መውሊድ ማን አከበረው?
1️⃣ አላህ - አዎ
ነቢዩ ﷺ የተወለዱ ቀን በመቶዎች የሚቆጠሩ ተአምራት ተመዝግቧል:: ሲነድ የነበረ የጣዖታውያን እሳት ጠፍቷል, የሮማና የፋርስ ቤተመንግሥት ተነቃንቋል, ከመወለዳቸው 50 ቀን ቀድሞ የአክሱም ሰራዊት በአእዋፍ ተደምስሷል, ብዙ ጅራታም ከዋክብት ተወንጭፈዋል, የጀነት በር ተከፍቷል, የጀሀነም በር ተዘግቷል::
2️⃣ ቁርአን - አዎ
በማያሻማና በግልጽ ቃላት በእዝነቱ ነብይ እንድንደሰት መክሯል:: ከሰበሰብነው ሁሉ በነቢዩ ﷺ መምጣትና በቁርአን መውረድ መደሰት እንደሆነ በሱረቱል ዩኑስ 10:57-58 ተቀምጧል::
3️⃣ መላኢካዎች - አዎ
ከአላህ ጋር በነቢዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ያወርዳሉ:: አማኞችም ታዘዋል:: ተጋብዘዋል::
4️⃣ ነቢዩ ሙሐመድ ﷺ - አዎ
የተወለዱባትን ሰኞ ዕለት ጾመዋል
5️⃣ ኸሊፋዎች - አዎ
የሰኞን መውሊድ የኻለፈ (የተቃረነ) ኸሊፋ አልተመዘገበም::
6️⃣ ሶሀቦች - አዎ
ነቢዩ ﷺ በመወለዳቸው ሰኞን ሲጾሙ ኖረዋል::
7️⃣ ቀጣይ ትውልዶች - አዎ
በመጾም እና ምስኪን ምግብ በማብላት አክብረዋል:: ምግብ ለአእዋፍ ተርፏል::
8️⃣ አራቱ ሊቃውንት - አዎ
የተቃረነ የለም:: በተመሳሳይ በፆም, ባሪያ ነጻ በማድረግና በሶደቃ አክብረዋል::
9️⃣ ዑለሞቻችን - አዎ
በጾም, ምስኪን በማብላት, በማዜም, ሌሊቱን ቆሞ በማደር አክብረዋል::
🔟 ወላጆቻችን - አዎ
ሸይኾቻቸው የሠሩትን በየቤታቸው ሠርተዋል::
1️⃣1️⃣ የነቢያችን ﷺ ዘመዶች - አዎ
የተወለዱ ቀን በሗላ በጠላትነት የተቃረናቸው አጎታቸው ሳይቀር ሱወይባ የምትሰኝን ባሪያ ነጻ አድርጓል:: በዚህም ሰኞ ዕለት የጀሀነም ቅጣት እንደሚበርድለት በሀዲስ ተነግሯል::
1️⃣2️⃣ አባታቸው ዐብዱላህ የተወለዱ ቀን ሳይቀር የነቢዩ ﷺ አያት ዓብዱልሙጦሊብ 12 ግመል አርደው ደግሰው አብልተዋል::
1️⃣3️⃣ ክርስቲያኖች - አዎ
ሥራ ዘግተው አብረው አክብረው ይውላሉ::
_____
↘️ ኢብሊስ - አይ
ነቢዩ ﷺ የተወለዱ ቀን እላዩ ላይ አፈር እየበተነ ጮሆአል:: አሁንም ይጮኻል, ያስጮኻል::
↘️ ወሃቢያ - አይ
የመውሊድ ቀን ሲረብሽ ሲጮህ ሲያንጉዋጥጥ ይውላል:: እስልምና ማለት መውሊድን መከልከል እስኪመስል ሌላ ሥራ ይተዋል::
ከሁለቱ ውጭ ወዳጅም ጠላትም አክብሮታል:: ያከብረዋል::