አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


የዮሐንስ ራዕይ 22፥11-14
«ዐመፀኛው ወደ ፊት ያምፅ፥ ርኩሱም ወደ ፊት ይርከስ፥ ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ፥ ቅዱሱም ወደ ፊት ይቀደስ አለ። እንሆ፥ በቶሎ እመጣለኹ፥ለያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋራ አለ። አልፋና ዖሜጋ፥ፊተኛውና ዃለኛው፥ መዠመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።
➘➘➘
@christian930
ግሩፕ፦ @AlphaOmega930
📩☞ @Kyrieelesion

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri




ዓለም ከመልእክታቱ አንፃር... dan repost
🟢🟡🔴
ጥር 21 | #እመቤታችን በማይነገር ክብር ዐረፈች።

#እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ቅድመ ዓለም በአምላክ ልቡና ታስባ ትኖር ነበር። ከነገር ሁሉ በፊት እግዚአብሔር እናቱን ያውቃት ነበር።

ከልጇ ዕርገት በኋላ በጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትን ሰብስባ ለጸጋ መንፈስ ቅዱስ አበቃች። በጽርሐ ጽዮንም ከአደራ ልጇ ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ለ15 ዓመታት ኖረች።

በእነዚህ ዓመታት ሥራ ሳትፈታ ስለ ኃጥአን ስትማልድ፣ ቃል ኪዳንን ከልጇ ስትቀበል፣ ሐዋርያትን ስታጽናና፣ ምሥጢርም ስትገልጽላቸው ኑራለች።

🌹 አስደናቂው ዕረፍቷ 🌹

ዕድሜዋ 64 በደረሰ ጊዜ ጥር 21 ቀን መድኃኒታችን አእላፍ ቅዱሳንን አስከትሎ መጣ። ኢየሩሳሌምን ጨነቃት። አካባቢውም በፈውስ ተሞላ። በዓለም ላይም በጎ መዓዛ ወረደ።

እመ ብርሃን ለፍጡር ከዚያ በፊት ባልተደረገ፣ ለዘለዓለምም ለማንም በማይደረግ ሞገስ፣ ክብርና ተአምራት ዐረፈች። ሞቷ ብዙዎችን አስደነቀ


"ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ፥
ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ" እንዲል።


ከዚህ በኋላ መላእክት እየዘመሩ፣ ሐዋርያቱም እያለቀሱ ወደ ጌቴሴማኒ፣ በአጎበር ሥጋዋን ጋርደው ወሰዱ።

በወቅቱ ግን አይሁድ በክፋት ሥጋዋን እናቃጥል ስላሉ ቅዱስ ገብርኤል (ጠባቂ መልአክ ነው) እነርሱን ቀጥቶ፣ ሥጋዋን ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ወስዶ ከዕፅ ሕይወት ሥር አኑሯታል። እንደ ልጇም ከሞት ተነሥታ አርጋለች።
-🌹-

ልደታቸው ከልደቷ፣ ዕረፍታቸው ከዕረፍቷ የተዋደደላቸው #አቡነ_ቀውስጦስ ዐረፉ።

ከቅዱስ ገላውዴዎስና ከቅድስት እምነ ጽዮን በእመቤታችን አማላጅነትና ብሥራት የተወለዱ ናቸው።

ባረፉም ጊዜ እመቤታችን በሰማይ መካከል ነፍሳቸውን በፈገግታ ተቀብላ "መታሰቢያህን ለሚያደርጉ ሁሉ በልጄ በረከት እበርካቸዋለሁ" ብላ ቃል ኪዳን ገባችላቸው።

ከጌታችን የተሰጣቸው ቃልኪዳን 👉 t.me/Ewnet1Nat/9819


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን እግዚአብሔር በዚ ዘመን ፈቃዱን የገለጸበት መልእክትና ከዘመኑም ጥፋት በሥጋም በነፍስም መትረፍያ ቃልኪዳን እንጂ ሃይማኖት አይደለም። ይሄ ለሚያምን ሰው የእግዚአብሔርን ቸርነት ማድነቂያ እንጂ መሰናከያ መሆን አልነበረበትም። እውነቱን በምን ልወቅ፣ በጥርጥርም ያለ በምን ልጽና ለሚል ሰው-
፩. በእምነት እግዚአብሔርን በመጠየቅ- ይሄ እግዚአብሔርን አባቱ ላደረገ፣ በንስሐ፣ በአቅሙ እንደፈቃዱ እየኖረ ላለ ሰው እርሱን መጠየቅ ድፍረትና ግብዝነት ሳይሆን የልጅነት ሥልጣኑ ነው። መጽሐፍ እንደሚል እግዚአብሔር የቅርብ አምላክ እንጂ የሩቅ ስላልሆነ በንስሐ፣ በጾም፣ በጸሎትና በዕንባ ለሚጠይቀው በሕልምም በራእይም በሕይወትም በሰውም ልቡናንም በመምራትና በማብራት እንዲሁም እንደየጸጋው ለጠየቀው ሰው እርሱ ባወቀ በተለያየ መንገድ መልስን ሊሰጥ የታመነ አምላክ ነው።
፪. መልእክቱን ከቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና አንፃር በመመርመር- ሁሉንም መልእክቶች ሆነ አባቶች ያስተላለፉትን ትምህርቶች በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዶግማና ቀኖና መነጽርነት ብንመረምረው ከአዕማደ ምሥጢር፣ ከሥርዓተ ቤተክርስቲያን፣ ከነገረ ማርያም፣ ከነገረ ቅዱሳን፣ ከአበው ትውፊትና ወግ ያፈነገጠው የቱ ላይ ነው? ስለቃልኪዳኑ ሰንደቅ ዓላማና የተከበሩ ቃላት ብናነሳ ከመጽሐፍ ቅዱስ የነ ሊቀ ነቢያት ሙሴና እስራኤላውያን፣ ከቅዱሳን ታሪክ ደግሞ የነ ቅዱስ አንባ አብራም ግብጻዊ ምሥክር አለን። ስለውግዘትም ብናነሳ ከመጽሐፍ ቅዱስ የነ ነቢዩ ኤልያስ ከቅዱሳንም የነ ቅዱስ በጸሎተ ሚካኤል ምሥክር አለን። ስለጽዋም ከመጽሐፍ ቅዱስ፣ ከታሪክ፣ ከአበው ትውፊት ብዙ ምሥክር አለን። በእግዚአብሔር መንፈስቅዱስ መሪነት ብንመረምረው ስለእውነተኝነቱ እንጂ የምንነቅፍበትን ነገር አናገኝም።
፫. የሕሊናና የዘመኑ ምሥክርነት- ራሱን ለማያታልልና እምነት ላለው ሰው በሐገራችንም ሆነ በዓለም እየሆነ ያለው በእግዚአብሔር ቁጣ እንደሆነ ይረዳል። መልእክታቱም ገና ከዓመታት በፊት ስለመጻኢ ሁኔታ በርግጥ መናገራቸው ከእግዚአብሔር መንፈስቅዱስ ስለመሆናቸው ማስረጃ ነው። “ትንቢትን አትናቁ፤ ሁሉን ፈትኑ መልካሙንም ያዙ፤”— 1ኛ ተሰሎንቄ 5፥20-21 እንደሚል መጽሐፍ ማነው ተናጋሪው በሚል የተላለፈውን መልእክት ሐሳብ ችላ ማለትና መናቅ ከጥፋት ይጥላል። ድምጹን ብቻ የሰሙት እነ አብርሃም እነ ኖኅ አንተ ማነህ ብለው እግዚአብሔር በክፉ ቢመራመሩት ዛሬ የእምነት አባቶቻችን አይሆኑም ነበር። የነነዌ ሰዎችም ከዛ በፊት ስለማያውቁት ስለነቢዩ ዮናስ ማንነት ቢመራመሩና ቢንቁ ንስሐም ባይገቡ በተቀጡ ነበር። ጃንደረባው ቅዱስ ባኮስ በፊት አይቶት ስለማያውቀው ስለቅዱስ ፊልጶስ ማንነት ቢመራመርና ቢንቅ ባልተጠመቀ ለኢትዮጵያም ምክንያት ባልሆነ ነበር። አሁንም እነማን ናቸው ሳይሆን መልእክቱ ምን ይላል ብለን በቅንነት እውነትን በመፈለግና በእግዚአብሔር መንፈስቅዱስ መሪነት እንፈትሸው። እኛም የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነታችን፣ በተስፋችነ በቃልኪዳናችን እንጽና። ጌታችን እንዳለው “ኢየሱስ ግን፦ ማንም ዕርፍ በእጁ ይዞ ወደ ኋላ የሚመለከት ለእግዚአብሔር መንግሥት የተገባ አይደለም አለው።” — ሉቃስ 9፥62 
ወደ ኋላ እንዳንመለከት ዕንቁአችን እንዳንጥል እንጽና እንበርታ !
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር!

19/05/2017 ዓ.ም


መጨረስ በራሱ ታላቅ ነገር ነው ወገኖቼ!!
-----/////////-------/////////--
በሩጫ የሚሮጥ ሰው ውድድር ውስጥ የገባ ሰው፡፡42 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውስጥ ገብቶ ከሆነ ያን ለመጨረሽ ብዙ ይሮጣል ብዙ  ይደክማል ፡፡ብዙዎች አስር ሺሆች ሆነው ሲሮጡ አይታችኀችኀል፡፡
ወደ መጨረሻ የሚመጡት  መቶ ሰው ሁለት መቶ ሰው   ምናምን ነው ወደ መጨረሻ የሚመጣው፡፡
መጨረስ በራሱ ታላቅ ነገር ነው፡፡ወገኖቼ !!
በማረግ በአንደኝነት በሁለተኝነት በሥስተኝነት በዓራተኝነት በአምስተኝነት በአስረኝነት እያለ መውጣቱን ተውት፡፡መጨረስ በራሱ በጎዳናው ላይ በሩጫው ላይ ተገኝቶ እፍጻሜው ድረስ መሄድ   ትልቅ ነገር ነው ወገኖቼ !!
📌 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
እምነት  ፤ ተስፋ ፤ ፍቅር ትምህርት  ክፍል -3ቀ ላይ የተወሰደ፡፡


ሁሉም ሰው ሁሉንም አያውቅም።
===================
ለነቢዩ ኢሳይያስ የተገለጸለት
ለነቢዩ ኤርምያስ የተገለጸለት
ለነቢዩ ሕዝቅኤል የተገለጸለት
እንዲሁም ለሁሉም ነቢያቶች የተገለጸላቸው ይለያያል።
ነገር ግን አንዱ ነቢይ ሁሉንም እኔ ብቻ ነው የማውቅ ብሎ ሌላውን ነቢይ ሲነቅፍ ሲተች አልታየም።
ለምሳሌ ድንግል በድንግልና ጸንሳ በድንግልና እንደምትወልድ ስሙንም አማኑኤል እንደምትለው ለነቢዩ ኢሳይያስ ተገልጾለት።ተናገረ።
ለነቢዩ ኤርምያስ ደግሞ በሠላሳ ብር እንደሚሸጥና ክርስቶስ እንሚባልም ተገልጾለት ተናገረ።
ነቢዩ ሚክያስም ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም እንደሚወለድ ተገልጾለት ተናገረ።
ሁሉም እግዚአብሔር የገለጸላቸውን ተናገሩ።
እግዚአብሔር እኮ ሁሉንም ለነቢዩ ኢሳይያስ  ገልጾለት ሁሉንም መናገር ይችል ነበር የሁሉም ክብር ይገለጽ ዘንድ እንጂ።
እናም ነቢዩ ኢሳይያስ  ሁሉንም አውቃለሁ ብሎ ነቢዩ ሚክያስ የተናገረውን ውሸት ነው ክርስቶስ በቤተልሔም አይወለድም አላለም።
ስለዚህ ሁሉም ሰው ሁሉንም አያውቅምና
ሁሉን አውቃለሁ ብሎ ምሥጢሩን ሁሉ ሳይመረምር ዝም ብሎ ከሚናገር ሰው በዚህ ዘመን መራቅ ብልህነት ነው።

ማቴዎስ 11፥6 ላይ እንደተጻፈው።ጌታ
ለድሆችም ወንጌል ይሰበካል፤ በእኔም የማይሰናከለው ሁሉ ብፁዕ ነው።

ሲል ተናገረ።እውነት በዚህ ዘመን በኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት የማይሰናከል ምንኛ ብጹዕ ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ ሰማይና ምድርን አሳልፎ ለፍርድ የሚመጣው እኮ ቀድሞ መጥቶ ተወልዶ ተጠምቆ ተርቦ ተጠምቶ ንስሓ ግቡ ብሎ የታመሙትን ፈውሶ ለምጻሞችን አንጽቶ ወንጌልን አስተምሮ ተሰቅሎ ሙቶ ተነስቶ አርጎ ይህንን ሁሉ አድርጎ ቃሉን በናቁት እና ባቃለሉት ላይ ነው የሚፈርደው።ይህንን ሁሉ ባያደርግ ኑሮ ለፍርድ ባልመጣም ነበር።
ታድያ ዛሬስ በዚህ አመጸኛ ትውልድ ላይ ይፈርድ ዘንድ ሥልጣን የተሠጠው ንጉስ ቴዎድሮስስ ቀድሞ ሳያስተምር የሚገሰጸውን ሳይገስጽ ሳያስጠነቅቅ እንዴት ይመጣል?
የሚፈርደው እኮ በዚህ መልእክቴ እንዲህ አላልኩህም ነበር?ለምን ቃሉን ሰምተህ ንስሓ አልገባህም ብሎ እኮ ነው?

እናም ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃንን መልእክትን  አጣጥሎ ልክ አዲስ እምነት እንደሆነ አድርጎ ህዝቡን ማሰናከል እጅግ ከባድ ፍርድ ውስጥ መግባት ነውና።
ሁሉም ሰው ሁሉን እንደማያውቅ ተረድተን መልእክቱ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን አምነን እስከ መጨረሻው ድረስ መጽናት ከመታደልም በላይ መታደል ነው።
የእግዚአብሔር እውነት ሁሌም አያዳላም።
ዲያቆን ቄስ ጳጳስ መነኩሴ መምህር ብሎ አያዳላም ካጠፋ አጠፋ ነው ንስሓ እንዲገባ ይገስጻል።ያማ ካልሆነ ምኑን እውነት ሆነ ታድያ?
ሁሉም ሰው ሁሉንም አያውቅምና በማንኛውም ሰው መሰናከል ከእውነት ፈቀቅ ማለት እውነትን አለማወቅ ነውና እስከ ሞት ድረስ የታመንን እንሁን
እውነት አርነት ያወጣናል እና።
ሁሉም ሰው ሁሉንም አያውቅም። አራት ነጥብ።
17/5/2017


እኛ ልጅ ለመኾን እንጠመቃለን፤ እርሱ ግን የክርስቲያኖች ኹሉ አባት ለመሆን ተጠመቀ።

✨ ጥምቀት-የኢያሱ ዮርዳኖስን ማሻገር-የጥፋት ውኃ ማቆም ያላቸው ግንኙነት

✨ በዓለ ጥምቀትን ምን ልዩ ያደርገዋል?


ዓለም ከመልእክታቱ አንፃር... dan repost
ጾመ ገሃድ (ጋድ) የቃሉ ትርጉም "ገሃድ" ሲል መገለጥ "ጋድ"ሲል ለውጥ ማለት ነው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደቱና የጥምቀቱ በዓል በሳምንት ሁለት ቀን በምንጾምባቸው ጾም በተሠራባቸው በረቡዕና በዓርብ የዋለ እንደሆነ የጾሙ ሥርዓት ሳያጠበቅ ፡
፩ኛ፡ ታህሣሥ ፳፰ ቀን ለ ፳፱ አጥቢያ፡
፪ኛ፡ ጥር ፲ ቀን ለ ፲፩ አጥቢያ በመንፈቀ ሌሊት ቅዳሴ እንዲፈፀምና ምእመናን በትንሣኤው የአከባበር ሥርዓት ዓይነት በዓሉን በደስታ እንዲያከብሩ አዝዘዋል፡፡ ስለዚህ የሁለቱም ማለት የልደት የጥምቀት ዋዜማ በጾም እንዲታሰብ ሆኗል፡፡ በአንድ በኩል የጌታን መገለጥ የምናስብበት ነው፡፡
መገለጥ ሲባልም እንደ በዓላቱ ጠባይ ሁለት ነው፡፡ በልደት መገለጥ ሲባል ሰው ሆኖ የማያውቅ አምላክ በሥጋ ሰው ሆኖ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ ስለተገለጠና ሰዎች ሊያዩት ሊዳስሱት ስለቻሉ ነው፡፡
በጥምቀት መገለጥ መባሉ ሰው የሆነው አምላክ በዓለም ሲኖር እስከ ፴ ዓመት ዕድሜው ድረስ ሰዎችን ለማዳን የመጣ መሲሕ የሆነው አምላክ አማኑኤል ኢየሱስ ክርስቶስ እሱ መሆኑን ሳያውቁ ከኖሩ በሁዋላ በ ፴ ዓመት ዕድሜው በዮርዳኖስ ወንዝ በዮሐንስ እጅ ሲጠመቅ አብ፡ "የምወደው ልጄ ይህ ነው እሱን ስሙት" ብሎ በሰጠው ምስክርነት ፡ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ ሲያርፍ በመታየቱ ነቢያት የተነበዩለት የሰው ልጆቾ መድኃኒት ሥግው አምላክ ማለት ሰው የሆነ አምላክ እሱ መሆኑ ስለተገለጠበት ነው፡፡
ጾመ ገሃድ ወይም ጋድ ቅዳሜ፡ እሁድ ቢሆን በሰንበት ጾም ስለሌለ ሥርዓተ ጾሙ ከጥሉላት ምግብ በመከልከል ብቻ ይፈፀማል፡፡
አለቃ አያሌው ታምሩ


መ/ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም ዓለም ያለ ሁሉ መልእክቱን ለማግኘት የሚፈልጉ ሰዎችን መርዳት ግዴታው ነው። ከብርቱ ቅጣት መፍሰስ ጀምሮ ሰዎች ለመዳን ይጥራሉና! ማምለጫውን ማሳየት ግዴታው ነው። በዚህም ለመነገድ የሚሞክር ይቀጣበታልና አገልግሎቱን በነጻ ይስጥ።
ውሳኔው ወደ አፈጻጸም ተሻግሯልና ያልጠበቅናቸው አገሮች ሕዝቦች የሚጠፉ ሲጠፉ የሚተርፉ ምሕረት ሲሹና ማምለጫ ሲፈልጉ በየትም ያለ የተዋሕዶ ኦርቶዶክስ ልጅ በትሕትና፣ በቅንነት፣ ራስን ዝቅ በማድረግ፣ መርዳት ዋናው ተግባርና ግዴታው ነው።
» በትምክህት የሚናገር የሚያደርግ የሚመጸደቅ ብርቱ ቅጣት ይጠብቀዋልና ከዚህ አጸያፊ ሥራ
ይቆጠብ።
» አንዳንድ መንግሥታቶች ቡድኖች ድርጅቶች ይጠቅመናል ባሉት ድርጅቶች የመከለሻ ዘዴ
ተጠቅመው ሊገልጹት ይችላሉና በጥንቃቄ ከያዛችሁት ኦርጅናል መልእክት ጋር አመሳክሩት።
» ማንኛውም የሀገር መሪ፣ የእምነት ድርጅት መሪ፣ የጦር መሪ፣ የደኅንነት መሪ፣ የምክር ቤት
አባላት፣ የመወሰኛ ምክር ቤት አባላት፣ የዓለም አቀፍ ድርጅት መሪዎች፣ የእርዳታ ድርጅት
መሪዎች፣ ዓለም አቀፍ የሙያ ማኅበሮች ኃላፊነት ያለበት የሕዝብ አመራር የያዘ በሙሉ ይህን
ትእዛዝ ያስተውል።
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት ሦስት


ዓለም ከመልእክታቱ አንፃር... dan repost
🟢🟡🔴
ጥር 7 | #በዓለ_ሥሉስ_ቅዱስ

አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም፥ በአካል፥ በግብር ሦስትነት፣ በባሕርይ በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው። በዚህ ጊዜ ተገኙ በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም። መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና።

ሩኅሩኀን ናቸውና በእናት ሥርዓት "ቅድስት ሥላሴ" እንላቸዋለን። የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም። የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል።


በዚህች ቀን በዓለ ሥላሴ የሚከበረው ስለ ሁለት ምክንያቶች ነው።

፩. ሕንጻ ሰናዖርን ማፍረሳቸው
፪. ቅዳሴ ቤታቸው ነው።


#_ሕንጻ_ሰናዖር
በአሁኗ ኢራቅ አካባቢ በነበረ ግዛት ከናምሩድ ክፋት በኋላ ሰናዖርና ወገኖቹ ከሰይጣን ተወዳጁ። ሰማይ ጠቀስ ሕንፃን ሠሩ። በክፋትም ሥላሴን ሊወጉ ተነሡ።

ርኅሩኀን ሥላሴ ግን የሰናዖር ሰዎች የሠሩትን አይተው ማጥፋት ሲችሉ አላደረጉትም። የባሪያቸውን የኖኅን ቃል ኪዳን አስበዋልና። ይልቁኑ "ኑ እንውረድ ቋንቋቸውን እንደባልቀው" አሉ እንጂ።

ከለዳውያን ልሳናቸው ተደበላልቆ 71 ቋንቋዎች ተፈጠሩ። እነርሱም ስምምነት አጥተው ተበተኑ። ሥላሴም ያን ሕንጻ በነፋስ ትቢያ እንዲሆን በተኑት። ስለዚህም እስከ ዛሬ ሥፍራው "ባቢሎን (ዝሩት)" ሲባል ይኖራል።

#_ቅዳሴ_ቤት
አድያም ሰገድ ኢያሱ በኢትዮጵያ በነገሡ በ10ኛው ዓመት (በ1684 ዓ.ም)
በጎንደር ከተማ ንግሥተ አድባራት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተሠርታ ተጠናቃለች።

በተሠራች በ16 ዓመቷ፣ ደጉ ኢያሱ ከተገደለ በኋላ ግን ቤተ ክርስቲያኑ በአደጋ ፈርሷል። ዛሬ የምናየው በ1708 ዓ.ም በልጁ በዓፄ ዳዊት ሣልሳዊ የታነጸውን ነው።

🍀 #ቅዱስ_ሶል_ጴጥሮስ ዕረፍቱ ነው፨

የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት፣ ከ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት አንዱ፣ የኒቂያ ጉባኤ ሊቀመንበር ከነበሩና አርዮስን ካወገዙ አንዱ የሆነ፣ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስን ያጠመቀ ሊቅ ነው።


ዓለም ከመልእክታቱ አንፃር... dan repost
🟢🟡🔴
ጥር 4 | #ቅዱስ_ዮሐንስ ወንጌላዊ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓሉ ነው።

๏ በጌታ ደረት ላይ የተጠጋ፥
๏ እሳቱ ያላቃጠለው፥
๏ መለኮት የሳመው
๏ ድንግል ያቀፈችው፣ የሳመችው
[
ቅዱስ ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ ] የዕረፍቱ (የተሰወረበት) በዓል ነው።

እርሱም ጌታችን እጅግ ይወደው የነበረው ሐዋርያ ነው። ጌታችንን እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ በመከተሉ ድንግል እመቤታችንን ተቀብሏል።

ከእርሷ ጋር ለ15 ዓመታት ቢቀመጥ መዝገበ ምሥጢር ሆነ። ስንኳን ከሰው ልጆች ይቅርና ከልዑላኑ መላዕክትም ማዕረጉ ከፍ አለ።

ሰው ቢበቃ መላእክትን ሊያይ ይቻለዋል። ቅዱስ ዮሐንስን ግን መላእክት ሊያዩት ይከብዳቸዋል:: ከፍጥረት ወገን ከእመ ብርሃን ቀጥሎ ክቡር እርሱ ነው

በከሃዲውና በጨካኙ በድምጥያኖስ ዘመን በጣዖት አምላኪዎች ተከሶ ለፍርድ ቀረበ፡፡ በፈላ ውኃ ካሠቃዩት በኋለ በፍጥሞ ደሴት አጋዙት፡፡ በዚያም ሳለ ራእዩን ተመልክቶ ጻፈው፡፡ በዚያም በ90 ዓመቱ ተሰወረ።
▰ ▰ ▰

ቅዱስ አባ መልከጼዴቅ ዘዋሸራ ዐረፉ።

እኚህ አባት የጌታችንን ሕማም በማሰብ ለወፎችን እጅግ ልዩ ምግብ በመመገባቸው ይታወቃሉ።


ዲቁናንና ቅስናን ከግብፅ ተቀብለው በዋሽራ 30 ዓመት በሹመት አገልግለዋል፡፡ ጻድቁ የሚታወቁበት ትልቁ ተጋድሎአቸው በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ሁልጊዜ ዓርብ ዓርብ ያከፍሉ ነበር፡፡

የመድኃኔዓለምን 13ቱን ሕመማተ መስቀሎች በማሰብ አናታቸውን በድንጋይ እያቆሰሉ ቁስሉ ሲተላ ትሉን ለወፎች ይመግቡ ነበር፡፡
▰ ▰ ▰

ዳግመኛም ተጋዳይ የሆነ በጥላው ብቻ ከይሲን የገደለ የደብረ ቢዘኑ #አባ_ናርዶስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው፡፡

«እርሱም እግሮቹ እስኪያብጡ ድረስ ቆሞ በመጸለይ የተጋደለ ነው›› በማለት ስንክሳሩ በአጭሩ የገለጸው ጻድቁ #አባ_ናርዶስ ዕረፍቱ ነው፡፡

http://t.me/Ewnet1Nat




ዓለም ከመልእክታቱ አንፃር... dan repost
🗣 እግዚአብሔር ይመስገን ! እኛ ስንናገር፤ ስንጮኽ ለማያምኑን ይኸው ማረጋገጫ !!

"አስቀድመን ብዙ ስለጮኽን ዛሬ እንኳን ዝም ከማለት በቀር ምንም አንልም"

📌 ሌላውን ዝርዝር ሁኔታ ወደጎን ላቆየውና በጣም የደነቀኝን ልጠቁማችሁ ...በጋራ (ከቫቲካን ካቶሊክ - ከነ ሰዶም ፍራንሲስ ጋራ) በጋራ ስርዓተ ጸሎት አድርሰዋል ይላል ይህ የማኅበረ ርኩሳን ድምፅ !!! አናንተ አርዮሳዊያን ፍርዳችሁን ጠብቁ ።።(ስምንት ነጥብ!)

📌 እንኳንም ወደወላጅ እናታችሁ ወደኢሉሚናቲ (ካቶሊክ) በሠላም ሄዳችሁ ¡ መልካም የሲዖል ጉዞ እነ ውጉዛን !!

#ለታሪክ_ትቀመጥ !!!
የካቲት 18/2015 ዓ.ም
t.me/Ewnet1Nat


ዓለም ከመልእክታቱ አንፃር... dan repost
› ከውስጧ የሚወጡ ሰዎች በእሳቱ ሲጤሱና እሳቱ ሲነድ ለአለም ሁሉ ይታያል ለታመኑ ወዳጆቿም ይተርፋል፡፡

› ከውስጡ የሚወጡ ሰዎች ቢኖሩም ለረጅም ጊዜ የፍርሃትና ድንጋጤው ጥላ-አይርቃቸውም፡፡

..... ሙሉውን ያንብቡት !👇👇👇
❗️ አሜሪካ (ታላቂቱ ባቢሎን) በእሳት እንደምትጠፋ ከመሆኑ አስቀድሞ መጋቢት 19/2001 ዓ.ም ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት 3 ምን ብሎ ነበር?


⚠️አይ ባቢሎን !(አሜሪካ) !አይ አውሮፓ !አይ ኤሽያ !አይ አፍሪካ !ወየው ላቲን አሜሪካ ! አይ አውስትራሊያ! አይ ዓለም! ወዴት  ነው መደበቂያው ? ተመዝናችሁ ቀለላችሁ (ማኔ ቴቄል ፋሬስ ) ስለዚህም በእሳት ወንፊት ትበጠራላችሁ፡፡
⚡️ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት አንድ ገጽ 6 በቀን 7/3/1998 ዓ ም የተጻፈ፡፡


ዓለም ከመልእክታቱ አንፃር... dan repost
የጥር አንዱ ግፍና አለቃ አያሌው የተናገሩት

"ምእመኑ የጥምቀት በዓል ላይ እንዳይገኝ ገዘቱ" ይለናል።

እውነተኛ አባት ግፍን ስለሚጸየፍ እንዲህ ይጋፈጣል። ያበረታል። ይመራል። በቤ/ክኗ ሐዘን ጊዜ ምእመኑን በእልልታ በታይታ 'አምልኮ' አያደነዝዙም።

ፍትሕ እስካልተገኘ ገጽታ ግንባታ፣ ለመንግሥት ድንፋታ ግድ አይሰጣቸውም። ለመዘመርም ለማልቀስም ጊዜ እንዳለው ያውቃሉ። (ከሚያዝኑ ጋር አብራችሁ አልቅሱ እንዲል ቅዱስ ጳውሎስ)

አንድ ሰው ሲገደል እንዲህ ካወገዙ በእኛ ዘመን ኖረው ሀገር ስትገደል ቢያዩ ምን ይሉ ይሆን!?

የሁለቱም አባቶቻችን በረከታቸው ትድረሰን።


ዓለም ከመልእክታቱ አንፃር... dan repost
#_ዝክረ_አበው | ጥር 1

በረከታቸው ይድረሰንና እኚህ አባት አባ (ባህታዊ) ፈቃደ ሥላሴ ይባላሉ።

በአዲስ አበባ በቅዱስ እስጢፋኖስ ቀዳሜ ሰማዕት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በወቅቱ ግፍን በማይፈሩት፣ ሽጉጥ (ታጣቂ) ይዘው በሚንጎማለሉት፣ ሲኖዶሱን የግላቸው ተጠሪ ባደረጉት አባ ጳውሎስ፥ በሽጉጥ ጥር 1 ዕለት በቅዱስ እስጢፋኖስ ታቦት ፊት ተገደሉ።

በሰማዕቱ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ዓመታዊ በዓል ዕለት፣ በታቦቱ ፊት ባህታዊ አባ ፈቃደ ሥላሴ እንደ ሰማዕቱ እስጢፋኖስ እውነትን እና ተግሣጽን ሳይፈሩ በወቅቱ በነበሩት አባ ጳውሎስ ላይ ፊት ለፊት በመናገራቸው በጥይት ተገድለዋል።

አለቃ አያሌው ያን ጊዜ ሊያስታውሱ "አባ ጳውሎስ እንደ ወጉ አባት ናቸውና 'ተው! እንዲህ አይደለም' ብለው መምከር እየቻሉ በዐውደ ምሕረቱ ላይ የሰው ደም አፈሰሱ።" ብለው ትምህርታቸው ላይ ጠቅሰዋል።

አምላከ ቅ/እስጢፋኖስ ለእኛንም በእውነት ለመመስከር፣ ለመጋደል ፈቃዱን ኃይሉን ይስጠን፤ ይድረሰን አሜን።

http://t.me/Ewnet1Nat




ዓለም ከመልእክታቱ አንፃር... dan repost
🟢🟡🔴
ታኅሣሥ 29 | የከበረች #የመድኃኔዓለም_የልደቱ ቀን ነች።

ይኸውም፥ ወር በገባ፦
⚜️ በ27 | እግዚአብሔር ወልድ/መድኃኔዓለም ለእኛ ድኅነት ተሰቅሎ የሞተበትን፣

⚜️ በ28 | እግዚአብሔር ወልድ/መድኃኔዓለም የተወለደበትን (በዘመነ ዮሐንስ) የጌና አማኑኤል (በ3ቱ ዘመናት)፣

⚜️ በ29 | እግዚአብሔር ወልድ/መድኃኔዓለም የተፀነሰበትን፣ የተወለደበትን፣ ከሙታን የተነሣበትን፣ ዳግም የሚመጣበትን በዓል (በዓለ እግዚአብሔር ወልድ የተባለውም ለዚህ ነው) እናከብራለን።
◦🍀◦🍀◦🍀◦

በተጨማሪ ታኅሣሥ 29 የነዚህ ቅዱሳን የልደት መታሰቢያ ነች፨ (ነገር ግን ከበዓላት ሁሉ የመድኃኔዓለም ልደቱ ይበልጣልና የእግዚአብሔር ወልድን በዓል ሰፊ ቦታ ሰጥተን እናከብረዋለን)

📍 ልደቶሙ #ለአብርሃ_ወአጽብሓ (ጽንሰታቸውም ልክ እንደጌታችን መጋቢት 29 ነው)

📍 ልደቱ #ለኢያሱ_መስፍን

📍 ልደቱ ለኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ( #ቅዱስ_አቤላክ/ባኮስ)

📍 ልደቱ #ለአባ_ጉባ (ከ9ኙ ቅዱሳን አንዱ)

📍 ልደቱ #ለቅዱስ_ላልይበላ (ላሊበላ)
📍 ልደቱ #ለቅዱስ_ነአኵቶ_ለአብ (ስንክሳር የተሰወረበት ቀን ይለዋል)

📍 ልደቱ #ለዳግማዊ_ቅዱስ_ቂርቆስ (የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የመጨረሻ ልጅ)

📍 ልደታ #ለቅድስት_ፍቅርተ_ክርስቶስ

📍 ልደቱ #ለቅዱስ_መዝራዕተ_ክርስቶስ

📍 ልደቱ #ለቅዱስ_ገብረ_መንፈስቅዱስ

📍ልደቱ #ለአባ_አብሳዲ ዘደብረ መጉና ልዕልት

በዛሬው ቀን ዕረፍታቸው የሆኑት፦
🔸 #ጻድቅ_ንጉሥ_አቃርዮስ ዐረፈ፣

🔸ገመላዊው #ቅዱስ_ቆሪል ዐረፈ፣

🔸#የአክሚም_ሰማዕታት መታሰቢያቸው ነው፡፡

✨🍀✨🍀✨
T.me/Ewnet1Nat


ዓለም ከመልእክታቱ አንፃር... dan repost
ከላይ የእሳት አይነት የአውሎ ንፋስ አይነት የጎርፍ የማዕበል የበረዶ አይነት እና ብዛት ፍፁም የሚጠርግህ  መቅሰፍት ይወርድብሀል። ውቅያኖሱ ይተፋሀል በማዕበሉ ይጠርግሀል። የምትጠጣው ውሀ መርዝ ሆኖ የስቃይ
ሞት ያሳይሀል። የምትበላው የምድሩም ፍሬ ስጋውም የባህሩም አሳም የገሙ የበከተ መርዝ ሆነው የሚገሉህ በምንም ዘዴ የማታክማቸው ይሆኑብሀል። ከከርሰ ምድር እሳተ ገሞራው ይበሳጭብሀል። በቁጣውም ይገነፍላል።
ምሽጌ ያልከው ምድርህም በከፍተኛ ርዕደ መሬት ያይቶም ተሰምቶም በማያውቅ ማግኒቲዩድ መጠን እየወጣ ወደ እሳት ጉያው ይከትሀል።
ፍርድአዘል መግለጫ ጥቅምት 21 2017 ዓ.ም



20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.