Ayu Zehabesha-Official አዩዘሀበሻ


Channel's geo and language: Ethiopia, English


ትክክለኛው የአዩዘሀበሻ ቻናል ይህ ብቻ ነው❗
ቻናላችንን Join በማድረግ በቀላሉ ፈጣን መረጃዎችን ይከታተሉ።
የውስጥ መስመር👉 t.me/ayulaw

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, English
Statistics
Posts filter


እርምጃ የሚወስዱት ድሮኖች በአዲስ አበባ ሰማይ ላይ‼️
ዛሬ በአዲስ አበባ ሰማይ ላይ የድሮን ስምሪት የተደረገ ሲሆን ድሮኖቹ ቅኝት ያደርጋሉ፣ ወንጀለኛን ይለያሉ፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም እርምጃ ይወስዳሉ ተብሏል።
=======================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


ኮስት ሼሪንግ‼️
መንግስት በዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ የወጪ መጋራት ክፍያ መጠን ጭማሪ አድርጓል‼️
መንግሥት የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች በወጪ መጋራት ፖሊሲ የሚከፍሉትን ክፍያ እስከ አምስት ዕጥፍ ገደማ አሳድጓል።
የወጪ መጋራት ክፍያ የተጨመረው፣ የአንድ ተማሪ የቀን የምግብ በጀት ከ22 ብር ወደ 100 ብር መጨመሩን ተከትሎ ነው ተብሏል። በአዲሱ ጭማሪ መሠረትም፣ ለአራት ዓመት የዩንቨርሲቲ ቆይታ አንድ ተማሪ ይከፍለው የነበረው ከ25 ሺሕ ብር የማይበልጥ ክፍያ ወደ 120 ሺሕ ከፍ ብሏል። 35 ሺሕ ብር ገደማ ይከፍሉ የነበሩት አምስት ዓመት የሚማሩ የምህንድስና ተማሪዎች ደግሞ ወደ 150 ሺሕ ብር አካባቢ እንዲከፍሉ ይደረጋል። ትምህርት ሚንስቴር አዲሱን የወጪ መጋራት ተመን ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገና ባይልክም፣ በቅርቡ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተጠቅሷል።  
#አዩዘሀበሻ
=======================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


🌟 በ4 ዓመት ውስጥ 5 ሳይት ማስረከባችንን ያውቃሉ ?
✨ አዎ አሁን ደግሞ 6ኛ ፕሮጀክት የሆነው ሳርቤት ቫቲካን ኢንባሲ አጠገብ
Jenboro real estate
     በጊዜ ግቡ
የጋራ መጠቀሚያ ሙሉ በሙሉ የተማሟላለት፦
የከርሰምድር ውሀ
ባክአፕ ጀኔሬተር
ፓርኪንግ (4 ቤዝመንት)
ቴራስ
ጅም ስፓ እና የልጆች መጫዎቻ
15 ሊፍት እና 2 escaleter lift
electric charge station
Security camera ....
በዓል ምክንያት በማድረግ በ1% ቅደመ ክፍያ ሽያጭ ላይ ነን!!!
ሰፊ የካሬ አማራጭ  ከምቹ አከፋፈል ጋር

ባለሁለት  መኝታ
106 ካሬ =>125,610ብር
123 ካሬ => 145,755ብር
,136 ካሬ=> 161,160ብር

ባለ ሶስት መኝታ
150 ካሬ =>177,750ብር
157 ካሬ =>186,045ብር
176ካሬ =>208,560ብር
181 ካሬ =>214,485ብር

የሱቆች አማራጭ
ከ17 ካሬ  => 36,890ብር
38  ካሬ  =>82,460ብር
52  ካሬ =>112,840ብር
78  ካሬ =>169,260ብር
84  ካሬ  =>182,280ብር
125 ካሬ =>271,250ብር ብቻ
ልብ ይበሉ ከላይ የተጠቀሱት 1% ቅድመ ክፍያ ናቸው
ለበለጠ መረጃ +251960777779 ሀሎ ይበሉ
https://t.me/apartmentandshopinfo


የመሬት መንቀጥቀጥ አማራ ክልል ተከስቷል‼️
ዛሬ ለሊት 10:46 ላይ በሬክተር ስኬል 4.9 የሚጠጋ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል። ይህ የሆነው ደግሞ ከአዲስ አበባ 133 ኪሎ ሜትር ላይ፤ በአማራ ክልል ልዩ ስሙ አልዩ አምባ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ላይ ነው።
አዲስ አበባ ላይ ለረጅም ሰከንዶች የቆየ ንዝረት ተሰምቷል።
=======================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


#ቴምር ሪልስቴት
😱7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ ለሽያጭ ያወጣናቸው 3 ሳይቶች
🎯1,አያት ሳይታችን
        👉 2መኝታ 87ካሬ
        ሙሉ ክፍያ 4,976,400ብር
         👉 3መኝታ 107ካሬ
        ሙሉ ክፍያ 6.1ሚሊዮንብር
         👉 3 መኝታ 121ካሬ
        ሙሉ ክፍያ 6.9ሚሊዮን ብር
🎯2,ተክለሃይማኖት ሆስፒታል ፊት ለፊት
         👉3 መኝታ 113ካሬ
         10%ቅድመ ክፍያ 1ሚሊዮን ብር
          ሙሉ ክፍያ 10,961,000ብር
         👉3መኝታ 119ካሬ
        10%ቅድመ ክፍያ 1.1ሚሊዮን ብር
        ሙሉ ክፍያ 11,543,000ብር
         👉ቀሪውን 90% በ15 ዙር ከፍለው የሚጨርሱት
🎯3,ፒያሳ (ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት) ጀርባ
         👉1 መኝታ 66ካሬ=
         10% ቅድመ ክፍያ 693,000ብር
         ሙሉ ክፍያ 6,930,000 ብር
         👉2መኝታ 71ካሬ
        10%ቅድመ ክፍያ 745,000ብር
        ሙሉ ክፍያ 7,455,000ብር
         👉2መኝታ 93ካሬ=
       10% ቅድመ ክፍያ 1,044,000ብር
       ሙሉ ክፍያ 10,044,000ብር
        👉3መኝታ 130ካሬ
      10%ቅድመ ክፍያ 1,365,000ብር
      ሙሉ ክፍያ 13,650,000ብር
        👉ቀሪውን 90% በ17ዙር ከፍለው         የሚጨርሱት
        👉30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251939770177
     +251996856273


የሞት ማምለጫ‼️
አዲሱ ቴክኖሎጂ ሰዎች ከሞቱ በኋላ ዳግም ህይወት ሊዘሩ ይችላሉ በሚል የተፈጠረ ነው❗

አዲሱ የሞት ማምለጫ ቴክኖሎጂ ይሳካለት ይሆን?

የሰው ልጅ በየጊዜው ህይወትን ቀለል የሚያደርጉ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል።

በእስካሁኑ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች አስደማሚ እና ሊሆን አይችልም የተባሉ ፈጠራዎች በሰው ልጆች ተሰርተዋል።

ይሁንና እስካሁን ሞትን ማምለጥ የሚያስችሉ ፈጠራዎችን መስራት ያልተቻለ ሲሆን ቱሞሮ ባዮ የተሰኘ ኩባንያ ግን ባልተሞከረውን መንገድ እየሄደ ይገኛል።

ይህ ኩባንያ አንድ ቀን ይሳካልኝ ይሆናል በሚል መሞታቸው በሐኪሞች የተረጋገጡ ሰዎችን አስከሬን በማጠራቀም ላይ ነው።

የዚህ ኩባንያ ዓላማ ሰዎች ህይወታቸው ከላፈ በኋላ በበጎ ፈቃደኝነት አስከሬናቸውን እንዲሰጡት ካደረገ በኋላ ወደ ማቀዝቀዣ ቦታ ይወስዳል።

የአስከሬኑ ቅዝቃዜ ዜሮ ድግሪ ሴንትግሬድ ከደረሰ በኋላ አስከሬኑ በቅዝቃዜ እና በሌሎች ተፈጥሯዊ ምክንያቶች እንዳይበሰብስ የሚያደርግ የተለያዩ ኬሚካሎችን ተጠቅሞ ባለበት እንዲቆይ ያዱርጋል።

ኩባንያው ይህን የሚያደርገው ሟቾች ወደ ዳግም ህይወት መመለስ ይቻላል የሚል ዕምነት ስላለው እና ሰዎችም ረጅም እድሜ በህይወት የመኖር ፍላጎት አላቸው በሚል ነው።

ሰዎች ይህን አገልግሎት ለማግኘት 200 ሺህ ዶላር መክፈል የሚጠበቅባቸው ሲሆን አብዛኞቹ ከፋዮች ምን አልባት ቴክኖሎጂው ከሰራ ብለው የሚያምኑ ናቸው ተብሏል።

ከኩባንያው መስራች አንዱ የሆኑት ኢምል ኬንድዚዮራ ለቢቢሲ እንዳሉት ሀሳቡ የተጀመረው አንዲት ስዊድናዊ በልብ ህመም ህይወቷ አልፏል ተብሎ በማቀዝቀዣ ውስጥ ከቆየት ከሁለት ሰዓት በኋላ ዳግም ዳግም ህይወት መዝራቷን ተከትሎ ነው ብለዋል።

እንዲሁም የሞተ የአይጥ አዕምሮን በዚህ የማቀዝቀዝ ቴክኖሎጂ አማካኝነት ዳግም እንዲመለስ እና በቀዶ ጥገና መልክ በሌላ አይጥ ካይ ተገጥሞ መስራቱ እንደተረጋገጠም ተገልጿል።

ይህ ተስፋ ሰጪ ምልክት በሰዎች ላይ ሊሰራ ይችላል በሚል እየሞከርነው ነው የሚሉት የኩባንያው መስራች የደንበኞቻቸው ቁጥር እየጨመረ እንደሆነም ተናግረዋል።

በተለይም በኮሮና ቫይረስ ወቅት ሞት ከመቼውም ጊዜ በላይ ቅርብ መሆኑን ተከትሎ ከቫይረሱ መከሰት በኋላ የደንበኞቻቸው ቁጥር ጨምሯልም ተብሏል።

የአንድን የሰውነት አካል በቀዶ ህክምና ወደ ሌላ ሰው መተከት ህክምና ሲጀመር ሰዎች ብዙ ተገርመው ነበር የተባለ ሲሆን ምን አልባት ከ10 ወይም ከ100 ዓመት በኋላ የሞቱ ሰዎችን ዳግም ወደ ህይወት መመለስ ሊጀመር እንደሚችልም ተስፋ ተደርጓል::
አልዐይን
=======================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


ሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ግመል ስጋ ዋነኛ መዳረሻ መሆኗ ተገለጿል‼️
ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ 50 ቶን የግመል ስጋ ወደ ውጭ መላኳን ገልጻለች። ከተላከው ስጋም 3 00 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ገቢ እንደተገኘ  የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት አስታውቋል። የግመልስ ስጋው ዋነኛ መዳረሻው ሳውዲ አረቢያ ስትሆን ሌሎችም ሀገራት የኢትዮጵያ ግመል ስጋን ለመግዛት ፍላጎታቸው እየጨመረ እንደሆነ ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል።
=======================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


መታወቂያ‼️
በመዲናዋ ተቋርጦ የነበረው በመሸኛ መታወቂያ የመስጠት ሥራ በከፊል መጀመሩ ተገለጸ‼️
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና ነዋሪነት አገልግሎት ባለፉት ዓመታት አቋርጦት የነበረውን በመሸኛ የሚሰጥ የመታወቂያ አገልግሎት መጀመሩን አስታውቋል፡፡

"ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች መሸኛ ይዘው ወደ ከተማዋ የመጡ እና ከዚህ በፊት 6 ወር የነበረው አሰራር ወደ ሦስት ወር ዝቅ ካለ በኋላ፤ መስፈርቱን ያሟሉ ነዋሪዎች ለምን መታወቂያ ማግኘት አልቻሉም?" ለሚለው ጥያቄ

የኤጀንሲው የነዋሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ "ኤጀንሲው ከዚህ በፊት የነበሩ ውይይቶችን አጠናቆ መታወቂያ መስጠት ጀምሯል" ብለዋል፡፡ ነገር ግን ሥራዉ የሚሰራው በበይነመረብ ላይ ባለ ሲስተም በመሆኑ መቆራረጦች እንዲፈጠሩ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

አሐዱም የሲስተሙን ችግር ለምን መፍታት እና ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት ማስጀመር አልተቻለም? ሲል የጠቃቸው አቶ ዮሴፍ፤ "ሲስተሙ እንዳይቆራረጥ የማድረጉ ሥራ ከአገልግሎቱ ውጭ በሆነ አሰራር የሚሰራ በመሆኑ ነው" ብለዋል፡፡

ተቋሙ አሁን ባለው አቅም ልክ በኤጀንሲው በኩል የሚሰጡ አገልግሎቶች እተከናወነ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም መሸኛ የሚያስገቡ ሰዎችን መረጃ የማመሳከር እና ትክክለኝነቱን የማረጋገጥ ተግባር እንዳለም አያይዘው ጠቅሰዋል፡፡

አገልግሎቱ ከክፍለ ሀገር በመሸኛ የሚመጣን ነዋሪ በተመለከተ መረጃዎች ተጣርተው ወረፋ እየጠበቁ ካሉት ከ42 ሺሕ በላይ አገልግሎት ፈላጊዎች መካከል ትክክለኛ መረጃ ያላቸውን ከሕዳር አንድ ጀምሮ አስተናግዳለሁ ያለ ቢሆንም፤ አገልግሎቹን በጊዜው አለመጀመሩን አሐዱ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

ይህንንም አገልግሎት ለማስጀመር የተገልጋዮችን ማስረጃ የማጣራቱ ሥራ እየተሰራ ቢሆንም፤ በተባለበት ቀን ለማስጀመር የሲስተም ብልሽት እንዳጋጠመው እና አዳዲስ ተመዝጋቢዎችን አሻራ መውሰድ ባለመቻሉ እንደዘገየ ማስታወቁም አይዘነጋም፡፡
አሀዱ
=======================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


ጠቃሚ መረጃ‼️
ሰሞኑን የፀደቀው የንብረት ማስመለስ አዋጅ 1364/2017 በግልጽ እንደሰፈረው ገዢ የሆነ ወገን የገዛውን ንብረት በተመለከተ ሻጭ ያንን ንብረት ሲያፈራ የገቢው ምንጭ ምን ነበር፣እንዴት አፈራው፣ያፈራው ንብረት በህጋዊ መንገድ ነወይ? የሚለውን ማረጋገጥ እንደሚገባ በግልጽ መቀመጡን አዩዘሀበሻ ተመልክቷል።
ስለዚህ ህጋዊ መሆኑን ማለትም ቤቱ በስሙ መሆኑን/ካርታ እና ፕላን በስሙ መሆኑን/ ወይንም የተሽከርካሪ ንብረት ሊብሬ በስሙ መሆኑን ብቻ አይቶ ግዢ መፈፀም በገዢ ላይ ኪሳራ ሊያስከትል እንደሚችል ይደነግጋል።
ስለዚህ ገዢ የሆነ ማንኛውም ግለሰብ/ቡድን/ንብረቱን ከመወረስ ለመዳን ምን ማድረግ አለበት?
ሻጭ የሚሸጠውን ንብረት እንዴት አፈራው?የገቢ ምንጩ ምን ነበር? አሰራሩ እንዴት ነበር? ለመንግሥት የሚከፍለው የታክስ እና የግብር መጠን ካፈራው ንብረት አንፃር ምን ይመስላል? የሚለውን ማረጋገጥ እንደሚገባ ያስገድዳል።
በመሆኑም ካርታ እና ፕላን እንዲሁም የተሽከርካሪ ሊብሬ ብቻ አይተን ግዢ መፈፀም በገዢ ላይ የሚያስከትለው ኪሳራ መኖሩን መገንዘብ ያስፈልጋል።
አዩዘሀበሻ አዋጁ አንቀጽ 25 ላይ እንደተመለከተው ከሆነ "በወንጀል የተገኘ ንብረት ከሆነ የተገዛው ፍሬ መንግሥት ይህንን በወንጀል የተገኘ ንብረት ግዢ ፈፅሞ ስሙ ወደ ገዢ ቢዞርም መንግሥት እንደሚወርሰው" በግልጽ ተቀምጧል።
በኋላ ክርክር ላይ የቅን ልቦና ገዢ ነኝ በሚል የሚቀርቡ መከራከሪያዎች ሆን ብሎ ንብረቱን ለመደበቅ የተጠቀማችሁበት ስልት ነው" በሚል በአዋጁ ላይ የተቀመጠ ሲሆን ንብረቱ ከመወረስ እንደማይድን አዩዘሀበሻ ተመልክቷል።
ይህ አዋጅ 10 አመት ወደ ኋላ ተመልሶ ተግባራዊ የሚሆን ነው(አዩዘሀበሻ)።
=======================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


#ቴምር ሪልስቴት
😱7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ ለሽያጭ ያወጣናቸው 3 ሳይቶች
🎯1,አያት ሳይታችን
        👉 2መኝታ 87ካሬ
        ሙሉ ክፍያ 4,976,400ብር
         👉 3መኝታ 107ካሬ
        ሙሉ ክፍያ 6.1ሚሊዮንብር
         👉 3 መኝታ 121ካሬ
        ሙሉ ክፍያ 6.9ሚሊዮን ብር
🎯2,ተክለሃይማኖት ሆስፒታል ፊት ለፊት
         👉3 መኝታ 113ካሬ
         10%ቅድመ ክፍያ 1ሚሊዮን ብር
          ሙሉ ክፍያ 10,961,000ብር
         👉3መኝታ 119ካሬ
        10%ቅድመ ክፍያ 1.1ሚሊዮን ብር
        ሙሉ ክፍያ 11,543,000ብር
         👉ቀሪውን 90% በ15 ዙር ከፍለው የሚጨርሱት
🎯3,ፒያሳ (ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት) ጀርባ
         👉1 መኝታ 66ካሬ=
         10% ቅድመ ክፍያ 693,000ብር
         ሙሉ ክፍያ 6,930,000 ብር
         👉2መኝታ 71ካሬ
        10%ቅድመ ክፍያ 745,000ብር
        ሙሉ ክፍያ 7,455,000ብር
         👉2መኝታ 93ካሬ=
       10% ቅድመ ክፍያ 1,044,000ብር
       ሙሉ ክፍያ 10,044,000ብር
        👉3መኝታ 130ካሬ
      10%ቅድመ ክፍያ 1,365,000ብር
      ሙሉ ክፍያ 13,650,000ብር
        👉ቀሪውን 90% በ17ዙር ከፍለው         የሚጨርሱት
        👉30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251939770177
     +251996856273


ታክስ‼️
የንብረት ታክስ ማን ስንት ይከፍላል?
ዜጎች የሚከፍሉት የግብር መጠን የሚወሰነው ባለፈው ታኅሳስ በጸደቀው የሪል እስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይት እና ግመታ አዋጅ መሠረት ነው። ይኸ የግብር አይነት አንድ ንብረት ከዓመት ዓመት በሚያሳየው የዋጋ ለውጥ ላይ የሚጣል ነው።
በአዋጁ መሠረት የንብረት ታክስ የሚከፈልበት ከአንድ ንብረት የገበያ ዋጋ 25 በመቶው ብቻ ነው። ይሁንና የገንዘብ ሚኒስቴር በጥናት ላይ በመመሥረት ታክስ የሚከፈልበትን ዋጋ ከፍ ወይም ዝቅ የማድረግ ሥልጣን ተሰጥቶታል።
አቶ ደሳለኝ ወዳጄ “ለቤት ከ0.1 በመቶ እስከ 1 በመቶ፤ ለመሬት ደግሞ ከ0.2 በመቶ እስከ 1 በመቶ” የንብረት ታክስ እንደሚከፈል አስረድተዋል። “የትኛውም ክልል ወይም የከተማ አስተዳደር ሲጀምር ከ0.1 በመቶ ነው” ያሉት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ “በአራተኛው ዓመት ላይ የመጨረሻው ላይ መድረስ አለበት” ሲሉ ሒደቱን አስረድተዋል።
ጭማሪውን “የሕዝቡን ፍላጎት፣ ስሜት እና አጠቃላይ አቅም” በማጥናት እና በመመካከር የመወሰን ሥልጣን ክልሎች ተሰጥቷቸዋል። አቶ ደሳለኝ ወዳጄ የንብረት ባለቤቶች የሚከፍሉት የግብር መጠን ምን ያክል እንደሚሆን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበ ማብራሪያን እየጠቀሱ ሲያስረዱ “20 ሚሊዮን ብር የሚገመት ቤት ያለው ሰው በዓመት አንድ ጊዜ ክፍያው 5,000 ብር ነው ሊሆን የሚችለው” ብለዋል።
10 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው ቤት 2,500 ብር፤ 5 ሚሊዮን ብር የሚገመት ቤት 1,250 ብር፤አንድ ሚሊዮን ብር የሚገመት ቤት ያለው 250 ብር ሊከፍል እንደሚችል ተናግረዋል። የንብረት ባለቤቶች ክፍያውን በአንድ ጊዜ ወይም ሁለት ጊዜ ማከናወን ይችላሉ።
የፌድራል እና የክልል መንግሥታት ተቋማት የንብረት ታክስ አይከፍሉም። “ለሕብረተሰቡ ነጻ የማኅበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች ለዚሁ አገልግሎት የሚጠቀሙበት ቦታ እና ሕንጻ” ከንብረት ታክስ ነጻ ሆኗል። የኃይማኖት ተቋማት ለአምልኮ እና ለመካነ-መቃብር አገልግሎቶች የሚጠቀሙባቸው ቦታዎች እና ሕንጻዎችም ተመሳሳይ ዕድል አግኝተዋል።
አዋጁ “ዝቅተኛ ገቢ ላለው አንድ ቤተሰብ በመኖሪያነት አገልግሎት እየሰጠ ያለ የመኖሪያ ሕንጻ” የንብረት ታክስ እንደማይከፈልበት ይደነግጋል። ይሁንና “ዝቅተኛ ገቢ” የሚለው መመዘኛ በምክር ቤቱ አከራካሪ ነበር።  
“አዲስ አበባ ላይ ያለ ዝቅተኛ ገቢ ከኑሮ ውድነት እና ከቤት ኪራይ ጋር ተያይዞ ወደ ክፍለ ሀገር ሲሔድ ከፍተኛ ሊሆን ይችላል” ያሉት የብልጽግና ፓርቲ አባል የሆኑት አለሙ ጎንፋ “ዝቅተኛ ገቢ ምንድነው?” ሲሉ ጠይቀዋል። “ጡረተኛ፣ ከ60 ዓመት በላይ ያለ ሰው፤ ገቢ የሌለው አይክፈል ከተባለ” በግልጽ ማስቀመጥ እንደሚሻል የመከሩት አቶ አለሙ “የማይከፍሉ” የንብረት ባለቤቶች በአዋጁ በግልጽ ካልሰፈረ “ዝቅተኛ” የሚለው መመዘኛ “መለኪያ የለውም” ሲሉ ሞግተዋል።
አዩዘሀበሻ
=======================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


“መፈንቅለ መንግስትን አታስቡ!” -ሌ/ጀነራል ዓለምሸት ደግፌ‼️
የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ አማካሪ ‹‹መንግስት በትጥቅ ትግል ሲገረሰስ መከላከያ ገለልተኛ ነው በሚል መርህ ምክንያት ዝም ብለን አናይም›› ሲሉ ጠንከር ያለ መልዕከት አስተላልፈዋል፡፡

ይህን መልዕክት ያስተላለፉት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ወታደራዊ አማካሪና የተኩስ አመራር ኃላፊ ሌተናንት ጀነራል ዓለምሸት ደግፌ ናቸው፡፡

‹‹ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱ አለ፤ ሠራዊቱም የተደራጀው ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን ለመጠበቅ ነው፡፡ ሥርዓቱም ማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ወደ ስልጣን የሚመጣው በምርጫ ነው ይላል፡፡ስለዚህ በምርጫ ያሸነፈው ኃይል ሀገሪቱን መንግስት ሆኖ ለማስተዳደር መብት ይኖረዋል፡፡ በዚያ ጊዜ ደግሞ እንደ መከላከያ ያለው ተቋምም ለመንግስት ይታዘዛል፡፡ መንግስት የሚሰጠውን ግዳጅ ይፈጽማል፡፡›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡

‹‹ አልያ በምርጫ ሳይሳካልህ ሲቀር ወይም ደግሞ የምርጫው ሂደት አልጣመኝም ባልክ ቁጥር ኃይል እያደራጀህ በትጥቅ አማራጭነት ወደ ሥልጣን የሚመጣ እንቅስቃሴ ካለ እንደ ኢትዮጵያ ላለ ሀገር ቀርቶ ለማንኛውም ሀገር የሚበጅ አካሄድ አይደለም ብለዋል፡፡ ጨምረውም የሕዝብን፣ የወጣቱን ሕይወት የሚቀጥፍ ስለሆነ፣ ንብረቱን የሚያወድም፣ ሀገሪቷን ከዕድገት ወደኋላ የሚመልስ ስለሆነ መከላከያ ይህንን መቆጣጠር ይኖርበታል ›› ሲሉ ተደምጠዋል።
#አዩዘበሀሻ
=======================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


ሙሉ ግንባታው ሊጠናቀቅ 2.4 በመቶ ብቻ የቀረው ታላቁ የ #ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ 80 ቢሊዮን ብር ያስፈልገዋል ተባለ‼️
የዛሬ 14 ዓመት ገደማ ለግንባታው የመሰረት ድንጋይ ሲጣል 80 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ነበር የተገለፀው።

አሁን ላይ ሙሉ ግንባታው ሊጠናቀቅ 2.4 በመቶ ብቻ የቀረው ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ቀሪ ስራዎች ለማጠናቀቅ 80 ቢሊዮን ብር ያስፈልገዋል ያስፈልገዋል መባሉን ሸገር ሬድዮ ዘግቧል።

ግንባታው 97.6 በመቶ እንደደረሰና ጥቂት የማጠናቀቂያ ስራዎች ብቻ እንደቀሩት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ የፕሮጀክት ፅህፈት ቤት ተናግሯል ተብሏል፡፡

ከ14 ዓመት አመታት በፊት የግንባታው መሰረት ድንጋይ ሲጣል 80 ቢሊዮን ብር ያስፈልገዋል ተብሎ የተጀመረው የታላቁ ህዳሴ ግድብ፤ የ2.4 በመቶ ስራም ቀርቶት ለምን 80 ቢሊዮን ብር እንዳስፈለገ በብዙዎች ጥያቄን ጭሯል።

በጉዳዩ ዙሪያ የህዳሴ ግድብን የቦንድ ሽያጭ ሲከውን የቆየውን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የካፒታል ገበያ ዳይሬክቶርት ዳይሬክተር አቶ ዳዊት አማረ ከሸገር ሬድዮ ለቀረበላቸው ጥያቄ የግንባታ ስራው በተለያ ደረጃ ስለሚመራ ስለዚህ ጉዳይ ፕሮጀክቱን የሚመሩት የስራ ሃላፊዎች ናቸው የሚያውቁት ብለዋል፡፡

ይሁንና ልማት ባንክ የቦንድ ሽያጭ ላይ እንደመሳተፉ እስካሁን ከህዝቡ ከ20.2 ቢሊየን ብር በላይ መዋጣቱን መናገር እንችላለን ብለዋል፡፡ ለማጠናቀቂያ ስራው ከሚያስፈልገው ገንዘብ ልማት ባንክ 10 ሚሊዮን ብር መስጠቱንም አቶ ዳዊት ተናግረዋል፡፡

ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤቱ በበኩሉ በዚህ ዓመት እስከ 1.6 ቢሊዮን ብር ከህዝቡ ለመሰብሰብ አቅዶ እየሰራ መሆኑን ተናግሯል፡፡

በዚህም ባሳለፍነው ዓርብ 110 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታስቦ በተካሄደ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ከፋናንስ ተቋማት መሰብሰብ የተቻለው 25.9 ሚሊዮን ብር ብቻ መሆኑን ዘገባው አመላክቷል፡፡
=======================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


ግዳጅ‼️
ሠላም #አዩዘሀበሻ የከበረ ሠላምታችንን እያቀረብን  " በቀን 05/05/2017 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ወደ ቦንጋ ከ65 ሰው በላይ አሳፍሮ ሲሄድ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ (TATA) መኪና ከጅማ አልፎ ሰቃ ከተማ ሊገባ ትንሽ ሲቀረው ትንሽዬ ጫካ ውስጥ የኦሮሚያ ትራፊክና መንገድ ትራንስፖርት መኪናው ለግዳጅ ይፈለጋል በማለት ህዝቡን ጫካ አስወርደው መኪናውን ይዘው ሄዱ። ብር ያለው አራት መቶ ከፍሎ በተለያየ ትራንስፖርት ሄደ ብር የሌለው እዛው ጫካ ውስጥ ቀርተዋል።
ከቢሮ ተጠርቶ የመጣው ሀላፊ ቢያንስ አራግፎ ይመለስ ብለን ስንጠይቀው አይመለከተንም የራሳችሁ ጉዳይ ግዳጅ ነው የሚበልጠው በማለት በሞተር ሳይክል እያሽከረከረ መኪናውን ይዞ ሄደ እንዲሁም ተሳፋሪዎቹ ለትራንስፖርት ከከፈልነው ብር ላይ የተወሰነ ብር ይመለስልን ብለን ጥያቄ ብናቀርብም አሽከርካሪና ረዳት አይቻልም የራሳችሁ ጉዳይ ብለው በማናውቀው ጫካ ውስጥ ጥለውን ሄዱ" ሲሉ ተሳፊሪ የነበሩ ሰዎች ጥቆማ አድርሰዋል።
አዩዘሀበሻ
=======================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


በአሜሪካ አዲስ የሰድ እሳት ተቀሰቀሰ‼️
በሎስ አንጀለስ የተቀሰቀሰውን የሰደድ እሳት ለማጥፋት እየታገለች ያለችው አሜሪካ በደቡባዊ #ካሊፎርኒያ ቬንቱራ ግዛት አዲስ ሰደድ እሳት ተቀስቅሶባታል።

“አውቶ ፋየር” የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሰደድ እሳቱ ሌሊት 7፡45 ሰዓት ላይ የተቀሰቀሰ ሲሆን በፍጥነት በሚጓዝ ነፋስ ታግዞ እየተስፋፋ  ይገኛል።

ሰደድ እሳቱ ከ2.02 ሄክታር መሬት በላይ ያቃጠለ ሲሆን፤ እሳቱን ለማጥፋት ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው።
Via:- CGTN
=======================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


ቆም ብሎ የነበረው ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ በድጋሚ እየተከሰተ ይገኛል።
ዛሬ ከደቂቃዎች በፊት ከምሽቱ 11:55 በሬክተር ስኬል 4.9 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ በመተሃራ መርቲ ተከስቷል።
ንዝረቱ በአዲስ አበባ ጭምር ተሰምቷል።
አዩዘሀበሻ
=======================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


ፀደቀ‼️
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በርካታ ትችቶችን ሲያስተናግድ የነበረውን #የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅን አፀደቀ‼️
👉ህዝቡ ዋጋ እየከፈለ ነው:-አባላቱ።
ቋሚ ገቢ ባላቸው ዜጎች ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ያሳድራል በሚል ስጋትና ትችት ሲቀርብበት የነበረው የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም ቀርቦ ጸደቀ።
በአዋጁ በተደነገገው መሰረት ለማንኛውም ንብረት የሚከፈለው ታክስ መጠን ከንብረቱ የገበያ ዋጋ ወይም ምትክ ዋጋ 25 በመቶ እንዲሆን ተደርጓል።
"ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው የከተማ ንብረት ዋጋ በበቂ ሁኔታ ታክስ እየተጣለበት ባለመሆኑ የመንግስት የገቢ ላይ እጥረትን አስከትሏል" ፤ "ይህም ሁኔታ በከተሞች ውስጥ ያለውን ያልተጣጣመ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ላይ አስተዋጽኦ አድርጓል" ሲሉ የዕቅድ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ በምክር ቤቱ ተገኝተው ለአባላቱ በሰጡት ማብራሪያ ገልጸዋል።

የፓርላማ አባላት በበኩላቸው ቋሚ ገቢ ባላቸው ዜጎች እና የመንግስት ሰራተኞች ላይ ከዚህ ቀደም የተጣሉ ታክሶች ሳይበቃ ላይ ሌላ ተጨማሪ ግብር እንዲከፍሉ መደረጉ ከፍተኛ ስጋት ይፈጥራል ሲሉ አሳስበዋል።
=======================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


የመሬት መንቀጥቀጥ  የሚስተዋልባቸዉ ቦታዎች ሙሉ በሙሉ በዉሃ ሊዋጡ እንደሚችሉ ስጋት እንዳለ ተገለፀ‼️
በአፋር ክልል የመሬት መንቀጥቀጥ የሚስተዋልባቸዉ ቦታዎች ሙሉ በሙሉ በዉሃ ሊዋጡ ይችላሉ  የሚል  ስጋት  እንዳለ በአፋር ክልል የዞን 3 ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዶ አሊ አቡበከር ከኢትዩ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቁይታ ገልፀዋል ፡፡

በአካባቢው ጥናት እያደረጉ ያሉት ከአዲስአበባ እና ከሰመራ ዩኒቨርስቲ የተውጣጡ የጂኦሎጂ ተመራማሪዎች የመሬት መንቀጥቀጥ ያለባቸው ቦታዎች  በውሃ ሊዋጡ ስለሚችሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ቦታውን መልቀቅ እንዳለባቸው ማስታውቃቸውን ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል፡፡

መሰል የተፈጥሮ ክስተት በሚስተዋልበት ወቅት ተገማች የሚደረጉ ሁኔታዎች የሚነሱ  ሲሆን ይህም  አካባቢዎቹ በዉሃ ሊዋጡ ይችላሉ የሚል ሳይንሳዊ ግምገማዎች መቀመጡን የጥናት ቡድኑ አባል ኖራ የኒምኦ ለኢትዩ ኤፍም አስታወቀዋል።

የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አብዶ አሊ ዜጎችን ከስፍራው የማንሳት እና ወደ ሌላ ቦታ የማዘዋወር ስራ እየተስራ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም  ከአዋሺ ፈንታሌ ወረዳ አራት ቀበሌዎች  እና  ከዱላቻ ወረዳ ደሞ ሁለት ቀበሌ ነዋሪዎችን እንዲሁም  የከሰም ስኳር ፋብሪካን  ስራተኞች ከስጋት ቀጠና በማንሳት ወደ ተሻለ ቦታ ማስፈር ተችሎል ብለዋል ፡፡

ከአዲስአበባ እና ከሰመራ ዩኒቨርስቲ የመጡ   ተመራማሪዎች ተጨማሪ ጥናቶች እያደረጉ መሆኑ  አንስተዉ ተጨማሪ የጥናት ውጤቶች ሲጠናቀቁ ለህዝብ  ይፋ እንደሚደረግ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዶ አሊ አቡበከር  አንስተዋል፡፡
=======================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


ተቀጡ‼️
ሰሞኑን በአፋር ክልል እና በተለያዩ አካባቡዎች የነዳጅ ዋጋ ይጨምራል በሚል ነዳጅ ጭነው ተደብቀው የነበሩ ከ200 በላይ ቦቴዎች እና 19 ማደያዎች ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ቅጣት ተጣለባቸው፣ ለ6 ወራት በነዳጅ ግብይት እንዳይሳተፉም ታግደዋል‼️
“በሀገሪቱ የነዳጅ አቅርቦት ችግር ሳይኖር” እጥረት እንዲከሰት እየተደረገ ያለው ሆን ተብሎ ሰራሽ የዋጋ ንረት እንዲፈጠር ለማድረግ ነው ሲል መንግስት ገለጸ፤ በማሳያነትም ጫካ እና ዱር ውስጥ ተደብቀው የነበሩ 250 የሚጠጉ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎችን መያዙን ጠቁሟል።

ቦቴዎች ከ10 እስከ 15 ቀናት ጫካ እና ዱር ውስጥ ቆመው እንደነበር የጠቆመው መንግስት ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት እና በተክኖሎጂ በመታግዘ መያዝ ተችሏል ሲሉ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ትላንት ጥር 5 ቀን 2017 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ አመላክተዋል፡፡

ቦቴዎቹና 19 ተባባሪ ማደያዎች ለ6 ወራት በነዳጅ ግብይት ውስጥ እንዳይሳተፉና ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ቅጣትም እንደተጣለባቸው ጠቁመዋል።
=======================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


በ #ሞያሌ የ14 አመት ታዳጊ ላይ የተፈጸመው ግድያ ቁጣ አስነሳ፤ በመንግስት ጽ/ ቤቶች ላይ ውድመት መድረሱ ተገለጸ‼️

በ #ኦሮሚያ ክልል #ቦረና ዞና በሞያሌ ከተማ ሸዋ ባር ቀበሌ የ14 አመት ታዳጊ “በፖሊስ አባላት” መገደሉ በነዋሪዎች ዘንድ ቁጣ ቀስቅሷል። ታዳጊው የተገደለው ባለፈው አርብ ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም "በፖሊስ ኃይሎች" በተተኮሰ ጥይት መሆኑ ተገጿል።

ግድያውን ተከትሎ የከተማው ህዝብ ባለፈው ቅዳሜ ተቃውሞ ሰልፍ የወጡ ሲሆን ፖሊስ ሰልፈኞቹን ለመበተን ተኩስ ከፍቶ በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የሞያሌ ከተማ ኮሚኒኬሽን ትናንት ባወጣው መግለጫ፤ በታዳጊው ላይ የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ ሰልፍ መካሄዱን ጠቅሶ "ጽ/ ቤቶችን ሰብሮ በመግባት የማውደም እና በእሳት የማቃጠል" ተግባር መፈጸሙን ገልጿል። ይህም ትክክል አለመሆኑንና የሰልፉን አላማ የምይወክል ነው ብሏል።
=======================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s

20 last posts shown.