የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር👏


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Religion


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮንና ስርዓትን የጠበቁ ያሬዳዊ መዝሙሮች ግጥማቸውን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ።@abnat19

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Religion
Statistics
Posts filter


#ዘጠኝ_ሰዓት_ሲሆን

ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን አባት ሆይ
በመስቀል ሆነህ አባት ሆይ
ድምጽህን በማሰማት አባት ሆይ
ነፍስህን ሰጠህ አባት ሆይ

ከዋክብተ ሰማይ በሙሉ ረገፉ
ጨረቃና ፀሐይ ደምን አጎረፉ
ብርሃናት ጨለሙ ጠፍተው ተለያዩ
ሥጋህን በመስቀል ተገልጦ ስላዩ
#አዝ
ጌታችን ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሳለ
አሰምቶ ጮኸ ተጠማሁ እያለ
ማርና ወተትን ለሚመግበው
ሐሞት አመጡለት ይቅመሰው ብለው
#አዝ
አካሉ ሲወጋ ውኃ ደም ፈሰሰ
በምድር ተረጭቶ ዓለምን ቀደሰ
የእሥራኤል ሴቶች ዋይ ዋይ ሲሉልህ
ለእነርሱ አዘንክ እንጂ ለአንተስ አላሰብክም
#አዝ
እናትህ ስታለቅስ በመስቃል ሥር ሆና
ዮሐንስን ሰጠህ ጠብቆ እንዲያፅናና
መላእክትም ታዩ አጋንንትም ሸሹ
የአይሁድ ሠራዊት ፈርተው ተረበሹ

ሊቀ-መዘምራን
ኪነ-ጥበብ ወልደ-ቂርቆስ


ጌታዬ ሆነ ደም ግባት አልባ

➮ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

ጌታየ ሆነ ደም ግባት አልባ፤
ጀርባዉ በጅራፍ ስለኔ ደማ፣
የኔን መገርፍ እረሱ ተገርፎ፣
ክብር አለበሰኝ እርሱ ተገፎ/2/፣


በሀሰት ሸንጎ ወጥመድ ተጠምዶ፣
ጌታ ተያዘ ህይወቴን ፈቅዶ፣
ክፉዎች ቢያዩት እንደ ወንበዴ፣
ለኔ ግን ሆኗል መዉጫ መንገዴ/2/፣


ታስረኃል ስለኔ ኢየሱስ መድኅኔ፣
ታስረኃል ስለኔ ኢየሱስ መድኅኔ፣


ጌታዬ ሆነ ደም ግባት አልባ፣
ጅርባዉ በጅራፍ ስለኔ ደማ፣
የኔን መገረፍ እርሱ ተገርፎ፣
ክብር አለበሰኝ እርሱ ተገፎ/2/፣


ሲዘብቱበት ምራቅ ሲተፉ፣
የማይደፈር ደፍረው ሲዘልፉ፣
በከበቡት ፊት ቃል ከለከለ፣
እኔ እንድናገር እርሱ ዝም አለ/2/፣


ታርደኃል ስለኔ ኢየሱስ መድኅኔ፣
ታርደኃል ስለኔ ኢየሱስ መድኃኔ ፣


ጌታዬ ሆነ ድም ግባት አልባ፣
ጀርባዉ በጅራፍ ስለኔደማ፣
የኔን መገረፍ እርሱ ተገርፎ፣
ክብር አለበሰኝ እርሱ ተገፎ/2/


ህይወት መንጭቷል ተወግቶ ጎኑን
ለከሳሾቹ ተርፏል ማዳኑ፣
እጅ እግሩን ምስማር ሲቸነክርዉ
የሞትን እሾህ ከኔ ነቀለዉ/2/፣


ተወጋ ስለኔ ኢየሱስ መድኃኔ፣
ተወጋ ስለኔ ኢየሱስ መድኃኔ፣


ጌታዬሆነ ደም ግባት አልባ፣
ጀርባዉ በጅራፍ ስለኔ ደማ፣
የኔን መገረፍ አርሱ ተገርፎ፣
ክብር አለበሰኝ አርሱ ተገፎ/2/፣


እርቃኑን ሆኖ ፈተነዉ ልብሴን፣
አንዲሁ ወዶኝ ጠጣ ቆምጣጤ፣
በምህረቱ ጥል ነብሴን አርክቶ፣
አለመለመኝ አርሱ ተጠምቶ/2/፣

ተጠማ ስለኔ ኢየሱስ መድኃኔ ፣
ተጠማ ስለኔ ኢየሱስ መድኃኔ፣


|°°ለጀማሪ የግእዝ ቋንቋ ወዳጆች ሁሉ
  🙌 ሰላም ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን የልሳነ ግእዝ ስልጠና በ @ye_mariam_agelgay እየሰጠን እንደሆነ ይታወቃል ሆኖም የጀማሪዎች ስልጠና  በቅርቡ በonline ስለሚጀመር በዚህ #ዙር ላይ 25 ተማሪዎች ብቻ ስለሚካተቱ ከወዲሁዠለጀማሪችሁን እንድታዘጋጁና በፍጥነት እንድትመዘገቡ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
#ለሁለት ወር የመማሪያ ሙሉ ክፍያ #250ብር ብቻ ከነ የምስክር ወረቀቱ ለበለጠ መረጃ በ @asrategabriel ያነጋግሩን አልያም በ +251970908094 ይደውሉልን።

   🤲ሰብሕዎ የልሳነ ግእዝ ማሰልጠኛ ተቋም🧑‍🎓


#ጾም_ወጸሎት

ጾም ወጸሎት ወተፋቅሮት
ሃይማኖት ወምጽዋዕት/ታድህን እሞት/(፪) ታበፅዕ መንግስተ ሰማያት
#ትርጉም
ጾምና ጸሎትና መፈቃቀር ሃይማኖት እና ምጽዋት ከሞት ታድናለች ለመንግስተ ሰማያትም ታበቃለች።

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
https://t.me/Yemezmurgtm
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯


በየገዳማቱ

በየገዳማቱ በየበረሃው ውስጥ
ስለተሰደዱት ፍቅርህን በመምረጥ
የዓለም ውዳቂ ምናምንቴ ሆነው
ስለ ፍቅርህ ሲሉ ክብራቸውን ትተው
እግዚአብሔር ሆይ ማረን /2/
አዝ

የዓለም ውዳቂ ጉድፍ በተባሉት
በምድር እየኖሩ በጽድቅ ህይወት ባሉት
ዓለም አና አምሮቷን ትተው በመነኑት
ኢየሱስ ሆይ ማረን እግዚአብሔር ሆይ ማረን /2/
አዝ

ህያዋን በሆኑት እስከ ዘለዓለም
ከኢየሱስ ጋራ ሞተው በመስቀል ዓለም
ዓለም የናቃቸው እነርሱም በናቁት
አምላክ እራራልን አትጨክን በእውነት /2/

ሊቀ መዘራን ይልማ ኃይሉ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️


ጌታየ ሆነ ደም ግባት አልባ
ጀርባዉ በጅራፍ ስለኔ ደማ
የኔን መገርፍ እረሱ ተገርፎ
ክብር አለበሰኝ እርሱ ተገፎ ( ፪ )

በሀሰት ሸንጎ ወጥመድ ተጠምዶ
ጌታ ተያዘ ህይወቴን ፈቅዶ
ክፉዎች ቢያዩት እንደ ወንበዴ
ለኔ ግን ሆኗል መዉጫ መንገዴ ( ፪ )
ታስረኃል ስለኔ ኢየሱስ መድሕኔ
ታስረኃል ስለኔ ኢየሱስ መድሕኔ

ጌታዬ ሆነ ደም ግባት አልባ
ጅርባዉ በጅራፍ ስለኔ ደማ
የኔን መገረፍ እርሱ ተገርፎ
ክብር አለበሰኝ እርሱ ተገፎ ( ፪ )

ሲዘብቱበት ምራቅ ሲተፉ
የማይደፈር ደፍረው ሲዘልፉ
በከበቡት ፊት ቃል ከለከለ
እኔ እንድናገር እርሱ ዝም አለ ( ፪ )
ታርደኃል ስለኔ ኢየሱስ መድሕኔ
ታርደኃል ስለኔ ኢየሱስ መድሕኔ

ጌታዬ ሆነ ድም ግባት አልባ
ጀርባዉ በጅራፍ ስለኔደማ
የኔን መገረፍ እርሱ ተገርፎ
ክብር አለበሰኝ እርሱ ተገፎ ( ፪ )

ህይወት መንጭቷል ተወግቶ ጎኑን
ለከሳሾቹ ተርፏል ማዳኑ
እጅ እግሩን ምስማር ሲቸነክርዉ
የሞትን እሾህ ከኔ ነቀለዉ ( ፪ )

ተወጋ ስለኔ ኢየሱስ መድሕኔ
ተወጋ ስለኔ ኢየሱስ መድሕኔ

ጌታዬሆነ ደም ግባት አልባ
ጀርባዉ በጅራፍ ስለኔ ደማ
የኔን መገረፍ አርሱ ተገርፎ
ክብር አለበሰኝ አርሱ ተገፎ ( ፪ )

እርቃኑን ሆኖ ፈተነዉ ልብሴን
አንዲሁ ወዶኝ ጠጣ ቆምጣጤ
በምህረቱ ጥል ነብሴን አርክቶ
አለመለመኝ አርሱ ተጠምቶ/ ፪ /

ተጠማ ስለኔ ኢየሱስ መድሕኔ
ተጠማ ስለኔ ኢየሱስ መድሕኔ

✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥


|°°ለጀማሪ የግእዝ ቋንቋ ወዳጆች ሁሉ
  🙌 ሰላም ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን የልሳነ ግእዝ ስልጠና በ @ye_mariam_agelgay እየሰጠን እንደሆነ ይታወቃል ሆኖም የጀማሪዎች ስልጠና  በቅርቡ በonline ስለሚጀመር በዚህ #ዙር ላይ 25 ተማሪዎች ብቻ ስለሚካተቱ ከወዲሁዠለጀማሪችሁን እንድታዘጋጁና በፍጥነት እንድትመዘገቡ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
#ለሁለት ወር የመማሪያ ሙሉ ክፍያ #250ብር ብቻ ከነ የምስክር ወረቀቱ ለበለጠ መረጃ በ @asrategabriel ያነጋግሩን አልያም በ +251970908094 ይደውሉልን።

   🤲ሰብሕዎ የልሳነ ግእዝ ማሰልጠኛ ተቋም🧑‍🎓


#አዘነች_ድንግል_አለቀሰች

አዘነች ድንግል አለቀሰች ፍጹም አምርራ
በአንድ ልጇ ምክንያት ደርሶባት መከራ
በአንድ ልጇ ምክንያት ደርሶባት መከራ/፪/

አዝ

በመንጻቱ ወር በዓርባኛው ቀን
ሥምዖን አረጋዊ ታቀፈ እና ጌታን
ትንቢት ተናገረ ተገልጾለት ሞቱ
በነፍስሽ ሠይፍ ያልፋል አንቺም እናቲቱ
ይኽንን መከራ ሲሠማ ጆሮዋ
አምርራ አለቀሰች አልቆም አለ ዕንባዋ

አዝ

በአሥራ ሁለት ዓመቱ ለማክበር በዓል
በኢየሩሳሌም ቢገኝ አማኑኤል
ሲጠይቅ ሲሠማ በቤተ መቅደሱ
የኦሪት ካኅናት ሲደነቁ በእርሱ
እስከ ሦስት ቀን ድረስ ብትልጣው ፈልጋ
ልቧ ተሠበረ በሐዘን አለንጋ

አዝ

ጠዋት በማለዳ በጲላጦስ ደጅ
ሲጸናበት አይታ የጨካኞች እጅ
ርቃኑን አድርገው ያለ አንዳች ጥፋት
ከግንድ ጋር አስረው ጀርባውን ሲገርፉት
እንዴትስ አታለቅስ እንዴት አታነባ
ሲገርፉት ሲያዳፉት ልጇን እንደ ሌባ

አዝ

የዓለሙን ፈጣሪ የዓለሙን ዳኛ
ንጹሑን ጌታ መሥሏቸው ቀማኛ
እጁን እና እግሮቹን በችንካር ወጥረው
በወንበዴ መሐል ሠቅለውን ብታየው
ድንግል አለቀሰች አልቻለች መጽናናት
ዕንባዋ ወረደ እንደ ክረምት ጅረት

አዝ

ዮሴፍ ኒቆዲሞስ በአንድ ሲማከሩ
ቅዱሥ ሐያል ብለው ገንዘው ሊቀብሩ
በአዲስ መቃብር በአሥራ አንደኛው ሠዓት
ሥጋውን አኑረው በድንጋይ ቢዘጉት
እያለች ዐነባች አንድ ልጄ እኮ ነው
ከእርሱ የሚቀድም ተከታይ የሌለው።


በድንግል_ትህትና

በድንግል ትህትና አለምተደነቀ /2/
እዉነተኛ መጠጥ ከሆዷ ፈለቀ /2/
ሰዉ የሚድንበት ሮማንና ገዉዝ /2/
ከሆዷ ፈለቀ እንደ ምንጭ እንደወንዝ /2/

አዝ

ፀጋን ስላደላት የመዉለድ ስጦታ/2/
በፍቅር ሳበችው የፍጥረቱን ጌታ /2/
ሰማያዊዉ አምላክ ከእርሷ ሥጋንነሳ /2/
ፀሐይ ስለወጣ ቀረልን አበሣ /2/

አዝ

እስኪ ተመልከቱት ይህንን ደስታ ይህን ታላቅ ነገር
ወልድን በመዉለዷ በፀጋ ሥንከብር /2/
ታላላቅ አንስቶች እናቶች ቢባሉም /2/
አምላክን በመዉለድ እርሷን አያህሉም /2/

አዝ

እስኪ ተመልከቱት ይህንን ደስታ ይህን ታላቅ ነገር
ወልድን በመዉለዷ በፀጋ ሥንከብር /2/
ታላላቅ አንስቶች እናቶች ቢባሉም /2/
አምላክን በመዉለድ ድንግልን አይቀድሙም /2/

አዝ

እግዚአብሔር ምድርን አየና በመላ /2/
ማርያምን አገኛት ከቤተ-መቅደሱ ከቤቱ ተጥላ
ከመላዕክቱ ጋር እየተጫወተች /2/
የሰማዩን መና እየተመገበች /2/


እጠበኝ ቆሽሻለው

እጠበኝ ቆሽሻለሁ
አምላኬ በድያለሁ
ያለናት ያሳደከኝ
ያላባት የጠበከኝ
   ያንሁሉ ዛሬ እረሳሁ
   እጠበኝ ቆሽሻለሁ (፪)

ከድንኳንህ ብታስገባኝ ሞገስ ሰጥተህ
የአፍኒን ምግባር ይዤ አስቀየምኩህ
ቅባ ሜሮን ያተምክበት ልጅነቴ
እንዳይጎድፍ ጠብቅልኝ ቸር አባቴ

ሃይል አኑረህ እንደ ሶምሶን በፀጉሬ
ጎልያድን አስጥለኸኝ በጠጠሬ
አቅም ቢያንሰኝ በስጋ ጦር ተሸንፌ
ደጅህ መጣሁ የንባ መባ ባይኔ አቅፌ

እንዳትረሳኝ በመዳፍህ ቀርፀኸኛል
እንዳተወኝ ያለመጠን ወደኸኛል
ባትሰነዝር ልትቀጣኝ የሞት በትር
የትግስትህ ሰሌዳ ነው ለኔ ክብር

ከከንፈሬ ጥበብ ፅፈህ ቅኔ ቢፈስ
በመታበይ አሳዘንኩት ያንተን መንፈስ
ፍቅር ግተህ ከቅፍህ ስር ያሳደከኝ
እባክህን በበደሌ አትቅሰፈኝ


𓆩 ዮሐንስን ይዛ 𓆪

ዮሐንስን ይዛ ወደ ቀራንዮ
ድንግል ማርያም ሄደች እያለች ወዮ
ሥለ ልጇ ሐዘን ሥለ መከራዋ
ያስገርም ነበረ የፈሰሰው ዕንባዋ /፪/

ዮሐንስ ቢደንቀው የሐዘኗ ጽናት
አነሳት ደግፎ በብርቱ ሊያጽናናት
ድንግልም አለችው ልጄ አሳዘነኝ
እሕት ወንድም የለው ላልቅስለት ተወኝ

ከሁሉም ይበልጣል ያስደፋል አንገትን የማርያም ሐዘን

መቅደላዊት ማርያም ሶሎሜ ዮሐና
ማርያምን አይዋት ጸንቶባት ሐዘኗ
በልቅሶዋ ጣዕም ተነክቶ ልባቸው
ዕንባን አፈሰሱ ውለታው ገብቷቸው

ከሁሉም ይበልጣል ያስደፋል አንገትን የማርያም ሐዘን

ራሔል አልቅሳለች ላላቀፈቻቸው
ድንግል ግን ብታለቅስ አዝላው ተሰዳ ነው
ያዕቆብም አልቅሷል በሌላ የሠው ደም
ማርያም ግን ብታለቅስ ፈሷል የልጇ ደም

ከሁሉም ይበልጣል ያስደፋል አንገትን የማርያም ሐዘን

ጠብቶ ስለአደገ የድንግልና ጡቷን
መቆም አልቻለችም ስታይ መጠማቱን
በደም ተሸፍኖ ብታየው ውበቱን
ለይልኝ አለችው ከሥጋዋ ነፍሷን

ከሁሉም ይበልጣል ያስደፋል አንገትን የማርያም ሐዘን

ዮሐንስን ይዛ ወደ ቀራንዮ
ድንግል ማርያም ሔደች እያለች ወዮ
ሥለ ልጇ ሐዘን ሥለ መከራዋ
ያስገርም ነበረ የፈሰሰው ዕንባዋ


ጌታዬ ሆነ ደም ግባት አልባ

➮ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

ጌታየ ሆነ ደም ግባት አልባ፤
ጀርባዉ በጅራፍ ስለኔ ደማ፣
የኔን መገርፍ እረሱ ተገርፎ፣
ክብር አለበሰኝ እርሱ ተገፎ/2/፣


በሀሰት ሸንጎ ወጥመድ ተጠምዶ፣
ጌታ ተያዘ ህይወቴን ፈቅዶ፣
ክፉዎች ቢያዩት እንደ ወንበዴ፣
ለኔ ግን ሆኗል መዉጫ መንገዴ/2/፣


ታስረኃል ስለኔ ኢየሱስ መድኅኔ፣
ታስረኃል ስለኔ ኢየሱስ መድኅኔ፣


ጌታዬ ሆነ ደም ግባት አልባ፣
ጅርባዉ በጅራፍ ስለኔ ደማ፣
የኔን መገረፍ እርሱ ተገርፎ፣
ክብር አለበሰኝ እርሱ ተገፎ/2/፣


ሲዘብቱበት ምራቅ ሲተፉ፣
የማይደፈር ደፍረው ሲዘልፉ፣
በከበቡት ፊት ቃል ከለከለ፣
እኔ እንድናገር እርሱ ዝም አለ/2/፣


ታርደኃል ስለኔ ኢየሱስ መድኅኔ፣
ታርደኃል ስለኔ ኢየሱስ መድኃኔ ፣


ጌታዬ ሆነ ድም ግባት አልባ፣
ጀርባዉ በጅራፍ ስለኔደማ፣
የኔን መገረፍ እርሱ ተገርፎ፣
ክብር አለበሰኝ እርሱ ተገፎ/2/


ህይወት መንጭቷል ተወግቶ ጎኑን
ለከሳሾቹ ተርፏል ማዳኑ፣
እጅ እግሩን ምስማር ሲቸነክርዉ
የሞትን እሾህ ከኔ ነቀለዉ/2/፣


ተወጋ ስለኔ ኢየሱስ መድኃኔ፣
ተወጋ ስለኔ ኢየሱስ መድኃኔ፣


ጌታዬሆነ ደም ግባት አልባ፣
ጀርባዉ በጅራፍ ስለኔ ደማ፣
የኔን መገረፍ አርሱ ተገርፎ፣
ክብር አለበሰኝ አርሱ ተገፎ/2/፣


እርቃኑን ሆኖ ፈተነዉ ልብሴን፣
አንዲሁ ወዶኝ ጠጣ ቆምጣጤ፣
በምህረቱ ጥል ነብሴን አርክቶ፣
አለመለመኝ አርሱ ተጠምቶ/2/፣

ተጠማ ስለኔ ኢየሱስ መድኃኔ ፣
ተጠማ ስለኔ ኢየሱስ መድኃኔ፣


ዘወትር እሻለሁ
በዘማሪት ሲስተር ፋሲካ መኮንን
+++

ዘወትር እሻለሁ አምላኬ አንዲት ነገር(2)
ለዘላለም በቤትህ በደስታ መኖር(2)

ቢርበኝ ቢጠማኝም ውሃ
ቢከብድም ኑሮ እንደበረሀ
ናፍቆቴ የልቤ መሻቷ
መኖር ነው ሳትለይ ከቤቷ

በዓለም ክብር ድንኳን ከምቀመጥ
በስጋ ምንም ብንቆጠቆጥ
በፀሎት ሁሌ የምለምነው
በቤትህ ዘለዓለም መኖር ነው

አላጎድል አትራፊ ነኝ እኔ
በቤትህ ስቀኝልህ ቅኔ
ምስጋናው ቅኔው ማህሌቱ
ማረፊያዬ ነው ቅዳሴው ሰአታቱ

ለምለም ነው መሰማሪያ መስክህ
ፀጥታ ሰላም ነው መንገድህ
መልካሙን ደስ የሚያሰኝህን
አያለሁ እየኖርኩ በቤትህ


ቅዳሴ ማርያም አዜማለው

ቅዳሴ ማርያም አዜማለው
ውዳሴሽንም አደርሳለው
መልክሽን ስደግም ለፍልሰታ
ተገለጪልኝ ጠዋት ማታ

በምን ስራዬ ነው ማይሽ
ምኞቴ ነው ስለምወድሽ
ፍቅርሽ ጠርቶኝ ለምስጋና
ተሰለፍኩኝ እንደገና
   ልቤ አንቺን ፈልጎይዞራል
   አየራትን ሰንጥቆ ይበራል
   አሳራፊው በምልጃሽ ማርያም/2/
   ያላንቺ የሚሆን የለም/2/
  
አዝ_____

በኔ ሀይማኖት ባንቺ ጸሎት
ፈውስ አገኘው ከመለኮት
በልቤ አይን እያየውሽ
በሀሳቤም አገኘውሽ
    ታቦት ነሽ የመንፈስ ቅዱስ
    ነሽና ያርያም እህት
    የምንጠጣሽ ንፁህ የምንጭ ውሃ/2/
    ሀብታችን ገንዘብ ነሽ ለደሀ/2/
  
አዝ_____

ቀርቢያለው በንስሀ
እዘኝልኝ አዛኝቷ
አለም ጠልፋ እንዳትጥለኝ
ጥበቃሽም አይለየኝ
     አይጠፋም ከሰው ልጅ ስተት
     ምክንያት ነሽ ለአለሙ ድህነት
     አክሚልኝ የልቤን ሀዘን/2/
     እማምላክ እመብርሀን/2/

አዝ___

ናዛዚቱ ለዮሴፍ
ምስጋና አለሽ ከአእላፍ
ስምሽ ስልጡን በእግዚአብሔር ዘንድ
ከአለም አንስት መርጦሻል ወልድ
       የሰማይ የሰማይ ደጅነሽ
       ያእቆብ በሎዛ ነው ያየሽ
       መመኪያችን የፅድቃችን አንባ/2/
       አሳስቢ ገነት እንድንገባ/2/

                    መዝሙር
      ✧ ዘማሪ ቀሲስ እንግዳወርቅ ✧




የኔ መሃሪ ሁሉን መርሻዬ
እንደ ሕልም አልፏል
ትላንትናዬ ባንተ ጌታዬ


አዳፋው ልብሴ ከነፃ
ከእዳ ከፈታኝ በነፃ
ለፅድቁ ባርያ ሆኛለው
ሳገለግለው እኖራለሁ

የእንባ ዘለላን ያቀፈው
አይኔም እልልታ ተረፈው
ደልዳዩ መዳፍ ደርሶልኝ
ተራራው ሜዳ ሆነልኝ

አይኖቼን ከጉድ ጋርዶልኝ
ክንዶቼን በጁ ይዞልኝ
ከእግሬ በታች ነው ወጀቡ
አሁን ታይቶኛል ወደቡ

ሰላም ይነፍሳል ዙሪያዬ
እረፍት ሆኖልኝ ጌታዬ
የባረከኝን ባርኬ
ተለወጠልኝ ታሪኬ

ብርሃንህ ገፏል ድቅድቁን
በልቤ ተክሏል ሰንደቁን
ተቆጣጥሮኛል መውደዱ
መንገዴ ሆኖአል መንገዱ

ያበቃው ነገር ቀጥሏል
ጭንቄ በሞቱ ተሰቅሏል
የኢየሱስ ሁኝዔ ምን አጣው
ሁሉን በስሙ ተወጣሁ

እንደኔ ማንን ታግሷል
ይቅርታ ፍቅሩን አልብሷል
ማይገባኝን አድርጎ
ያሳለፈኝን ሸሽጎ

መልካም ነው ለኔስ መልካም
ፀጋው ያገዘኝ ስደክም
ሞትኩኝ ስል ምህረት ደርቦ
አቆመኝ በሕይወት አስውቦ

ዘማሪ የአብቃል ደሳለኝ




የአንተ ሥራ

ያንተ ስራ /፫/ ለዓለም ይወራ (፪)

በዮሐስ ወንጌል በምዕራፍ አምስት
መፃጉ ተብሎ ተኝቶ ባራት
ዘመን ያስቆጠረ ሰላሳ ስምንት
ተነሳ ተባለ አገኘ ማህረት

ያንተ ስራ /፫/ ለዓለም ይወራ (፪)

ሰውነቱ ደቆ እጅግ የታመመ /፪/
በእርሱ ድንቅ ሥራ አልጋ ተሸከመ /፪/

ያንተ ስራ /፫/ ለዓለም ይወራ (፪)

ወገን ያልነበረው ወድቆ የተረሳ /፪/
ምህረት አገኘና በድንገት ተነሳ /፪/

ያንተ ስራ /፫/ ለዓለም ይወራ (፪)

ያዳነው ኢየሱስ መሆኑን ሲናገር
ያልተፈቀደውን ይኸው ሰንበት ሲሽር
አየነው ሰማነው አያሻም ምስክር
ብለው ተነሱበት በጠማማ ምክር

ያንተ ስራ /፫/ ለዓለም ይወራ (፬)


Forward from: ࿇EL҉O҉H҉E҈ P҉I҉C҉T҉U҉R҉E҈S҉࿇
✨ ELOHE PICTURE

"ሁሉ ነገራችን በእግዚአብሔር ላይ ከጣልን በዛው ልክ ደግሞ በሁሉ ነገራችን የእግዚአብሔር እጅ ሲሰራ እናየዋለን ”

♡ ㅤ  ⎙ㅤ    ⌲        ✉️    Lᶦᵏᵉ   ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
ቶሎ ቶሎ እንድንለቅ ሪያክሽን እንዳይረሳ ❤️
     ➪ ꌗꃅꍏꋪꍟ ꌩꂦꀎꋪ ꎇꋪꀤꍟꈤꀸ

🔻🔻ይቀላቀሉን 🔗🔗⏰
https://t.me/+Ci5F1FcleWtlZThk



20 last posts shown.