ረመዳን የምንቀበለው
በቁርኣን ወይስ በመንዙማ?
ነብያዊ አስተምህሮቱ ይህ ነበር፦
አቢ ኡማማህ (ረድየላሁ ዐንሁ) የአላህ መልዕክተኛ (ሠለላሁ ዓለይሒ ወሠለም) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦
«ቁርንን አንብቡ እሱ (ቁርአን) የትንሣኤ እለት ለአንባቢው አማላጅ ሆኖ ይመጣልና:: »
(ሙስሊም ዘግበውታል።)
መጠሪያችን "የቁርኣን ህዝቦች" ነበር ዛሬ ላይ ያለው ተጨባጭ ግን ሌላ ነው
«ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ» ይሉ ዘንዳ ሰዎች በምላሳቸው ባይናገሩትም ተግባራዊ ንግግራቸው ግን ያ ዑመተል ቁርአን !!! ስትል አቦ ፋራ አትሁን "ያ ዑመተ ነሺዳ" "ያ ዑመተ መንዙማ" ነው የሚባለው የሚል ድባብ አለው::
ስንቶቻችችን ለማስተዋል ሞክረን ይሆን!???
እስኪ ታዘቡ ነገር ዓለሙ እኮ መላ ቅጡ ጠፍቷል ! ...
ስልኮች፣ ኮምፒዩተሮች ብቻ ምን አለፋችሁ ዘመናዊ የመጠቃቀሚያ ንብረቶቻችን ቁርአንን Unsuported file format ያሉት ይመስል የቁርአን ድርቅ መቷቸዋል :: እንደው ነፍሱን ተጭኖ "ለበረካው" ብሎ የጫነባቸውም Folder ሠጥቷቸው memory space ከመያዝ ውጪ አድማጭ አጥተዋል ::
ምክንያቱ ወዲህ ነው፦
"ኢስላማዊ አዋርድ" ላይ ተሸላሚና ተፎካካሪ "ነጠላና ጋቢ" የሆኑ "አስለቃሽ" "መሳጭ" እየተባሉ የሚለቀቁ ከሀያሉ ጌታ ቃል በላይ ቅድሚያ የተሰጣቸው የሠዎች ግጥምና ዜማ ተደመጠውና ተሐፍዘው (ተሸመድደው) ስላላቁ ነው ::
ምን ይደረግ ብለህ ነው! ወዲህ ወደ ቁርኣን ተጣሪው ሲሸማቀቅ ፣ ሲሽመደመድና ሲልፈሰፈስ ፤ ወዲያ ሙነሺዱ ጥርስን አብቅሎ፣ ዳዴውን ጨርሶ ፈረጠመ።
ሱናው ጭሰኛ ቢድዓው ባላባት ሆነ! ነሺዳውን ትተህ ቁርኣኑን አዳምጥ ስትለው "ደግሞ ጀመረው" ይልና እዚህ የማልጠቅሰው ውርጅብኝ ያወርድብሃል!
አንተ ስድቡን አጣጥም እኔ ፅሁፌን ቀጠልኩ …
እና እላችኃለሁ ወዳጆቼ!
ታላቁን እንግዳችንን የቁርኣን ወር ረመዷን ለመቀብል በጉጉት ስንጠብቅ ፣ ለ11 ወራት አብዛኞቻችን አኩርፈነው የነበረውን ቁርኣን የሚነበብበት ጊዜ መጣ ብለን ስንፈነድቅ።
ለካ እዚህ ጋር ሌላ ዱብዳ መጥቷል፦
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከቱ የመጡ የነሺዳና የመንዙማ አይነቶች (አዘጋጆቹ አሰቡትም አላሰቡትም) ሙስሊሙን ዑማ ከቁርኣን የሚለያዩ መቀሶች ሆነዋል።
ረመዷን ሲመጣ ሰው የተለያዩ ቃሪኦችን ሲዲ ከመግዛት ይልቅ ፣ ወሩን እግር በእግር ተከታትለው የሚወጡ አዳዲስ የነሺዳና የመንዙማ ሲዲና ካሴቶች ሲሸምት እየታዘብን ነው!
የመሳጂድ በራፎች በአዳዲስ ነሺዳና መንዙማ (መርዙማ) ፖስተርና ድምፆች እየታመሱ ይገኛል።
በጣም እኮ ነው ልብ የሚያደማው!
ሱረቱል ቂያማን በላጥ ላጥ ቀርተን እያለፍን በነሺዳና መንዙማ ተፈኩር እያደረግን እናለቅሳለ....
"ቢያለቅስ" አንተ ምን አገባህ የእንባ ትራፊክ / ባንክ ልትሆን ነው? የሚል አይጠፋም! ልክ ነው "ትራፊክ አልሆንም" ግን…
«إِنَّ فِي ذَلِكَ لَذِكْرَى لِمَن كَانَ لَهُ قَلْبٌ أَوْ أَلْقَى السَّمْعَ وَهُوَ شَهِيدٌ
[سورة ق الآية 37]
«በዚህ ውስጥ ልብ ላለው ወይም እርሱ (በልቡ) የተጣደ ሆኖ (ወደሚነበብለት) ጆሮውን ለጣለ ግሳጼ አለበት» (ቃፍ 37)
እንባው ከተቅዋ የሚመስለን ካለን እንዳንሸወድ ለማለት ያክል ነው...
"ተቅዋ ማለት ዐይንን እያሻሹ ማልቃቀስ ሳይሆን አላህ ዘንድ ያስቀጣኛል ብለን የምናስበውን መጥፎ ስራ ለአላህ ብለን እርግፍ አድርጎ መተው ነው "
ይላሉ ዑለማዎቻችን! ለተቅዋ ከሰጧቸው የተለያዩ ትንታኔ መካከል ነው።
ተቅዋ የሚገኘው በቁርአን ሲያለቅሱ ፣ ሲመከሩ ፣ ሲገሰፁ ከምንም ነገር በላይ ለእርሱ ቅድሚያ ሲሰጡና ሲተገብሩት ነው::
ብዙ ቢያስብልም በዚህ ተብቃቃሁ!
ለዛሬ ራሴን የምገስፅበትን እናንተን የማስታውስበትን ፅሁፍ በዚህ አበቃሁ::
የፅሁፉ አላማ ሌሎችን ማነወር ፈፅሞ አይደለም! በስህተቶች ላይ መተራረም ፣ ሙስሊሞችን ወደ ቁርኣን መጣራት ስህተትንና ስህተተኞችን ማውገዝ ብቻና ብቻ ነው።
የፃፍኩት ያሰብኩትን ነው ፤ ያሰብኩትም የፃፍኩትን ነው!
እንደ ወንጀላችን ሳይሆን እንደራህመቱ የሚያኖረን ጌታ ምስጋና ይገባው::
ያ አላህ! ሙስሊሙን ዑማ ከነሺዳና መንዙማ ፍቅር አላቀህ የቁርኣንን ፍቅር በልባችን አድርግልን! አንተ ሁሉን ቻይ ነህና!
ቁርአንን አንብበው ሰርተውበት የቂያማ እለት ምልጃ ከሚሆንላቸው ያድርገን !!!
አላሁመ አሚን!!!!
👇👇👇👇👇
https://telegram.me/tewihd