☞ጥር 15 የህፃኑ ቂርቆስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ዓመታዊ በአል በሰላም
አደረሳችሁ፡፡
☞ቂርቆስ ማለት የኤፍሬም ቀለም ማለት ነው፡፡ አባቱ ቆዝምሳ እናቱ እየሉጣ
ይባላሉ፡፡
☞እየሉጣ ማለት ምልእት ሃይማኖት ማለት ነው፡፡
☞ሀገሯ ሮም ነው፡፡ አለእክስንድሮስ በነገሠ ጊዜ በሃይማኖት ምክንያት
በምእመናን ላይ ሰደት ደረሰባቸው፡፡
☞ኢየሉጣም የ3ዓመት ልጇን ሕፃኑ ቂርቆስን ይዛ ከሮም ጠርሴስ ተሰዳ
ተቀመጠች፡፡
☞ንጉሡ ከርስቲያኖችን ወደ ሸሸብበት ሀገር ደርሶ አገኛቸው ተይዛ ቀረበች፡፡
☞መኩኑንም ሀገርሽ የት ነው፡፡ ሰምሽ ማን ይባላል ? አላት፡፡ እሷም ሀገሬ
አንጌቤን ዘርም ስሜ ክርስቲያን ነው፡፡ ከአንተ ሸሽቼ ብወጣ አገኘኸኝ አለችው፡፡
☞መኮኑኑም ሽምሽን ግለጪ ለጣኦቴ ስገጂ አላት እንዳትሞቺ ሲል ጠየቃት፡፡
ሞት የሚሽር ስሜ ኢየሉጣ ነው አለችው፡፡ ለአማልክቴ መስዋዕት አቅርቢ አላት፡፡
እሷም እውነቱን ለማወቅ ከፈለግኽ መልዕክተኛ ልከኽ የ3 ዓመት ልጄን
አስመጣና የምናመልከውን እሱ ይነግርሃል አለችው፡፡
☞ያን ጊዜ ወታደሮቹን ልኮ ቂርቆሴን አግኝተው አመጡለት፡፡ ሲመጣም ስምህ
ማነው አለው? ከንጹሕ ምንጭ ከማይጠፋ ውሃ የተገኘ ክርስቲያን ነው
የምባለው አለው፡፡ ስሜን የምትሻ ከሆነ ቂርቆስ ነወ የምባለወ አለው፡፡
☞መኩንኑም ስታድግ ሹመት ሽልማት አሰጥሀለሁ በወርቅ በብር አከብርኻለሁ
ለአማልክቴ ስገድ አለው፡፡ እሱም የሰይጣን ወዳጅ የበጉ ሥራ ጠላት ዘወር
በልልኝ አለው፡፡ በዚህም ተነዶ ቆዳውን አስገፈፈው፡፡ እንደ ገና በእናቱና በእሱ
አፋንጫ ጨውና ሰናፍጭ አሰጨመረባቸው፡፡
☞ያንጊዜ መራራው ለጉሮሮቸው ጣፋጭ ሆነላቸው፡፡ ከመዐር ከስኳር ይልቅ ላፌ
ጣፈጠኝ እያለ ይዘምር ጀመር፡፡
☞መኮንኑም 14 ችንካር አሠርቶ በእሳት አግሎ 7 በእየሉጣ 7 በቂርቆስ ላይ
እንዲቸነክሩ አዘዘ፡፡ ያን ጊዜ ቂርቆስ ዐይኑን ጆሮውን አፍንጫውን አፋን ልቡን
ቸነከሩት፡፡ በጌታ ፈቃድ ብረቶቹ ጤነኛ ኾኑ፡፡ ከዚያ በኃላ አይን የሚያወልቅ
ዐንገትን የሚሰብር አፍንጫን የሚበሳ ምላስን የሚቆርጥ ጉልበትን የሚሰብር
የሥቃይ መሣሪያ አሠርቶ በጽኑ አመቃያቸው፡፡ በተጨማሪም መጋዝ አድርጎ
ከቅባትና ከጨው ጋር በብረት ምጣድ ቆላቸው፡፡ ጌታችን ከሞት አድኖ
አሰነሳቸው፡፡
☞መኮንኑም በእውነት ከሞት ከተነሣችሁ ያደረጉት ጫማ ሕያው ኹኑ ይነሣል
አለ፡፡ ጫማው በቅዱስ ቂርቆስ ጸሎች በሬ ኹኖ ከአንገቱ ፍየል ወጣ፡፡ ብዙ ሺ
ሰወች በልተው በቅቷቸው ተርፏቸዋል፡፡ ይህ በቂርቆስ ጸሎት ተደረገ፡፡ በዚህ
አፎሮ የሕፃኑን ምላስ አስቆረጠው፡፡ ጌታም እንደነበረ አድርጎ መለሰለት፡፡
☞እንደ ገና በብረት ውሃ አፍልቶ እንዲከቷቸው አዘዘ፡፡ እናት እየሊጣ ፈራች እናቴ
አይዞሽ አናንያን አዛርያን ሚሳኤል ያደነ ፈጣሪ ያድነናል እያለ አበረታት ጸሎትም
አደረጉ መንግስተ ሰማያትን አይታ ኅይል አግኝታ ተጽናናች፡፡ ሐምሌ 19 ቀን በጋን
በተፈላ ውሃ ገቡ፡፡ ቅዱስ ገብርኤል እንደ አይን ጥቅሻ እንደ ማዕለዳ ውርጭ
አደረገው፡፡
☞ከዚያ ጌታ የልብህንመሻት ለምነኝ አለው፡፡ ቂርቆስም ሥጋዬን በመሬት
አይቀበር መታሰቢያን ለሚያደርጉ ቤተክርስቲያኔን ለሚሰሩ ዜና ተጋድሎዬን
ለሚጽፍ ለሚያኑብ መባዕ ለሚሰጡ በቤተ ክርስቲያኔ ገብቶ ለሚጸልየው
ፍላጉቱን ስጠው ኃጢአቱንም ይቅር በለው፡፡ ስሜ በተጠራበት ማየ ጸሎት
በተረጨበት ቤተ ክርስቲያኔ በተተከለበት የሰው በሽታ የከብት ዕልቂት የእኽልና
የውሃ ጥፋት አይኹን የሚል የምህረት ቃል ኪዳን ተቀበለ፡
☞የህጻኑ የሰማዕቱ የቅዱስ ቂርቆስ እና የእናቱ የእየለጣ የጸሎታቸው በረከት አይለየን።
+(ገድለ ቂርቆስ ወ እየሉጣ)
#መልካም የጥምቀት በዓል
ለመቀላቀል
👉
@ortodoxtewahedo.