቁ፡፡እኔም ባሉት ተስማምቼ ቁጭ ብለን ማውራት ጀመርን፡፡ ለመጀመሪያ ግዜ ከክፍል ቀረው፡፡ ቁጭ ብለን ማውራት ከመጀመራችን ስልኬ ጠራ፡፡ ወንድሜ ነው!
#ክፍል_ሶስትን_ለማንበብ_የቸኮለ👉👍
⭕️ታሪኩ ከተመቻችሁ 👍👈 በመንካት #VOTE ያድርጉልን ለኛም ብርታት መስጠት ነው!!
.............ይቀጥላል............✍
🎙ግሩፑን ለማግኘት
@Mtshaf_bicha
@Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩 @Eyos18 አድርሱን
📗📒📕📗📒📕
Join&share
@EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚