"የህወሓት አማጺያን በሰሜን ጎንደር 119 ሰዎችን መግደላቸውን ነዋሪዎችና ባለስልጣን ተናገሩ
በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን በዳባት ወረዳ ጭና በሚባል አካባቢ የህወሓት ታጣቂዎች 119 ንፁሃን ሰዎችን መግደላቸውን ነዋሪዎችና የወረዳው አስተዳዳሪ ለቢቢሲ ተናገሩ።
ግድያው የተፈጸመው አካባቢው በህወሓት ኃይሎች ቁጥጥር ስር በቆዩባቸው ቀናት ውስጥ መሆኑንና ሽማግሌዎች፣ ሴቶችና ህጻናት በተፈጸመባቸው ጥቃት መገደላቸውን ተናግረዋል።
የጭና አጎራባች ቀበሌ አብጥራ፣ ነዋሪ የሆኑት አቶ አስማረ ታፈረ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ነሐሴ 12/2013 ከቀኑ 9፡00 ጀምሮ በአካባቢው የህወሓት ኃይሎች በመግባት ተኩስ መክፈታቸውንና ውጊያ መካሄዱን አመልክተዋል።
ጦርነቱ እስከ ነሐሴ 29/2013 ዓ.ም ድረስ መካሄዱን የሚገልፁት አቶ አስማረ፣ እስካሁን ድረስ ተገድለው የተገኙ 119 ሰዎች በጦርነቱ ያልተሳተፉ የአካባቢው ነዋሪዎች መሆናቸውን ያስረዳሉ።
"ይህ ቁጥር መሞታቸው ታውቆ ለቅሶ እየተለቀሰ ያለ ነው" በማለት ይህ ቁጥር ከዚህም በላይ ሊጨምር እንደሚችል ነዋሪው ይናገራሉ።
አማጺያኑ በወሰዱት እርምጃ በወረዳው ነዋሪ የሆኑ አዛውንት፣ ህጻናት ቀሳውስት እና ሴቶች መገደላቸውንም አክለው ተናግረዋል።
አቶ አስማረ ከአንድ ቤተሰብ አምስት እና ስድስት ሰዎች የሞቱ መኖራቸውንም ለቢቢሲ ገልጸዋል።
ሌላው የአካባቢው ነዋሪ የሆኑት አቶ ሞላ ውቤ የተፈጠረውን ለቢቢሲ፣ በስፍራው ከነሐሴ 12/2013 ጀምሮ ግጭት ሲካሄድ እንደነበረ አመልክተዋል።
ነገር ግን የህወሓት ታጣቂዎች ወደ ጭና ሲገቡ ምንም ዓይነት ጥቃት እንዳልደረሰባቸው ገልፀው፣ "ጦርነቱ ሲፋፋም እና አማጺያኑ መሸነፋቸውን ሲያውቁ አዛውንት፣ ሕጻናት፣ ሴቶች እንዲሁም እንስሳትን እየገደሉ ሄደዋል" ብለዋል።
አቶ ሞላ ከአንድ ቤተሰብ አራት ሰዎች፣ ቀሳውስትን እንዲሁም ወንድማማቾችን እና ነፍሰ ጡር ሴትን ጨምሮ መገደላቸውን በስም እየጠቀሱ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
እነዚህ ሰዎች በአጠቃላይ በውጊያ የተሳተፉ አለመሆናቸውን በመግለጽም፣ አማጺያኑን በየቤታቸው ሠንጋ አርደው ሲያበሏቸው የነበሩ ሰዎች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ገልጸዋል።
በጭና ቀበሌ ከአማጺያኑ ጋር ለአስራ አንድ ተከታታይ ቀናት ውጊያ ሲካሄድ እንደነበር የሚናገሩት የዳባት ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሰውነት ውባለም፣ የህወሓት ኃይሎች "እንስሳትን እና የአርሶ አደር ንብረቶችን መዝረፍ . . . እንዲሁም ማበላሸት" መፈጸማቸውን አመልክተዋል።
አስተዳዳሪው አክለውም በወረዳው ለተከታታይ አስራ አንድ ቀናት እስከ ነሐሴ 29/2013 ዓ.ም ድረስ የዘለቀ ውጊያ እንደነበርም አረጋግጠዋል።
እንደ አቶ ሰውነት ከሆነ በዚህ ሳምንት በአካባቢው ላይ በተደረገ ቅኝት የበርካታ ንፁሃን የአካባቢው ነዋሪዎች የጅምላ መቃብር ተገኝቷል።
አቶ ሰውነት ከአካባቢው ማኅበረሰብ እንዲሁም ከተገኙ የጅምላ መቃብር አረጋገጥን ባሉት መሰረት እስካሁን ድረስ 119 ሰዎች መገደላቸውን እንዳወቁ ገልጸዋል።
የወረዳ አስተዳዳሪው እስካሁን ድረስ ባለው መረጃ፣ ዛፍ ጋር ታስረው የተረሸኑ ሴቶች፣ አዛውንቶች፣ ህጻናት እና ከቅዳሴ እየተመለሱ የነበሩ ቀሳውስት ጭምር መኖራቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ጥቃቱ ለምን እንደተፈፀመ ሲያብራሩም "በቀላሉ ሊያሳልፋቸው ያልቻለ ሕዝብ በመሆኑ፤ ከተስፋ መቁረጥ የተነሳ ነው" በማለት፤ አማጺያኑ አባሎቻቸው ሲማረኩ እንዲሁም ከፍተኛ ጉዳት ሲደርስባቸው "በብስጭት" ጭና ቀበሌ ላይ በንጹሃንና በጦርነቱ ተሳታፊ ባልሆኑ ዜጎች ላይ ጭፍጨፋ አካሂደዋል ብለዋል።
የህወሓት ኃይሎች በአካባቢው ለቀናት መቆየታቸውን የተናገሩት ነዋሪዎችና አስተዳዳሪው "በአካባቢው በተደረገው ከባድ ውጊያ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው እየተሸነፉ ወደ ኋላ ሲመለሱ ነው ሲቀልቧቸው የከረሙ ንጹሃንን በበቀል ገደሉ" በማለት አቶ አስማረ አስረድተዋል።
አካባቢውን እንደተቆጣጠሩ "እኛ ችግር ያለብን ከመንግሥት ጋር ነው፤ ከእናንተ ጋር አይደለም" በማለት ለነዋሪው ይናገሩ እነደነበር የገለጹት አቶ አስማረ፣ በኋላ ግን ጦርነቱ እየተጧጧፈ ሲመጣ ንፁሃንን ገድለዋል ብለዋል።
በአማጺያኑ ተገድለዋል ከተባሉት ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች ባሻገር፣ አሁንም በአካባቢው ያልተገኙ እና የጠፉ ሰዎች መኖራቸውን ነዋሪዎች ገልጸው "ተይዘው ተወስደው ይሆናል" ሲሉ ይናገራሉ።
ጦርነቱን በመሸሽ ወደ ሌላ ቀበሌ የተሻገረ፣ በዋሻ ውስጥ የተደበቀ እንዲሁም ተጨማሪ የተገደለ ሰው እንደሚኖር ያላቸውን ግምት ነዋሪዎቹ አክለው ለቢቢሲ ገልፀዋል።
አቶ ሞላ ውቤ እስካሁን ድረስ 119 ሰዎች መገደላቸው በነዋሪው ቢቆጠርም ቁጥሩ ግን ከዚህ በላይ ከፍ ሊል እንደሚችል ያላቸውን ስጋት አስረድተዋል።
ባለፉት ሁለት ወራት ኃይሎቹን ወደ አማራ ክልልና አፋር ክልል ያሰማራው ህወሓት በሰሜን ጎንደር ጭና ውስጥ በታጣቂዎቹ ተፈጸመ ስለተባለው የንጹሃን ጅምላ ግድያ እስካሁን ያለው ነገር የለም።
ጭና ቀበሌ የገጠር ቀበሌ መሆኗን እና በእርሻ የሚትዳደሩ ገበሬዎች የሚኖሩባት፣ ከከተማ ርቃ የምትገኝ ስፍራ እንደሆነች የወረዳው አስተዳዳሪ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የህወሓት ታጣቂዎች ወደ ዳባት ጭና ከመድረሳቸው በፊት፣ አዳርቃይ እንዲሁም ደባርቅ ወረዳ ላይ ከፍተኛ ጥቃት መፈፀማቸውን አስተዳዳሪው ጨምረው ገልፀዋል።
በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ ከህወሓት ኃይሎች ነጻ ከወጣ ከቀናት በኋላ የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ንጹሃን የተቀበሩበት የጅምላ መቃብር እንዳገኘ ያስታወቀው የዞኑ አስተዳደር ነው።
በዚህም የህወሓት ኃይሎች በወረዳው ውስጥ "ጭና ተክለ ሐይማኖት በተባለ ቀበሌ ቀሳውስትን ጨምሮ በንጹሃን ሰዎች ላይ ነሐሴ 26 እና 27 የጅምላ ግድያ ፈጽመዋል" በማለት በአንድ መቃብር ብቻ 47 አስከሬኖች እንደተገኙ ገልጿል።"
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈
𝐉𝐨𝐢𝐧👉 @Ummah_Tube