ማስጠንቀቂያ :- 1ሚሊየን ብር ሊቀጡ ይችላሉ
አለማወቅ ከቅጣት አያድንም
👉 በባህሪው አደገኛ የሆነ ደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ በወንዝ ዳርቻ ያሰወገደ ድርጅት አንድ ሚሊዮን ብር ይቀጣል፣
👉 ደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ ወንዝ ላይ የጣለ ግለሰብ 500 ሺህ ብር ይቀጣል
👉 ፍቃድ የወሰዱም ሆነ ሳይወስዱ ፍሳሽን ቀጥታ በወንዞች ዳርቻ ሲያስወግዱ ቢገኙ 100 ሺህ ብር ይቀጣሉ፣
👉 በወንዝ ዳርቻና አካባቢ መጸዳዳት ሁለት ሺህ፤
👉 የፈሳሽ ማጣሪያ ሳይኖር በወንዝ ዳርቻና አካባቢ ተሽከርካሪ ማጠብ 400ሺህ ብር፤
👉 እንስሳትን ማሰማራት፣ ማስገባት ከተፈቀደው ውጪ ተሽከርካሪ ማሽከርከር 30 ሺህ ብር
👉 ለመዝናኛ፣ ለመናፈሻና ለፖርክ ከተፈቀደ ውጪ ግንባታ መገንባት 200 ሺህ ብር፤
👉 ከአምራችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ማንኛውም ያልታከመ ቆሻሻ መልቀቅ 300 ሺህ ብር ያስቀጣል፣
👉 ኬሚካል ነክ ቆሻሻዎችን የማከሚያ ዘዴ ሳይጠቀም የለቀቀ ግለሰብ 50 ሺህ፤ ድርጅት 300 ሺህ ብር ይቀጣሉ፣
👉 ማንኛውም በካይ ቆሻሻ ከተፈቀደ የፈሳሽ ማጠራቀሚያ ውጪ ያፈሰስ ግለስብ 50 ሺህ ድረጅት 400 ሺህ ብር፤
👉 የአትክልትና ፍራፍሬ ተረፈ ምርቶችን በወንዝ ዳርቻ ማስወገድ ግለሰብ 20 ሺህ፣ ድርጅት 100 ሺህ፤
👉 ዘይት፣ ጨዋማ ፈሳሽ፣የሞተር ዘይት፣ ነዳጅ ሳሙና ነክ ነገሮችን በወንዝ ዳርቻ ያስወገደ 400 ሺህ ብር ይቀጣል፣
👉 ማንኛውም ያልተጣራ ቆሻሻ ወደ ወንዝ መልቀቅ ግለሰብ 150 ሺህ ድርጀት 300 ሺህ ይቀጣል፣
👉 ፍቃድ ሳይሰጠው ያልታከመ ቆሻሻን ወደ ወንዝ ያስወገደ ግለሰብ 15 ሺህ ብር ድርጅት 40 ሺህ ብር ይቀጣል፣
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
https://t.me/Tamrinmedia