ግጥም ብቻ 📘


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።
@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha
@leul_mekonnen1

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


--------💕አትጥፊ ከቤቴ💕--------
እኔ አቅም አልባ ሀጥያት ያደከመኝ፣
መፈጠር ትርጉሙ ጠፍቶኝ ያባዘነኝ፣
የዓለም ብልጭልጯ ስቦ ያባከነኝ።

ሞትን ያላሰበው ይህ ሞኝ ልቤ፣
ዛሬ አቅም አጥቶ ወድቋል ከአንዱ ግርጌ።
ልጥራሽ ድንግል ብዬ ስሚኝ እመቤቴ፣
ሀጥያት ባቆሸሸው ባደፈው እኔነቴ፣
ድረሺልኝ ድንግል ሳጠፋ ህይወቴ።

የሰውነት እድፍ ይለቃል በውሃ ፣
የልብስም እድፍ ይነፃል በውሃ ፣
ነፍሴ ቆሽሻለች ልትቀር ነው በረሀ፣
ድንግል ጥሪኝና ልንፃ በንስሀ።

ከአምላክ የተሰጠሽ ልዩ ስጦታዬ፣
ከጭንቀት ገላጋይ ሀጥያትን ማብቂያዬ።
ለልቤ ሠላሟ ፈውስ ነሽ ለህይወቴ፣
ወላዲተ አምላክ አትጥፊ ከቤቴ።


                   በሳምሪ የዝኑ ልጅ
                    
@getem
@getem
@getem


.........


   ኣይሁዳዊ ኣማነኝ
ሰቅለኀዋል ቢሉኝ፤ ኣሮ ይስቃል ጥርሴ     ኣይቀርም ኣምናለሁ፤ይጠብቃል ነፍሴ
..
..
ላልሞገታቸው
ዳሰውት ኣይተውት፤ኣምነዋል መምጣቱን
መሢሕ ባጣ ጊዜ፤እክዳለሁ ሞቱን

ቀላል መሰላቸው፤ለሰቀለ ማመን
ልጇን ለገደለ፤እናት ኣትለመን
ሞቷል ያልኩ እንደሆን
እኔ ገዳይ ልሆን
ዶሮ ቢጮህ እንኳ
    እጠብቀወለሁ ጆሮዬን ደፍኜ
ስገርፈው ኣላወኩት
               ከሸንጎ ላይ ሀኜ



ኣይሁዳዊ ኣማኝ ነኝ
ድንግል እደጠፋ፤በሀገሩ ሳቀው
መሢሕ እንዲወለድ
ነፍሴ የሚናፍቀው

       By @Mad12titan


@getem
@getem
@getem


ሢቃተ ሆሄ


   ጬኸት....
      ጬኸት
          ጬኸት
የሆሄያት ሲቃ
የሙሾ ድለቃ
ቃል ለዛውን ቢያጣ
ቅኔ ወዙ ቢነጣ
ሆሄያት ታመሙ
ሢቃ ድምጽ አሰሙ
       ያን ጊዜ
ገጣሚ ብእሩን ኣነሳ፤ከሆሄያት ድርድር
ከህመም ከሢቃ፤ስንኙን ሊያዋቅር
    ደራሲ ኣነባ
    የሆሄያት እንባ
ከወረቀቱ ላይ
ከነተበው ልቡ፤ከዘመኑ ሲሳይ
    ደራሲ ኣነባ
    የሆሄያት እንባ
ህይወቱን ሊገርፈው
በቅኔ ሊዘርፈው
ሆሄ ደረደረ
ቃላት ሰበጠረ
ሀረግ ኣዋቀረ
ሆሄያትም ታመሙ
ሢቃ ድምጽ ኣሰሙ
  ስንኙም ቤት መታ
  ግና የ ማታ ማታ
ሚስኪኑ ገጣሚ ቤት ለመታው ግጥሙ
በቆሰሉ ሆሄያት ህመም በሚያዜሙ
ፊደል ኣቀናብሮ በቃል በዘመነ
ቤት ለመታ ግጥሙ
ቤት መድፊያ እሱ ሆነ


ተጻፈ by @Mad12titan

@getem
@getem
@getem


"ደደብ" አለ ተበሳጭቶ
አይሆኑ ንክ ስነካካው
ምስኪን ነብስን የገፋ ለት
በምን ነበር የተመካው
እሳት መዞ ካፎቱ ላይ
ግንባሬ ላይ አስቀመጠው
'ተኩስ' አልኩት በጀግንነት
ድኩም ነፍሴን ምን በወጣው

የተነፋው የታች ቦርጩ
በደሃ ኪስ የጠገበ
የሱን ጎጆ ልስን ሲያበጅ
የኛን ድንኳን አረገበ
ሽፍን ጭንብል ለፊቱ መልክ
ቢፈለስፍ ጥሩ መስሎ
ባዶ እንደሆን ያው ባዶ ነው
እንጨት አይሆን ክሰል ከስሎ
ዲግሪ ዲስኩር ተጫጭኖ
ምሁር ነኝ ቢል የተማረ
የኛን ህይወት ጣል አድርጎ
የሱን ህይወት አሳመረ

"እናት አልባ"....አልኩት
በጭካኔ መንፈስ
አይኑ ካይኔ ፈጦ
ተኮሰብኝ እሳት ጥይት
ካፎቱ ላይ ሹል አውጥቶ
ደም ይረጫል ከደረቴ
ወለል ክፍሉን አበስብሶ
የተበደልኩ እኔ ሳለሁ
ይገለኛል ከሱም ብሶ

ዙፋን አርጎት ወንበር ስልጣን
       ለተመካ በሰዓቱ
ጊዜ እንደሆን ሰው አይደለም
     ያሳየዋል ሁሉን ፊቱ
ከዕለታት መሐል አንዲት ዕለት ቆጥሮ
ክፍያ አለው ሁሉም ምላሽ
አይዘገይም ጊዜ ቀጥሮ

"ደደብ" አለ ተበሳጭቶ
አይሆኑ ንክ ስነካካው
ምስኪን ነብስን የገፋ ለት
በምን ነበር የተመካው
እሳት መዞ ካፎቱ ላይ
ግንባሬ ላይ አስቀመጠው
'ተኩስ' አልኩት በጀግንነት
ድኩም ነፍሴን ምን በወጣው

ተኮሰብኝ አካሌ ላይ
ገድል ፃፈ...ሰብሮ ገድል
በጊዜ ላይ ለነገሰ
አያነሳም የፅዋ ድል

ለፍቶ መና...ለፍቶ ከንቱ
በሆነባት በዚች አለም
የጊዜ ነው እንጂ
የሰው ጀግና የለም


ዮኒ
    ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem


እንባ

ጥቋቁር ደመና፤ከጋረደው ሰማይ
ከባህር ከወንዙ፤ከውርቂያኖሱ ላይ
ተኖ የጎደለ፤እንባ ኣለ የሚታይ
የአንደኛዉ ለቅሶ፤ለአንደኛዉ ሲሳይ።

ተጻፈ by @Mad12titan

@getem
@getem
@getem


ዕለት ዕለት፤
ቀን እና ሌት፤

በሃሳቤና ግብሬ፤
በከንቱ ምግባሬ፤
ጌታዬን ቸንክሬ፤

በሚስማር ወጋሁት፤
ዳግመኛ ሰቀልኩት፤
በመስቀል አዋልኩት፤

ልክ እንደ ፃዲቅ ሰዉ፤
ራሴን ቆጥሬ፤
ሌላዉን ስኮንን ፤
ቃሉን ተዳፍሬ፤

ያደፈዉ መንፈሴን፤
በነጭ ነጠላ ፤
በአልባስ ሸሽጌ፤
ይምረኝ እንደሆን፤
እጠብቀዋለዉ፤
እርሱን......
ተስፋ አድርጌ፤


ዔደን ታደሰ

@ediwub
@getem
@getem


ጊዜ የጻፈው ግጥም

ሀገሬ ስትቆስል
አቁስሏን በስንኝ ልስል
ግጥሜን ላሰፍር ሌጣ ወረቀት ላይ
የቁስሏን መዳን የኔን ማርፈድ ሳላይ
ግጥሜን ሳበቃ
ከምእናቤ ኣለም ከሀሳቤ ስነቃ
የሀገሬ ቁስል ጠባሳዋ ድኖ
የጻፍኩትኝ ግጥም
ጠበቀኝ ጥቅስ ሆኖ

ገጣሚ @Mad12titan

@getem
@getem
@getem


ከእባብ ቆዳ ትል ይውጣ
የሰው ህሊና በቁም ይፍሰስ
እየተላጠ ቆዳው በደም
የአምላክ ዙፋን በሰው ይርከስ ፣

ሌት አጋንንት ይሰማሩ
መናፍስት ነፍስን ይግዙ
ክዋክብት ይረጋግፉ
በአምላክ ፊት ይጠልዝዙ

ጥንቆላ ገደል ይግባ
ገደል ገብቶ ቤቱን ይስራ
መተት ሁሉ ይንሰራፋ
የጠንቋይ ስም ባለም ይብራ

ሰማዬ ደም ይልበስ
ትል ይትፋ ምድር ሁሉ
ዳቢሎስ ነጭ ይልበስ
በሰው እቅፍ ይታለሉ

ሳር ቅጠሉ እባብ ይሁን
ወንዙ ሙሉ ጫካ መንፈስ
ንፁሃን ይደራመስ
እባብ ባለም ነጥቆ ይንገስ

ያለንበት ባለም  ሁሉ፥
እኛ ሁሉ የምንሆነው
እባብ ልንገል ምናሴረው
ለእባብ ነበር የምንወልደው ፣
እንዲህ ነበር ያገሬ ሰው ፣
ከሰይጣን ጋር ሚዋሰበው
እንዲህ ነው ያገሬ ሰው...
ራሱን ነው ያረከሰው...

@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት

@getem
@getem
@paappii


( አግዘኝ ...)
=============

ጌታ .....
አየህልኝ አይደል
ክንዴን ተንተርሳ ይህችን ደግ ሴት
አቅፈዋት ይቅርና ገና ስትታሰብ
የምትሞላ በሀሴት !!

እውነቷን ውበቷን ሰጥታ ለእኔነቴ
ከአንተ በታች አምናኝ ስትገባ ቤቴ
አመሌ እሾህ ሆኖ ወግቶ እንዳያደማት
ነገዬ ጨልሞ ረዝሞ እንዳይደክማት
ሰላም እንዳትራብ መውደድ እንዳይጠማት

አበርታኝ አደራ ...
ከፊት ይልቅ ዛሬ አትለይ ከጎኔ
ከሌለኸኝ በቀር ፍቅሯን ለብቻዬ
አልችለውም እኔ !!!


By @kiyorna

@getem
@getem
@paappii


አጎት

አጎት መካሪዬ ፣ ጋሻ መከታዬ፣
አባት ፣ወንድም፣ ጓደኛ፣ ነህ ሀለኝታዬ።

ሀ ሁ.....በቆጠርኩበት ፣ በጥንቱ ጊዜያት፣
ብዕር ይዘህ መርተህ ፣ ደረስኩ ላለሁበት።

ልክ እንደ ጓደኛ ፣ ሁነህ ስትጫወት፣
ሚስጥሬን ነግሬህ ፣ ምክር ምትሞላበት፣
አጎትየው ልብህ ፣ ፍቅር  ነው የሞላበት።


                   በሳምሪ የዝኑ ልጅ
                   16-03-2017 ዓ.ም


@getem
@getem
@getem


ፍካሬ ዓለም
_____

(እሳት ወይ በረዶ)

የዓለምን ፍፃሜ.. ቀድመውን ያሰሉ
ትንቢት ተናጋሪ.. ብዙ ፃፎች አሉ፣
ምድር የምትጠፋው
በእሳት ነው የሚሉ።

ሌሎች በፊናቸው.. ጥልቅ የመረመሩ
የእሳቱን ፍፃሜ.. የተጠራጠሩ፣
የምድሪቱን መጥፊያ.. በውል ሲቀምሩ
በረዶ ይላሉ።

በፍካሬ ዓለም.. እጅግ ተመስጬ
ልመርጥ ብሞክር.. መፅሐፍ ገልጬ...
አንዴ በነበልባል... ደግሞ በአመዳይ፣
ምድር ስትከፈን.. ሲደረመስ ሠማይ፣
በትኩስ ቀዝቃዛው.. ዓለሙ ተንዶ...
መጥፊያችን ቸገረኝ... እሳት ወይ በረዶ?

ካየሁት ከማውቀው፣
ነገሩን ሳስበው....
ከነበልባል ስሜት.. ምኞት ካልተገራ፣
ከሚንቀለቀለው... የቁጣ ገሞራ፣
ከደምፍላት ግልቢያው
ልጓም ካላበጀ
እየገነፈለ ሀገሩን ከፈጀ... ፣
ካየሁ ከሰማሁት..
ነገሩን ሳስበው...
አላወላውልም እመሠክራለሁ፣
እሳት ኃይለኛ ነው!
በእሳት ትጠፋለች ዓለም በፍፃሜ፣
ከሚሉትም ጋራ ይሠምራል አቋሜ።

ነገር ግን ምድሪቱ
የምትጠፋበቱ፣
ሁለቴ ደጋግሞ ይሁን ከተባለ፣
ለመጥፊያ፣ ለመጥፊያ...
ሌላም መንገድ አለ፦

በቀዘቀዘ ልብ... ጥላቻ ሲነግስ...
በቀል ሲያንሠራራ.. ቂሙ ሲወራረስ...፣
ጥላቻ በርክቶ.. ማዕበል ሲያስነሳ
ሰውን ሰው ሲበላ፣ ዘመንን ሲነሳ...
ይህንም አውቃለሁ...
እመሠክራለሁ...፣
ለመቅሰፍት ለመቅሰፍት..
ለመጥፊያ ለመጥፊያ፣
በረዶም በቂ ነው
ዓለምን ለማጥፊያ
እንደ እሳት ቋያ።

— ሮበርት ፍሮስት፣ Fire and Ice (1920)፣
/ዝርው ትርጉም የራሴ/


@getem
@getem
@paappii


ለስጦታ ሥዕል ማሳል ምትፈልጉ በ +251984740577 ይደውሉ።

ወይም @gebriel_19 ላይ አናግሩኝ

@seiloch
@seiloch


ፍንዳታ
.
.
መቃብር ባልገባም፤
በለቅሶ በዋይታ፤
እርግጥ ነዉ ሞቻለሁ፤
የፈነዳሁ ለታ።
@ediwub
@getem
@getem


...ቃሌን
ውበት እረጋፊ አላቂና አብቂ
ስስትን ማልሻ አፍቃሪህ ናፍቂ
ገደብ የማላውቀው እኔ ያንተ ጠባቂ
አርጅተን እስክንሔድ በሽበት ተከበን
ቃሌን አላጥፈውም አፈቅራለው አንተን
BY
@Hanipia

@getem
@getem
@Hanipiagetem


።።።።።።።።ቃል የለኝም።።።።።።።።

አልቆጭም በማፍቀሬ ፣
አልተጎዳሁ በማረሬ።
ዉስጤን ቢያመኝ ብትርቂኝም፣
አንቺን የግል ማድረግ ብያቅተኝም።
።።።። ለመሄድሽ ቃል የለኝም።።።።።
ልቤ ቆስሎ ባያገግም፣
ለፍቅርሽም ባያስደግም።
አንቺን ለማየት ብታደልም፣
በመድረክሽ ብታደምም።
።።።።።ሄድሽ ብዬ አልገግምም።።።።
የሄድሽ እለት ልቤ ቢተክዝም፣
ለሌላ ሴት እንዲህ አልፈዝም።



የምር ከፍቶኝ በነበረ ሰዐት የተፃፈ ግጥም
ቀን አርብ 03:24 ማታ
ማጀቢያ ሙዚቃ : ዳዊት ፅጌ ( ልቤ ሰዉ )
ምንጭ: እሷ ( ግራ ለገባት )
ገጣሚ: እኔ ( መሄዷን እያወቀ ላፈቀረ )


ገጣሚ : @papiel16

@getem
@getem
@getem


መናፈቅ ማለት …
ከወትሮው በድንገት
ከከተማ ግፊያ
ከሰፊው ገበያ
ከሰው ትርምስ
ከህይወት ግብስብስ
አረፍ ብለው ባልጋ
ከራስ ጋር ሲወጋ
የአስቴር እና ኤፍሬም
አባባይ ሙዚቃ ...
አንጀትንን ሲገርፍ
ትዝታን ሲያነቃ
እንዲህ ይመስለኛል !
..
መናፈቅ ማለት..
በቡሄ አመሻሽ
እርግት ባለ ሰማይ
ልጅነት ሲወያይ
ሲሸት የኩበት ጭስ
የአሪቲ ቃና መንደርን ሲዳብስ
ውብ አደይ አበባ ምድሪቷን ሲያነግስ
እንዲህ ይመስለኛል !
..
መናፈቅ ማለት ..
እኔና አንቺ አፍረን
ከዓይን ተሸሽገን
ከመስቀል ዳመራ
ሸሽተን ከጓደኞች
ፈልገን ሰዋራ ...
ተቃቅፈን እየሄድን
ውሎን ስንጋራ
ስትሰጪኝ ፖፖቲን
‘’ፖስት ካርዴስ ?’’ ብለሽ
ኪሴን ስትዳብሽኝ
እንዲህ ይመስለኛል ።
..
መናፈቅ ማለት …
ትምህርት ሊዘጋ ወቅት
ድራማ ተውነን
በሰኔ ሰላሳ ለመታየት ደምቀን
በድራማው መኃል
ፈልገን ስህተት
ከልብ የሳቅን ዕለት
ከሳቅን በኋላ
ኩሪፊያ ሲከተለን ...
ድፍን ሶስት ወራትን
ያለመገናኘት ፍርሀት ሲውጠን
ስትሰናበችኝ በጥልቁ ዝምታ
ዓይንሽን እያየሁ
ዓይኖቼን እያየሽ
የቆዘምን ለታ …..
እንዲህ ይመስለኛል ።
..
መናፈቅ ማለት …
የሽፍታ ፍርሀት
ነፍስያን ሳይንጣት
በ አራት እግር ጉዞ
የመኪናን መስኮት
በራስ ተመርኩዞ
የገጠርን መስመር
አንዱን መንገድ ይዞ
ተራራውን ማየት
እሸቱን መጎምዠት
ከገበሬ ቁና
በቆሎ መሸመት
የፀሀይዋን ግባት
አሻግሮ መቃኘት
እንዲህ ይመስለኛል።

መናፈቅ ማለት …

(ሚካኤል አ )


@getem
@getem
@getem


እንደምትወዳት ንገራት,

(በእውቀቱ ስዩም)
ሕይወት የብድር በሬ፥መቼ ሁሌ ይጠመዳል
ለጊዜው ብቻ የመጣ፥ ጊዜው ሲደርስ ይሄዳል
የተሰጠህ ጸጋ ሁሉ፥ ደሞ ካንተ ይወሰዳል::

ቀለበት፥ አምባር አይደሉም
እጅህ ላይ ሁልጊዜ የሉም
-ቀናት ሳምንታት ወራት
ዛሬውኑ ፥አሁኑኑ፥ እንደምትወዳት ንገራት::

አበቦች ሁሉ ሳይረግፉ
ምኡዝ ሽታዎች ሳይጠፉ
ያጸድ በሮች ሳይቆለፉ
በንቦች ጎዳና ላይ፥ተርቦች ሳይሰለፉ
በንፋስ ክንፍ ሳይመታ
ሕይወት የላምባ መብራት
አሁንኑ ዛሬውኑ ፥እንደምትወዳት ንገራት፤

ርቃ ሳትገሰግስ
ገና ስንቋን ስትደግስ
እንዲሁ እንዳማረባት
ቀልብህ እንደቀረባት
መቃብር በመዳፉ
እንደጠጠር ሳይቀልባት
አፈሩን ሳትዛመድ
ወደማትቀባው አመድ
ወደማትስበው አየር
ሳትቀየር
አንትም አንደበት ሳለህ፥ እሷም ጆሮ ሳያጥራት
ዛሬውኑ! አሁኑኑ! እንደምትወዳት ንገራት።

@getem
@getem
@paappii


ወደድኩሽ ካለኝ በኃላ......

ስደዉል ስልኩን ቢዘጋም
ስቀጥረዉ ቢቀርብኝ
መልዕክቴን አይቶ ዝምቢል
በድንገት ባገኘዉ እንኳ በፍጥነት ከኔ ገሸሽ ቢል....

እኔ ልሙት ይወደኛል.......

ቢፈራኝ ነዉ እንጂ ፍቅሬ ቢያስጨንቀዉ
ምን እላት እያለ ስለሚ'ያሳስበዉ
ስልኩን የማይመልስ ትቶኝ የሚሮጠዉ

ሌላ ጊዜ እድል ቀንቶኝ
በአንዲቷ ቀን ካፌ ቀጥሮኝ
አይኖቹ ከስልኩ
አያየኝም ብዬ ያልኩ
ሌላ ሴት እያየ በድንገት ሲጠቅሳት
አይኔ ካይኑ ተገጫጨ
የያዘዉ ብርጭቆ ከእጆቹ አሟለጨ

ፈገግ አልኩ ደነገጠ
ምንን ያህል ቢወደኝ ልቡ የቀለጠ?
አወይ አጋጣሚ ብዬ ተገረምኩ
ይሄኔ ሲያየኝ ደንግጦ ነዉ አልኩ

እኔን ይንሳኝ ይወደኛል ስላችሁ
ደግሞ የዛሬዉን ጉዱን ልንገራችሁ

መጥሪያ አምጥቶ እጆቼ ላይ አስቀመጠ
ላገባ ነዉ ብሎ ልክ እንደ ልማዱ ደሞ ፈረጠጠ

ገለጥኩት.......
የልቤ ከምላት ከኔዉ ጓደኛ ጋር
የሚሆናት አጋር

ምን ያክል ቢወደኝ
እንዴት ቢሳሳልኝ
አወይ የሱ ፍቅር

የልቤ ምላትን እንደ ልቡ አድርጐ
እኔን ለማስደሰት ሚያገባት ሰርጐ

ይወደኝ አይደለ?

💕ትዝታ ወልዴ(@Tizita21)

@getem
@getem


#የእንቢታሽ ሱሰኛ!
(ሚካኤል አስጨናቂ)

አንቺን በማሰብ ውስጥ መደሰት ለምጄ
ፍቅርሽ ሱስ ሆኖብኝ ... ማንነቴን ክጄ
ባንቺ መወድስ ስም ክታብ አሰርቼ
ስምሽን አንግቼ …

እንደ አሞራ ዙሬሽአንዣብቤ በላይ
አንቺን ሳይሽ ፣ ‘ዋይ ፣ ዋይ …’

አጃኢብ ነው መቼም!

ስትሄጅ ተራመድሁ... ስትቆሚ ቆሜ 
ባንቺ ስፍር ልኬት.. .በጠርዝ ተመድሜ
ከዕድሜ ከዘመኔዓመታት ቆንጥሬ
ከእንቢታሽ ጋራበእልህ ሰክሬ
ስንኞችን ጭሬ.. .
አንቺን በመጀንጀንጀንልማድ ተጠፍሬ
በሚጣፍጥ ህመም ...
ብቻዬን በአርምሞስብሰለስል ኖሬ

ከሀሳቤ ማግስት ... በስንኜ ድርድር 
ቃላት ድል ነስተውሽበኃይላቸው በትር
እኔም በተራዬ ፣ መፈቀር ስጀምር
“ፍቅርህን ተቀበልሁ” ያልሽኝ ጊዜለታ 
ፍቅርሽ ጥሎኝ ጠፋትዝታሽ ተረታ።

(እንቢ በይኝ ዳግም
እልህን ላጣጥም ። )

@getem
@getem
@getem


አዎ !
ለጊዜውም ቢሆን ፤ ግፍ ያደነዝዛል
በደል ያስተክዛል
ጊዜም ጠብን ሽሮ ፤ ወደፊት ይጓዛል
በልብ ሰሌዳ ላይ ፤ ቂም ይደበዝዛል
በነገ ያመነ
ልጁን ቀብሮ መጥቶ ፤ ሚስቱን ያስረግዛል ።

By bewuketu Seyoum

@getem
@getem
@paappii

20 last posts shown.