‹‹አይገርምም? ››አላት፡፡
ምን እንዳስገረመው ስላልገባት‹‹ምኑ?›› ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹ቅድም እዛ ካፌ ለአስተናጋጁ 5 ብር ቲፕ ሰጠሸ…አሁን ደግሞ ለእኛ አንድ ሺ ብር ጭማሪ ተሰጠን፡፡››
‹‹እሱስ ይገርማል…እውነትህን ነው፡፡››
‹‹አሁን ምን እናድርግ?››
‹‹እስከዛሬ አድርገነው የማናውቀውን ሌላ አንድ ነገር እናድርግ፡፡››አለችው ..ሀሳቡ ድንገት ነው በአእምሮዋ ብልጭ ያለው፡፡እሱ ያሰበችውን ለመስማት በጉጉት ይጠብቅ ጀመር፡፡
‹‹ምን እህቴ..?››
‹‹አልጋ ተከራይተን እንደር፡፡››
‹‹ምን?››ግራ ገባው ፡፡..እንዴት አሰበችው ሲል ተገረመ….?በቅፅበት በምታመጣቸው አስደንጋጭ ሀሳቦች ሁሌም እዳስደመሙት ነው፡፡ማብራራቷን ቀጠለች‹‹አዎ ይሄን ሁሉ ብር ይዘን ለምን እዚህ አፈር ላይ እንተኛለን፡፡ሻወር ወስደህ…ንፅህ አልጋ ላይ አንሶላ ገልጠህ ከላይ ንፅህ ብርድ ልብስና አልጋ ልብስ ደርበህ..ግድግዳና ጣሪያ ያለው ቤት ውስጥ መተኛት አልናፈቀህም..?››
‹‹በጣም እንጂ እህቴ በጣም ናፍቆኛል…ግን እውር ገና አይኑ እንደበራለት ምርኩዙን እንደሚጥል እኛም እንዳዛ መሰልን፡፡››አላት
‹‹ግድየለህም ይምሰል….በል ተነስ…..››ተያይዘው ሆቴሎች በርከት ብለው ወደሚገኙበት ሰፈር ሄዱ፡፡ መታወቂያ ስላልነበራቸው እና እድሜያቸውም ገና ጮርቃ በመሆኑ ምንም እንኳን ብሩ ቢኖራቸውም ቤርጎውን መከራየት ቀላል አልሆነላቸው፡፡ግን እነሱም በተለይ ኑሀሚ በቀላሉ ተስፋ የምትቆርጥ ልጅ ስላልሆነች ሌላ ዘዴ ዘየደች ፡፡ለአልጋ ክፍሏ ተጨማሪ 50 ብር ሰጥተው ያሰቡትን አልጋ አግኝተው በአሰቡት መንገድ ለማደር ቻሉ፡፡ያም ካሰቡት በላይ ጥልቅ ደስታና ለፍፁምነት የተጠጋ እርካታ አጎናፀፋቸው፡፡ናኦል በጥዋት ነበር ኑሀሚን አግለብልቦ ከቤርጎ ይዞት የወጣው፡፡ ሲቀሰቅሳት‹‹ወንድሜ ደግሞ ምን አለ ትንሽ ብንተኛ..?›ብላ ለምናው ነበር፡፡
‹‹ምነው ለሊቱን ሙሉ ተኝተሸ አይደል ያደርሽው ?አልጠገብሽም?››
‹‹እንዴ ትቀልዳል እንዴ ?እንዲህ እይነት ምቹ ክፍልና አልጋ ውስጥ ስልሳ ሶስት ቀን በተከታታይ ብተኛ እራሱ አልጠግብም፡፡››ስትል የእውነት የምታስበውን ነገረችው፡፡
‹‹እንደዛ ከሆነ ምን ችግር አለ? ብር አለን ዛሬ ማታም ደግመን እናድራለን..፡፡››ቃል ገባላት፡፡
‹‹አንተ ልጅ ይሄን ምቾት ለምደህ ወደጎዳናችን አልመለስም ብለህ እንዳታስቸግረኝ፡፡››ስጋቷን ተነፈሰች፡፡እንዲህ ልትናገር የቻለችው..በራሷ ሀሳብ ውስጥ እየበቀለ ያለው ተመሳሳይ ስሜት ስላለ ነው…ምን አለ ወደእዛ ጎዳና ባንመለስ የሚል…እሱም‹‹ባልመለስ ደስ ይለኛል.፡፡ለማንኛውም አሁን ቶሎ እንሂድ ምስራቅ መጥታ እንዳታጣን፡፡››አላት፡፡
‹‹ብታጣንስ ምን ችግር አለው?››በብስጭት ጠየቀችው፡፡
‹‹እንዴ ቁርስ ገዛልሻለሁ ብያትለሁ እኮ..አሁን ብታጣን ብሩን ሰስተን ነው የሚመስላት…ትቀየመናለች፡፡››
ሳቀችና‹‹ይሁንልህ፡፡››ብላ ክፍሉን ለቃ መንገድ ጀመረችለት፡፡ ..እሱም በደስታ ከኃላ ተከተላት፡፡ማደሪያቸው የነበረ ቦታ ሲደርሱ ገና አንድ ሰዓት ከሩብ ነበር…ምስራቅን ለማግኘት ግን እስከሁለት ሰዓት መጠበቅ ነበረባቸው፡፡
‹‹ጩጬዎቹ ሰላም ናችሁ?››በተለመደ ሰላታዋ ተቀላቀለቻቸው፡፡
‹‹አለን..ሰላም ነን…ቆየሽ፡፡››አላት ናኦል፡፡
‹‹ባሌ አለቅ ብሎኝ ነው የቆየሁት››ስትል መለሰችለት፡፡፡
‹‹እንዴ..ባል አለሽ እንዴ?››በድንጋጤ እና በቅሬታ ጠየቃት፡፡፡
‹‹አለኝ ..ግን ፀባይ የለውም ..ሌላ ባል ካገኘው እፈታዋለሁ፡፡››አለችው፡፡
‹‹አዎ ብትፈቺው ይሻላል፡፡››አላት ናኦል
‹‹ፈታውስ ….አንተ ልታገባት ነው?››ኑሀሚ በንዴት ጠየቀችው፡፡
‹‹እስካድግ ከጠበቀቺኝ አገባታለሁ፡፡››
ምስራቅም‹‹አረ ጠብቅሀለው፡፡››አለችው በፈገግታ ተሞልታ፡፡
‹‹ብትጠብቅህስ ምን ዋጋ አለው…አንተ እስክታድግ እኮ እሷ ታረጃለች፡፡››ኑሀሚ ነች አብሻቂ ንግግር የተናገረችው፡፡
ናኦል እንደመበሳጨት ብሎ‹‹አንቺ ደግሞ ታርጃ ምን ችግር አለው…አሁን እንሂዳ ..ቁርስ እንብላ፡፡››አለ
‹‹..እኔም የመጣሁት ለቁሩሱ ነው፡፡››ብላ ተያይዘው ሄዱ፡፡እስከ 3 ሰዓት ድረስ እዛው ቁርስ ቤት ሲበሉና የባጥ የቆጡን እያወሩ ሲጫወቱ ነው የቆዩት፡፡
ከዛ ድንገት ‹‹የሆነ ቦታ አብራችሁኝ ትሄዳላችሁ?››ስትል ጠየቀቻቸው፡፡
‹‹የት?››ኑሀሚ በተለመደ ጥርጣሬዋ ጠየቀች፡፡
‹‹እሱ ሚስጥር ነው..ስንደርስ ታዩታላችሁ፡፡››
‹‹እሺ እንሂድ››ነኦል በግብዣው ተስማምቶ ከመቀመጫው ቀድሞ ተነሳ፡፡ምስራቅ እየፈገግች ኑሀሚ እየተነጫነጨች ከኃላው ተከትለው ተያይዘው ሄድ፡፡ቀጥታ ታክሲ ተራ ነበር ይዛቸው የሄደችው፡፡ከዛ ስታዲዬም ተሳፈሩ፡፡ከዛ ጎተራ ታክሲ ውስጥ ገቡ፡፡መጨረሻ ሲደርሱ ወረዱና ፡፡በእግር መጓዝ ጀመሩ፡፡በዝምታ ወደምትወስዳቸው እየተከተሏት ነው፡፡ቀጥታ ወደኮንደሚኒዬም ነው ይዛቸው የሄደችው፡፡አንዱ ኮንዲንዬም ውስጥ ይዛቸው ገባችና በደረጃው እየወጡ የመጨረሻ ፎቅ ላይ ወደሚገኝ ክፍል ይዛቸው ገባች ፡፡ቁልፍ ከኪሷ አወጣችና ከፈተቸ፡፡ቀድማ ገባችና ‹‹ግቡ›› አለቻቸው…ግራ በመጋባትና በመደነቅ ተከትለዋት ገቡ፡፡
የሚያምር ቤትና የሚያማማሩ እቃዎች ያሉበት ባለሁለት መኝታ ክፍል ቤት ነው፡፡ሳሎኑ መሀከል ወለል ላይ ቆመው በመገረምና በመደነቅ ዙሪያ ገባውን እየተቁለጨለጩ ማየት ቀጠሉ፡፡እለፉና ሶፋው ላይ ተቀመጡ፡፡
‹‹በስመአብ ዘናጭ ቤት ነው…የድሮ ቤታችንን ይመስላል…ያንቺ ነው እንዴ?››ናኦል በአድናቆት እንደተሞላ ጠየቃት፡፡
‹‹አይ የወንድሜ ነው…ታስሮብኛል ያልኳችሁ ወንድሜ፡፡››
‹‹እ ነው… ታድሎ…››
‹‹ምን ታድሎ ትላለህ ..አምስት አመት እኮ ነው የተፈረደበት…ገና እስር ቤት ከገባ ስድስት ወሩ ነው..ቢያንስ ከሶስት አመት በላይ አዛ ይኖራል፡፡››
‹‹ያሳዝናል…››
‹‹አዎ ያሳዝናል..በሉ ዘና በሉ ፡፡ሱቅ ደርሼ መጣሁ፡፡›› ብላ ቴሌቪዢኑን ከፈተችላቸውና የፈለጉት ጣቢያ ላይ መቀያየር እንዲችሉ ሪሞቱን አቀብላቸው ወጥታ ሄደች፡፡
ኑሀሚም ኮቴዋ መራቁን እርግጠኛ ከሆነች በኃላ‹‹አልሰማ አልከኝ እንጂ ንግሬሀለው››አለችው፡፡
‹‹ምኑን ነው የነገርሺን?››
‹‹ይህቺ ሴት ማፍያ ነገር ነች…እያት እስኪ በየቀኑ እንድ አዲስ ነገር ታሳየናለች፡፡››
‹‹ቢሆን ግን ለእኛ እኮ ደግ ሆናልላለች፡፡››
‹‹የሸከከኝ እኮ እሱ ነው፡፡ለምን ደግ ሆነችልን….?ለምን አላማ ፈለገችን…?ብቻ ዝም ብለህ እትንሰፍሰፍላት፤በጥንቃቄ ተከታተላት፡፡››
በምትናገረው ነገር ሙሉ በሙሉ ባያምንበትም ከእሷ ጋር ጨከን ብሎ መከራከሩን ሳላልፈለገ ‹‹እሺ እንዳልሽ፡፡››አላት፡፡
ወዲያው ምስራቅ በኩርቱ ፔስታል ሙሉ የቤት አስቤዛ ገዝታ መጣችና ፍሪጅ ውስጥ ትጠቀጥቀው ጀመር፡፡
../////
ካርሎስ ከጥልቅ እንቅልፉ ባኖ ሲንሳቀስና ነበር እሷም ከጥልቅ ትዝታዋ ባና ከሀገር ቤት የቆየ ታሪኳ አሁን ወዳለችበት ነባራዊ ሁኔታ የተመለሰችው ፡፡በዛ ድቅድቅ ለሊት በአማዞን ጥቅጥቅ ደን ማህፀን ውስጥ የተንጠለጠሉበት ግዙፍ ዛፍ ቀርንጫፍ ላይ ከአንድ ጎረምሳ ደረት ላይ ተለጥፋ መገኘቷን ስተስበው ተአምር የሚያስብል ሆኖ ነው ያገነችው፡፡
ይቀጥላል
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
https://t.me/manbabemulusewyaderegal
https://t.me/manbabemulusewyaderegal
https://t.me/manbabemulusewyaderegal
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️