📡 አል-ቡርሀን ኢስላማዊ ስቱድዮ
📌 አንዳንድ ምክር ከተሞክሮ አለም ቁ02‼
🔮 ነሲሀ፣ ኢፋዳ፣ በያን፣ ተንቢህ‼⑤ለአላማ ለመኖር
👉 አንድ ሰው በላጤነት ዘመኑ ሲኖር የማያስበውን ሁሉ ትዳር ከመሰረተ በኋላ ማሰብ ይጀምራል‼
በየሁሉም ወደፊት ለሚጠብቀው ነገር መጨነቅ ሳይሆን ራሱን "አለብኝ" ብሎ ያዘጋጃል‼
💥ሚስቴ ብትታመም፣ ቤተሰብ ብትዘይር
💥ሚስቴ የሚያስፈልጋት አስቤዛ፣ የቤት እቃ፣ መኖሪያ ቤት
💥ሚስቴ በዲኗ ለመጠንከር የሚያስፈልጋት ድጋፌ
💥ልጅ ስወልድ በተርቢያ አስተናነፁ
💥ቤተሰቦቻችን፣ ዘመዶቻችን፣ አማችቻዎቻችን እንዴት ደዕዋ እንደሚደረግላቸው
💥ስራዬ እና ዲኔን አብሬ እንዴት አብሬ እንደማስኬድ
💥ሌሎች መሰል በላጤነት ዘመን ትዝ የማይሉ የህይወት ውጣ ወረድ ግዴታዎች እና መሪ ቃላቶች ሲመጡ እና መታሰብ ሲጀመር
👉አሉባልታ ወሬ (አሉ ተባሉ) ይተዋል‼
👉ስራ ተወጥሮ ተስተካክሎ ይሰራል‼
👉ቂርዓት ላይ ይወጠራል‼
👉አላማ ይያዛል‼
⑥ሀዘን ማቃለል
👉 የሰው ልጅ በዚች ድብልቅልቋ በወጣች ዱኒያዊ ምድር ላይ ሲኖር
በአንድ ቀን ውስጥ እከሌ ጋር ሰርግ አለኝ ብሎ ሲሄድ
እከሌ ሞተ ለቅሶ አለብህ ተብሎ ይነገረዋል‼
ለቅሶ አለብኝ ብሎ በሀዘን አንገት ሲሄድ ሰርግ አለብህ ተብሎ ደስታ ጋር ይደባለቅበታል‼
ይቺ ምድር በራሳችን የህይወት መስኮት እና መነፀር ቆም ብለን ከማስተዋል ጋር ካየናት ድብልቅልቅ ያለ ስሜቶች የሞሏት ህይወት ናት‼
በዚህ ወቅት ችግር እና ስቃይ ሲፈራረቁ በማፅናናት፣ በማረጋጋት፣ ሀዘንን በማስረሳት በአብሮነት በብልሀት መፍትሄ በማፈላለግ እና
በደስታም ጊዜ ደስታን ደስታ ይበልጠዋል እና የደስታ ማጣፈጫ ቅመም እና ደስታው ከልክ አልፎ ወደ አመፅ እንዳይሄድ መጠን መጣኝ እና ለጭማሬው ሰበብ እንዲሆን በምስጋና አስታዋሽ የሆነው
ከሰዎች ሁሉ ከፍተኛውን እና ብዙውን ሚና የሚጫወተው እንደ እናታችን ኸዲጃ አይነት የትዳር አጋር ነው‼
እንደ ኸዲጃ ራሷን ሙሉ በሙሉ ባይሆንም፣ ግማሹን መሆን ቢያቅትም ግን ግን አርአያ አድርጎ በመያዝ ከዘመኑ ካሉት ሰዎች አመለካከት በመውጣት ቀደምቶችን ለመምሰል ጥረት በማድረግ ላይ ቢዚ የሆነ ሰው ጋር መጣር ለአኼራ ትልቅ ስንቅ መሰነቅ ሰበብ መያዝ ነው‼
ከዚህ በተቃራኒ ከሆነ ግን እንደው ከጊዜ ብዛት ከትግል በኋላ አሏህ የተሻለ ነገር አምጥቶ መቀየር መስተካከል አለ እንል ካልሆነ በስተቀር ቁሞ መቅረት የተሻለ ነው‼
⑦ከስህተት መታረም
👉 የሰው ልጅ ሲባል ፍፁም አይደለም‼ ስህተት መሳሳት አለ‼ ነውር የሚሆነው መሳሳት ሳይሆን ከስህተታችን አለመታረም ነው‼
ስህተታችንን ልክ እንደ መስታወት አጎልተን የምናይበት ሰበቡ ማንኛውም ሙስሊም ወንድም እና እህት ከመሆኑ ጋር ግን ብዙዎቹን በደንብ አብጠርጥሮ ስር ሰደድ በሆነ መልኩ ራሳችንን አይተን የምንፈትሸው በትዳር አጋር አማካኝነት ነው‼
ለምን ቢባል ብዙ ጉድለቶች፣ ጥፋቶች፣ ስህተቶች፣ ነውር ነገራቶች ሊኖሩብን ይችላሉ‼
1,ጥቂቱን ካልሆነ በስተቀር ብዙውን ሌሎች ሰዎች ሊያውቁብን አይችሉም የትዳር አጋር እንጂ
2,ጉድለቶቻችንን ከምን አንፃር የተከሰተ እንደሆነ አውቆ
ለጉድለታችን መሙሊያ በቂ እና አጥጋቢ መፍትሄ የሚያስቀምጥልን ሰው ልክ እንደ ትዳር አጋር የሆነ የለም‼
3,እኛም ጉድለቶቻችን ለመሙላት ነው ብሎ ከሚመክሩን ሰዎች ውስጥ
ድክመታችንን ሰበብ በማድረግ ቅስማችንን ሊሰብረን፣ ዝቅ አድርጎ በንቀት ሊያየን፣ በህይወታችንን ሊጫወትብን ሳይሆን
የእውነት የእኛን የተሻለ ደረጃ ደርሶ መገኘት ፈልጎልን ነው ብለን የምናምነው ሰው የለም የትዳር አጋር ቢሆን እንጂ
ምክንያቱም ለጋራ እድገት ሲባል .....
ግን የትዳር አጋር አመራረጥ መስፈርት በሸሪዓዊ መልኩ ተደርጎ ከተስተካከለ
በመካከል ላይ ወጣ ያሉ ሀያዕ፣ እዝነት እና ፍቅር ያልተላበሱ አጉል ባህሪያቶች ከተወገዱ ነው‼
⑧በረካ ለማግኘት
👉 ይህ ሲባል ብዙ ሰው ኧረ የምን በረካ እንደው ትዳር ይዤ ወጪ እዛ ላይ
በማወጣው ነገር ደግሞ በረካ አግኝቼ በተብቃቃሁ‼
ጭራሽ ኢባዳ ላይ ተዳከምኩ‼ ትሉ ይሆናል‼
ይህንን መሰረት አድርጋችሁ ተንተርሳችሁ ትዳር በረካ አያስገኝም ከማለት በፊት ዘወር በማለት ቅድሚያ ራስን መፈተሽ እና በደንብ ማየት ማስተዋል አለብን‼
ይህ የሆነበት ምክንያት
1,በመህር መብዛት
በረካ ያለው ትዳር
መህሩ የቀለለው ነው‼
ይህ ማለት ሰለፍይ እህቶቻችንን በአውሬ እጅ ላይ ለመጣል መንገድ ማምቻቸት አይደለም‼
እንድሁም አውሬዎች እጅ ላይ ገንዘብ ሞልቷል‼
አሏህን ፈሪዎች ሚስኪኖችን ማባረር እና በአውሬዎች እጅ ከገቡ በኋላ መህሩን በመመለስ ለመውጣት ነገራቶችን ማክበድ ነው የሚሆነው‼
አሏህ ለመሳኪኖች ለድሆች ሊያከብራቸው በእጃቸው ላይ ያለችው ትንሽዬ ነገር ላይ በረካ በመጨመር እንዲበዛላቸው ያደርጋቸዋል‼
በተቃራኒው ደግሞ ሀብታሞች ዘንድ ብክነት፣ አለመርካትን ይሰልጥባቸዋል አሏህ የሰጣቸውን ኒዕማ በአግባቡ እስካልተጠቀሙበት ድረስ
2,የመብቃቃት ሂክማ ማጣት
👉ብዙ ሰዎች በትዳር አለም ሲኖሩ መረጋጋትን የሚያጡበት ጭንቀት ቢዚ የሚያደርጋቸው ለኢባዳ ጊዜ የሚጣበቡበት ምክንያት ውስጥ አንዱ ገቢ እና ወጪን ያመጣጠነ የመብቃቃት ሂክማ ማጣት ነው‼
ሽሮ ላይ ስኳር ጨምሩ‼
ለእንቁላል ጥብስ ስፕራይት አቅርቡ‼
ልጆቹን በአካፋ አጉርሱ‼ እየተባለ
ለኢባዳ ክፍት የሆነ ሰላማዊ ኑሮ መኖር ጀነት ካልሆነ ዱኒያ ላይ ለማሰብ ቀርቶ ለመመኘት ይከብዳል‼
🖇በአጭሩ ከተሞክሮዬ አለም በዚች 1ወር ከ19 ቀኔ እንኳ ሁሉንም መዘርዘር ባልችልም ዋና ዋና የምለውን እንደ ትምህርት መውሰጃነት ይጠቅማል ብዬ ስላሰብኩኝ አካፍያችኋለው‼
ሌሎችም ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች ሊኖሩ ይችላሉ‼
ከውርቅያኖስ በሻይ ማንኪያ ያክል ኧረ በመርፌ ቀዳዳ ያክል ነው የጠቀስኩላችሁ‼
ገና ገና ያልተደረሰበት ኒዕማ ብዙ አለ‼ የተደረሰበትንም ዘርዝሬው አላልቅ ብሎኛል እንኳን ሌላ ልጨምር‼
ብቻ ብቻ እኔን መሰል ትዳርን ሲሸሽ የነበረ ሚስኪን ባይሆን መስፈርቱን ነፍሲያ በምትወደው ሳይሆን ሸሪዓዊ በሆነ መልኩ አድርጎ
ከዚያም ነፍሲያው ያልወደደችውን ነገር ሳትወድ በግዴታ እንድትወድ በማድረግ ለገባበት ሰው አሏህን ለማምለክ ሰላማዊ እና ምቹ መፍትሄ አበጅቷል አህባቢ‼
ይህንን መልዕክት ሳጋራችሁ ለትዳር ቅስቀሳ አስቤ
ከዛ ሰውን ወደ ትዳር የሚስቡ ፅሁፎችን ድርድር ሳይሆን
መጀመሪያ ወደ ትዳር የሚስቡ ኒዕማችን እና የአሏህ ጥበብ አየሁ
ከዛ ወደ ትዳር ቅስቀሳ ገፋፍቶኝ አጋራኋችሁ‼
👉ላጤ ሆይ‼ የምልህ ነገር ቢኖር
1,መስፈርትህን በሸሪዓዊ መልኩ አድርግ በነፍሲያህ እንዳትወስን‼ ያለበለዚያ ቁመህ ቅር‼
2,ከባለ ትዳሮች ተሞክሮ ትምህርት ውሰድ‼ የሚጠበቅብህን ሀላፊነት፣ ግዴታ፣ ህይወት እወቅ‼
3,ስለሚገጥምህ ኒዕማ ማመስገን እና በዚክር፣ በዱዓ፣ በኢባዳ፣ በሶብር፣ በፍቅር፣ በእዝነት፣ በፅናት፣ በጀግንነት ለመኖር ራስህን አዘጋጅ‼
🖌 اخوكم ضغير الفقير إلى الله طالب العلم ومحب الدعوة السلفية
بن علي الحبشي الأثري وفقني الله وإياكم
🖋 የእናንተው ታናሽ ወንድም አሏህ መልካሙን ነገር ሁሉ ለእኔም ለእናንተም ሁላችንንም ይግጠመንና
📆 29/05/2017 ሀሙስ
📅 06/02/2025 Thursday
📆 ٠٧/٠٨/١٤٤٦ (ሀሙስ) الخميس⌚️ 04:55 (ከረፋዱ)
🛣 ደሴ/ወሎ, ኢትዮጵያ📲 አጠቃላይ ፕሮግራሞቻችንን በሶሻል ሚዲያ ለመከታተል
🖥 በTelegram Channel
🔗https://t.me/Al_Burhan_Islamic_Studioo/5432