የኒቃብና የትምህርት ጉዳይ የሰሞኑ መነጋገሪያ ሆኗል !ነገሩ አሁን ይግነን እንጂ ፀረ ኒቃብ የሆኑ ስልጣን አለን ባዮች ድሮ ነው ኒቃብን ሲያጥላሉ የነበሩት። ከዚህ ጋር ተያይዞ ዩኒቨርስቲ በነበርኩበት ወቅት የማስታወሰውን ልንገራችሁ እኔ ተመርቄ ከወጣሁ አንድ አመት ሆኖኛል ግቢ በነበርኩበት ሰአት የዩኒቨርስቲው የሙስሊም ተማሪዎች ተወካይ ነበኩ በዚህም ምክንያት በዩኒቨርስቲው አስተዳደር በኩል ለሙስሊሞች ያላቸውን ጥላቻ ለማየት ቅርብ ነበርኩ። ለሙስሊሞች ያላቸው ጥላቻ ንቀት እጅግ ይለያል ሙስሊም በዚህ ደረጃ እንደሚጠሉ የተገለጠልኝ ያኔ ተወካይ በሆንኩበት ሰአት ነበር። የሚገርማችሁ እኔ ፍሬሽ ሆኝ ስገባ ኒቃብ ለባሽ አልነበረም 2ኛ ወይም 3ኛ አመት አካባቢ አንድ ልጂ ኒቃብ ለብሳ መጣች በዚያ ኒቃብ ምክንያት ብዙ ጫና ነበረባት ለዛውም በግቢው ብቸኛ ኒቃቢስት እሷ ብቻ ሆና እንዲሁ መገመት ትችላላችሁ። አልሃምዱሊላህ እሷ ኒቃብ ባዳረገች በአመቱ በዩኒቨርስቲው የኒቃቢስቶች ቁጥር ከሚያስቡት በላይ ጨመረ ያኔ ጫና ለመፍጠርና ኒቃብ ለማስወለቅ ያላደረጉት ጥረት አልነበረም። እኔ በሰአቱ የሙስሊም ተማሪዎች ተወካይ ነበርኩ በየግዜው ክላስ እያለኝ እራሱ በኒቃብ ጉዳይ ከሌሎች ወንድሞቼ ጋር በመሆን ሰብሰባ ይጠሩን ነበር። ታዲያ ሲሰብቡን ኒቃብ ያውልቁ ፊታቸው ገልጠው እንደማኛውም ተማሪ መንቀሳቀስ አለባቸው የሚል ሀሳብ ቀጥታ ትእዛዝ ተሰጠን። ይህን የማታደርጉ ከሆነ በእነሱም በእናንተም ላይ እርምጃ እንወስዳለን ከትምህርት ትባረራላችሁ አሉን። አስቡት እኔና ወንድሞቼ በዛ ዩኒቨርስቲ ያሉ ሙስሊም ተማሪዎች ሁሉ ጉዳይ አማና በኛ ላይ ወድቋል በአንድ በኩል ደግሞ ተመርቀን መውጣት እና የቤተሰቦቻችንን አደራ መወጣት አለብን።
ከሁለቱ እንዱ መምረጥ ለኛ ከባድ ነው ቢሆንም አሏህ ጥንካሬውን ሰጥቶን የፈለጉትን ያምጡ እኛ እህቶቻችን ኒቃብ አውልቁ የሚል ትእዛዛት አንሰጥም አልናቸው። በዚሁ ስብሰባው ያለ ስምምነት ተጠናቀቀ። ከስብሰባ ከወጣሁ በኋላም በስልክ እየደወሉ ብዙ ማስፈራሪያ ዛቻ ያደርጉብኝ ነበር።
ሌላው ኒቃቢስት እህቶችን ላይ ላይብረሪ ኒቃብ ለብሳችሁ መግባት አትችሉም .ከግቢ ውጭ ስትወጡ (ከመስጂድ) ስትመለሱ ፊታችሁን ገልጣችሁ ለጥበቃዎች ማሳየት አለባችሁ,ካፌ አትስተናገዱም አስከ ማለትና መታወቂያ ( ID) እስከመንጠቅ ደረሱ ።
ያኔ እኔ በቀዳሚነት የመጀመሪያ ተወካይ ብሆንም ሌሎችም ሶስት ወንድሞቼ አብረው ነበሩና ነገሩ እየተባባሰ ሲመጣ ቁጭ ብለን ሹራ አደረግን። ከዚያም በአንድ ሀሳብ ተስማማን እሱም ምንድነው እኛ ለብቻችን ብንጋፈጣቸው ከትምህርት እንባረራለን የእህችንም ኒቃብ ይወልቃል። ሰለዚህ ነገሩን ተማሪዎች ሳይሰሙ እና ነገሮች ውጥቅጣቸው ከመውጣቱ በፊት በዩኒቨርስቲው አካባቢ ያሉ ሼኮችን ጣልቃ እንዲገቡበት አደረግን ። እነሱም አሏህ እረጂም ጤና እድሜ ይስጣቸው ሀሳባችንን ተቀብለው በአካል በዩኒቨርሲቲው በመገኝት ፕሬዝዳንቱ እና ሴኔት አባላት ጋር ተነጋገሩ። ይህኔ ነበር አላማው የከሸፈባቸው። ነገሩ ከተማሪ አይወጣም እዚሁ አለባብሰን እርምጃ ወስደን እናስተካክላለን ያሉት ነገር ማህበረሰቡ ዘንድ እንደደረሰ እና ሌላ ነገር እንደሚያስከትልባቸው ሲያቁ በዚያው ፀጥ አሉ ።
ከዚህ ጋር ተያይዞ ምን ያክል ለሙስሊም ጥላቻ እንዳላቸው የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተወካይ በሆንኩበት ግዜያት በደንብ አይቻለሁ። ሙስሊም ተማሪዎችን ለመንካት ሆን ተብሎ የሰአት ገደብ በማድረግ የመغሪብ እና ኢሻ ሰላት መስጂድ ሄደን እንዳንሰግድ ያደርጉ ነበር ። እሱ አልበቃ ብሎ መስጂድ ቆይተው የሚመጡትን ልጆች የት ነበራችሁ ተብሎ ውጭ በር ላይ አናስገባም ይላሉ ሲፈልጉ ID ይነጥቃሉ። ሲያሻቸው ደግሞ ሰብስበው በዱላ ይገርፍሉ ይሄን ያክል ነው ጥላቻቸው ። የሚገርማችሁ ረመዳን ከመግባቱ በፊት ቀድመን ቀኑን በደብዳቤ ያሳወቅናቸው ቢሆንም ዩኒቨርሲቲው ለሙስሊሙ ያለው አመለካከት ጥሩ ስላልነበረ ተዘናግተው ቆይተው። ረመዳን የመጀመሪያ ቀን ደረሰ ከዚያም የመጀመሪያው ተረዊህ ሰላት ተሰገሰዶ ካበቃ በኋላ ዩኒቨርሲቲ ካፌ እንደተዘጋጀ ሄደው መጠቀም እንደሚችሉ መልዕክት አስተላልፍ ካሉኝ በኋላ እኔም አስተላለፍኩ ከመስጂድ ተመለስን ከምሽቱ 5 ሰአት አካባቢ ካፌ ምግብ አልተዘጋጀም መልዕክቱን አድርስ ብለው ደወሉልኝ። ያኔ የተሰማኝ ሰሜት እኔ ነኝ የማውቀው ምክንያቱም ቀድመን በደብዳቤ እና በአካል ጭምር በመሄድ ረመዳን መቼ እንደሚጀምር በአካል አሳውቀናል። ሆኖም አልተዘጋጀም። ከዚያ በዘለለ ሰሁር ካፌ እንደሚያዘጋጅ መልዕክት አስተላልፈናል። ተማሪው ካፌ አለ ሰለተባለ ከውጭ ምግብ ይዞ አልገባም። ገዝቶ እንደይጠቀም ደግሞ አሰቡት ከምሽቱ 5 ሰአት ሰለሆነ ሁሉም ላውንቾች እና ካፌዎች ተዘግተዋል።
ያኔ እኔ መልዕክት ቀድሜ ካፌ እንደሚጠቀሙ እንዳስተላለፍኩና ከዚህ በኋላ ምንም ማድረግ እንደማልችል ነግሬ ሰሁር ላይ ምግብ ዩኒቨርስቲው የማያዘጋጅ ከሆነ ለሚፈጠረው ነገር ሀላፊነቱን አልወስድም ብየ ሰልኬን ዘጋሁ። እነሱም የሚፈጠረው ችግር ስላሳሰባቸው እንደምን አዘጋጅተው ለስሁር አደረሱ። እሱን ተወጣሁ ስል በዚያው የረመዳን የመጀመሪያ ቀን ላይ በቀል በሚመስል መልኩ ሌላ መልዕክት ደረሰኝ እሱም ምንድነው። ሙስሊሞች ከሚጠቀሙበት ከተለመደው ቦታቸው ተነስተው አዲስ እየተሰራ ያለ ያላላቀ ካፌ ውስጥ ኢፍጣር እንደሚደረግ እና ነባሩ የሙስሞች ካፌ ለካፊሮች እንዲሆን ተወሰኖል አሉኝ። የሚገርማችሁ አዲስ ካፌ የምላችሁ ጭራሽ ምንም የማይመች ከመሆኑ ጋር ሴት እና ወንዶች መቀመጫ ለመለየት ጭራሽ የማይመች ከመሆኑ ጋር ለኒቃቢስት እህቶቻችን ጭራሽ ፈተና የሆነ ካፌ ነው።
ሰለዚህ ምክንያቱን ካስረዳሁ በኋላ በሀሳቡ እንዳልተስማማሁ እና በነባሩ ካፌ መዘጋጀት እንዳለበት ነገርኳቸው እና ስልኬን ዘጋሁ። ወዲያው ምን ብለው እንደነገሩት አለውቅም። የዩኒቨርስቲው ፖሊስ ቤሮ ትፈለጋለህ ተባልኩ። እኔም ሄድኩ ስሄድ ሁለት ሙስሊም ጠል የሆኑ ኒቃብ ያውልቁ የሚሉ አንድ እንስፔክተር እና ኮማንደር ቤሮ ጠበቁኝ። ሰገባም የተሰጠኝ የመጀመሪው ነገር ማስፈራሪያ ነበር ተው ተማሪችን አታሳምፅ በተዘጋጀው ቦታ ላይ ይመገቡ። መልዕክት አስተላልፍ ሳታስተላልፍ ቀርተህ ምንም አይነት ችግር ቢፈጠር ከትምህርት ትታገዳለህ....አንተ አሸባሪ ነህ ......ያላሉኝ የለም።
እኔም አዲሱ ካፌ ለኒቃቢስት እህቶቻችን እንደማይመች እንዲሁም ሴትና ወንድ መቀመጫ ለመለየት እንደሚያስቸግር ረጋ ብየ ባስረዳቸውም አልሰሙኝም። እንደውም ከነገርኳቸው በኋላ ጭራሽ ባሰባቸው ። በቃ ምንም አይነት ችግር ቢፈጠር ሀላፊነቱን ትወስዳለህ ብለውኝ ከቢሮ ወጣሁ።
ከዚያም ከወጣሁ በኋላ የግቢው ፕሬዚዳንት ደወለልኝ ያለውን ነገር ነገርኩት ..በጭራሽ. እንደማይሆን ሙስሊሙን ተማሪ እስከወከልኩ ድረስ ሀላፊነቴን መወጣት እንደ አለብኝ እና አዲሱ ካፌ እንደማንጠቀም እንደማይመች ተነጋገርን። እሱም ያለውን ሁኔታ ተረዳኝ በነባሩ ካፌ እንዲጠቀሙ እኔ አስተካክለው አለ። እንዳለውም ከስንት ጭቅጭቅ በኋላ በነባሩ ካፌ እንድንጠቀም ተደረገ። የሰላት ሰአትም በዛው ኢሻንም ተረዊህም ሰግደን እንድንገባ ተፈቀደ።
እናም እስከ አሁን ባለኝ መረጃ መሰረት ከዚያ ግዜ ጀምሮ ኒቃብ መልበስ ይቻላል ሰላታቸውንም ሰግደው ነው የሚገቡት። ስለዚህ በቀጥታ የሚመለከታችሁ አካላት ነገሩን ችላ አትበሉት!!! ቋሚ ህግ ይውጣለት።
✍️ ወንድማችሁ ራማስ አልሀናኒ
➢
t.me/FKR_ESKE_JENET