ፍቅር እስከ ጀነት (𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨)


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ሀላሌ ነሺ አሉ !!
ከወንዶቹ ሁሉ አይንሺ ለኔ አድልቶ
ልብሽ ከወደደኝ ሁሉን ነገር ትቶ
ወላጅም ከሰጠ ሽማግሌ መጥቶ
ኒካህ ከታሰረ ሁሉም ተመቻችቶ
ልቤም ይረጋጋል ያሰብኩት ተሞልቶ፡፡
📝 ወንድማችሁ ራማስ ኢብኑ በድሩ 🍃

ለአስታያየትዎ ☞ @fkr_eske_Jenet_Bot

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


🌹ጥሩ_ ትዳር _ትፈልጋለህ??!

ከፈለክ ኢማም አህመድ ኢብን ሀንበል (አላህ ይዘንላቸው) ልጃቸው ሲያገባ የለገሱት ምክር እኔም አንተንም ስለሚመለክት ጆሮህን አውሰኝ! !

☞ ልጄ ሆይ እነዚህን አስር ነገሮች ለባለቤትህ መፈጸም ካልቻልክ በትዳር ህይወትህ ደስተኛ መሆን ስለማትችል ምክሬን ጠበቅ አድርገህ
ለመያዝ ሞክር፦

“①- ሴት ልጅ ምቾትን ስለምትፈልግ ያለህን ነገር ሳትሰስት አጋራት

②- ሴት ፍቅርህን እንድትገልጽላት ትሻለች። (ባገኘከው አጋጣሚ) ፍቅርህን ከመግለጽ ወደኋላ አትበል

③- ሴቶች ግትር ወንዶችን ይጠላሉ። ደካማ ወንዶችን ደግሞ ይንቃሉ አንተጥንካሬ በሚያስፈልግበት ቦታ ጠንካራ ሌላ ጊዜ ደግሞ ገር ለመሆን ሞክር።

④- ሴቶችን መልካም ንግግር፡ ውብ ገጽታ ንጹህ ልብሶችና ጥሩ መአዛ ስለሚማርካቸው ሁሌም እነዚህ ነገሮች እንዲኖሩህ ጥረት አድርግ

⑤- ለሴት ቤቷ የቤተ መንግስት ያህል ክብር የምትሰጠው ስፍራ ነው ቤቷ ስትሆን ዙፋኗ ላይ በክብር የተቀመጠች ንግስት ያህል ክብር ይሰማታል በምንም ተአምር ይህን ቤተ መንግስቷን የሚያፈርስባትን ነገር እንዳትፈጽም ከንግስና ዙፋኗ ላይ ልታወርዳትም አትሞክር ይህን ካደረክ ንግስናዋን እንደመቃወም ይቆጠራል። ለንጉስ ንግስናውን ከመቀናቀን የበለጠ ትልቅ ወንጀል የለምና ጥንቃቄ አድርግ።

⑥- ሴት የቱን ያህል ብትወድህም ቤተሰቧን ማጣት አትፈልግም አንተን ከቤተሰቦቿ በላይ እንድትወድህ ለማድረግ አትጣር ይህን ማድረግ ፍጻሜው የማያምር ጠላትነትን ሊያመጣብህ ይችላል።

⑦- ሴት ከጎንህ (ጠማማ አጥንት) መፈጠሯን አትዘንጋ ይህ አፈጣጠሯ የውበቷ ሚስጥር መሆኑን እወቅ። ትንሽ ስህተት ባየህ ቁጥር አቃናታለሁ እያልክ እንዳትሰብራት ተጠንቀቅ። ስብራቷ ፍቺ ነው ላቃናት ከሞከርኩ ትሰበራለች በማለትም የባሰ እንድትጠም መንገድ አትክፈትላት መካከለኛ ሰው ሁንላት።

⑧- ሴት አንዳንዴ የዋልክላትን ውለታ ልትዘነጋ ትችላለች (ስትናደድ) ያደረክላትን ነገርም ልትክድ ትችል ይሆናል ነገር ግን እንዲህ አደረገች በማለት ብቻ እንዳትጠላት ይህን ባህሪዋን ባትወድላት ሌሎች የሚስቡህ ብዙ ባህሪዎች እንዳሏት አትዘንጋ።

⑨- ሴት አካላዊ ድካምና ስነልቦናዊ ጫና ሊያርፍባት ይችላል በዚህን
ወቅት አላህ (ሱብሀነሁ ወተአላ) የግዴታ አምልኮዎችን (ሰላትና ጾም) ሳይቀር ውድቅ አድርጎላታል። በዚህን ጊዜ እዘንላት ትእዛዝ አታብዛባት።

⑩- ሴት አንተ ዘንድ ያለች (የፍቅር) ምርኮኛህ መሆኗን አትዘንጋ ምርኮኛህን በጥሩ ሁኔታ ያዛት እዘንላት በድክመቷ (የምትፈጽመውን ስህተት) እለፋት ምርጥ የሂዎት አጋርህ ትሆናለች።

══ •⊰✿ 🌹 ✿⊱• ═
t.me/FKR_ESKE_JENET




​​ስለ ፍቅር

ፈልገነው አስበነው፣ አባዝተን፣ ቀንሰን አሊያም ደምረን የምናገኘው ቀላል ስሌት አይደም። ፈሪ ሆንክ ደፋር፣ ሀብታም ሆንክ ደሀ፣ ማንም ሆነክ ምንም የማይደንቀው፣ በማንኛውም የሰው ልጅ ልብ ውስጥ በራሱ ጊዜና መንገድ ሰርጎ የሚገባ የተፈጥሮ ፀጋ ነው። ይህን የተሳጠንን ታላቅ ፀጋ (በረከት) መቋደስ መታደል ነው። እስቲ ስለ ፍቅር ካነሳን አይቀር ስለአንድ እውነተኛ የፍቅር ታሪክ ገጠመኝ ላውጋችሁ ልብ ብላችሁት በትእግገስትም አንብቡት፡፡

አንድ በጣሙን ደሃ የሆነ ሰው ከሚስቱ ጋር ይኖር ነበር፡፡ አንድ ቀን ሚስቱ ጸጉሯን የምታበጥርበት ማበጠሪያ እንዲገዛላት ጠየቀችው፡፡ ባል በጣም አዘነ፡፡ በኪሱ አንዳችም ገንዘብ ስለሌለው እያዘነ እንደማይችል ገለጸላት፡፡ ሌላው ይቅርና በቅርቡ ማሰሪያው ለተበጠሰበት የእጅ ሰዓቱ እንኳ ማሰሪያ መግዛት ስላልቻለ በኪሱ ይዞት እንደሚዞር ማሰሪያው የተበጠሰውን ሰዓት እያሳየ እንደማይችል ገለጸላት፡፡ ሚስትም ነገሩን ተወችው፡፡ ባል ወደ ሥራ ሲሄድ በአንድ የሰዓት መሸጫ በኩል ሲያልፍ ወደ መሸጫው ገብቶ ማሰሪያው የተበጠሰውን ሰዓት ሸጠ፡፡ ሌላ ሱቅ ገባ፡፡ ለሚስቱ በጣም የሚያምር ማበጠሪያ ገዛ፡፡ ምሽት ላይ ከስራ ወደ ቤት ሲመለስ ዋንኛ ዕቅዱ ለሚስቱ እንዴት ያንን የሚያምር ማበጠሪያ እንደሚሰጣት ነበር፡፡ ሚስቱን ሲያያት ግን ደነገጠ፡፡ ያ የሚያምረው ዘንፋላ ጸጉሯ በአጭሩ ተቆርጧል፡፡ ባለማመን እንደተዋጠ የገዛላትን ማበጠሪያ ከቦርሳው አውጥቶ ወደ እሷ ቀረብ ሲል አይኗ በእንባ እንደረጠበ በእጆቿ መሃል የያዘችውን ነገር ተመለከተ የሰዓት ማሰሪያ፡፡ ሰዓቱን ሸጦ ማበጠሪያ እንደገዛላት ሁሉ፣ ለካንስ እሷም ያን ዘንፋላ ጸጉሯን አስቆርጣ ሸጣ የሰዓት ማሰሪያ ገዝታለት ነበር፡፡ ሁለቱም ፍቅር በልባቸው እየነደደ በእንባ ታጠቡ……..

ፍቀር ራሱን እንጂ ሌላ ምንም አይሰጥም ከራሱ እንጂ ከሌላ ከማንም አይቀበልም ፍቅር ለፍቅር በቂ ነውና፡፡ ፍቅር ብዙ ነገር ነው ተፅፎ ተነግሮና ተገልፆ የማያበቃ ለከት የሌለው፣ ልንገድበው የማንችል የተፈጥሮ አምባገነን ነው። ፍቅር ውስጣችን ሰርጎ ከገባ ተልካሻ ነገሮች አይምሮአችን ውስጥ ቦታ የላቸውም። ፍቅር ያለ ቦታው የአባጨንጓሬን ያህል ይኮሰኩሳል ቢሆንም በፍቅር አይን ሁሉም ነገር ትክክል ሰለሆነ በዚህ መኮስኮስ ውስጥም ፍቅር አለ። በፍቅር አለም አለመግባባት አልያም ግጭቶች መፈጠሩ አይቀሬ ነው ምክንያቱም ሰው ሆኖ ፍጹም የለምና ነገር ግን ይቅር ማለት ሁልጊዜ አንተ ተሳስተሃል ማለት አይደለም አንዳንድ ጊዜም ላለህግንኙነት ዋጋ መስጠት ራስ ወዳድነትን መስበር ማለት ነው። ሁላችንም ፍቅርን እንደ ሸማ ለብሰን በፍቅር ኖረን በፍቅር እንድናልፍ አሏህ ይርዳን አሚን !

📝 ራማስ አልሀናኒ

▬▬▬๑۩🌹۩๑▬▬▬
t.me/FKR_ESKE_JENET




ህመሙን ተቀበሉት!

የትኛውም ውሳኔ የራሱ ተመጣጣኝ ዋጋ አለው፤ የትኛውም ተግባር የራሱ ግብረመልስ፣ የራሱ ውጤት አለው። ለውሳኔያችሁ መታመን፣ ተግባራችሁን እስከመጨረሻው ማስኬድ፣ ጥረታችሁንም መቀጠል አምናችሁ መቀበል ላለባችሁ ህመም ያጋልጣችኋል። ህመሙን እንደ ጥፋት፣ ስቃዩንም እንደ ቅጣት የምትመለከቱ ከሆነ ግን ዳግም አዲስ ውሳኔ መወሰንና እንደገና አዲስ ተግባር የመሞከር ድፍረት እያጣችሁ ትመጣላችሁ። የምትችሉት አንድ ነገር ነው፦ ጥፋቱን ሳይሆን ህመሙን መቀበል፣ ውጣውረዱን እንደ ቅጣት ሳይሆነ ነገ ውጤት ሊያመጣ እንደሚችል ግበዓት መውሰድ። የሞከራችሁት ነገር በሙሉ ባልተሳካ ቁጥር እራሳችሁን ጥፋተኛ ማድረግ ተነሳሽነታችሁን እየገደለ፣ አቅማችሁን እያሳነሰና ዋጋ እያሳጣችሁ እንደሚመጣ አስተውሉ።

አዎ! ጥፋቱን ተውት ህመሙን ተቀበሉት! የሚያሳድጋችሁን ህመም፣ የሚቀይራችሁን ህመም፣ ደረጃችሁን የሚጨምረውን ህመም ተቀሉት። ሃሳባችሁ ትልቅ ሲሆን ህመማችሁም ትልቅ ይሆናል፣ ተግባራችሁ ፈታኝ ሲሆን ጥረታችሁና ድካማችሁም እንዲሁ ፈታኝ ይሆናል። በጥረታችሁ መሃል የምታጠፉትን ጥፋት፣ የሚያጋጥማችሁን ውድቀት፣ የሚደርስባችሁን ጫና፣ የምታጡትን ሰውና የምትከስሩትን ገንዘብ እንደመማሪያ እንጂ እንደ ሌላ የስጋት ምንጭ አትውሰዱት። ምንጊዜም የጥፋተኝነት ስሜት እስረኛ ያደርጋችኋል፤ በስህተታችሁ በተፀፀታችሁ ቁጥር ወደፊት መጓዝ ያቅታችኋል፣ ሃሳባችሁ እንዲሁ ያስፈራችኋል፣ ምኞታችሁ ከንቱ ሆኖ ይቀራል፣ የራሳችሁ እንቅፋት እራሳችሁ ትሆናላችሁ፣ ሳታውቁት ለዘመናት በተመሳሳይ አስተሳሰብ ተመሳሳይ ስፍራ እራሳችሁን ታገኙታላችሁ።

አዎ! ሀቢቢ..! ጥፋቱ እንደጥፋት፣ ስህተቱም እንደስህተት ይቀመጥ፣ ይልቅ ከጥፋቱ ቦሃላ ከደረሰብህ ህመም፣ ከስህተቱ ቦሃላ ካጋጠመህ ስቃይ በሚገባ ተማር። ትሞክራለህ ትሳሳታለህ፣ አዲስ ነገር ትጀምራለህ ታጠፋለህ፣ ነገር ግን በሂደቱ ውስጥ መማር ከቻልክ ነገሮች ሁሉ የማይቀየሩበት ምክንያት አይኖርም። በህመም ውስጥ ተምሮ መውጣት፣ በስቃይ መሃል እራስን ፈልጎ ማግኘት መቻል የትልቁ አላማህ አካል መሆን ይኖርበታል። ስቃይ የመኖር እጣፋንታ ነው፣ ህመም የህይወት አንድ አካል ነው። ነገር ግን ለምን እየተሰቃየህ ነው? ለምን ብለህ እየታመምክ፣ ዋጋ እየከፈልክ ነው? የሰዎችን ኢምፓየር ለመገንባት ወይስ የእራስህን ለመመስረት፣ ሰዎችን ለማበልፀግ ወይስ እራስህን ከእስር ነፃ ለማውጣት? ምክንያትህን በሚገባ እወቀው፣ ባወከው ልክ ለላቀቀው ህመም እራስህን አዘጋጅ፣ ሁሌም ከርሱ ተማር፣ እራስህንም አብቃበት። ከዚያ በዘለለ ምርጫህ ትክክለኛ እንዲሆን በዱአ በርታ !!!

rel='nofollow'>➢t.me/FKR_ESKE_JENET








የአስቸጋሪው ጊዜያችሁ ውበት!

በሕይወታችሁ እጅግ አስቸጋሪ በተባለው ጊዜአችሁ ውስጥ የምታዩት ውብ የሆነ ነገር ቢኖር፣ በአካባቢያችሁ የሚገኙ ሰዎችን እውነተኛ ቀለምና ማንነት የማየታችሁ እውነታ ነው ። ተጠቀሙበት!

t.me/FKR_ESKE_JENET




አንዳንድ ሰዎች የሰዎች መድሀኒት ናቸው ፤ ከእነሱ ጋር አንድ ሰዓት ያህል ብቻ ብትቆይ ራሱ ሁሉም ነገር የተሻለ እንደሆነ ይሰማሀል ።

@Fkr_eske_jenet




🩸 ስሜትን ለመቆጣጠር 4 መንገዶች!

አንድ ጥናት እንደሚያመላክተው ሁለት ሰዎች እየተነጋገሩ ሳለ፣ የአንደኛቸው አእምሮ የሌላኛቸውን የመምሰል አዝማሚያ አለው። ይህም ማለት ሚስትህ በቁጣ ስትናገርህ፣ ያንተም ምላሽ በቁጣ የተሞላ ይሆናል፤ ልጅህን በስክነት ውስጥ ሆነህ ስታናግረው፣ የእርሱም አእምሮ የሰከነ ይሆናል።

ወዳጅህ ሲስቅ አንተም ትስቃለህ፤ ወይም እርሱ ሲያዛጋ አንተም ማዛጋት ትጀምራለህ። ሁሉም ስሜቶች ተላላፊ ናቸው፤ ልክ እንደ ጉንፋን። ፍርሃት፣ ጭንቀት፣ ሃዘን ሁሉም ከሰው ወደ ሰው ይጋባሉ።

ስሜቶችህን ለመቆጣጠርና ወደ ከፍታ ለመድረስ የሚያስችሉህ መንገዶች:-

አንድ- በየዕለቱ፤ ጠዋትና ማታ ለአስር ደቂቃዎች ያህል አዝካሮችን በል ።

ሁለት- ከሰዎች ጋር መልካም የሆነ ግንኙነት እንዲኖርህ አድርግ፤ ሳቅህንና መልካም ሃሳቦችህን አጋባባቸው።

ሶስት- በሄድክበት ሁሉ ያንተን እርዳታ የሚሹ ሰዎችን በተቻለህ አቅምም እርዳቸው። ይህም ሁላችንም አንድ ለመሆናችን እና የሌላው ደስታ ያንተም ደስታ እንደሆነ ማስታወሻ ይሆንሃል።

አራት- ያበሳጨህን፣ ያናደደህን ነገር ሁሉም ከአሏህ የመጣ መሆኑን አውቀህ ሶብር በማድረግ ባንተ ላይ የመጣውን መጥፎ ነገር በመልካም ቀይረው !!!

t.me/FKR_ESKE_JENET




የማንም አደለንም።! የአሏህ ነን ወደ አሏህ ተመላሾች ነን              
╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-


t.me/FKR_ESKE_JENET




#ፈገግ_እያሉ_ፀጥ_ብለው_ይኖራሉ

አሉኮ አንዳንዶች ••••
ውስጣቸው ላይ ከባድ የሚባል ችግር አለ ፣ የተደራረበ ሀዘንና ብሶት ላያቸው ላይ ጭነዋል፣ የኔ የሚሉትና የሚረዳቸው ሰው ቢያገኙ ሊያወሩት የሚፈልጉት ብዙ እምቅ ህመም አለ ፣ የህመም ስሜቱ እንደነሱ የሚሰማው ስሩ ሽጉጥ አድርጎ አይዞህ (አይዞሽ) ብሎ የሚያባብላቸው የራስ ሰው ቢኖራቸው የሚያለቅሱት ዕልፍ የሂዎት ቁስልና የተጠራቀመ የመኖር እንቅፋት አለ እነሱ ግን እንዲህ ሆንን ይህ ገጠመን, ብለውም ለማንም ምንም አያወሩም ፣ አብረሀቸው ስትኖርም በትንሽ ትልቁ ሲያማርሩ ወይ ደግሞ እድላቸውን ሲረግሙ አንዴም አትሰማቸውም ••| በቃ ፈገግ እያሉ ፀጥ ብለው ይኖራሉ። የዛ አይነት ሰዎች ይክፋቸውም ደስተኛ ይሁኑም በውል አያስታውቁም በዚህ የተነሳ በአንዳንድ ሠዎች ዘንድ
" ውስጣቸው አይገኝም " አልያም ደግሞ "እሱ ምን አለበት" "እሷ ምን አለባት" ሲባሉ ይሰማሉ በጣም የሚገርመው ግን ይሄን ተባልን ብለው እንኳ ስላሉበት ሁኔታና ችለውት እየገፉት ስላሉት የቀን ጥቁር ለማብራራት አይሞክሩም። ብቻ ፈገግ እያሉ ፀጥ ብለው ይኖራሉ አንዳንዴ በዙሪያቸው ያሉ ሰዎች እንዲህ ሆንን የሄ ነገር ገጠመን እያሉ ሲያማርሩና ሲያለቃቅሱ ሲሰሙ እነሱ ካሳለፉትና አሁንም ቁመውበት ካለው የሂዎት ውጣ ውረድ አንፃር "እሱ ምን አለበት" "እሷ ምን አለባት" የተባሉትን ነገር አስታውሰው •• አይ እዳር ያለ ሰው•• ብለው በሆዳቸው ያቺን የተለመደች ፈገግታቸውን ብለጭ እያደረጉ ፀጥ ብለው ይኖራሉ ። ዞረው በተስፋ ወደሚያልሙት ፣ ይሻል ይሆናል ብለው በምኞት ወደሚጓጉለት ነጋቸው እያነከሱ ያዘግማሉ ••• ማንከሳቸውን ግን እነሱ እንጂ ሌላው አያውቀውም አይ ሰው ብርቱ !!! ሀቂቃ ተገረምኩባችሁ ጀግና ናችሁ ። አሏህ ሀጃችሁን ያውጣላችሁ። አሏህ ለሁሉም ችግር መፍትሄ አለው አይዞን!!!

t.me/FKR_ESKE_JENET







20 last posts shown.