Deacon Chernet


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Religion


ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤አሜን
2ኛ ጴጥ 3፡18
በተዋህዶ እምነታችን ፀንተን እንኑር !
ጥቆማ ወይም ጥያቄ ካላቹ በዚህ የተለግራም ቦት👉🏽https://t.me/Cher2112bot ይጠቀሙ

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Religion
Statistics
Posts filter


አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት

ቅድስት ቤተክርስቲያናችን እምነቷን የምትገልጽበት ለሰዎችም የምታስተምርበትና የምትመስከርበት አምስት እዕማደ ምሥጢራት አሏት።

"ናሁ ኅቡዓ ነገረ እነግረከሙ” እነሆ ኅቡዕ (ምሥጢር) እነግራችኋለሁ ፩ ቆሮ: ፲፭: ፶፩ (15፡51) እንዳለ እነዚህ አምስቱ ምሥጢራት አምስቱ ኅቡዓት ተብለውም ይነገራሉ፡፡ አምሰቱም ነገረ መለኮት ናቸው።

#አምስት፡- ቁጥራቸውን ይገልፃል

#አዕማድ፡- ማለት ምስሶዎች ማለት ነው። አንድ ቤት ሲሠራ ሊቆምና ጠንካራ ሊሆን የሚችለው በአዕማድ (ምሰሶዎች) ነውና። ለሃይማኖታችንም መሠረታዊ ምስሶዎች አሏት።

#ምሥጢር፡- ለወዳጅ የሚገለጽ ነገር ሲሆን ለሚያምኑ ሁሉ የሚገለጽና በእምነት ብቻ የሚረዱት በመሆኑ ምሥጢር ይባላል።

አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት የሚባሉትም፡-

1.ምሥጢረ ሥላሴ
2.ምሥጢረ ሥጋዌ
3.ምሥጢረ ጥምቀት
4.ምሥጢረ ቊርባን
5.ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ናቸው።

አንድ ክርስቲያን እነዚህን ጠንቅቆ ከተረዳ መሠረቱ ጠንካራ ዐለት ይሆናል። ለዚህም ነው ቅዱስ ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮ.፲፬:፲፱ (14፥19) ላይ "ወባሕቱ በቤተ ከርስቲያን እፈቅድ ኀምስቲ ቃላተ እንግር በልብየ ከመ ለባዕዳንሂ እምሃር እስመ ይኄይስ እምእእላፍ ቃል በነገረ በሐውርት” “አምስት ቃላት በእእምሮዬ ልናገር እወዳለሁ"ብሎ የአምስቱን አዕማደ ምሥጢር በአውነት ለምአመናን ያስተምር የነበረው።

#በቀጣይ ግልጽ በሆነ መንገድ አጠር አጠር አድርገን ምሥጢረ ሥላሴን እናያለን


#አስተርዮ_ማርያም

የማይታየው የታየበት፣ የራቀው የቀረበበት፣ የረቀቀው መለኮት በገዘፈ ሥጋ ማርያም የተገለጠበት፣ የወልድ ልጅነት በአብና በመንፈስ ቅዱስ የተመሰከረበት፣ በልደቱ፣ በጥምቀቱ አንድነት በሦስትነት እንዲሁም መለኮት በሥጋ ሥጋም በመለኮት በተዋሕዶ ተገልጦ ምሥጢሩ ገሃድ የሆነበት የመገለጥ የመታየት ጊዜ የሆነው ወቅት በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ዘመነ አስተርዮ እየተባለ ይጠራል፡፡

በዚሁ በዘመነ አስተርዮ መካከል የሚገኝ ስለሆነ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም “በዓለ ዕረፍት አስተርዮ ማርያም” እየተባለ ይጠራል፡፡ ይህ አስተርዮ ማርያም የምንለው ታላቅ በዓል እናታችን እመቤታችን ከዚህ ዓለም ድካም ያረፈችበት መታሰቢያ ሲሆን ቀኑም ጥር ፳፩ ነው፡፡

ሰማይና ምድር የማይወስኑትን የወሰነች፣ ሞትን በሞቱ የመሻር ሥልጣን ያለውን፣ ዓለምን በመዳፉ የጨበጠውን የወለደች ክብርት ቅድስት እመቤታችን ከዚህ ዓለም ድካም የምታርፍበት ቀን በደረሰ ጊዜ ይኸውም ጥር ፳፩ ቀን በዕለተ እሑድ በ፷፬ ዓመቷ፣ በ፵፱ ዓ.ም መንፈስ ቅዱስ የዕረፍቷ ጊዜ መድረሱን ነግሯት በልጇ መቃብር ሆና ጸሎት ታድርስ ነበር፡፡

እንዲህም ብላ ጸለየች፤ ‹‹ልጄ ወዳጄ ሆይ ልመናዬን ተቀብለህ ደቀ መዝሙርህን ዮሐንስን በዚህች ሰዓት አምጣው፤ እንዲሁም በሕይወተ ሥጋ ያሉ ሐዋርያትን ሁሉንም፣ ነፍሳቸውንም የለየሃቸውን አምጣቸው፤ አንተ የሕያዋንና የሙታን አምላክ ነህና›› አለች፡፡ (የጥር ፳፩ ስንክሳር)

በዚህ ጊዜ ዮሐንስን ደመና ተሸክማ ከኤፌሶን አመጣችው፤ ምስጋናም አቀረበላት፤ ሁሉም ሐዋርያት የሞቱትም ከመቃብር ተነሥተው ወደ እመቤታችን ደርሰው ሰገዱላት፡፡ እንዲህም ስትል ጠየቀቻቸው፤ ‹‹ትነግሩኝ ዘንድ እሻለሁ፤ ከዚህ ዓለም እንደምለይ ከወዴት ሰማችሁ?›› አለቻቸው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስና ሐዋርያት ሁሉም ‹‹ወደ አንቺ እንድንመጣ መንፈስ ቅዱስ አዘዘን፤ በደመና ላይም በተጫን ጊዜ ወደ አንቺ እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥነን ደረስን›› አላት፡፡

በዚያን ጊዜ የክብር ባለቤት ልጇ ወዳጇ ኢየሱስ ክርስቶስ እልፍ አእላፍ መላእክቱን አስከትሎ ወደ እርሷ መጣ፡፡ (ጥር ፳፩ ስንክሳር)
እንዲህም አላት ‹‹እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍሽ መጥቻለሁ›› አላት፡፡ እርሷ ግን ‹‹ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑህን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀኔ ተሸክሜህ፤ በድንግልና ወልጀህ እሞታለሁን?›› አለችው፡፡

በዚህ ጊዜ በሲኦል የነበሩ ነፍሳትን ሁሉ አሳያትና ‹‹እናቴ ሆይ ሞትሽ ለእነዚህ ሁሉ ነፍሳት መዳን ምክንያት (ቤዛ) ይሆናቸዋል›› አላት፡፡ ‹‹እነዚህን ሁሉ ከማርክልኝስ ይሁን›› አለች፡፡ በዚህ ጊዜ ቅድስት ሥጋዋን ከክብርት ነፍሷ ለይቶ በቃለ አቅርንት በይባቤ መላእክት በክብር ነፍሷን ዐሳረጋት፡፡ (መዝገበ ታሪክ ቁጥር አንድ ገጽ ፻፶፭፣ ጥር ፳፩ ስንክሳር)

የአምላካችን እግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና ተረዳኢነት አይለየን፤ አሜን!!!

#ማህበረ_ቅዱሳን


ኢትዮጵያና ሕገ ኦሪት

አሞጽ ፱፡፯ (9፡7) "የእስራኤል ልጆች ሆይ እናንተ ለአኔ እንደ
ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል እግዚአብሔር" ይህም ምን ይገልጽልናል ብሎ
ለሚጠይቅ ነገሩ እንዲህ ነው ዛሬ አሰራኤል ታቦቱ የላትም።
የዚህ ምሥጢር ባለቤት ግን ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ናት።

በአጠቃላይ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከፍጥረት ጀምሮ የብሉይ ኪዳንን እምነትና ሥርዓት ጠብቃ አስጠብቃ እግዚአብሔርን በማምለክ የጸናች አገር ናት፡- ቅድመ ክርስትና ይህ የብሉይ ኪዳን መሥዋዕት እየተሠዋባት የነበረች አገር እንደነበረች በሁሉም የአገሪቷ ከፍል ያለ የሃይማኖት መገለጫ የታሪከ ማስረጃ የባህልም ምስከርነት አለ።

ለምሳሌ፡- በመላው ኢትዮጵያ የብሉይ ኪዳን መሥዋዕት ይቀርብባቸው የነበሩ የንዋየ ቅድሳት ምስክሮች አሉ። ኢትዮጵያ በዚያ ዘመን ለአምላኳ መሥዋዕተ ቁርባን ታቀርብ ነበር። ነቢዩ ሶፎንያስ እንዲህ ሲል ትንቢት ተናገረ “ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ የሚማልዱልኝ የተበተኑት ሴቶች ልጆቼ ቁርባኔን ያመጡልኛል” በግእዙ እንዲህ ይለዋል። “እምነ ማዕዶተ ፈለገ ኢትዮጵያ ያመጽኡ ሊተ መሥዋዕተ” የዚህም ትርጓሜ “ከኢትዮጵያ ወንዝ ጀምሮ መሥዋዕቱን ያመጡልኛል።“ ሶፎ ፫፡፲ (3:10)

እንዲህ ባለ ሁኔታ ኢትዮጵያ ለአንድ አምላከ እየሰገደች እርሱን ብቻ እያመለከች ሀገረ እግዚአብሔር ሆና አምላክ ከሰማያት ወርዶ ከድንግል ማርያም ተወልዶ፣ ተጠምቆ፣ በመሰቀል ተስቅሎ፣ ደሙን እፍስሶ፣ ሥጋውን ቆርሶ፣ ዓለምን ሁሉ ያድናል እያለች የተቆጠረው ሱባዔ የተነገረው ትንቢት ይፈጸማል አምስት ሺህ አምስት መቶ የኃጢአት የጨለማ ዘመን ያበቃል እያለች የነቢያትን ትንቢት በመጋራት በእምነት ፀንታ ስትኖር ዘመኑ ሲፈፀም በትንቢቱ መሠረት ጌታችን አኛን ለማዳን ሰው ሆነ ተዋሕዶ ሃይማኖት በዚህ ተጀመረች ኢትዮጵያም የመጀመሪያዋ ከርስቲያን ሀገር ፤ለመሆን በቃች።

#ከላይ ኢትዮጵያና ሕገ ወንጌል (ክርስትናን) አለ

ለተፈጠረው ቅደምተከተል ይቅርታ እንጠይቃለን




ኢትዮጵያና ሕገ ወንጌል (ክርስትና)

ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ በሕገ ልቡና በሕገ ኦሪት ሰለማመኗ የነገረን መነሻው መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ስለከርስትናውም መጽሐፍ ቅዱሰ አንዲህ ይላል። የሐዋርያት ሥራ ፰፡፳፮ (8፥ 26) የጌታም መልአከ ፊሊጶስን ተነሥተህ በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ ወደሚያወርደው ምድረ በዳ ወደ ሆነ መንገድ ሂድ አለው። ተነሥቶም ሄደ።

እነሆም ሕንደኬ በመጠሪያ ስሟ ጌርሳሞት የተባለች የኢትዮጵያ ንግሥች አዛዥና ጃንደረባ የነበረ በገንዘቧም ሁሉ የሠለጠነ አንድ የኢትዮጵያ ሰው ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳኬም መጥቶ ነበር። ሲመለስም በሠረገላ ተቀምጦ የነቢዩን የኢሳይያሰን መጽሐፍ ያነብ ነበር። ፊሊጶሰም አፉን ከፈተ ከዚህም መጽሐፍ ጀምሮ ሰለ ኢየሱስ ወንጌል ሰበከለት ሁለቱም ወደ ውኃ ወረዱ አጠመቀውም።

እንግዲህ ልብ እንበል
* ጃንደረባው አማኝ ነበር
* ወደ ኢየሩሳሌም የሄደው ሊሰግድ ነበር
* የኢሳይያስን ትንቢት ያነብ ነበር
እነዚህ ከላይ ያየናቸው ማሰረጃዎች ኢትዮጵያ የብሉይ ኪዳን እምነት አማኝ የነበረች ሀገር መሆኗን የሚገልጽ ነው።

ከዚህ ቀጥሎ ደግሞ ሰንመለከት
ፊልጶስ ስለ ኢየሱሰ ወንጌል ሰበከለት ጃንደረባው ኢየሱስ የአግዚአብሔር ልጅ አንደሆነ አመነ ተጠመቀ እነዚህ ማሰረጃዎች ደግሞ የክርስትናን እምነት የሚገልጹ ናቸውና ኢትዮጵያ ከ33 ዓ.ም ጌታ ከሞት ተነሥቶ ካረገ በኋካ ወዲያው ክርሰትናን_እንዳመነች የሚያሳይ የእግዚእብሔር ቃል ነው።

ጃንደረባው በመንፈስ ቅዱስ ተጠምቀዋል ይልቁንም ለመላው አፍሪካም ሐዋርያ ሆኗል። “ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች” መዝ. ፷፯፡፴፩ (67፥31) ተብሎ የተነገረው የነቢዩ ዳዊት ትንቢታዊ መዝሙር በዚህ እንደተፈጸመ እንገነዘባለን። ከዚያን ሰዓት ጀምሮ ከርስትና በኢትዮጵያ እየተስፋፋች የወለደ እግዚአብሔር ሰው መሆን ይሰበክባት ጀመር።

ይልቁንም ደግሞ በ33ዐ ዓ.ም ክርስትና የመላው የኢትዮጵያ እምነት በመሆን ብሔራዊ እምነት ሆነ፡፡ ከዛም በዓለም ላይ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ከርስቲያን ሀገር ሆነች።

ወስብሓት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!

#በቀጣይ አምስቱን አዕማደ ምሥጥራት አጠር አድርገን ተራ በተራ እናያለን




ወይንኬ አልቦሙ
የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም

በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፥ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤

ኢየሱስም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ።

የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት፡— የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም፡ አለችው።

ኢየሱስም፡— አንቺ ሴት፥ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም፡ አላት።

እናቱም ለአገልጋዮቹ፡— የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ፡ አለቻቸው።

አይሁድም እንደሚያደርጉት የማንጻት ልማድ ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር፥ እያንዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር።

ኢየሱስም፡— ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው፡ አላቸው። እስከ አፋቸውም ሙሉአቸው፡ አላቸው። እስከ አፋቸውም ሞሉአቸው።

አሁን ቀድታችሁ ለአሳዳሪው ስጡት አላቸው፤ ሰጡትም።

አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ ከወዴት እንደ መጣ አላወቀም፤ ውኃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር፤ አሳዳሪው ሙሽራውን ጠርቶ፡—

ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፥ ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፤ አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል፡ አለው።

ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ። (ዮሐ 2፥1- 11)

የሰውን ችግር ተረድታ ለልጇ የምታሳስብ፣ ልመናን የምታቀርብ፣ መልስ የምታሰጥን እናት የሰጠን አምላካችን እግዚአብሔር ስሙ ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁንልን።

ልጆቿ እንድንሆን የረዳን፣ ፍቅሯንም በዕድሜ ዘመናችን ያበዛልን፣ ምስጢሩንም የገለጸልን መድኃኔአለም ኢየሱስ ክርስቶስ ስሙ ለዘለዓለም የከበረ፣ የተመሰገነ ይሁንልን።

አማላጅነቷ፣ ጸሎቷ፣ ፍቅሯ፣ በረከቷ ከሁላችንም ጋር ጸንቶ ይኑር!

አሜን!


ከተራ_ምንድን_ነው?

እንኳን ለከተራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን! ተጠምቀ ሰማያዊ በእደ መሬታዊ!

ከተራ 'ከበበ' ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡

በጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰቡ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላሉ፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥሉ ይውላሉ፡፡ የምንጮች ውኃ እንዲጠራቀም ይከተራሉ (ይገድባሉ) ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ በመገደብ ለመጠመቂያ (ለጥር 11) ዝግጁ የሚያደርጉበት ዕለት ነው፡፡

በተጨማሪ በአቅራቢያ የሚገኙት ቤተክርስቲያናት ተሰብስበው ከዚሁ ከተቆፈረው ገንዳ ወይም ከተገደበው ጅረት አጠገብ ባለው ዳስ ወይም ድንኳን ታቦቶቻቸውን ያሳድራሉ ሊቃውንቱም በዚያው እግዚአብሔርን በማህሌት ሲያመሰግኑ ያድራሉ።

በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የመሄዱ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቱ የጌታችን፣ ምሳሌ ሲሆኑ ካህናቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ምሳሌ ናቸው፡፡ መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡


ኢትዮጵያና ሕገ ልቡና

ሕገ ልቡና ማለት ሕገ ኦሪት በሙሴ አማካኝነት እግዚአብሔር ለሕዝቡ እሰከሰጠበት ጊዜ ድረስ ያለው የሰው ልጅ ይጠቀምበት የነበረ ዛሬም የሚሠራ ያልተፃፈ ሕግ ወይም የአእምሮ (ጠባይዕ) ነው።

ይህ የአእምሮ ጠባይዕ ለሰው ልጆች በእግዚአብሔር አምላክ የተሰጠው ታካቅ ፀጋ ስለሆነ ከፉንና ደጉን ጽድቅና ኩነኔውን ይለዩበት ዘንድ የሚያስችላቸው የኅሊና ሕግ ነው።
ለኅሊና መገዛት መልካም ነው።

ይህን የልቡና ሕግ በኛ ውስጥ የቀረፀው ገና ሲፈጥረን እንደሆነ ማስተዋል ይገባናል። ”እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው በአፍንጫውም የሕይወት እሰትንፋስን እፍ አለበት ሰውም ሕያው ነፍሰ ያለው ሆነ” ዘፍ፡ ፪፡፯ (2¹7)

“እንግዲህ ይህች ሕያዊት የሆነች ነፍሳችን ናት የፈጠራትን የእግዚእብሔርን ትእዛዝ ሰለምትረዳ እኛም በእውነተኛ መንገድ እንድንሄድ የምትጠራን ይህም ሕገ ልቡና ነው።
ከብር ምስጋና ይግባውና አምላካችን ኢየሱሰ ክርስቶሰ በኦሪትም በወንጌልም የነገረን ይሀንን ነው።

“አፍቅሮ ለእግዚአብሔር አምላክከ በኵሉ ልብከ፡ ወበኵሉ ነፍሰከ ወበኵሉ ሐይለከ፡ ወበኵሉ ሕሊናከ"
“እግዚአብሔር አምላክህን በፍጹም ልብህ፡ በፍጹም
ሰውነትህ፡ በፍጹም ኃይልህም፡ በሐሳብህም ሁሉ ውደደው ዘዳ (6:10) ሉቃ ፲:፳፯(10:27)

እንግዲህ ይህንን ያሀል ስለ ሕገ ልቡና ካየን የኢትዮጵያ ሕዝብ በዚህ ሕግ መሠረት እንደ ተጠቀመበትና አምላኩን እንዳመለከበት ብዙ ግልፅ ማሰረጃዎች አሉ ሰለዚህ ኢትዮጵያ እግዚእብሔርን የምታውቀው በኦሪት ጊዜ ብቻ ሳይሆን ከዚያ በፊት ከፍጥረት ጀምሮ ነው፡፡

ምሳሌ ፡-
ሕገ ኦሪት የተሰጠው በሙሴ ነው ሙሴ ሕግን ከመቀበሉ በፊት እግዚአብሔርን አማኝ ነው የፈርዖንን ቤት ሹመት የናቀው በእምነት ነው። ዕብ. ፲፩፥፳፫-፳፰ (11፥23-28)

ይህ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ያገባት ሚሰቱ ኢትዮጵያዊት እንደሆነች መጽሐፍ ቅዱስ በኦሪት ዘኁልቍ ፲፪፡፩ (12*1) ይገልፃል። ይህች የሙሴ ሚሰት ሲፓራ እግዚአብሔርን ከሚያምን ቤተሰብ የተወለደች ነበረች። ይልቁንም አባቷ የእግዚአብሔር ካህን ነበረ።

ይህ የሙሴ አማት የሲፓራ አባት ዮቶር በሌላ ስሙ ራጉኤል የተባለው ኢትዮጵያዊ የእግዚአብሔር የሕግ መጽሐፍ እንዲህ ይላል ዘጻ ፲፰፡፲፪ (18፡12) እግዚአብሔርንም እንዲህ እያለ ያመሰግን ነበር ዘጸ ፲፰፡፲ (18፡10) እንግዲህ ይሀ የሚገልጽልን ኢትዮጵያ ከሕገ ኦሪት በፊት በሕገ ልቡና ለአምላኳ እንደ አቤል እንደ ኢዮብ መሥዋዕት የምታቀርብ የእግዚአብሔር ሀገር መሆኗን ነው፡፡ ታላቁን ሊቀ ነቢያት ሙሴን የማታምን የካሀነ ጣዖት ልጅ ያገባ ብሎ ማሰብ አላዋቂነት ከመሆኑም በላይ የሙሴን ክብር ዝቅ ማድረግ ነው።

ንግሥተ ሳባ ወይም ንግሥት አዜብ ተብላ የምትጠራው ኢትዮጵያዊት ንግሥት ማክዳን ብንመለክት እግዚአብሔርን ማመን የጀመረችው ኢየሩሳለም ሄዳ ከመጣች በኋላ ሳይሆን ከመሄዷ በፊት አስቀድሞ በሕገ ልቡና ፈጣሪዋን የምታውቅ መሆኗን የእግዚአብሔር ቃል ይመሰከርልናል። ኢትዮጵያ በሕገ ልቡና ሀገረ እግዚአብሔር ሰለሆነች ንግሥስቲቷም ወደ ኢየሩሳለም ወደ ንጉሥ ሰሎሞን የሄደችበት ምክንያት በተመሳሳይ እምነት ያለች እሰራኤልን በሰሎሞን ምከንያት ያገኘችውን በረከት ለመመልከትና አግዚአብሔርን ለማመሰገን ነበር።

“አንተን የወደደ በእስራኤልም ዙፋን ያስቀመጠሀ
አምላክህ እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን“ ፩ነገ ፲፡፱ (10፡9) በማለት ምስክርነቷን ገልጻለች። ይህን ማለቷ ንግሥቲቷ ኢትዮጵያ እግዚአብሔርን ታውቀውና ታመልከው ስለነበር ነው። ለዚህም ነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ከርስቶስ ለእምነት ምሳሌ አድርጎ በወንጌል ያስተማረን አንዲህ ብሎ

“ንግሥተ እዜብ ትትነሣእ አመ ዕለተ ደይን ወትትፋታሕ ምስለ ዛ ትውልድ ወታስተኀፍራ እስመ መጽአት እምአጽናፈ ምድር ትስማዕ ጥበቢሁ ለሰሎሞን“

“ንግሥተ እዜብ በፍርድ ቀን ተነሥታ ከዚህ ትውልድ ጋር ትፋረዳለች፡ ታሳፍራታለች፡ የሰሎሞንን ጥበብ ትሰማ ዘንድ ከምድር ዳርቻ መጥታለችና ሲል መሰከሮላታል።” ማቴ ፲፪፡፵፪ (12፡42) ሉቃ ፲፩፡ ፴፩ (11:31)

ንግሥተ አዜብ ወደሀገሯ በተመለሰች ጊዜ ሀገራችን ያን ጊዜ ሕገ ኦሪትን ተቀብላ ሃይማኖተ ኦሪትን ብሔራዊ እምነት አድርጋለች፤ ቀድሞ ያለውንም አጽንታለች። ይህም የሚፈጸመው በቃል ኪዳኑ ታቦት ነውና ከንጉሥ ሰሎሞን በወለደችው በቀዳማዊ ምኒልከ ጊዜ በእግዚአብሔር ፈቃድ ታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ ገባች።

#በቀጣይ ኢትዮጵያና ሕገ ኦሪትን - ከሙሴ አስከ ዮሐንስ መጥምቅ ያለውን እንመለከታለን!




ሦስቱ ሕግጋት

ሕገ ልቡና - ከአዳም እስከ ሙሴ

ሕገ ኦሪት - ከሙሴ አስከ ዮሐንስ መጥምቅ

ሕገ ወንጌል - ከዮሐንስ መጥምቅ እስከ ምጽአት

”ኦሪትኒ ወነቢያትኒ አሰከ መጥምቁ ዮሐንስ እምትካት ስበኩ በእንተ መንግሥተ አግዚአብሔር”

“ኦሪትም (ሕግ) ነቢያትም ከጥንት ጀምሮ አስከ ዮሐንስ ድረስ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት አሰተማሩ።” ሉቃ፡፲፮፡፲፮(16:16)

እግዚአብሔር አምላካችን የፈጠረውን የሰውን ልጅ ወደ ሕይወት ይመልስ ዘንድ በተለያዩ ዘመናት አርሱን የሚያውቁበት ለአርሱም የሚገዙበትን መንገድ ሰጥቶታል። አነዚሀም ሕገ-ልቡና፣ ሕገ-ኦሪት እና ሕገ ወንጌል ናቸው፡፡

የሰው ልጅ ፍጥረት ሁሉ አምላኩን ለማወቅ እነዚህ ሕግጋት ይገልጹለታል ከአነዚህ የወጣ የለም። ያለ ሕግ የሚሠራ ሁሉ ያለ ሕግ ይቀጣልና፡፡ የሚገርመው ነገር እነዚህን እሟልታ በዓለም ላይ ያለች ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት፡፡

በሦስቱም ሕግጋት አግዚአብሔርን እያመለከች በመኖሯ አምልኮተ እግዚአብሔርም ስላልተቋረጠባት ቅዱስ ዳዊት ስለዚህም ነበር
“ኢትዮጵያ ታበጽሕ አደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር”
“ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች “ መዝ- ፮፯፡፴፩ (67፡ 31) ያለው!


#በቀጣይ ኢትዮጵያና ሕገ ልቡናን እያለን ሦስቱንም ሕግጋት ተራ በተራ ግልጽ በሆነ መንገድ እንመለከታለን


ተዋሕዶ

ተዋሕዶ የቃሉ ትርጉም ግእዝ ሲሆን የሚያበሥረንም የአምላካችን የአግዚአብሔርን ሰው የመሆን ምሥጢር ነው። ይህም ገና ያኔ በኦሪት ዘፍጥረት ፫፡፳፪ (3:22) “አግዚብሔር አምላክም አለ አነሆ አዳም መልካምንና ከፉን ለማወቅ ከአኛ አንደ አንዱ ሆነ” የሚለው አምላካዊ ቃል የተፈጸመበት የሰው ልጅ የመዳን ዜና ነው።

ተዋሕዶ ስንል ማን ከማን ተዋሐደ?

በዮሐንስ ወንጌል ፩፡ ፲፬ (1፥14) ላይ "ውአቱ ቃል ሥጋ ኮነ”
ያ ቃል ሥጋ ሆነ ይለናል ያ ቃል የተባለው አግዚአብሔር ነው።

“ሥጋ” የተባለው ደግሞ ሰው ነው።ከዚህ የወንጌል ምሰጢር የተነሣ ተዋሕዶ ማለት አካላዊ ቃል የተባለ አግዚአብሔር ወልድ ሥጋ ከተባለ ሰው ያለመለየት፣ ያለመቀላቀል፣ ያለድማሬ አንድ ሆነ። በተዋሕዶ ከበረ ስለዚህ አምካካችን እግዚብሔር እኛን ለማዳን ሲል ከአመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ።

ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ ስንል የአሷን ባሕርይዋን ባሕርይ አደረገ። ሥጋም የአምላክን ባሕርይ ባሕርዩ አደረገ።

ይህ ምን ማለት ነው?

አካላዊ ቃል አግዚአብሔር፡- አይዳበሰም፣ አይታይም፣ አይጨበጥም፣ አይዳስስም፣ አይበላም፣ አይጠጣም፣ አያንቀላፋም፣ አይሞትም እነዚህ ሁሉ የሚሰማሙት ለሰው (ለሥጋ) ነው። አምላካችን ከድንግል በተወለደ ጊዜ ግን በተዋሕዶ የስውን ባህርይ የራሱ አደረገ።

በአጭሩ የሠራዊት ጌታ አግዚአብሔር ካለ አባት ከአመቤታችን ተወልዶ ሥጋን ተዋሕዶ (3ዐ) በሠላሳ ዘመኑ ተጠምቆ በቀራኒዮ ተሰቅሎ በጐልጐታ ተቀብሮ ሞትን ድል አድርጎ ተነሥቶ ዐረገ በተዋሐደው ሥጋ ዳግም ለፍርድ ይመጣል “ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ አንዳያችሁት አንዲሁ ይመጣል“ ሥራ. ፩:፲፩ (1:11) ሥጋን ለብሶ አንዳረገ አንዲሁ ይመለሳል በመንግሥተ ሰማያት ለዘላለም ይኖራል ብሎ ማመን እውነተኛ የተዋሕዶ እምነታችን ነው።

የማይመረመር የማይለወጥ ቃል የሚለወጥ ሥጋን ተዋሐደ መለወጥ ይሰማማው የነበረ ሥጋን የማይለወጥ አደረገው። ሰለዚህም በተዋሐደው በመዋቲ አዳም ሥጋ ተገለጠ የማይለወጥ ባሕርይ ያለው ቃል የሚለወጥ ባሕርይ ባለው ሥጋ ሞተ በፍዳ የተያዙትን በወንጌሉ አዳናቸው

ሃይማኖተ አበው።

ስለዚህም ወገኖች ሆይ:- አምላካችን በደሙ የመሠረተልንን የነጻች እምነታችንን እሰከ መጨረሻ ካፀናን የከብሩ ወራሾች የስሙ ቀዳሾች አድርጎ በከብር ያኖረናል። ”ሕጉንም በቀንና በሌሊት የሚያሰብ _ እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደተተከለች ፍሬዋን በየጊዜው አንደምትሰጥ ዛፍ ይሆናል።” መዝ.፩፡ ፪ (1፥2)

የመጀመሪያ አምነታችንን አሰከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ የከርሰቶሰ ተካፋዮች እንሆናለን" ዕብ ፫፥፲፬(3:14)

ይህ የቅዱሰ ጳውሎሰ ቃል በአምላካችን ስው መሆን (ተዋሕዶ) ያገኘነውን የልጅነት ፀጋ ያሳያል።ከፅንሰታችን እሰከ ዕለተ ሞትታችን ኋላም እሰከ ዕለተ ምጽእት በዚች ተዋሕዶ ሃይማኖት ጸንተን የቀደመች ልጅነታችንን ብንጠብቅ ከከርሰቶሰ ጋር አንድ እንሆናለንና።

ተዋሕዶ የአግዚአብሔር ሰው የመሆን ምሥጢር ነው። ከድንግል ሰው የሆነው ቃል የተባለ እግዚአብሔር ወልድ እርሱ አምካክ ነው። ሰው በመሆኑ ከእምላክነቱ እንዳች አልጎደለውም።

ተዋሕዶ የቃለ እግዚአብሔር ከአመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ የመንሣት (የመዋሐድ) ምሥጢር ታላቅ ነው። እርሱ የዳዊት ልጅ አንደሆነ አንዲሁ የዳዊት ፈጣሪ ነው። ከአብርሃም ዘር እንደተገኘ እንዲሁ ከእብርሃም በፊት ነበረ።

ማቴ. ፩፡፩ ፳፪፡፵፩: ፵፭ (22፡41-45) ዮሐ ፰:፶፰(8:58)

@Deaconchernet


ኦርቶዶክስ

ኦርቶዶክስ የሚለው ቃል የግሪከ ቃል ሲሆን “ኦርቶ“ (ኦርቶስ) ማለት ቀጥ ያለ ማለት ሲሆን “ዶከስ” ማለት ደግሞ እምነት ማለት ነው። ስከዚህ ኦርቶዶክስ ማለት ቀጥ ያለ፣ የጸና፣ የቀና እምነት ማለት ነው።በብሉይ ኪዳንና በአዲስ ኪዳን እንደተገለጸልን ቀጥ ያለ እምነት ወይም እውነተኛ ሃይማኖት ተብላ በእምላካችን የተመሠረተችው ኦርቶዶከስ ተዋሀዶ ናት። ቀድሞ በነቢዩ በኤርምያስ የቀደመችው መንገድ ብሎ ያናገረ ጌታ በመዋዕለ ሥጋዌው ባስተማረን ወንጌል ጠባቢቱ በር ጠባቢቱ መንገድ ብሎ ኦርቶዶከስ የሕይወት መንገድ መሆኗን እስተምሮናል። መሥርቷታልም።

“እግዚእብሔር እንዲህ ይላል ። በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፡ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፡ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደሆነች እወቁ በእስዋም ላይ ሂዱ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፡ እነርሱ ግን እንሄድባትም አሉ።” ኤር ፮፡፲፮ (6፡16)

“በጠበበው ደጅ ገቡ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ መንገዱም ትልቅ ነውና ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው። ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ መንገዱም የቀጠነ ነውና። የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው ማቲ ፯:፰፫-፰፬ (7:13-14)

ከሁለቱ ጥቅስ ልብ የምትሉት ነገር ብዙዎች ይህችን አውነተኛ መንገድ አንደማይቀበሏት ነው። ከሐድያን መናፍቃን የተበረዘና የነቀዘ እምነት እንዲሁም ከወንጌል ውጪ የሆነ የፍልስፍናን ትምህርት ወደ ቤተ ከርስቲያን ለማስገባት በሚጥሩበትም ጊዜ ቅዱሳን አባቶች 318ቱ ሊቃውንት አርዮስንና መሰሎቹን አውግዘው እኛ እሱ ጌታችን የመሠረተልንን ነቢያት ትንቢት የተናገሩላትን፣ ሐዋርያት የስበኩላትን ፣ሰማዕታት የሞቱላትን ቀጥ ያለች እምነት ይዘን እንሄዳለን ብለው ሥርዓት ስለደነገጉ እምነታችንም ኦርቶዶከስ ተብላ ትጠራለች።

“የአግዚአብሔርን ቃል የተናገሯችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታችሁ ምስሉአቸው። ኢየሱስ ከርስቶስ ትናንትና ዛሬ አስከ ዘላለም ያው ነው። ልዩ ልዩ ዓይነት በሆነ በእንግዳ ትምህርት አትወሰዱ” ዕብ.፲፫፡፯ (13፥7)

@Deaconchernet


የመመኪያችን ዘውድና የንጽሕናችን መሠረት

ክርስቶስ ተጸነሰ - ተወለደ ስንል ለዚህ ሁሉ ምሥጢር ማካተቻና የድኅነታችን መጀመሪያ : የመመኪያችን ዘውድና የንጽሕናችን መሠረት ድንግል ማርያም ናትና ከፈጣሪ ቀጥሎ ታላቅ ክብር : ምስጋና : ስግደትና ውዳሴ ለእርሷ ይገባታል። መድኅናችን ክርስቶስ ያዳነን በእርሷ ምክንያት ነውና።

ሠለስቱ ምዕት ይህንን ምሥጢር ሲያደንቁ እንዲህ ብለዋል፦

• በሥጋ ማርያም ጌታ ተጸነሰ
• በሥጋ ማርያም ጌታ ተወለደ
• በሥጋ ማርያም ጌታ አደገ
• በሥጋ ማርያም ጌታ ተጠመቀ።
• በሥጋ ማርያም ጌታ አስተማረ
• በሥጋ ማርያም ጌታ ተሰቀለ
• በሥጋ ማርያም ጌታ ሞተ
• በሥጋ ማርያም ጌታ ተነሳ
• በሥጋ ማርያም ጌታ ዐረገ
• በሥጋ ማርያም ጌታ በአባቱ ቀኝ ተቀመጠ
• በሥጋ ማርያም ጌታ ዳግመኛ በሕያዋንና ሙታን ላይ ይፈርድ ዘንድ ከመለኮቱ ኃይል ጋር ይመጣል። (መጽሐፈ ቅዳሴ)

በዚያውም ላይ ለዘለዓለም ድኅነት የምንመገበው የጌታ ሥጋና ደም መለኮት የተዋሐደው የድንግል ማርያም ሥጋና ደም ነው።

ለድንግል ማርያም ክብርና ውዳሴ ከስግደት ጋር ይሁን!

የድንግል ማርያም ልጅ አማኑኤል ክርስቶስ በርሕራሔው ይማረን። ከበረከተ ልደቱም ያሳትፈን።

"እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፤ እንዲህ ሲል "የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የሚወለደው በመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ። ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።" ይህም ሁሉ የሆነ ከእግዚአብሔር ዘንድ በነቢይ የተነገረው ይፈፀም ዘንድ ነው ፤ እንዲህ ሲል፦ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል፤ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው።ማቴ. ፩፥፳-፳፫

ከዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ


#ቅዱስ_አግናጥዮስ      

"ክርስትያን ተብዬ ብቻ መጠራት የምፈልግ አይደለሁም ፤ ይልቁንም መሆንን እፈልጋለሁ ... ስጋዬን ለአውሬዎች ይስጡት በአውሬዎቹም ጥርስ ልፈጭ ፤ ንጹህ የክርስቶስ ህብስት ሆኜ ልገኝ ፤ ከአካሌም ምንም አያስቀሩ ፣ ምናልባት ለእናንተ ሥራ እንዳልሆንባችሁ፡፡

[ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾክያ ለአራዊት ሊሰጥ ለሰማእትነት እየሄደ ሳለ ለሮሜ ሰዎች ከላከው መልእክት]

"በቅዱስ መስቀል አምሳያ ዘወትር ያለ ድካም ለጸሎት ለሚዘረጉትና በአሥር ጨካኝ ወታደሮች በብረት ሰንሰለት ታስረው ለተጎተቱት እጆችህ ሰላምታ ይገባል። ጵጵስናን ከቅዱስ ጴጥሮስ የተቀበልክ ሰማዕተ ክርስቶስ ቅዱስ አግናጥዮስ ሆይ ፣ ከታሰርኩበት የኃጢአት ሰንሰለት በተሰጠህ ሰማያዊ ሥልጣን ፍታኝ በብርሃን እጆችህም በፍጹም በረከት ባርከኝ።"
                                  
"ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ለማስተዋል ፥ ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ ፥ እስከ እግዚአብሔርም ፍጹም ሙላት ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ።"
~|ኤፌ.፫፥፲፰

የአባታችን የቅዱስ አግናጥዮስ የከበረች ጸሎቱና ምልጃው አይለየን። ከበረከቱ ይክፈለን።

@Deaconchernet
@Deaconchernet
@Deaconchernet


#የሚታየውንና የማይታየውን ሁሉ ያከናወንክ፣ የሁሉ ፈጣሪ፥ የሁሉ ጌታ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፣ እልፍ አእላፋት መላእክት የሚያመሰግንህ፣ ትእልፊተ አእላፋት ሊቃነ መላእክት የሚገዙልህ ዐይኖቻቸው ብዙ የሆኑ ኪሩቤል የሚቀድሱህ ክንፋቸው ስድስት የሆኑ ሱራፌል ያለማቋረጥ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ቅድስናን የሚቀድስ፣ የአማልክት አምላክ የጌቶች ጌታ፣ የነገስታት ንጉሥ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት፣ ብርሃናትን የተጎናጸፈ እያሉ የሚያመሰግኑህ፤ አንተ ወደህ ፈቅደህ ልጅህን ከአተ ዘንድ ወደ እኛ ላክኸው፤ እርሱም ቃልህ ነው።

የጠፉትን የሚናገሩ በጎች የሚባሉ የሰው ልጆችን ወደ አንተ ይመልሳቸው ዘንድ። እንደ ፈቀደ ከአባቱና ከመንፈስ ቅዱስ ሳይለይ ከሰማያት ወረደ። ከቅድስት ድንግል ማርያምም ሰው ሆነ። ይህንን ሁሉ ያደረግኸው ለሰው ልጆች መድኀኒት ይሆን ዘንድ ነው። ከጨለማና ከሞት ጥላ አወጣኸን፤ አንተን ወደማወቅም መራኸን፤ አቤቱ የአባቶቻችን አምላክ ሆይ መድኀኒታችን ለመሆን ሰው በሆነ በዋህድ ልጅህ፤ እነሆ ጌታ ይህ ዐመፀኛ ከሐዲ በሙሽራህ  ላይ ያደረገውን ተመልክተሃል።

የቤተ ክርስቲያንህን ልጆች እንደያዛቸውና እንደ በግና ፍየል እንዳረዳቸው። የሕዝብህንና የርስትህን ልጆችም እንዳጠፋቸው። ስለ ወንድሞቼ ስለ ምእመናን ቀንቻለሁና በመሲሕ መስቀል ኀይል ይህን የእኛንና የአንተን ጠላት እወጋው ዘንድ እወጣለሁ። እነሆ እኔ በአንተ እና በዋህድ ልጅህ፣ አመንኩ በመሠዊያው ቀንድም ተማጸንኩ በሃይማኖትህም ጸናሁ።

ስለዚህም ስምህን የሚያውቁ አምላካቸው ወዴት አለ እንዳይሉኝ ከተስፋዬ አታሳፍረኝ። በብዙ አበሳየና ኃጢአት ምክንያት ጸሎቴን ባትሰማኝ ስእለቴንም ብትተዋት እንኳን አቤቱ በዚህች ሀገር ግደለኝ እንጂ ስምህን ለማያውቁ ከሐዲ ጠላቶችህ ርስትህን አታሳልፋት። እኛ ሕዝቦችህ የመንጋህም በጎች ነንና። እስከ አለምም እናመሰግንሃለን።

#እኛም አለማዊ ጌጣችንን፣ የኃጢአት ልብሳችንን አውልቀን፤ ትህትናን ተላብሰን በተሰበረ ልብ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንግባ። ዲያቢሎስ የከፈተብንን ጦርነት ድል እንነሳ ዘንድ እግዚአብሔርን እንለምነው። ዋናችን ይህን አስተምሮናልና። የእግዚአብሔር ሀይል እንጂ ንግሥናው ይህን እንደማያደርግ አውቋልና፤ ለኛም ባለጸጋነታችን ድልን አያደርግም።

#ኢትዮጵያንም እንደ ጥንቱ ከራሷ አልፋ ለሌሎች የምትተርፍበትን ዘመን ያምጣልን። አሜን።


   
     ምንጭ: የናግራን ሰማዕታት


#ንጉሥ ካሌብ በጨካኙ አይሁዳዊ ፊንሐስ ጭፍጨፋ ሚሰቃዪትን ክርስቲያኖች ለማዳን ወደ ናግራን ለጦርነት ከመዝመቱ በፊት፤ ነገሥታት የሚለብሱትን ጌጥና ልብሱን አወለቀ።

ከዚያም ቅጠል ለብሶ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገባ። የመሠዊያውን ቀንድ ይዞ ዐይኖቹን ወደ ሰማይ በማቅናት እንዲህ ሲል ጸለየ 👇


#ሃይማኖትና ምግባር

እግዚአብሔር አምላክ በመጻሕፍቱ እንደነገረን በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርሰቲያን ወደ መንግሥተ ሰማያት ለመግባት የሚያስፈልጉ ሁለቱ ዓቢይ ነገሮች ናቸው።

እነዚህም ሃይማኖትና ምግባር ናቸው። ይህም እምነትና መልካም ሥራ ማለት ነው።

ሃይማኖትና ምግባር _ በአንድ ላይ ካልተጣመሩ መዳን እይቻልም። ሃይማኖት ብቻውን ወይም ምግባር ብቻውን አያድንም።

ቅዱስ ያዕቆብ ይህን ሲገልጽ ሰይጣን ያምናል መልካም ሥራ ሰለሌለው አይድንም ብሎ ሁለቱ ካልተዋሓዱ ትርጉም አንደሚያጣ ተናግሯል።

“አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል።" ያዕ ፪(2:19)

ስከዚህ በእምነት ብቻ እድናለሁ ብሎ ማሰብ ከእግዚአብሔር ቃል ውጪ ነው። ስለዚህ ነው ሐዋርያውም ጨምሮ በምሳሌ ሲያስተምረን፡-

“ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው፡፡“ ያዕ ፪፡፳፮ (2፡26)

ስለዚህም ከአንድ ክርሰቲያን ምግባር ወይም በጎ ሥራ መሥራት ከሃይማኖት ጋር መንግሥተ ሰማያትን ለመውረስ የሚያበቃ ነው። በማቴዎስ ወንጌል እንደተጻፈ ጌታ ለፍርድ ሲመጣ የሚጠይቀው የምግባር ጥያቄ ነው።

ማቴ ፳፭ ፦ ፴፬ (25:34)። ጻድቃንም ሆኑ ኃጥአን በምድር የሚሠሩት ይከተላቸዋል።

“ሥራቸውም ይከተላቸዋል“ ራዕ ፲፬፡፲፫ (14፡13)

ይሀን ሳንረዳ በዕምነት ብቻ ወይም በጸጋው ብቻ እንድናለን ብለን በጎ ምግባርን ሳንፈጽም ብንቀር አስደንጋጭ የሆነ የጌታ ቃል በአኛ ላይ ተቃቷል ፡-

“በስማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም…..የዚያን ጊዜም ከቶ አላውቃችሁም እናንተ ዓመፀኞች ከእኔ ራቁ ብዬ እመስከርባቸዋለሁ።” ማቴ ፯፡፳፩-፳፫ (7:21-23)

”አሁንስ ምሳር ደግሞ በዛፎች ሥር ተቀምጧል እንግዲህ መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል ወደ እሳትም ይጣላል።”
ሉቃ ፫:፱ (3:9)

ይህ ሁሉ የወንጌል ቃል የሚመከረን ሃይማኖትን ከምግባር አስተባብረን በመያዝ ለመንግሥተ ሰማያት የበቃን እንሆን ዘንድ ነው። ምከንያቱም የከብር ጌታ ለሁሉ ሳያዳላ የሚፈርደው እንደ ሥራችን መጠን ነውና።

”አንተ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ፍዳውን ትስጣለህና። " መዝ ፷፩፡ ፲፪ (61፡12)

“እነሆ በቶኰ አመጣለሁ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።” ራዕ ፳፪፡፲፪(22:12)

”በጎ ሥራ የሚሠሩ ሰዎችን ግን እግዚአብሔር ከመከራው ሁሉ እንደ ጠበቀው እንደ ኢዮብ ባሮቹ ይሆኑ ዘንድ እግዚእብሔር በበጎ ሥራው ሁሉ ይጠብቃቸዋል።” ፩መቃ ፴፮፡፲፮ (36፡16)

ሃይማኖትና ምግባርን ይዘን በቀኙ ለመቆም ያብቃን።
አሜን!


@Deaconchernet
@Deaconchernet
@Deaconchernet


#በዓታ ለማርያም

ታኅሣሥ በባተ በሦስተኛው ቀን የሚታሰበውና የሚከበረው በዓል ‹‹በዓታ ለማርያም›› በመባል ይታወቃል፡፡ ከእናቷ ከቅድስት ሐና እና ከአባቷ ቅዱስ ኢያቄም በስዕለት የተወለደችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት የከበረ እንደመሆኑ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ታከብረዋለች፡፡

በዓት ቃሉ የግእዝ ሲሆን ቤት ማለት ነው፡፡ ደጋጎቹ የእግዚአብሔር ሰዎች ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሐና ልጅ አጥተው ለብዙ ዘመናት ከመኖራቸው የተነሣ በኀዘን ፈጣሪያቸውን ሲማጸኑ ቃል በመግባት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሦስት ዓመት ሲሆናት በእግዚአብሔር ቤት ትኖርና ታገለገል ዘንድ በቤተ ክርስቲያን እንድትኖር ስለሰጧት በዓሉም ስያሜውን በዚያ መሠረት አግንቷል፡፡

በዚያን ጊዜም በቤተ ክርስቲያን ያገለግል የነበረው ካህኑ ዘካርያስ ስዕለታቸውን አስተውሶ ቅድስት ድንግል ማርያምን ሊቀበላት ሲቀርብ እንደ ፀሐይ የምታበራ ሕፃን ሆና አገኛት፤ በመገረምና በመጨነቅም ከወላጆቿ ጋር ምን ሊመግቧት እንደሚችሉ በመጨነቅ ላይ ሳሉ ሕዝቡ በተሰበሰበበት መካከል መልአኩ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ይዞ ከሰማይ ወረደ፡፡ ካህኑ ዘካርያስም ለእርሱ የመጣ መና መስሎት ሲቀረብ ወደ ላይ ተመለሰበት፡፡ በዚያ የተሰበሰቡት ሰዎችም እያንዳንዳቸው ቢሞክሩ በተመሳሳይ መልኩ ተመልሶ ወደ ላይ ራቀባቸው፡፡

‹‹ምን አልባት ለእንግዶች የመጣ ሀብት እንደሆነ›› ብለው ቅድስት ሐና እና ቅዱስ ኢያቄም እንዲቀርቡ ቢደረግም ለእነርሱም ራቀባቸው፡፡ ካህኑ ዘካርያስም ቅድስት ሐናን ‹‹እግዚአብሔር የሚያደርገውን የሚያውቅ የለምና ልጅቷን ትተሸ ወደዚህ ነይ›› አላት፤ ሆኖም ግን ቅድስት ማርያም እናቷ ትታት ስትሄድ መከተል ጀመረች፤ ምርርም ብላ አለቀሰች፡፡

በዚህም ጊዜ መልአኩ ፋኑኤል ወደ እርሷ ቀርቦ አንድ ክንፉን አንጥፎ አንድ ክንፉን ጋርዶ መገባት፤ ከዚያም በክብር ዐረገ፤ ሊቀ ካህናቱና ሕዝቡም ‹‹የምግቧ ነገር ከተያዘልን በቤት እግዚአብሔር ትኑር›› ብለው ወደ ቤተ መቅደስ አስገቧት፡፡
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ሰማያዊ ኅብስትና መጠጥ እየተመገበች  በቤተ መቅደስ  ለ፲፪ ዓመታትም ኖራለች፡፡
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና ተራዳኢነት አይለየን፤ በረከቷ ይደርብን፤አሜን! 

ምንጭ፡- ነገረ ማርያም

@Deaconchernet
@Deaconchernet
@Deaconchernet


#ስለ_እርሱ_አንብቡ

እግዚአብሔር በአሳባቸሁ ውስጥ እንዲኖር ስለ እርሱ አብዝታችሁ #አንብቡ ።
እርሱን ለማወቅ ስለ እርሱ #አንብቡ ። እርሱን ካላወቃችሁት እንዴት እርሱን ልትወዱት ትችላላችሁ ?

ስለ እርሱ #አንብቡ ፤ ስታነቡ ግን በሳይንሳዊ ወይም በፍልስፍና ጠባይ አታንብቡ ወይም ደግሞ ስለ እርሱ ጥናታዊ ጽሑፍ ወይም ትምህርት ለመስጠት አታንብቡ ። ነገር ግን ወደ እርሱ ጥልቀት ለመግባት ወይም እርሱ ወደ እናንተ ጥልቀት እንዲገባ #አንብቡ።

ለነፍሳችሁ ውድ የሆኑትን የእርሱን ባሕርያት ለማወቅ ስትሉ #አንብቡ ይህ እውቀት አሳባችሁ ከእርሱ ጋር እንዲጣበቅና ፍቅሩ ከእናንተ ልብ ጋር እንዲቀናጅ ያደርግላችኋልና ። ስለ ስምምነቱ ስትሉም #አንብቡ ። ከወደዱት ሰዎች ጋር ስላለው ግንኙነት በጠላቶቹ ላይ ስላለው አቋም ስትሉ #አንብቡ !

እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቀምሳችሁ ታዩ ዘንድ ስለ እርሱ #አንብቡ ። ታዲያ ንባባችሁ ለልባችሁ ምግብ እንዲሆን እንጂ እንዲሁ ተራ ንባብ እንዲሆን አትፍቀዱ ።

ስለ እግዚአብሔር ብዙ ካነበባችሁ በእርሱ ዘንድ ያለውን ፍጹምነት በሙሉ ታገኛላችሁ ።

ከወደዳችሁት ስለ እርሱ ማንበባችሁን ትቀጥላላችሁ ። እግዚአብሔር ስለ እርሱ የሚያነቡትን ስለ እርሱ ዜና የሚጠይቁትን ከእርሱ ታሪኮች መካከል አንዱን ለማወቅ የሚናፍቁትንና እርሱን የሚያደንቁትን ሰዎች ይወዳቸዋል ።

ስለ እርሱ ከመጽሐፍ ቅዱስ ወይም ከአባቶች ብሒሎች ወይም ከቤተክርስቲያንና ከቅዱሳን ታሪክ ልታነቡ ትችላላችሁ ። በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የእግዚአብሔር እጅ ለመዳሰስ ስትሞክሩ በጥበቡ በኃይሉና በርኅራኄው ውስጥ እንደምትወዱት ታውቃላችሁ ።

#አቡነ_ሺኖዳ_ሳልሳዊ

@Deaconchernet
@Deaconchernet
@Deaconchernet

20 last posts shown.