القناة التعليمية الرسمية للدعوة السلفية في الحبشة


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


☞ዋናውን የቴሌግራም ቻናላችንን ለማግኘት @AbuYehyaAselefy በዚህ ይቀላቀሉ!!
➲የዩቲዩብ ቻናላችንን ለማግኘት እና ቤተሰብ ለመሆን ⬇️
https://youtube.com/channel/UCrHkOu8UyG5-TDewqfcQG5Q
💡☞ለአስተያየት ወይንም ለጥቆማ እንዲሁም ስህተት ካያችሁብኝ በፍጥነት በዚች ይጠቁሙኝ ☞ @AbuYehyabot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


👉  ከረመዳን በፊት

=> ሙስሊሞች አላህ ምንዳቸውን እጥፍ ድርብ ለማድረግ ከተደነገጉላቸው ዒባዳዎች አንዱ የረመዳን ወር ፆም ነው

➽ በዚህ ወር የመልካም ስራ በሮች ክፍት ይሆናሉ የመጥፎ ስራ በሮች ይዘጋሉ። ሙስሊሞች በገራላቸው መልካም ስራ ተሳትፈው እጥፍ ድርብ የሆኖ ምንዳ እንደሚያገኙ በወሕይ ተረጋግጦላቸዋል።
የዚህ ወር መምጣት በጣም በናፍቆት ይጠብቁታል። እየአንዳንዱ ሙስሊም በሕይወት ይህን ወር አግኝቶ ከምንዳው ለመቋደስ ጌታውን ይለምናል። ውስጡ በሐሴት ተሞልቶ ቀኑን ይጠባበቃል። ይሁን እንጂ አብዛኛው ሙስሊም ወሩ ከመግባቱ በፉት ለውጫዊ ዝግጅት ትልቁን ቦታ ሲሰጥ ይታያል። ዝግጅቱ ቤት ቀለም ከመቀባት ምንጣፍ ከመቀየር አንስቶ የተለያዩ የቤት ማስዋቢያዎችን ሲገዛ ከዛም የተለያየ የምግብ አይነት ሲያዘጋጅ ማየት የተለመደ ነውይህ ተግባር ሱና ነው ካልተባለና ማባከን ከሌለበት ችግር የለውም። ከዚህ በላይ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ውስጥን ማሳመር ላይ ነው ለረመዳን ማረፊያ የሚሆነውን ቀልባችንን ማስዋብ ለሱ የሚሆን ቀለብ ማዘጋጀት ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው። ከረመዳን በፊት ልንሰራቸው ከሚገቡ ተግባራቶች ጥቂቶቹን እንይ
እውነተኛ ተውበት
✅ ቁርጥ ያለ ንያ
✅ ዱዓእ ማብዛት

ቁርኣን መቅራት መለማመድ
ዚክር ማብዛት
መልካም ሰዎችን መወዳጀት
ስለረመዳን ህግጋት መማር
ለረመዳን ዒባዳ ፕሮግራም ማውጣት
የቀን ተቀን ስራን መመርመር
ድሆችን ማስታወስ

በዱንያ ጉዳይ የተጣሉትን ሰው አውፍ ማለት
የጀማዓ ሶላት ማዘውተር
ሰዎችን ላለመበደል መሞከር
በመልካም ማዘዝ ከመጥፎ መከልከል
ፆመኞችን ለማስፈጠር መዘጋጀት ሌሎችን በእውቀትም በጉልበትም መርዳት
ተሸጋጋሪ ዒባዳዎችን ማብዛት
የረመዳንን ትሩፋት ማወቅ ባወቁት መስራት የሚሉት ጥቂቶቹ ናቸው


አላህ በረመዳን ደርሰው ከሚጠቀሙት ያድርገን!!!

🔎 ለረመዳን ቤትን ማስዋብ⁉️
🎙በኡስታዝ አቡ ሀመዊያህ ሸምሱ ጉልታ አላህ ይጠብቀው!
👇👇👇
https://t.me/AbuYehyaAselefy/12506

http://t.me/bahruteka


شروط الصلاة.pdf
172.5Kb
📙 የኮርሱ ኪታብ ይህ ነው።

በሸይኽ ዐብዱል ሀሚድ

ቀጥታ ስርጭት በዚህ ተከታተሉ

አቡ ዒምራን
https://t.me/AbuImranAselefy?livestream=1c3dafd67239477bf9

የሱና ብርሀን
https://t.me/kedrAbuabderehman?livestream=574dafea01c8ece6b7


Muhammed Mekonn dan repost
ሀገር-አቀፉ ዳዕዋ

    ጀ
        መ
             ረ


🏝 ርዕስ፦
የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት

🎙 በተወዳጁ ኡስታዛችን ኡስታዝ ሙሐመድ ኪርማኒ አላህ ይጠብቀው

⏸ #ኢትዮጵያ ደቡብ ክልል #ሌራ_ከተማ

🌍 ሳትርቁ ጠብቁን ሸርም አድርጉ

🏝           ➘➘➘
https://t.me/AbuImranAselefy?livestream=1c3dafd67239477bf9


Muhammed Mekonn dan repost
🤲 ሁላችሁም አርሂቡ 🤲

ከሰሜን ወሎ - ከውቢቷ ሐራ፤
ጉዞ ወደ ደቡብ - ወደ ስልጤ ሌራ
ለትልቅ አለማ - ለኮርስ ለሙሐደራ፤
በሱና አሊሞች - ኪታብም ሊቀራ፤
በሀቅ ለመመካከር - ሊባበሉ አደራ፤
ብርሃን ለማብራት - የተውሂድን ጮራ፤
በቁርዓን በሐዲስ - ሁሉም እንዲመራ፤
ጭለማን ለመግፈፍ - የጀሂሊያን ስራ፤

ለመናድ ለማፍረስ - የሺርክን ተራራ፡፡
ሱናን ለማስፋፋት - ሀቅን ሊያበስሩ፤

ቢድዓን ለመግታት - ባጢል ሊሰባብሩ፤
የአምቢያዎችን ስራ - በህብረት ሊሰሩ፤
ዛሬ ተራ ደርሷት - ሌራ ላይ ሰፈሩ፡፡
ብዙም አትገረም - በሐራ ጀግኖች ስራ፤
ይህ አዲስ አይደለም - ያለ ነው የነበረ፤
ወፍም ትበራለች - ከአምሳያዎቿ ጋራ፤
ይህ ግን መታደል ነው - ለሁሉ አይገራ፤
ከሩቅ ከአማራ ክልል - ከሰሜን ወሎ ሐራ፤
ወደ መዕከላዊ ኢትዮጵያ - ወደ ስልጤ ሌራ፤
ሰሜን ደቡብ ሰይል - በዘር ሳይለያይ ጎራ፤
በአላህ ገመድ ተሳስሮ - በአንድነት በጋራ፤
ተውሂድን ለመስፋፋት - ለዲን መስራት ስራ፤
የእውነት መታደል ነው - ለሁሉ ሰው አይገራ፤
ከሩቅ የመጣችሁ - ከሰሜን ወሎ ሐራ፤
አላህ ይቀበላችሁ - ይህን ድንቅ ስራ፤
ሁላችሁም አርሂቡ - የመጣችሁ ሌራ፤
በተለይ ከሰሜን ወሎ - ከውቢቷ ሐራ

እንደ አጋጣሚ ሆኖ - ባልመጣም ወደ ሌራ፤
ሰለፊዮች ሁሉ - የመጣችሁ ከየትም ስፍራ፤
ለአላህ ብዬ እወዳችሃለሁ - ከልብ ያለ ጉራ፤
ወንድማችሁ (ኢብኑ ኑሪ) - ከስልጤ ሳንኩራ፡፡

✍️ (ኢብኑ ኑሪ) የካቲት 7/2017
                 ስልጤ (ሳንኩራ)

🏝 ግጥሟን “ራየቱ ኢብኑ ኑሪ” ብለናታል። ወንድማችንን አላህ ይጠብቅልን

🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣ 
╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞

🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy


📙 ከሙብተዲዖች ጋር መቀማመጥ ያለው አደጋ!

ታላቁ የየመኑ ሊቅ ሙሀመድ አሽ’ሸውካኒይ ረሂመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦

«قال الله تعالى "وَإِذَا رَأَيْتَ الَّذِيْنَ يَخُوْضُوْنَ فِيْ آيَاتِنَا فَأَعْرِضْ عَنْهُمْ حَتَّىٰ يَخُوْضُوْا فِيْ حَدِيْثٍ غَيْرِهِ" الأنعام: ٦٩

አላህ ጀለ ወዓዘ እንዲህ አለ "እነዚያንም በአንቀጾቻችን የሚገቡትን ባየህ ጊዜ ከእርሱ ሌላ በኾነ ወሬ እስከሚገቡ ድረስ ተዋቸው፡፡" አንዓም 68

وفي هذه الآية موعظة عظيمة لمن يتسمح بمجالسة المبتدعة، الذين يحرفون كلام الله، ويتلاعبون بكتابه وسنة رسوله صلى الله عليه وسلم ويردون ذلك إلى أهوائهم المضلة وبدعهم الفاسدة، فإنه إذا لم ينكر عليهم ويغير ما هم فيه فأقل الأحوال أن يترك مجالستهم، وذلك يسير عليه غير عسير.

በዚች አንቀፅ ውስጥ እነዚያ የአላህን ንግግር የሚያንሻፍፉ፣ በመፅሀፉ እና በመልእክተኛው መንገድ የሚጫወቱ፣ ያንን ሁሉ ወደ አጥማሚ ስሜታቸው እና ወደ ተበላሸ ፈጠራቸው የሚመልሱ የሆኑትን ሙብተዲዖችን በመቀማመጥ ለሚተሻሽ ሰው ሁሉ ትልቅ ምክር አለ። እሱ ካልተቃወማቸው እና እነሱ ያሉበትን ሁኔታ የማይቀይር ከሆነ፤ ያለበት ትንሹ ሀላፍትና እነሱን መቀማመጥ መተው ነው። ይህም ደግሞ በሱ ላይ ቀላል ነው ከባድ አይደለም።"

وقد يجعلون حضوره معهم مع تنزهه عما يتلبسون به شبهةً يشبهون بها على العامة ،فيكون في حضوره مفسدة زائدة على مجرد سماع المنكر.

ሰውዬው ከነሱ ቢድዓ የጠራ ከመሆኑም ጋር ከነሱ ጋር መቀማመጡን በተራው ማህበረሰብ ላይ የሚያወዛግቡበት ብዥታ ሊያደርጉት ይችላል። ስለዚህ እነሱ ጋር በመቀማመጡ መጥፎን ነገር ከመስማት በሻገር ተጨማሪ ውድመት ይከሰታል።

وقد شاهدنا من هذه المجالس الملعونة ما لا يأتي عليه الحصر، وقمنا في نصرة الحق ودفع الباطل بما قدرنا عليه، وبلغت إليه طاقتنا.

በርግጥ ከነዚህ የተረገሙ መቀማመጦች የማይገደቡ በርካታ ነገራቶችን አይተናል። ሀቅን በመርዳት እና ባጢልን በመገፍተር የቻልነውን ልክ እና አቅማችን በደረሰችው ቆመናል።

ومن عرف هذه الشريعة المطهرة حق معرفتها، علم أن مجالسة أهل البدع المضلة فيها من المفسدة أضعاف أضعاف ما في مجالسة من يعصي الله بفعل شيئ من المحرمات

ይቺን ንፁህ የሆነችዋን ሸሪዓን ተገቢ የሆነን መገንዘብ የተገነዘበ ሰው የአጥማሚ ፈጠራ ባለቤቶችን መቀማመጥ ከአደጋ ሆኖ በውስጡ ከክልክሎች አንዱን በመስራት አላህን የማመፅ ባልተቤቶችን መቀማመጥ ውስጥ ካለው አደጋ የእጥፍ እጥፍ እንደሆነ ያውቃል።

ولاسيما لمن كان غير راسخ القدم في علم الكتاب والسنة فإنه ربما ينفق عليه من كذباتهم وهذيانهم ما هو من البطلان بأوضح مكان، فينقدح في قلبه ما يصعب علاجه ويعسر دفعه فيعمل بذلك مدة عمره ويلقى الله به معتقدا أنه من الحق ،وهو من ابطل الباطل وأنكر المنكر.


በተለይ ደግሞ በቁርአን እና ሀዲስ እውቀት እግሩ ያልጠለቀ ለሆነ አካል! ምናልባትም ከመዘባረቃቸው እና ከመዋሸታቸው የሆነ በጣም ግልፅ በሆነ ደረጃ ያለ ባጢል ሊደበቅበት ይችላል። ከዚያም መታከሙ የሚያስቸግር እና መገፍተሩ የሚከብድ የሆነ ነገር በልቡ ላይ ይጫራል። እድሜ ልኩ በዚያ ባጢል ይሰራ። በጣም ግልፅ ከሆኑ ውሸቶች እና በጣም ግልፅ ከሆኑ መጥፎዎች የሚቆጠር ሆኖ ሳለ ሀቅ ነው ብሎ ያሰበ ሲሆን አላህን በዛ ባጢል ይገናኛል።»

اهـ فتح القدير سورة الأنعام: الآية ٦٩.

ዛሬ ዛሬ ግን በርካታ ከመንሀጅ የተፍረከረኩ የሆኑ አካላት ከቢድዓ ባልተቤቶች ጋር በመስለሀ ስም አድርገው የሚቀማመጡ፣ የሚጓዙ፣ የሚሳሳቁ፣ የሚወዳደሱ፣ የሚሿሿሙ፣ የሚተጋገዙ፣ እና የሚተሻሹ በርካታ ናቸው። በጣም የሚያሳዝነው እነሱን አይቶ የሚፍረከረከው በበርካታ የሚቆጠር ወጣት ክፍል ነው። አላህን የሚፈሩ ቢሆኑ እዛ የሚገኝ የሆነን ያልተረጋገጠ ጥቅም አይኖች ከሚያዩት ግዙፍ ግዙፍ መፍሰዳዎች ጋር ባላወዳደሩ ነበር። በርግጥ ለኡማው መስለሀ በሚል ይቀባቡት እንጂ የሚፈልጉት የግል ጥቅምን ነው። ስልጣን፣ ገንዘብ፣ እውቅና እና ክብር ፈልገው እንደሆነ እያየን ነው። አላህ ሁሉንም ቀናውን መንገድ ይምራው።


✍ በወንድም፡ ሙሀመድ አል-ወልቂጢይ

t.me/abuzekeryamuhamed
t.me/abuzekeryamuhamed


🔸 አዲስ ሙሀደራ

🔊 “ስለ ቁርአን!!”

🎙በኡስታዝ ሙሀመድ በረካ አል-ኪርማኒይ (ሐፊዘሁላህ)

ሌራ ኢማሙ አህመድ መስጂድ የተደረገ

t.me/abuzekeryamuhamed
t.me/abuzekeryamuhamed


↪️ ሙሐደራ ቁጥር 015

🔈 የሙሀደራው ርእስ "የፆም ህግጋት ክፍል አንድ 01"

🔈  محاضرة بعنوان "أَحْكَامُ الصِّيَامِ"

🎙በወንድም አቡ ዘከሪያ ሙሀመድ አል-ወልቂጢይ (ሀፊዘውላህ)

t.me/alwelkitymuhadra
t.me/alwelkitymuhadra


🔸 አዲስ ሙሀደራ

🔊 “እንግዳን በክብር ማስተናገድ በኢስላም አስተምሮ!!”

🎙በሸይኽ አቡ ዐብዲል ሀሊም ዐብዱል ሀሚድ ያሲን አል-ለተሚይ (ሐፊዘሁላህ)

ሌራ ኢማሙ አህመድ መስጂድ የተደረገ

t.me/abuzekeryamuhamed
t.me/abuzekeryamuhamed


አዲስና ወቅታዊ ትምህርት
     ¯¯¯¯¯¯¯

📖 اسم الكتاب:-
↩️
مُذَكِّرَةُ فِيْ أَحْكَامِ الصِّيَامِ
📖 የኪታቡ ስም፦
↪️  ሙዘኪረቱን ፊ አህካሚ ሲያም

🏝 ⇣⇣⇣•••⇣⇣⇣ 
📢[ክፍል አስራ አንድ]
   ➶➹➶➹➶➹

📄ሪሳላዋን በ𝕡𝕕𝕗 ለማግኘት
➘➷➴➘➷
http://t.me/AbuYehyaAselefy/9710

📝 📝تأليف፡- العلامة أبو إبراهيم محمد بن عبد الوهاب الوصابي العبدلي «رحمه الله» (ت: ١٤٣٦ه‍)
📝 ፀሐፊ፦ አል-ዓላማህ አቡ ኢብራሂም ሙሐመድ ብን አብዱልወሐብ አላህ ይዘንላቸው!

🎙الأستاذ الفاضل أبي أنس أبي جعفر محمد أمين السلفي «حفظه الله»
🎙
በውዱ ኡስታዛችን ኡስታዝ አቡ አነስ [አቡ ጀዕፈር] ሙሐመድ አሚን አላህ ይጠብቀውና

🏠ቦታ፦ 🕌 በሰለፍዮች ፉርቃን መስጂድ [ሸዋሮቢት ከተማ] የተሰጠ ወቅታዊ ኮርስ

        •┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•

ይ   ቀ   ጥ   ላ   ል
👇👇👇 ጆይን ብለው ይከታተሉ
https://t.me/+w-uAkEZwibVlNzM8

📱⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣
https://t.me/AbuYehyaAselefy
https://t.me/AbuYehyaAselefy
https://t.me/AbuYehyaAselefy




⛔️ ቫላንታይን!! ❪Valentine❫


ቫይረስ ነው ለኢስላም ጠንቅቀህ እወቀው፤
ላጤ ከሆንክ አግባ ተሰተር በጊዜው፤
ንቃ እንዳትሸወድ በፈረንጅ ሱና፤
ታች ላይ አትበል ቀጥ በል ግባና፤
ይጥፋ የፍቅር ቀን የኛ አይደለምና፤
ንፁህ ሁነህ ኑረው የኢስላምን ጎዳና።

➠📱👇👇👇👇
https://t.me/AbuYehyaAselefy
https://t.me/AbuYehyaAselefy
https://t.me/AbuYehyaAselefy


⛔️የፍቅረኛሞች ወይስ የዝሙተኞች ቀን?!
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯

"መልከ ጥፉ በስም ይደግፉ" እንደሚባለው ዝሙትን አሰማምረው ስሙን ቀይረው ያበረታታሉ። ነጭ ነጩን ስናወራ ቅር አይበላችሁ!። ሺርኩን ሺርክ ነው፣ ቢድዓውን ቢድዓ ነው፣ ሀራሙ ስሙን ቀያይሮ ሲመጣም ሀራም ነው ስንል ቅር ሊላችሁ አይገባም!፣ እውነታውን መቀበል ነው። የዝሙተኞችን ቀን ስሙን ቀያይረው የፍቅረኛሞች ቀን ቢሉ ያው በኒካህ ያልተሳሰሩ ተቃራኒ ፆታዎች “ያለ ኒካህ የተፋቀርንበትን ቀን ታሳቢ አድርገን አብረን እንዝናና አብረን እንደር” ተብሎ ዚና የሚሰራበት በዚህ አመለካከት ለተዘፈቁ ሰዎች የዝሙተኞች ቀን እንጂ የተለየ ነገር የለውም።

ምናልባትም አንዳንድ ሰዎች “የዚና ቀን ለማለት ይከብዳል” በማለት ድክም ያለች ምክንያት ያነሳሉ፣ ምክንያታቸውም "ተፋቅረው ወደ ኒካህ የሚሄዱ አሉ፣ ስለዚህ ያንን ቀን ቢያከብሩት ምንችግር አለው?!" የሚሉና ሌሎችንም መሰል ምክንያቶች የሚያነሱ አይጠፉም። ሲጀመር ከኒካህ በፊት መፋቀር ሚባል ነገር የለም!። እስቲ የሚከተሉትን ነጥቦችን እንመልከት:-

①, ቀኑ ስያሜውን ያገኘውና መከበር የጀመረው በማን እና መቼ ነው? ካልን፣ ያው በከሀዲ ፈረንጆችና በዝሙተኞች ከሚል መልስ የተለየ ነገር አናገኝለትም። ሌሎችም በነሱ ቀንተው ነው “ፍቅረኛዬ” ወይም ሴትና ወንድ ሆነው እያለ “ጓደኛዬ” በሚል ስም በዝሙት ሲንዘላዘሉ ቆይተው መጀመሪያ የተገናኙበት ቀን ታሳቢ በማድረግ ይህን ቀን የሚያከብሩት። ይህ ታዲያ የዝሙተኞች ቀን ለመሆኑ ዋና ማሳያ ነው።

②, በእለቱ በተለየ መልኩ ወጣቱን ለዝሙት ይበልጥ የሚያነሳሱ ተግባሮች ይከናወኑበታል። በማህበራዊና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች የተለያዩ አጋጣሚዎችን እያነሱ ወጣቱን ትዳር ከሚባለው ነገር አርቀው “ፍቅረኛሞች” በሚል የዝሙት ህይወት እንዲኖር ያበረታቱታል።

③, በስርኣቱ ሸሪዓ እንደሚያዘው ኒካህ አድርገው ቢሆን ኖሮ የኒካህ ቀን ብለው ነበር የሚሰይሙት እንጂ የፍቅር ቀን ብለው አይሰይሙትም ነበር፣ ምክንያቱም በእስልምና መፋቀር ከኒካህ በኋላ ነው። ይህም ቢሆን እስልምና እውቅና ያልሰጠው ሌላኛው የቢድዐ ተግባር ሆኖ ሀራም ይሆናል።

④, ሌላው የጀመሩት አይሁዶች እና ክርስቲያኖች ናቸው። በአይሁድና ክርስቲያን መመሳሰል ደግሞ ወንጀሉ የከፋ ነው። ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) "በሰዎች የተመሳሰለ ሰው እርሱ ከነርሱ ነው" ብለዋል። ሰዎች ማለት አይሁድና ክርስቲያኖች ማለት ነው።

⑤, ሰዎች ከትዳር ርቀው "ፍቅረኛዬ፣ ወንዱ ሴት ጓደኛዬ፣ ሴቷም ወንድ ጓደኛዬ" እየተባባሉ በዝሙት እንዲቆዩ ለዝሙትና ለዚህ ሸሪዓን ለጣሰ ግንኙነት እውቅና መሰጠትም ነው። በሸሪዓችን ያለ ኒካህ የተቃራኒ ፆታ ጓደኝነት የሚባል ነገር ሀራም (ክልክል) ነው!!

እንዲህ ያሉ ከባባድ ወንጀሎችን ምንም ያህል ስማቸውን እየቀያየሩ የተፈቀዱ በማስመሰል ሙስሊሙ ዘንድ ቢያቀርቧቸውም፣ ያው ወንጀል ከመሆናቸውና ሀራም ከመሆናቸው የሚቀየሩ ነገር የለም።

የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ስለ አስካሪ መጠጥ ሲናገሩ "ያለ ስሙ ይጠሩታል…" ብለው ነበር፣ እንዳሉትም አስካሪ መጠጦች ስማቸው እየተቀያየረ ብቅ ሲሉ ዓሊሞች ደግሞ "ስሙ ቢቀያየርም እውነታውን አይቀይርም" እያሉ ሀራምነቱን ለአማኙ ማህበረሰብ ግልፅ እያደረጉ ሙስሊሙም እየተጠነቀቀ ቀጥሏል። ልክ እንደ አስካሪ መጠጡ ሌሎች ከባባድ ወንጀሎችንም ስማቸውን እየቀያየሩ ያለ ስማቸው ቢጠሯቸውም ልንሸነገል አይገባም።

የእስልምና እና የሙስሊሙ ጠላቶች ሙስሊሙ ማህበረሰብ ፈፅሞ የማይደራደርባቸውና እውቅና ሊሰጣቸው የማይችልባቸውን ከባባድ ወንጀሎችን ስማቸውን ቀያይረው እያመጡ በእስልምና ዘንድም እንደ ሀላል (የተፈቀዱ) ለማስመሰል ይሞክራሉ። ይህን ጊዜ ሙስሊሙ ነቅቶ "የስም መቀያየር እውነታን ሊቀይር አይችልምና" ሀራሙን ሀራም ነው እምነታችን አይፈቅደውም ሊላቸው ይገባል።

በምንም አቅጣጫ ከሀዲዎች ቆሻሻና የሸሪዓችን እሴቶችና ድንቅ የሆኑ ስነ-ምግባሮችን ሊንዱብን የሚችሉ ባህላቸውን እኛ ላይ እንዲጭኑብን ልንፈቅድ አይገባም!። በተቃራኒ ፆታዎች ግኑኙነት ዙሪያ የሙስሊሙ ትክክለኛው እምነት፣ ባህልና እሴት ሴትን ልጅ ፍቃደኝነቷ ከተረጋገጠ በኋላ በኒካህ ከሀላፊዎቿ ወስዶ በማግባት በትክክለኛ ውዴታ ተንከባክቦ እያኖሩ ጥሩ ትውልድን ማፍራት ነው።

አላህ ዝሙትን ከሌሎች ከባባድ ወንጀሎች በተለየ መልኩ "ዝሙትን አትቅረቡት!!" ብሎ በሩቁ ነው ያስጠነቀቀው። ይህ ማለት ወደ ዝሙት መጓዝ ይቅርና ጭራሹኑ ወደ ዝሙት መዳረሻ የሆኑ ነገሮች በጠቅላላ የተከለከሉ (ሀራም) ናቸው ማለት ነው።

የዝሙተኞችን (የፍቅረኛሞችን) ቀን እንጠየፍ‼
ሙስሊም የዝሙተኞችን ቀን አያከብርም‼
ለዝሙተኞች ቀንም እውቅና አይሰጥም‼።
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join ያድርጉና ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa


Muhammed Mekonn dan repost
🏝 ልዩ ሀገር አቀፍ የዳዕዋና ኮርስ ፕሮግራም

👉 በአላህ ፈቃድ የዲን ትምህርት ድግስ ከቀን 07/06/2017 የጁመዓ ኹጥባ እና ሶላት ጀምሮ  ለተከታታይ 3 ቀናቶች ተዘጋጅቷል።

 🏞 ቦታሌራ ከተማ በኢማሙ አህመድ መስጂድ እና መድረሳ ተሰናድቶ ይጠብቃችኋል።

🪑 በዝግጅቱ ላይ ከሚገኙ ውድና ብርቅዬ መሻይኾች መካከል፦
🎙 አሸይኽ ዐብዱልሐሚድ ያሲን (ከለተሞ)
🎙 አሸይኽ ሙሐመድ ሀያት (ከወሎ ሐራ)
🎙 አሸይኽ ሙሐመድ ጀማል (ከኮምቦልቻ)
🎙 አሸይኽ ሙባረክ አልወልቂጢይ (ከቀቤና)
🎙 አሸይኽ አብድል ከሪም (ከኦሮሚያ ጅማ)
🎙 አሸይኽ መህቡብ (ከሳንኩራ)     
🎙 አሸይኽ አህመድ ወሮታ (ከጎንደር)
🎙 አሸይኽ አወል (ከዳሎቻ)

በተጨማሪም በቀጥታ ስርጭት
🎙 አሸይኽ ሁሴይን መሀመድ (ከሳዑዲ አረቢያ)
🎙 አሸይኽ አቡ ዘር ሀሰን (ከሳዑዲ አረቢያ)
🎙 አሸይኽ ሀሰን ገላው (ከባህር ዳር)
🎙 አሸይኽ ዩሱፍ አህመድ (ከባህር ዳር)

👉 እንዲሁም እንደ ኡስታዝ ባህሩ ተካ አቡ ዑበይዳህ የመሳሰሉ በርካታ ኡስታዞች የሚታደሙበት ደማቅ ፕሮግራም ነው።

👉 ከሚሰጡ ኮርሶች መካከል፦
📚 شُروطُ الصَّلاةِ وَواجِباتُها وَأركانُها
📚 የሶላት መስፈርቶች ማዕዘናቶቿ እና ግደታዎቿ

📝 للشـيخ محمد بن عبد الوهاب النجدي
🎙 በሸይኽ አብዱልሐሚድ ብን ያሲን አል`ለተሚይ
       
👌 የሀቅ ወዳጆች ሁሉ በአክብሮት ተጋብዛችኋል እንዳትቀሩብን!

♨️ ማሳሰቢያ፦ ሁላችሁም ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ እና የማታ ልብስ እንዳትዘንጉ።

👌 አላህ ካለ ሩቅ ላላችሁ 𝙡𝙞𝙫𝙚 ላይ እናካፍላችኋለን
🏝           ➘➘➘➘ 
https://t.me/AbuImranAselefy

🔎 ሸር በማድረግ ለሰለፍዮች በሙሉ የማድረስ ሀላፊነታችንን እንወጣ!

👌 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚 𝕤𝕙𝕒𝕣𝕖 sʜᴀʀᴇ


📙 ከቁርአን ጋር በተያያዘ የሀዲስ ድርሺያ ምን እንደሆነ ታውቃለህ?

የዘመናችን ታላቅ ሙሀዲስ የነበሩት ሸይኽ ሙሀመድ ናሲሩዲን አል’አልባኒይ ረሂመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦

«تعلمون جميعا أن الله تبارك وتعالى اصطفى محمدا بنبوته واختصه برسالته فأنزل عليه كتابه القرآن الكريم وأمره فيه - في جملة ما أمره به - أن يبينه للناس فقال تعالى "وَأَنْزَلْنَا إِلَيْكَ الذِّكْرَ لِتُبَيِّنَ لَلنَّاسِ مَا نُزِّلَ إِلَيْهِمْ" النحل ٤٤.

አላሁ ጀለ ወዓላ ሙሀመድን ነብይ በማድረግ እንደመረጣቸው፣ ረሱል በማድረግ እንደነጠላቸው ሁላችሁም ታውቃላችሁ። ከዚያም የተከበረውን ቁርአን ቀስ በቀስ አወረደባቸው። ቁርአን ውስጥም አዟቸዋል። ካዘዛቸው ትዛዞች መካከል ቁርአንን ለሰዎች እንዲያብራሩ አዟቸዋል። ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ይላል "ወዳንተ ሀዲስን አውርደናል ለሰዎች የተወረደላቸውን  (ቁርአንን) እንድታብራራላቸው" አነህል 44

والذي أراه أن هذا البيان المذكور في هذه الآية الكريمة يشتمل على نوعين من البيان.

እኔ እንደሚመስለኝ በአንቀፁ ውስጥ የተጠቀሰው ማብራራት ሁለት አይነት ማብራራትን ያካትታል።

الأول: بيان اللفظ ونظمِه وهو تبليغ القرآن وعدم كتمانه وأدائه إلى الأمة كما أنزله الله تعالى على قلبه صلى الله عليه وسلم وهو المراد بقوله تعالى"يَاأَيُهَا الرَّسُولُ بَلِّغْ مَا أُنْزِلَ إِلَيْكَ مِنْ رَبِكَ" المائدة  ٦٧ .........

አንደኛ፦ ቃሉን እና የቃሉን አቀማመጥ ማብራራት ነው። እሱም ቁርአንን ማድረስ ነው። ቁርአንን አለመደበቅ እና ለኡማው ልክ እንደተወረደ አድርጎ ማድረስ ነው። ይሄኛው በዚህ አንቀፅ የተጠቀሰ ነው "አንተ ረሱል ሆይ ከጌታህ ወዳንተ የተወረደውን አድርስ" አል’ማኢዳ 67 …

والثاني: بيان معنى اللفظ أو الجملة أو الآية الذي تحتاج الأمة إلى بيانه وأكثر ما يكون ذلك في الآيات المجملة أو العامة أو المطلقة فتأتي السنة فتوضح المجمل وتخصص العام وتقيد المطلق وذلك يكون بقوله ﷺ كما يكون بفعله وإقراره.

ሁለተኛው፦ ለኡማው መብራራት ሚያስፈልገውን አንቀፇን ወይም የቁርአኑን ቃል ወይም አረፍተ-ገሩን ማብራራት ነው። ብዙ ግዜ ማብራራት ሚያስፈልጋቸው አንቀፆች ጠቅለል ያሉ ወይም ልቅ የሆኑ ወይም ሁሉ አካታች የሆኑ አንቀፆች ናቸው። ከዚያም ሀዲስ ይመጣና ጠቅለል ያለውን ያብራራል ልቅ የሆነውን ይገድባል ሁሉን አካታች የሆነውን ይነጥላል። ይህም ደግሞ በነብዩ ንግር ነው የሚሆነው። በተግበራቸውና በማረጋገጫቸውም እንደሚሆነው ሁሉ።»

اهـ منزلة السنة في الإسلام وبيان أنه لا يستغنى عنها ص: ٦ - ٧

t.me/abuzekeryamuhamed
t.me/abuzekeryamuhamed


የወር አበባ ላይ ሆና ዒባዳ
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯🔍

👌 ከአንዳንድ ሴቶች በስተኩል በተዳጋጋሚ ከሚመጡ ጥያቄዎች መካከል አጭር ማብራሪያ የተሰጠበት

⁉️ ጥያቄ አንድት ሴት ሀይድ ላይ ሁና ቁርአን መቅራት በእጇም ይሁን በጀዋል መቅራት ትችላለችን ወይስ አትችልም?

👉
በዚህ ጉዳይ ዙሪያ በአጭር ማብራሪያ ሰፋ ያለ ትምህርት አዘል ምክር ተዎስቶበታል።

🎙 الشيخ أبو منصور محمد حياة الولوي المدرس في مدينة هرا - حفظه الله تعالى-

🎙
በሸይኻችን አቡ መንሱር ሸይኽ ሙሐመድ ሀያት አል-ወሎውይ አላህ ይጠብቃቸው

🌐 @SheikMohmmedHyatHara

🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣ 
╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞

🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy


ለረመዳን ቤትን ማስዋብ⁉️
🔎 =======>


👉 ቢድዓህ ነች
👉 ረመዳን የአምልኮ ወር ነው
👉 ቀለም መቀባት
👉 የተለያዩ የቤት ማስዋቢያዎችን መግዛት
👉 ምንጣፍ መቀየር ......

🎙الأُسْـتَاذُ أَبُو حَــــمَوْيَة شَمْسُــو غُلْتَا «حَفِظَهُ اللَّهُ»
🎙
በኡስታዝ አቡ ሀመዊያህ ሸምሱ ጉልታ አላህ ይጠብቀው!

👇👇👇 ጆይን ብለው ይከታተሉ
https://t.me/+w-uAkEZwibVlNzM8

📱⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣
https://t.me/AbuYehyaAselefy
https://t.me/AbuYehyaAselefy
https://t.me/AbuYehyaAselefy


🔸 አዲስ ሙሀደራ

🔊 “ነሲሀ እና ታማኝነት!!”

🎙በሸይኽ አቡ ዐብዲል ሀሊም ዐብዱል ሀሚድ ያሲን አል-ለተሚይ (ሐፊዘሁላህ)

ሌራ ኢማሙ አህመድ መስጂድ የተደረገ

t.me/abuzekeryamuhamed
t.me/abuzekeryamuhamed


📢 ወሳኝ የሆነ ወቅታዊ ትምህርት
     ======>


🎁 ረመዷንን በእውቀት እንፁም!

 🏝 ⇣⇣⇣•••⇣⇣⇣ 
📢[ክፍል አራት]
   ➶➹➶➹➶➹

👉 የኪታቡ ስም፦
📚 مَجَالِسُ شَهْرِ رَمَضَانَ
📚 መጃሊሱ ሸሕሪ ረመዷን


📄 ሪሳላዋን በ𝕡𝕕𝕗 ለማግኘት
➘➷➴➘➷
t.me/AbuYehyaAselefy/12448

📝 ፀሐፊ፦ የተከበሩ ሸይኽ ሙሐመድ ብን ሷሊሕ አል’ዑሰይሚን አላህ ይዘንላቸውና!

🎙በኡስታዝ አቡ ጀዕፈር / አቡ አነስ  ሙሐመድ አሚን አላህ ይጠብቀውና

🏘 ቦታ፦ በሸዋሮቢት ከተማ በፉርቃን መስጂድ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ ባለው ወቅት እየተሰጠ ያለ ደርስ

🔎 📱⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣
https://t.me/AbuYehyaAselefy
https://t.me/AbuYehyaAselefy
https://t.me/AbuYehyaAselefy


አዲስ ልዩ የኮርስ ፕርግራም
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯👌

🏝 በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ሰለፍዮች ጀመዓ የተዘጋጀ የኮርስ ፕሮግራም

🔍 عنوان : "مجمل أحكام الصيام"
🔎 ርዕስ፦ «ጥቅል የፆም ፍርዶች»

📝 لفضيلة الشيخ الدكتور محمد بن سعيد رسلان حفظه الله
📝 የተከበሩ ሸይኽ ዱክቱር ሙሐመድ ሰዒድ ረስላን አላህ ይጠብቃቸው!


🕌 አል-አቅሷ የወራቤ ዩንቨርሲቲ ሰለፊይ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓህ

🕌 مسجدالأقصى جماعة السلفيين في جامعة ورابي

🕌 Al-Aqsua Werabe university selefy Muslim students jemeáh.

🛣️ አድራሻበወራቤ ዩኒቨርስቲ ከመማሪያ ህንፃ 1 (Block 1) በታች ማህበረሰቡ በሚጠቀመው ቧንቧ ገባ ብሎ

👉 በዚህ ግሩፕ በቀጥታ ስርጭት ስለምናስተላልፍ ሁላችሁም ተቀላቀሉ
🏝   ➘➴➘    ✅ ⬇️⬇️⬇️⬇️
https://t.me/WRU_Selefy_Students
https://t.me/WRU_Selefy_Students
https://t.me/WRU_Selefy_Students


||- አዲስና ወቅታዊ ትምህርት
    ¯¯¯¯¯¯¯
📖 اسم الكتاب:-
↩️ «تذكرة الصوام بشيء من فضائل الصيام والقيام وما يتعلق بهما من أحكام»
📖 የኪታቡ ስም፦
↪️ «ተዝኪረቱ አስ’ሱዋም ቢሸይኢን ሚን ፈዷኢሊ ’ሲያሚ ወልቂያም ወማ የተዓለቁ ቢሂማ ሚን አሕካም»

🏝 ⇣⇣⇣•••⇣⇣⇣ 
📢[ክፍል ሰባት]
   ➶➹➶➹➶➹

📄ሪሳላዋን በ𝕡𝕕𝕗 ለማግኘት
➘➷➴➘➷
https://t.me/AbuYehyaAselefy/12386

📝 تأليف፡- فضيلة الشيخ العلامة عبد الله بن صالح القصير - رحمه الله -
📝 ዝግጅት፦ የተከበሩ የሆኑት ሸይኽ አል’ዓላማህ ዐብዱሏህ ብን ሷሊህ አል’ቁሶይር አላህ ይዘንላቸውና!

🎙الأستاذ الفاضل أبي أنس أبي جعفر محمد أمين السلفي «حفظه الله»
🎙
በውዱ ኡስታዛችን ኡስታዝ አቡ አነስ [አቡ ጀዕፈር] ሙሐመድ አሚን አላህ ይጠብቀውና

🏠ቦታ፦ 🕌 በሰለፍዮች ፉርቃን መስጂድ [ሸዋሮቢት ከተማ] የተሰጠ ወቅታዊ ትምህርት

        •┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•

👇👇👇 ጆይን ብለው ይከታተሉ
https://t.me/+w-uAkEZwibVlNzM8

📱⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣
https://t.me/AbuYehyaAselefy
https://t.me/AbuYehyaAselefy
https://t.me/AbuYehyaAselefy

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.