🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ይህ ቻናል ቁርኣን እና ሐዲስ መሰረት በማድረግ የመልካም ቀደምቶቻችን ፋና በመከተል ስለ እስልምናችን የምንማማርበት እና የምንመካከርበት ቻናል ነው።
✍እስልምና አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው‼
👇🏾👇🏾👇🏾
@hamdquante
አስተያየትዎ ይበልጥ ይገነባናል
👉🏿 @hamdquante_bot👈🏿

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter



አንዳንድ ሰዎች ትተውህ ሲሄዱ;
በቃ ሰላምህን አገኘህ: ዕረፍት ተደወለ እንደማለት ነው!!!





https://t.me/hamdquante



የትም ቦታ ብትሆን አላህን ፍራ!!
ከሚለው እና
"በካሜራ ዕይታ ውስጥ ነዎት"
ከሚለው የቱ የበለጠ ያስፈራናል??




ገና ብዙ እኮ ነው የሚቀረን
https://t.me/hamdquante


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
🇸🇾
     በሶሪያው ድል ያስደሰትከን አላህ

🇾🇪
     በየመን ምድርም ሱንዮች አንግሰህ
       🤲 ደስታችን ሙሉ አርግልን🤲



የየመን ሙጃሂዶችም በዱዓችሁ አግዟቸው!!
    https://t.me/hamdquante



ወይ በተሻለ ተክቶልህ, አልያም ትክክለኛው ጊዜ አልደረሰም ሊሆን ይችላል እንጂ;
አላህን ለምነኸው የሚከለክልህ ነገር የለም!!


📖{وَآتَاكُم مِّن كُلِّ مَا سَأَلْتُمُوهُ…}
{የለመናችሁትን ሁሉ ሰጥቷችኋል…}

   [ኢብራሂም:³⁴]





https://t.me/hamdquante



   አንድ ሰው እንቅልፉን በተኛ ጊዜ "በሕይወት ካሉ ሰዎች በበለጠ ለሞቱ ሰዎች የቀረበ ነው" ብላችሁ የመላሳችሁ; 👍በትክክል መልሳችኋል።

ለዚህም አመላካች የሆነው መረጃ፦
    ነብዩﷺ አንድ ሰው ከመተኛቱ በፊት የሚያደርጋቸው አዝካሮች ሲያስተምሩ: እንዲህ እንዲል አዘዋል………
«اللهم إن أمسكت روحي فارحمها، وإن أرسلتها فاحفظها بما تحفظ به عبادك الصالحين»
«አላህ ሆይ! ነፍሴን በዝያው ከያዝካት እዘንላት፤ የመለስካት እንደሆነ ደጋግ ባሮችህ በምትጠብቅበት ነገር ጠብቃት።»



  ከሓዲሱ: የተኛ ሰው ነፍሱ ከተመለሰለት ነው እንጂ ለሞት ቅርብ እንደሆነ መገንዘብ እንችላለን።






https://t.me/hamdquante


ሳትመልሱ እንዳትተኙ!! አንድ ሰው እንቅልፉን በተኛ ጊዜ የበለጠ ቅርብ የሚሆነው ከሞቱ ሰዎች ጋ ነው? ወይስ በሕይወት ካሉ ሰዎች ጋ??
Poll
  •   በሕይወት ካሉ ሰዎች ጋ!!
  •   ከሞቱ ሰዎች ጋ!!
  •   ወላሁ አዕለም!!
591 votes



ያስተውሉ!!

"ድንገት ተገናኘን, ድንገት መጣን, ድንገት ተከሰተ, ድንገት ምናምን………" አይባልም።

ምክንያቱም፦
በአላህ ውሳኔ (ቀደር) እንጂ በድነገት የሚከሰት ነገር የለም!!


የፈለግንበት ኒያችን አላህ የሚያውቀው ቢሆንም, ክፉ አመለካከት ኖሮን ባይሆንም; ስህተት ከሆኑ አባባሎች ምላሳችን መራቅ አለበት።




https://t.me/hamdquante



ያስተውሉ!!

"በድሎኛል, አላህ ይበድለው" አይባልም።
ምክንያቱም፦
አላህ በየትኛውም መልኩ በዳይ አይደለም።


የበደለህ አካል አላህ እንዲዝልህ፣ እንዲበቀልልህ መለመን ትችላለህ። ቃላቶች ግን መምረጥ አለብህ።




https://t.me/hamdquante



    እሷን ለማግባት አባቷን ዐስር ዓመታት ማገልገል?
      ምን ቢኖራት ነው??


📖{قَالَ إِنِّىٓ أُرِيدُ أَنْ أُنكِحَكَ إِحْدَى ٱبْنَتَىَّ هَٰتَيْنِ عَلَىٰٓ أَن تَأْجُرَنِى ثَمَٰنِىَ حِجَجٍۢ ۖ فَإِنْ أَتْمَمْتَ عَشْرًۭا فَمِنْ عِندِكَ ۖ وَمَآ أُرِيدُ أَنْ أَشُقَّ عَلَيْكَ ۚ سَتَجِدُنِىٓ إِن شَآءَ ٱللَّهُ مِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ}
{"እኔ ከእነዚህ ሁለት ሴት ልጆቼ አንዲቷን ላጋባህ እሻለሁ። ስምንት ዓመታት ልታገለግለኝ; ዐስር ብትሞላም ከአንተ ነው። ባንተ ላይ ማስቸገርንም አልሻም፡፡ አላህ የሻ እንደሆነ ከመልካሞቹ ሆኜ ታገኘኛለህ" አለው፡፡}

     [አል_ቀሰስ:²⁷]


  ምን ዐይነት ሴት ብትሆን ነው? ምን ቢኖራት ነው? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ይሆን ዘንድ ከነበሯት ነገሮች ሁሉ ውድ የነበረው አላህ እንዲህ አወድሶ ያወሳልናል።

📖{فَجَاءَتْهُ إِحْدَاهُمَا تَمْشِي عَلَى اسْتِحْيَاءٍ…}
{ከሁለቱ አንዷ በሐያዕ የምትሄደ ሆና መጣቸው…}


   በውበቷ, በቁመናዋ, ወይም በሌላ ዝናዋ ሳይሆን; ለአንዲት ሴት ልጅ ከሁሉም ነገር የበለጠ በሆነው ነገሯ "በሐያዕዋ" አላህ ገለፃት!!




https://t.me/hamdquante



አንድ ሰው ሌሎች ለማሳደግ በሚጥረው ልክ;
የእሱም እድገት ይጨምራል!!





https://t.me/hamdquante



ዲንህ የተማርከው ከተኩላዎች እንደሆነ;
ዶሮ መስረቅ መቻል ከራማ ነው ብለህ ታምናለህ!!




https://t.me/hamdquante


✍️
    ለአእምሮ ባልተቤቶች………

📖{قَالَتَا لَا نَسْقِي حَتَّى يُصْدِرَ الرِّعَاءُ وَأَبُونَا شَيْخٌ كَبِيرٌ}
{እረኞቹ ሁሉ መንጋዎቻቸው እስከ ሚመልሱ ድረስ አናጠጣም። አባታችንም ትልቅ ሽማግሌ ነው አሉት}
      [አል_ቀሰስ: 23]

💫የአባታቸው ሽምግልና፣
     💫የስራቸው አድካሚነት፣
        💫የከብቶቻቸው መጠማት;


  ከወንዶች ጋ ለመቀላቀል (ኢኽትላጥ) ለመፍጠር ምክንያት አልሆናቸውም።

♻️ዛሬ ላይ ምንም ዐይነት ዑዝር ሳይኖራችሁ ሴቶቻችሁ ወደ ገበያም ይሁን አካዳሚ የምትማግዱ አባቶች አላህ ፊት ምላሻችሁ ምንድን ነው??

♻️ዑዝር የማይሆኑ ዑዝሮችን "ለዑዝር ነው" እያላችሁ ለሙስሊሞች ኢኽትላጥ የምታግራሩ ፈትዋ ሰጪዎች ይህንን የቁርኣን አንቀፅ ቆም ብላችሁ ማስተንተን እንዴት ተሳናችሁ??

♻️ፊትሽ በቢጫ, ከንፈርሽ በግራጫ ቀለም ለቅልቀሽ ክብር እና ሓያሽ አራግፈሽ ምንነቱ ከማይታወቅ ወንድ ሁሉ እየተጋጋጥሽ የገበያ ባንዲራ የሆንሽው እቴ:
እንደው ራስሽ ከእነዚህ ዕንቁዎች ጋ አመዛዝነሽ ስታይው ስለራስሽ ምን ይሰማሻል??





🤲اللهم ردنا إليك ردا جميلا🤲
https://t.me/hamdquante



    ድብርት, ደስታ እና አዘኔታ ተፈራረቁብኝ!!

  ወፍራም ድምፅ ባለው ስፒከር የተከፈተው ሙዚቃ አጠገብህ ካለው ሰው ጋ እንኳ መደማመጥ አያስችልም፤ የምሽቱ አየር እና የመንገድ ክፍት መሆኑ ተመችቶት ታክሲው እያሽከረከረ ሳይሆን እያዘለለ የሚነዳው ነው የሚመስለው። መጨረሻችን ለመድረስ ቢያንስ ከጉዞው አንድ ሦሥተኛው ያህል ሲቀረን ጋቢና ተቀምጠው ከነበሩት አንደኛው መውረጃው ደርሶ ወረደ።

  ወደ ታክሲው የገባው የመጨረሻው ሰው እኔ ነበርኩኝ፤ መቀመጫዎቹ ሁሉ ሞልተው ስለ ነበር ለትርፍ በተዘጋጀው ጣውላ ጫፍ ላይ ነበር የተቀመጥኩት። ስለነበርም ጋቢና የነበረው ተሳፋሪ ሲወርድ ረዳቱ ጋቢና እንድገባ ጋበዘኝ።

  ጋቢና ገብቼ የመሀለኛው ወንበር ላይ ተቀመጥኩኝ። እዚህጋ ነው ክስተቱ………
  ሹፌሩ ወዴትም መጠጋት ላይችል ነገር ክብሩን ለመግለፅ በሚመስል መልኩ ተጠጋልኝና "አሰላሙ ዐለይኩም" አለኝ።
  የዘፈኑ ጩኸት፣ የፀጉሩ አፈራረዝ፣ ከለበሰው የጂንስ ቁምጣ ጋ ተዳምሮ በተለምዶ "የዱርዬ" የሚባለው ገፅታ ያሟላ ነበር። ያቀረበልኝ ሰላምታ ከመለስኩለት በኋላ: "የምር ሙስሊም ሆኖ ነው እንዲህ የሆነው?" የሚል ጥያቄ ተፈጠረብኝና ቀና ብዬ የመኪናው ዳሽቦርድ ስመለከት በተለያዩ ኢስላማዊ ጥቅሶች ተጨናንቋል።

   "ሙስሊም ሆኖ እንዲት እንዲህ ይበላሻል?" የሚል ድብርት ያዘኝ፤
  "እንዲህ ለብሶ, እንዲህ እያዘፈነም እስልምናውን አይረሳም? ለሙስሊም ወንድሙ ፍቅር ያሳያል?" የሚል ደስታም በውስጤ ያቃጭላል፤

በመጨረሻም………
   "ዘመናዊነት" በሚል ክፉ መንፈስ የሙስሊም ወጣቶች መበላሸት እና ኢስላማዊ ባህል ማጣት ውስጤ ተረብሾ ለእኔም ለእሱም አዘንኩኝ።

🤲አላህ ወደ እሱ ያማረ የሆነ መመለስ ይመልሰን🤲




🖊ሐምዱ ቋንጤ ከፉርቃን ሰማይ ስር!!
https://t.me/hamdquante



    አኼራ ባይኖር በሻርን ባስታወስን ቁጥር ማበዳችን ነበር!!
  አላህ ዘንድ በድሎ የሚድንም ይሁን: ተበድሎ የሚከስር የለም!!


   "በሻር አል_አሰድ" የተባለው የዘመናችን ፊርዐውን እስካሁን ከሰራው ከፊሉን እንጂ ከአሁን በኋላ ስለ ሚኖረው ሕይወቱ የምናውቀው ነገር የለም። ቀሪ እድሜው በዚሁ የኩፍር ዐቂዳ እና ጁርም ጨርሶት ጀሀነም ይወረወራል? ወይስ በእድሜው መጨረሻ ቀልቡ ለስልሶ በተውበት ታጥቦ ከደጋጎች ተርታ ይሰለፋል? የሚለው አላህ ብቻ ነው የሚያውቀው። ስለሱ አኼራ መተንበይም ይሁን መደምደም አንችልም፤ ከመሆኑም ጋ…… እንደሱ ያሉ ወደር የለሽ አረመኔዎች በጁርማቸው ልክ የእጃቸው የሚያገኙበት እና በጅምላ የተጨፈጨፉ በርካታ ንፁሃኖች ለተሰራባቸው ግፍ ካሳ የሚያገኙበት "አኼራ" የተባለ የክፍያ ሀገር ባይኖር: ምን አልባትም ብዙ ሙጅሪሞች ባስታወስን ቁጥር በቁጭት እና በሀዘን ለእብደት እንቃረብ ይሆን ይችል ነበር።

  የበሻር የአኼራ እጣ_ፋንታው ከላይ በተገለፀው መልኩ ማወቅ ስለ ማንችል; በምናባችሁ አንድ ገፀ_ባህሪ ሳሉና ስለሱ እንተርክ………


አንድ ሰው ነው…………
   በዱንያ ላይ ማንኛውም ሰው ሊነቀንቀው የማይችል የተመቻቸ ስልጣን እና የበረታ ሰራዊት አለው። የፈለገውን ያስራል፣ ያሻው ይገርፋል፣ የፈለገው ይሰቅላል፣ ከፈለገው ይዘርፋል፣ እጅግ በጣም በርካታ የሆኑ በሚሊየን የሚቆጠሩ ንፁሃኖች በበደል ጨፍጭፎ ገድሏል፣ ሰዎች በሕይወት ሳሉ ያቃጥላል፣ ሰውነታቸው እየቆራረጠ ያሰቃያል፣ እስከነ ሕይወታቸው ይቀብራቸዋል፣ በጣም ብዙ ብዙ የሆኑ ግፎች ይፈፅማል።

  ይህ ሰው አኼራ የሚባል ሀገር ባይኖር ዱንያ ላይ ምን ዐይነት እርምጃ ቢወሰድበት ለሰራቸው ግፎች ተመጣጣኝ የሚሆን ቅጣት የሚያገኝ ይመስላችኋል???
  በፍፁም ተመጣጣኝ የሚሆነው ቅጣት አታገኙም። "በእሳት ይቃጠል" ብትሉ, እሱ ብዙ ሰዎች አቃጥሏል: ስለዚህ የአንድ ሰው ብቻ ነው ለእሱ የሚደርሰው፤ "በዘይት መጠበስ አለበት" ብትሉ, እሱ ብዙ ሰዎች በዘይት ጠብሶ አሰቃይቷል: ስለዚህ የአንድ ሰው ድርሻ ብቻ ነው እሱ የሚያገኘው። ስለዚህ ምንም ዐይነት እርምጃ ቢወሰድበት ለሰራው በደል ተመጣጣኝ ሊሆንለት አይችልም።

ይህ ብቻም አይደለም………
  ቁጥራቸው እጅግ በጣም በርካታ የሆኑ ተበዳዮች ወይም ተገዳዮች ሁላቸውም ለደረሰባቸው በደል ካሳ ማግኘት ይፈልጋሉ። ይህ ደግሞ በዱንያ ላይ ሊከፈላቸው አይችልም። ምክንያቱም ሰዎቹ ሙተው ከዱንያ ወጥተዋል።

  እንግዲያውስ አላህ ዘንድ በድሎ የሚተርፍም ይሁን ተበድሎ የሚከስር የለምና ሁሉም የሚገባው የሆነ ምንዳ እና ቅጣት አኼራ ላይ ያገኛል።

  አኼራ ላይ "ጀሀነም" የምትባል ለበደለኞች የተዘጋጀት የስቃይ ሀገር አለች። ዱንያ ላይ የትኛውንም ያህል የገዘፈ በደል ሰርቶ የሞተ ሰው ይህ ጀሀነም ውስጥ ለሰራው በደል የሚገባ የሆነ ቅጣት ያገኛል። ጀሀነም ውስጥ ሕይወትም ሞትም የለም። ሕይወት እንዳይባል ሞት የሚያስመኝ የስቃይ ሕይወት ነው፤ ሞት እንዳይባል እየተቃጠለ እየተሰቃየ ይኖራል እንጂ ሙቶ አይገላገልም። አንድ ሰው ዱንያ ላይ ሚሊየን ሰዎች አሰቃይቶ እንደሆነ ጀሀነም ውስጥ ሚሊየን ጊዜ ይሰቃያል። አንዴ ተቃጥሎ, አንዴ ተሰቃይቶ አያበቃም።

አላህ እንዳለው፦
 📖{كُلَّمَا نَضِجَتْ جُلُودُهُم بَدَّلْنَاهُمْ جُلُودًا غَيْرَهَا لِيَذُوقُوا الْعَذَابَ}
{ቆዳቸው በተቃጠለች ልክ ቅጣት እንዲቀምሱ ሌሎች ቆዳዎች እንቀይርላቸዋለን።}

  [አል_ኒሳእ:⁵⁶]
  ሰውነቱ አንዴ ተቃጥሎ ሲያልቅ ሌላ ቆዳ ይቀየርለትና በድጋሚ ሌላ ስቃይ ይቀምሳል። እያለ… እያለ… ይሰቃያል።

  "እሱ ለሰራው በደል እና ግፍ በዚህ መልኩ እየተሰቃየ የሚገባውን ቢያገኝም
   በእሱ ግፍ እና በደል የደረሰባቸው ሰዎች ካሳቸው የሚያገኙት በምን መልኩ ነው?"
የሚለው ሌላው ጥያቄ ነው።
 አኼራ ላይ? አዎን በትክክል ካሳቸውን ያገኛሉ!!

  በዱንያ ቆይታ በሌሎች ላይ በደል አድርሶ በደሉን "ይቅር" ሳይባል ወይም ካሳ ሳይከፍል የሞተ ሰው አይቀሬ በሆነ መልኩ አኼራ ላይ ለተበዳዮች ካሳቸው እንዲከፍል ይደረጋል። ይህንን ግልፅ አድርጎ የሚያስረዳ ሓዲስ ነብዩ እንዲህ ነግረውናል።

  ከዕለታት በአንዱ ቀን የዕዝነቱ ነብይﷺ ከውድ ባልደረቦቻቸው በተቀማመጡበት ነብዩ ለሰሀባዎች ጥያቄ አቀረቡ። "መናጢ ደሀ ማን እንደሆነ ታውቃላችሁን?" አሏቸው። ሰሀባዎች ሲመልሱ "ደሀ ማለት ምንም ዐይነት መጠቃቀሚያ ቁስም ይሁን ሀብት የሌለው ነው" አሉ። ነብዩ "ትክክለኛ ደሀ ማለትማ፦ አንድ ሰው ነው: የቂያማ ቀን በርካታ ሰላት፣ ምፅዋት፣ እና ጾም ይዞ ይመጣል፤ ከዚያም የዘረፋቸው፣ የደበደባቸው፤ የገደላቸው ሰዎች ይመጡና ለዚህ ከምንዳው: ለዛኛውም ከምንዳው እየተሰጠ የሰውየው ምንዳ ለተበዳዮች ተከፋፍሎ ያልቃል። ለተበዳዮች ካሳቸው ተከፍሎ ሳያበቃ የሰውየው ምንዳ ካለቀ: ከወንጀላቸው እየተነሳ ሰውየው ላይ ይጫንና ወንጀላቸው ተሸክሞ ወደ ጀሀነም ይወረወራል።" ብለው አስረዷቸው።

   "በዳዩ ሰውዬ ካፊር (ምንም ምንዳ የሌለው) ቢሆን ለተበዳዮች ምን ሊሰጥ ይችላል?" ለሚለው ጥያቄ ይህ ሐዲስ አጥጋቢ መልስ ይሰጣል። ከተበዳዮች ወንጀል እየተነሳ በዳዩ ላይ ይደረብና በስቃዩ ላይ ስቃይ እንዲጨምር ይደረጋል። በዚህ ሰበብ እነሱም ወንጀላቸው ይቀንስና ደርሶባቸው ለነበረው በደል ካሳ ይሆናቸዋል።

  አላህ ዘንድ በድሎ የሚተርፍም ይሁን ተበድሎ የሚከስር የለም!!
  ይህንን ስትረዳ እንደ በሻር ባሉ ፊርዓውኖች ላይ የነበረህ ቁጭት ፋታ ያገኛል።




🖊ሐምዱ ቋንጤ ከፉርቃን ሰማይ ስር!!
https://t.me/hamdquante


🇸🇾
  አላህ ዘንድ በድሎ የሚተርፍም ይሁን ተበድሎ የሚከስር የለም!!

  ይህንን ስትረዳ: እንደ በሻር ባሉ ፊርዓውኖች ላይ የነበረህ ቁጭት ፋታ ያገኛል።



በሰፊው እንመለስበታለን 👇👇👇👇

        https://t.me/hamdquante



አላህ ከፈጠራቸው ኸልቆቹ ሁሉ ርካሹ
ዱንያ ናት

ይላል ዛሬ በሰገድንበት የጁሙዐ ኹጥባ


🤲አላሁመ ርካሽ በሆነችዋ አትፈትነን🤲





    {…ከሰዎች…} ተብሎ ለተወሰኑት ቢገለፅም ሁላችንም የወደቅንበት ከባዱ ፈተና!!
  ሲደላን አምልከን ሲከፋን እንተዋለን


አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል፦
📖{وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يَعْبُدُ ٱللَّهَ عَلَىٰ حَرْفٍۢ ۖ فَإِنْ أَصَابَهُۥ خَيْرٌ ٱطْمَأَنَّ بِهِۦ ۖ وَإِنْ أَصَابَتْهُ فِتْنَةٌ ٱنقَلَبَ عَلَىٰ وَجْهِهِۦ خَسِرَ ٱلدُّنْيَا وَٱلْءَاخِرَةَ ۚ ذَٰلِكَ هُوَ ٱلْخُسْرَانُ ٱلْمُبِينُ}
{ከሰዎችም (ከኢማን) በጫፍ ላይ ሆኖ አላህን የሚገዛ ሰው አለ፡ መልካም ነገር ቢያገኘው በእሱ (በአምልኮው) ይረጋል፤ መከራ ብታገኘው በፊቱ ላይ ይገለበጣል፤ የቅርቢቱን ዓለምም የመጨረሻይቱንም ከሰረ፡፡ ይህ እሱ ግልጽ ኪሳራ ነው፡፡}


  ከመሃላችን አላህ የጠበቀው ካለ እንጂ የሁላችንም ባህሪ ነው።
  ስራው ሞቅ ሲል፣ አየሩ ሲደራ፣ ቤትና ሰፈር ሚያስጨንቅ ነገር ሲጠፋ፣ የምቾት አየር መተንፈስ ስንጀምር:
  ማሻ አላህ!! ዒባዳ ላይ፣ ደርስ ላይ፣ ነሲሀ ላይ፣ ሰደቃ ላይ በሁሉም ነገር ነሻጣ ይኖረናል።

  ልክ ስራው ሲጠፋ፣ አየሩ ሲቀዘቅዝ፣ አንዳንድ አስጨናቂ ጉዳዮች ሲገጥሙን የነበረችዋ ቲንሽዬ ኢማን ትሟጠጥና በሀሳብ እና በትካዜ ተወረን የዒባዳ ተነሳሽነታችን ይከስማል፤ እንኳንስ ተጨማሪ ዒባዳ ዋጂባቶች ላይ እንኳ ዕርጋታ አይኖረንም።

ይህ…………
   ሁላችንም ዘንድ የሚስተዋል ትልቅ ፈተና በመሆኑ ረሳችንን ገምግመን ማስወገድ ይኖርብናል።
 



አላህ ከዱንያ ፈተና ይጠብቀን እናጂ የኔው የባሰ ነው!!
https://t.me/hamdquante



ባለ ጊዜ ብትሆን አትበል እዩኝ እዩኝ
ጊዜህ ሲያበቃ ይመጣል ደብቁኝ!!




https://t.me/hamdquante


🇸🇾🤝🇵🇸
  {…فَانتَقَمْنَا مِنَ الَّذِينَ أَجْرَمُوا وَكَانَ حَقًّا عَلَيْنَا نَصْرُ الْمُؤْمِنِينَ}
{…ከእነዝያ ካመፁት ተበቀልን: ሙእሚኖች መርዳትም በእኛ ላይ የተገባ ሆነ።}



  የማይታጠፍ የማይቀየር የሆነ የረቡል ዓለሚን ቃል_ኪዳን ነው!!

☝️አላህ………
    ከሙጅሪሞች ተበቅሎ ምእመናኖች ይረዳል። ዛሬ በሶሪያ ቅቤ የጠጣው አንጀታችን ነገ በፈለስጢን ተደግሞ ደስታችን ሙሉ ይሆናል።
  የልዕለ ሀያሉ አላህ ቀል ነውና አትጠራጠሩ!!




https://t.me/hamdquante

20 last posts shown.