Awtar Express አውታር


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


በቻናሉ
#ፈጣን ፥#ትኩስ #ወቅታዊ እና #አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል
🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
Get updated information on our Channel
Share For Your Friends
ለማንኛውም ሀሳብ፣አስተያየት፣ጥቆማ እና ማስታወቂያ ለ ማሰራት ከ ስር ባለው ሊንክ ላይ ይፃፉልን ።
@awtarex

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


በአዲስ አበባ በሬክተር ስኬል 5 ሆኖ የተመዘገበ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ተሰማ

በአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ ምሽት 2 ሰዓት አካባቢ በሬክተር ስኬል 5 ሆኖ የተመዘገበ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ተሰምቷል፡፡

በአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት በአዲስ አበባ ተደጋጋሚ የመሬት ንዝረት መከሰቱን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶ/ር ኤሊያስ ሌዊ ለ EBC DOTSTREAM አረጋግጠዋል።

በዚህ ሳምንት በአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ በተደጋጋሚ እየተከሰተ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ኤሊያስ፤ ምሽቱን በሬክተር ስኬል 5 ሆኖ የተመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ በአዲስ አበባ በተደጋጋሚ መሰማቱን ተናግረዋል።

በአካባቢው ያለው የቅልጥ ዓለት ድንጋይ (ማግማ) እንቅስቃሴ አሁንም በመቀጠሉ የመሬት መንቀጥቀጥ በተደጋጋሚ እንዲከሰት ማስቻሉን ዶ/ር ኤሊያስ ጨምረው ገልጸዋል።


አል-ሲሲ ምን እያሉ ነው ?

ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ ከባህር በር ጋር በተያያዘ የመግባቢያ ስምምነት ከተፈራረሙ ማግስት አንስቶ ከሶማሊያው መሪ ጋር እየተደዋወሉ እና እየተገናኙ ፦
" ° አይዟችሁ እኛ አለን ፤
  ° ከፈለጋችሁ ወታደርም እንልካለን ፣
  ° የጦር መሳሪያ ድጋፍም ይኸው፣
  ° በሰላም ማስከበርም እንሳተፋለን ፣
  ° እናተን ማንም እንዲነካ አንፈቅድም " እያሉ ሲለፍፉ የከረሙት የግብጹ መሪ አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ አሁን ደግሞ የአንካራውን ስምምነት " በቅርበት እየተከታተልን ነው ፤ መረጋጋትንም ሊያመጣ ይችላል " የሚል ዲስኩር ይዘው ብቅ ብለዋል።

ድሮውንም የኢትዮጵያ ነገር አይኗን የሚያቀላው ግብፅ ከመግባቢያ ስምምነቱ  (MoU) በኃላ ስለ ኢትዮጵያ ብዙ አሉታዊ ነገር ስታወራ ፣ የማጠልሸት ስራ ስትሰራ ነበር የከረመችው።

ትላንት የግብፁ መሪ አል-ሲሲ በቅርብ ኢትዮጵያ መጥተው ከነበሩትና የኢትዮጵያ የባህር ባር ጥያቄን በይፋ ከደገፉት የፈረንሳዩ ፕሬዜዳንት ማክሮን ጋር የስልክ ውይይት አድርገው ነበር።

በዚህም ወቅት ፥ አል ሲሲ በቱርክ አሸማጋይነት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የፈረሙትን ስምምነት ጠቅሰው " በቅርብ እየተከታተልን ነው ፤ ስምምነቱ በአፍሪካ ቀንድ ፀጥታ እና መረጋጋት ሊያመጣ ይችላል " ሲሉ ተናግረዋል።

" ይህ ስምምነት በአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት እንደሚያመጣ ተስፋ አለኝ ዓለም አቀፍ ሕግን ተከትሎ ሊሆን ይችላል። በአፍሪካ ቀንድ ያለው መረጋጋት እና የግብፅ ብሔራዊ ጥቅምት የተሳሰሩ ናቸው " ሲሉ እንደገለጹም ተነግሯል።

አል-ሲሲ " ለሶማሊያ ድጋፍ ለማድረግ እንሰራለን ይህ ድጋፍ በሁለትዮሽ ግንኙነት አሊያም በአፍሪካ ሕብረት የሰላም አስከባሪ ሚሽን አማካይነት ነው " ብለዋል።

ግብፅ ፤ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ቁርሾ ውስጥ በከረሙበት ወራት ስታወጣ የነበረው መግለጫና ስታደርግ የነበረው እንቅስቃሴ ሀገራቱን ወደ መግባባትና ሰላም እንዲመጡ ለማድረግ ሳይሆን ነገሩን ለማጋጋል ፣ ለማባባስ ፣ የለየለት ቀውስና ጦርነት እንዲፈጠር ለማድረግ የታስበ እንደሆነ አመላካች እንደነበር ብዙዎች የሚገልጹት ነው።

#Ethiopia🇪🇹




Forward from: Mollalgn Yosef
#ዶክተር_ደጀኑ_የፀዳው

የሸጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር
#በጉበት_ቫይረስ_ተጠቅቶ በአገር ውስጥ ሕክምና ሊሻለው ባለመቻሉ ውጭ አገር ሂዶ እንዲታከም የሕክምና ቦርዱ ወስኗል።
በውጭ #የጉበት_ንቅለ_ተከላ ሕክምና ለማድረግ #ከ3_ሚሊዮን_ብር_በላይ ተጠይቋል።
ህበረተሰቡን በቅንነት እና በታማኝነት ሲአገለግል የነበረው ወንድማችን ዛሬ የወገኑን እገዛ ይፈልጋል። ስለሆነም ከታች በተዘረዘሩት የዶ/ር ደጀኑ የፀዳው ስም በተከፈቱ የባንክ አካውንቶች እምችሉትን ድጋፍ እንድታደርጉ በፈጣሪ ስም እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፡ 1000217153615
ዳሸን ባንክ፡ 5393386593011
አዋሽ ባንክ፡ 01320856564800
አማራ ባንክ፡ 9900000367517
አባይ ባንክ፡ 2131011149567010


12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በድጋሚ ለሚፈተኑ ተፈታኞች በራሳቸው የሚመዘገቡበት አድራሻ ይፋ ሆነ‼️
12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በድጋሚ የሚፈተኑ ተፈታኞች በራሳቸው የሚመዘገቡበትን አድራሻ https://register.eaes.et/Online በመጠቀም በበየነ መረብ መመዝገብ እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

ይህ የበይነ መረብ ምዝገባ መተግበሪያ ራስ አገዝ (self services ) ሲሆን ተመዝጋቢዎች የሚፈልጉትን ድጋፍ በመጠየቅ ከማዕከል ማግኘት እንደሚችሉ አስታውቋል።

ከዚህ መልዕክት ጋር የተያያዙ መረጃዎች ተመዝገቢዎች በቀላሉ መመዝገብ እንዲችሉ አጋዥ ስለሆኑ እንዲጠቀሙባቸው አሳስቧል።


#አዲስአበባ #አሶሳ

➡️ " በስራ ዘመን ቆይታዬ ይህን ያህል ክብደት የሚመዝን ልጅ ሲወለድ የመጀመሪያው ነው " - ዶ/ር ረታ ትዕዛዙ (ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል

👉 " የ3 ቀን ጨቅላ ህፃን አንገቷ ላይ በአፈጣጠር ትልቅ እብጠት ይዛ የተወለደች ቢሆንም የተሳካ ቀዶ ህክምና ተደርጎላታል አሁን በተሻለ የጤና ሁኔታ ላይ ናት " - አሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል


በአዲስ አበባ ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ቤቴልሄም አመኑ የተባለች እናት 6 ኪሎ ግራም የሚመዝን ወንድ ልጅ በተደረገላት የቀዶ ህክምና በሰላም ተገላገለች።

የሆስፒታሉ የማህፀን ስፔሻሊስት እና የዲፓርትመንት ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ረታ ትዕዛዙ ለኢቢሲ በሰጡት ቃል " በስራ ዘመን ቆይታዬ ይህን ያህል ክብደት የሚመዝን ልጅ ሲወለድ የመጀመሪያው ነው " ብለዋል።

ልጆች ከ5 ኪሎ በላይ ሆነው ሲወለዱ የሚደረግላቸው ህክምና መኖሩን የገለጹት ዶ/ር " ለልጁ የህክምና ክትትል እየተደረገለት ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

በሌላ መረጃ በአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል የተሳካ ቀዶ ህክምና ተደርጓል።

የ3 ቀን ጨቅላ ህፃን አንገቷ ላይ በአፈጣጠር ትልቅ እብጠት (Bilateral huge cystic hygroma) ይዛ የተወለደች ስትሆን  በእብጠቱ ምክንያት ጡት መጥባትም ሆነ እንደ ልቧዋ መተንፈስ አትችልም ነበር።

በ13/4/17 ዓ/ም በሆስፒታሉ የተሳካ ቀዶ ህክምና ተደርጎላት አሁን በተሻለ የጤና ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ ተገልጿል።

አሁን እንደልቧ መተንፈስ ጡት መጥባትም ጀምራለች ተብኳል።

በህክምናው ላይ የተሳተፉ ባለሞያዎች ፦
🙏 Surgeons ፦ ዶ/ር ሮቤራ ተሾመ እና ዶ/ር መብራቴ ወ/መድህን
🙏 Anaesthesiologist ፦ ዶ/ር ሲሳይ እብስቱ
🙏 Anesthesia team: ደመቀ ወ/ኪዳን፣ ተሰፋዬ አሰፋ እና ሰለሞን አዳሙ
🙏 Scrub Nurse ፦ሲ/ር ሳይሽልዋል ወርቁ (ቹቹ)
🙏 Circulator Nrs ፦ አልሃጅ ሀሰን እንደሆኑ ሆስፒታሉ አሳውቋል።




#ለጥንቃቄ

ቴሌግራም ላይ የሚላኩላችሁ ሊንኮች ከመረጃ መንታፊዎች ሊሆን ስለሚችል ከማታዉቁት ሰዉ የሚደርሳችሁን የቴሌግራም ሊንኮች እንዳትከፍቱ - ኢንሳ ‼️


ዛሬ ማለትም ታህሳስ 17 /2017 ዓ.ም ጀምሮ ብዙ የቴሌግራም አካውንቶች ከላይ በተጠቀሰው የማስገሪያ (phishing link) እና ሌሎች ተጨማሪ ማስገሪያዎች አማካኝነት መረጃዎች እየተመዘበሩ ስለሆነ ከማንኛውም የቴሌግራም ተጠቃሚ (ከምታውቁትም ይሁን ከማታውቁት ) ግለሰብ ሊንክ ቢላክላችሁ መክፈት እንደሌለባችሁ እና ወዲያውኑ እንድታጠፉት እናሳስባለን‼️

©ኢንሳ


ኤርትራ ከሶማሊያ ጋር ያላትን ዲፕሎማስያዊ ግኑኙነት ልታቋርጥ እንደምትችል ገለፀች

ኤርትራ በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል ተፈጥሮ የነበረውን አለመግባባት ለመፍታት በቅርቡ በቱርክ አደራዳሪነት የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ ከሶማሊያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን ልታቋርጥ እንደምትችል ገልፃለች ሲል ሶማሊያ ጋርድያን ዘግቧል።

ቢቢሲ ሶማሌ እንደዘገበው ከሆነ ደግሞ የአስመራው መንግስት ስምምነቱ “በጥድፍያ የተፈፀመና አሻሚ ነው ሲል ነቅፎታል።የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ አብዱልቃድር ኢድሪስ ሶማሊያ እንደ አንድ ሉዓላዊ ሀገር ከውጭ ሀገራት ጋር ዲፕሎማሲያዊ ስምምነቶችን የመፈፀም መብት ቢኖራትም ሶማሊያ በችኮላ ስምምነቱን ትቀባለለች የሚል ሀሳብ በኤርትራ በኩል እንዳልነበረ ገልፀዋል።

ኢድሪስ በመቀጠልም የኢትዮጵያ ፍላጎት በሶማሊያ የንግድ ወደብ በማረጋገጥ ላይ ሳይሆን በቀይ ባህር ዳር ወታደራዊ የባህር ኃይል ምሽግ ማቋቋም ነው ብሏል። ሶማሊያ የኢትዮጵያን እንዲህ አይነት ስትራቴጂካዊ መሰረት ለማግኘት ያነሳችውን ጥያቄ ከተቀበለች ኤርትራ እንደ ትልቅ የደህንነት ስጋት እንደምትቆጥረው በማስጠንቀቅ ይህም ከሶማሊያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደገና እንድታጤን ያስገድዳታል ብሏል። 

በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል የተደረገው ስምምነት በቱርክ ግፊት በችኮላ የተፈፀመ ስምምነት ነው ያሉ ሲሆን በበርካቶች ዘንድ ሰፊ ቅሬታን ፈጥሯልም ብለዋል።
======================


ደቡብ ሱዳን ለፓርላማ አባላት ያለደመወዝ የአራት ወራት እረፍት ሰጠች፡፡

ጁባ በሱዳን በተከሰተው ጦርነት ምክንያት ነዳጇን ለዓለም ገበያ ማቅረብ አልቻለችም።

ይህም ከፍተኛ የበጀት ቀውስ ውስጥ ከቷት የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ ከተከፈላቸው 10 ወር አልፏቸዋል።

የበጀት እጥረቱን ለማስታገስ የምክር ቤት አባላት ያለደመወዝ የአራት ወር እረፍት እንዲያደርጉ የተወሰነ ሲሆን፥ የምክርቤት አባላቱ አስቸኳይ ጉዳይ ካጋጠመ ይጠራሉ ተብሏል።


የስራ ቅጥር ማስታወቂያ | የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ

ለቢሮው እና በስሩ ለሚገኙ ጤና ተቋማት የኮንትራት ሰራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር ታህሳስ 15 ቀን 2017 ዓ ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ለአስር ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ መመዝገብ የሚቻል መሆኑን የሚገልጽ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡
ሆኖም ለኮንትራት ሰራተኛ ቅጥር ማስታወቂያ በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ 03 (ሶስት) የስራ ቀናት ብቻ መሆኑን እየገለፅን ከዚህ በታች በተቀመጠው የስራ መደቦች ላይ መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 03 (ሶስት) የስራ ቀናት ውስጥ የህጻናት እንክብካቤ ሞግዚት ውጪ በኦላየን ብቻ በታች ባለው ማስፈንጠሪያ (ወይም ሊንክ) በመጠቀም መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

11 last posts shown.