Ibn Seid
👉 ከረመዳን በፊት
=> ሙስሊሞች አላህ ምንዳቸውን እጥፍ ድርብ ለማድረግ ከተደነገጉላቸው ዒባዳዎች አንዱ የረመዳን ወር ፆም ነው።
➽ በዚህ ወር የመልካም ስራ በሮች ክፍት ይሆናሉ የመጥፎ ስራ በሮች ይዘጋሉ። ሙስሊሞች በገራላቸው መልካም ስራ ተሳትፈው እጥፍ ድርብ የሆኖ ምንዳ እንደሚያገኙ በወሕይ ተረጋግጦላቸዋል።
➧ የዚህ ወር መምጣት በጣም በናፍቆት ይጠብቁታል። እየአንዳንዱ ሙስሊም በሕይወት ይህን ወር አግኝቶ ከምንዳው ለመቋደስ ጌታውን ይለምናል። ውስጡ በሐሴት ተሞልቶ ቀኑን ይጠባበቃል። ይሁን እንጂ አብዛኛው ሙስሊም ወሩ ከመግባቱ በፉት ለውጫዊ ዝግጅት ትልቁን ቦታ ሲሰጥ ይታያል። ዝግጅቱ ቤት ቀለም ከመቀባት ምንጣፍ ከመቀየር አንስቶ የተለያዩ የቤት ማስዋቢያዎችን ሲገዛ ከዛም የተለያየ የምግብ አይነት ሲያዘጋጅ ማየት የተለመደ ነው። ይህ ተግባር ሱና ነው ካልተባለና ማባከን ከሌለበት ችግር የለውም። ከዚህ በላይ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ውስጥን ማሳመር ላይ ነው። ለረመዳን ማረፊያ የሚሆነውን ቀልባችንን ማስዋብ ለሱ የሚሆን ቀለብ ማዘጋጀት ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው። ከረመዳን በፊት ልንሰራቸው ከሚገቡ ተግባራቶች ጥቂቶቹን እንይ፦
✅ እውነተኛ ተውበት
✅ ቁርጥ ያለ ንያ
✅ ዱዓእ ማብዛት
✅ ቁርኣን መቅራት መለማመድ
✅ ዚክር ማብዛት
✅ መልካም ሰዎችን መወዳጀት
✅ ስለረመዳን ህግጋት መማር
ለረመዳን ዒባዳ ፕሮግራም ማውጣት
የቀን ተቀን ስራን መመርመር
ድሆችን ማስታወስ
✅ በዱንያ ጉዳይ የተጣሉትን ሰው አውፍ ማለት
✅ የጀማዓ ሶላት ማዘውተር
✅ ሰዎችን ላለመበደል መሞከር
✅ በመልካም ማዘዝ ከመጥፎ መከልከል
✅ ፆመኞችን ለማስፈጠር መዘጋጀት ሌሎችን በእውቀትም በጉልበትም መርዳት
✅ ተሸጋጋሪ ዒባዳዎችን ማብዛት
የረመዳንን ትሩፋት ማወቅ ባወቁት መስራት የሚሉት ጥቂቶቹ ናቸው።
✅ አላህ በረመዳን ደርሰው ከሚጠቀሙት ያድርገን!!!
http://t.me/bahruteka