አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ dan repost
📍
በስተመጨረሻም፥
#ለኢትዮጵያ_የዓለም_ብርሃን_ቤተሰቦች፦
[📍] የተሸከማችሁት ኃላፊነት ትልቅ ነው። በማስተዋል ተጓዙ ለሌላው ብርሃን ሆናችሁ ተመላለሱ። የሚዘምቱባችሁን፣ የሚያስከፏችሁን፣ የሚያሰድዷችሁን ሁሉ ግድየለም ታገሷቸው። በፍቅር በትዕግሥት ልታስረዷቸው ሞክሩ። እምቢ ካሉ ከጸኑባችሁ ደግሞ ልቀቁላቸው አካባቢያቸውን። ትቢያውንም እያረገፋችሁ ከእግራችሁ ላይ መሔድ ነው። ያ ቀዬ ግን በኋላ ላይ ከባድ አደጋ ውስጥ ይወድቃል። እነዛም ሕዝቦች ይጎዳሉ። ግን ያ እንዳይሆን ምከሯቸው።
[⚜️] እናንተ ደግሞ እርስ በራሳችሁ እግዚአብሔር በሚወደው መንገድ ላይ ቆማችሁ በፍቅር መተሳሰብ በእምነት መጽናት ይገባችኋል። እግዚአብሔር አሁን ሥራውን ጀምሮ በፊት ለፊት እያያችሁ፣ እየሰማችሁ ነው፤ እያስተዋላችሁ ነው።
[⚜️] ጉድለታችሁን አርሙ ታላላቆቻችሁን አክብሩ ወንድሞቻችሁን አክብሩ ውደዱ ተዋደዱ።
[⚜️] ጽዋችሁን አክብራችሁ ያዙ።
[⚜️] በወንድምህ ላይ የምትነቅፈው ነገር እንኳን ቢኖርህ በትሕትና ነው መነጋገር ያለብህ። በመከባበር ነው መነጋገር ያለብህ! እግዚአብሔር ፍቅርን ነው እንጂ የሚወደው ጸብን አይወድም። ትሕትና ነው እንጂ የሚወደው ትዕቢትን አይወድም። እውነትን እንጂ የሚወደው ሐሰትን አይወድም። ስለዚህ ወደ ስህተት አሠራር ወደ ተሳሳተ አካሄድ አትሒዱ። እምነታችሁን የሚፈትን፣ እምነታችሁን የሚያውክ የስህተት አሠራር ውስጥ እንዳትገቡ ተጠንቀቁ።
[⚜️] ንስሐ ሁልጊዜ ግቡ! በእግዚአብሔር ፍቅር ተመላለሱ። ፍቅርን አጽኑ። በወንድማማች መዋደድ በፍቅር ተሰባሰቡ፤ ተነጋገሩ፤ ተመካከሩ፤ ተዋደዱ። በጽዋችሁም ፍቅር ይንገሥበት። ጠብ ጭቅጭቅ አያስፈልግም።
[⚜️] መማክርቶችን አክብሩ! በዚህ ሰዓት እናንተ እየመሩ ያሉ፥ ይነስም ይብዛም መንፈሳዊ ምሪትን የሚሰጡ ከእግዚአብሔር የተሰጧችሁ ወንድሞቻችሁ ናቸው። አክብሯቸው! አትናቁ! ይሄ ንቀት ማንጓጠጥ እኔ አውቃለሁ ባይነት እነዚህ ሁሉ የእግዚአብሔር ሕዝብ የሚሠራው ባሕርይ አይደለም፤ ምክራችን ይሄ ነው።
[⚜️] በአሁኑ ጊዜ መንፈሳዊ መነቃቃት ሊኖረን ይገባል! በጾም በጸሎት ልንተጋ ይገባል። ቃሉን ደግሞ ያልሰማችሁ በደንብ ያላነበባችሁ ደግሞ አንብቡ ትምህርቶቹን ተከታተሏቸው። ስሟቸው። የእግዚአብሔርን ቃል በተከታታይ ትምህርት እየሰጠን ነው። እነሱን አድምጡ።
[⚜️] ዝግጅትም ይኑራችሁ! ከዚህ በላይ ምን ምልክት ትፈልጋላችሁ? ቀድሞ ስንት ጊዜ ጀምሮ እኛ ለዝግጅት መክረናል። አሁንም ዝግጅት ይኑራችሁ! ደካማ አትሁኑ! በመንፈስ ጠንካራ ሁኑ!
[️⚜️] ግዴታችሁን፥ አሥራት በኩራታችሁን፣ ቸርነት ማድረጋችሁን፣ ጸሎታችሁን እነዚህን ሁሉ እንደጀመራችሁት መጨረስ፣ መሔድ፣ መጓዝ! ሁሉንም ነገር በካሳ ታገኙታላችሁ። ሁሉንም ነገር በበረከት መልሱን ታገኙታላችሁ። እርስ በርሳችሁ ስለጤና፣ ስለ ሰላም፣ ስለ ፍቅር ስለ ውስጣችሁ አንድነት ስለዚህ ሁሉ ጸልዩ።
[📍] እግዚአብሔር እንዲያጸናችሁ፣ እንዲተክላችሁ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር ደጋግማችሁ አቤት በሉ ምክራችን ይሄ ነው።
➻ የኢ.ዓ.ብ መግለጫ፥ ጥቅምት 21፥ 2016 ዓ.ም መግለጫ (2)
⌚️️ ከ1፡04፡28 - 1፡09፡00