ደዕወቱል ፊርቀቱል ናጂያ በአማን ጤና ሳይንስ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ቅድሚያ ለተውሒድ

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


በሰላም አደረሳችሁ


السلام عليكم ورحمت الله وبركاته ያኡመተል ኢስላም በአላህ ፍቃድ ነገ ቅዳሜ መጋቢት 24/2014 የረመዳን የመጀመሪያ ቀን መሆኑ ተረጋግጧል እንኳንም ለተከበረው ረመደዷን


السلام علكم ورحمت الله وبركاته ውድ ወንድም እና እህቶች በመቀጠልም እንኳን ለታላቁ ወር ለረመዷን አላህ በሰላም አደረሳችሁ እንድሁም ለተመራቂወች ለመመረቅ አበቃችሁ ግን ስትመረቁ አምስግኑ እንጂ አላህን እንዳታምፁ


ቦታ ሸሸቃ መሰጅድ መድረሳ ውስጥ


ااسلام عليكم ورحمت الله وبركاته ውድ የተከበራችሁ የሱና ወንድም እህቶቼ ባለፈው ሳምንት ለ8 ሰአት የተባለው የዳእዋ ብሮግራም ነገ እሁድ ከጧቱ 3 ሰአት ከ20 ይጀምራል ኡስታዞች ስለተጋበዙ እንዳታረፍዱ


As wr wb የተከበራችሁ ወንድም እና እህቶች የፊለፊታችን አርብ ማለትም በ3 /7/2013 ከሱር በሗላ ሽሽቃ መስጅድ እንገናኝ


Forward from: Mizan Aman Health science college
ለኮሌጃችን አንደኛና ሁለተኛ ዓመት ተማሪዎች በሙሉ
******************************

የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚካሄደው ከቀን 22-25/6/2013 ዓ.ም መሆኑን እየገለፅን ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኋላ የሚመጣውን ማንኛውንም ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡


ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም !
ሚ/አ/ጤ/ኮ

የካቲት 16/06/ 2013


Forward from: طه خضر أبوعبد الله
‏قال الشيخ الألباني رحمه الله:

"يريدُ المسلمون إقامَةَ الدّولة المُسلمة، ولا يستطيعون إقامة مسجدٍ على السُنّة".

📚[ الهدى والنور١٠٦٨]


Forward from: Nesiha Channel
🔻የረሳነው መስታዎት
▱▰▱▰▱▰▱
°
አካልህ ተውቦ
ገፅታህ አብቦ
ሰውነትህ ደምቆ
መልክህ አሸብርቆ

መደነቅ ያማረው፣
መኮፈስ ያጓጓው፣
መስታወት ያሰኘው፣
‘እየኝ’ ያለህ ’ለታ፣
እፍኝ አፈር ዘግነህ ተመልከት በጌታ!!
ተመልከት በአላህ!
ተመልከት በቃሉ
ቋንቋ ብሄር ሰጥቶ ቢያግባባህ ጀሊሉ
ዘር እየመነዘርክ ትጎራለህ አሉ!

ወንድማለም!
እስኪ
ተመልከት ከጭቃው፣ ተመልከት ከምድሩ
አንተን አንተን ይላል፣
ዘመድ ከዘመዱ ሰውም ከ አፈሩ!

መልክህ ረጋፊ ነው፣
ቀለምህ ጠፊ ነው፣
ቋንቋህ አላፊ ነው፣
ብሄርህ ትርፍ ነው፣
አካልህ ፈራሽ ነው፣
ዋናው ማንነትህ አፈር ነው ጭቃ ነው።


ወንድሜ!
እስኪ አትንጠራራ
አትደርስም ተራራ!
እስኪ አትንገዳገድ
ምድር ላትሰረጉድ
አፈር ነህ ያ’ፈር ልጅ
የግም ጭቃ ውላጅ!

አፈር ነው መነሻህ
አፈር ነው መድረሻህ
አፈር መጀመሪያህ አፈር መጨረሻህ
ነገም ከ አፈር ነው ዳግም ’ምትወጣ

እንደተበተነ እንደ መንጋ አንበጣ!!

ከጭቃ ተሰርቶ፣
ከጭቃ ተነስቶ፣
በቆሻሻ መውጫ ሁለት ጊዜ ወጥቶ፣
መሬት አይንካኝ ሲል
በኩራት ሲፏልል፣
በትእቢት ሲሸልል፣
አይደንቅም ወይ ከቶ!!
አይ የሰው ልጅ!!

✍ ኢብኑ ሙነወር
▰▱
Join
▽▼
t.me//Nesihachannel




Forward from: ابو العسيا/عباس محمد امان


Forward from: Seada Ahmed
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ እንዴት ናቹ ውድ እህቶቼ ተመራቂ ተማሪዎች ግቢ ሲጠሩ አልሀምዱሊላህ ተባብለናል ታስታውሱ እንደሆነ እስከ 24 አፓረንት እንዲወጡ ግቢው አሳስቦአል እና አሏህ ካለ እኛም መጠራታችን አይቀርም ድሮም ሙሀመድ ወንድማዊ ምክሩን ሲለግሰን ከካፊር ሴቶች አንድላይ አትከራዩ ፣ኮሌጅ ሰፈር ቤት አትከራዩ ፊትና ላይ ትወድቃላቹ ሲለን ነበር አሁን ያለው አልቀረም የዱርዬዎች መሰብሰቢያ
በሆነው ኮሌጅ ሰፈር የእህቶቻችን ስም ጠፉቶአል አሏሁ ሙስተአን
እህቶቼ ወሏሂ አላህን እንፍራ አሏህን እንፍራ አሏህ በልባችን ያሰብነውን ያውቃ እንኳን በጨለማ ለምንሰራው አሏህ ለኛ ከደም ስሮቻችን በላይ ቅርብ እንደሆነ ነግሮናል አሁን እንደምትሰሙት ነው ጠዋት ያየነው ሰው ከሰአት በሞት እናጣዋለን ማታ በሰላም የተኛውን ጠዋት በሞት እናጣዋለን የኛስ አሁን ነገ ከነገ ወዲያ አናውቅም አሁንም ቢሆን አሏህ ይሄን ሁላ ኒእማ ውሎልን ሳለ አሏህን ምናምፅ እህቶች አሏህን እንፈረው ወሏሂ አሁንም ነፍሳችን እስከምትወጣ የተውበት በር ክፍት ነው ወደአሏህ እንመለስ ወደ ጨለማው ፣እውነተኛ ቤታችን ከመግባታችን በፊት በተለይ ኮሌጅ ሰፈር ያላቹ እህቶች አላህን ፍሩት ለምትመረቁበት ሰአት ላደረሳቹ አላህ ያልጠተራን እህቶች ኮሌጅ ሰፈርና ሲኒ ማዶ አትከራዩ በይቀርበኛል ሰበብ አሏህ በሰጣች እግራቹ ተራመዱበት የት ጠፋ ምትከራዩት መስጂድ ሰፈር ካልተገኝ ወፍጮ ሰፈር ካልተገኘ ቻይና ካምፕ ለምን ለምን እራሳችንን ለወንጀል እናዘጋጃለን ለምን
ተኩላዎች የሞሉበት ቦታ እንሄዳለን ለምን እባካቹ እህቶቼ የኔ መስታወት እናንተ ናቹ የናንተ መስታወት እርስ በራሳችን ነን ካልሆነ ተያይዘን ገደል እንገባለን
እና ወደ አሏህ እንጠጋ ሁሉ ነገራችን አሏህ ያስተካክላዋል አሏህን መፍራት የነገሮች ሁሉ ቁንጮ ነው እኔ ከናንተ ሰለምሻል አይደለም ። መስታወታችን እርስ በራሳችን ነን ብያቹ አለሁ በዱንያም ለአሏህ ብለው ተዋደው ለሱም ብለው ተመካክረው በአሄራ በዚያ በጭንቁ ቀን በአርሹ ጥላ ስር ከሚያስጠልላቸው ባሮቹ ያድርገን ወሏሁ ተአላ አእለም ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ


ቶሉ መድረሳው እንገናኝ የአካባቢው ልጆችም ስላሉ አርፍዳችሁ እንዳታስጠብቁን አደራ


የተከበራችሁ ወንድም እና እህቶች እንደት ናችሁ ነገ እሁድ ማለትም በ16 ሁላችሁም ተመራቂ ተማሪዎች ሸሸቃ መድረሳ እንገኛኝ አሱርን መስጅድ ስገዱና ወዲያው




Forward from: TAWHEED CHANNEL
🌘 የሙመዪዓዎች ሴራ
ሙመዪዓዎች ኢኽዋኖች ለብዙ አመታት ሲጠቀሙበት የነበረውን ሰለፍዮችን የመበታተን ሴራ በጣም በተቀናጀና በረቀቀ መልኩ እየተጠቀሙበት ነው በዚህም መጀመሪያው ስራ
የባህር ዳር ሰለፍዮችን መለያየት
ቀጥሎ ስልጤ ዞን ያሉ ሰለፍዮችን በአብዛኛው ሙሪድ በማድረግ
በፅናት የቆሙት ከብዙ የመመለስ ሙከራ በኃላ ታፔላ በመለጠፍ እንዲጠሉ ማድረግ ባይሳካም
አልቆመም አ/አ ያሉ ሰለፍይ ወንድሞች ተለያይተዋል የሚል ብዥታ በመፍጠር በማደናገር ከዚያም ሰዎች በሰለፍዮች ላይ እምነት እንዲያጡና ሰለፍያን እንዲጠሉ ማድረግ በአላህ እገዛ ከዚያም በባህር ዳር መሻኢኾች አማካይነት ወንድሞች ውዥንብሩን አጥፍተው ራቁታቸውን እንዲቆሙ መሆኑ
አላበቃም ጉራጌ ዞን ላይ መዋቅር ዘርግቶ መስጂዶችን መቆጣጠር
በተለይ እነሞር ያሉ ሰለፍይ ወንድሞችን በድብቅ ሴራ በመከፋፈል እነሞር ላይ ያለውን የሰለፍያ ዳዕዋ ለመበተን በጣም የረቀቀ ስራ መስራት
የሚቀጥለው ታርጌት ከሚሴ ሲሆን
እዛ ያሉትን ሰለፍዮች መለያየት ከተቻለ ከወንድማችን ኸድር አሕመድ አጠገብ ቅርንጫፍ መክፈት ካልሆነም ከሚሴ ላይ ማንኛውም ቦታ
በዚህ መልኩ የሰለፍያ ዳዕዋ እያበበ ያለበት በመከታተል እንዲጠወልግ ማድረግ ከዛም ሁሉንም ወደ ተምዪዕ አዳራሽ መክተት
የሚጠቀሙበት ሹብሃት
ሰለፍዮች ክፍለ ሀገር ላይ ተውሒድን ማስተማር እንጂ ሚንሀጅ አያስፈልግም የሚል ሃሳብ እንዲቀበሉ ማድረግ
ልብ በል ሚንሀጅ ተውሒድ አይደለም ማለት ነው
ከሽርክና ከሽርክ አራማጆች ማስጠንቀቅ ነው ሚንሀጅ የሚባለው ይህ ትልቅ የተውሒድ ክፍል ነው
ከቢዳዓና ከሙብተዲዕ ማስጠንቀቅ ትልቅ የተውሒድ ክፍል ነው
ነገር ግን በሰዎች ላይ ብዥታ ለመፍጠርና ወደ ተመዩዕ ለመንዳት የሚጠቀሙበት ስልት ነው ተጠንቀቁ
ሌላው ክፍለ ሀገር ላይ ያለው ሰው ሁሉም አንድ አይነት አይደለም ተማሪ ወጣቶች ሚዲያ የሚከታተሉ
ያለውን ልዩነት ማወቅ የሚፈልጉ ኪታብ የቀሩ ከፈጅር በኀላ እና በተለያዩ ወቅቶች እነርሱን የሚመጥኑ ደርሶችን የሚፈልጉ
ለእነዚህ ተማሪዎች ስለሙመዪዓ እና ኢኽዋን ማስተማር አያስፈልግም በሚል ነው ኡስታዞችን የሚያባሩት
ሌላው በመከራ መስጂድ የሚመጣ ሶላት ሲሐርም ሸኾች ሊቆዩልኝ ብሎ የሚሓርም እንኳን ስለ ተሕዚርና ስለ ረድ ስለሽርክ ለመናገር እንኳን ጥንቃቄ የሚፈልጉ በጣም ጥሩ ቃላት ተመርጦ በለሰለሰ አገላለፅ ዳዕዋ እንዲሰሙ የተለያዩ ማቆያዎችን እየተጠቀምክ ዳዕዋ የምታደርግላቸው ናቸው
ሙመዪዓዎች ግን ሰላትና ጦሃራ ለማያውቅ ሚንሀጅ አያስፈልግም እያሉ ማለዘብ ነው አላማቸው
በመሆኑም የተከበራችሁ በሀገሪቱ የተለያየ ክፍል ያላችሁ ሰለፍዮች ይህን ሴራ ተረድታችሁ አንድ በመሆን በመነጋገር የሰለፍያን ዳዕዋ የመጠበቅ አደራ አለባችሁ
በተለይ በዚህ ወቅት ከምን ግዜውም በላይ አንድ መሆን መነጋገር መተጋገዝ የሚያስፈልግበት ጊዜ ነው
አላህ በየቦታው ያሉ ሰለፍዮችን አንድ አድርጎ ድል እንዲሰጣቸው የለፍያ ባንዲራ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ዱዓእ ማድረግና ለተግባሩም እራስን ማዘጋጀት ያስፈልጋል
http://t.me/bahruteka


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
"አር ማረኝ"
~
ተውሒድን አጥብቀህ ተማር። ተውሒድ ለኣኺራ ብቻ አይደለም ፋይዳው። ለዱንያም መከበሪያህ ነው።
ተውሒድ #ካልተማርክ

• ጉጉት ትፈራለህ፣
• አይጥ ትለማመጣለህ፣
• ውሻ አላዘነ ብለህ ትሸበራለህ፣
• የቁራ ድምፅ ከመንገድ ይመልስሃል፣
• እጅ ወይም አንገት ላይ በታሰረ እርባ ቢስ ክር ትተማመናለህ፣
• ዛፍ ላይ ክር ትተበትባለህ፣ ቅቤ ትቀባለህ፣
• እጅህን ስላሳከከህ ትደሰታለህ፣ (ሰዎች እጃቸውን ሲያሳክካቸው ምን እንደሚሉ አስታውስ)
|
• ተውሒድ ካልተማርክ ከሶላት የተኳረፈ ገሪባ "ዐርሽ ላይ ነው የምሰግደው" እያለ ይጫወትብሃል። ጠንቋይና ወልይ ይምታታብሃል።
• ሃያሉን ጌታ ጥለህ ሙታን ትማፀናለህ፣ (ይልቅ እነሱን መለመንህን ትተህ ለነሱዱዓእ አድርግላቸው)
• ተውሒድ ካልተማርክ "ማርያም በሽልም ታውጣሽ"፣ "የማርያም መቀነት"፣ "የማርያም ፈረስ"፣ "ማርያም ስማህ ነው"፣… እያልክ ክርስትና ክርስትና የሚሸት ኹራፋት ታራምዳለህ።
• የአምስት ብር ጎመን የማያክል አረንጓዴ መርዝ (ጫት) መቶ ሁለት ብር ገዝተህ "የዱዓእ መሳሪያ" እያልክ ትጃጃላለህ፣
• የሁለት አመት ህፃን የሚፀየፈውን አፈር "ቱራብ" እያልክ በጥብጠህ ትጠጣለህ፣
• አዎ ተውሒድ ካልተማርክ የተቀበረ ብር አገኛለሁ ብለህ ጠንቋይ እየቀለብክ በእጅህ ያለውን ገንዘብ ታጣለህ፣
• ልጅህ ሲባልግ፣ ሲያፈነግጥ ዝም ብለህ ተውሒድ ሲማር፣ ሶላት ሲሰግድ፣ መስጂድ ሲያዘወትር፣ ጥሩ ጓደኛ ሲይዝ እሪ ትላለህ፣ (እንዲህ ነው የሸይጧን መጫወቻ መሆን)
• ተውሒድ ካልገባህ ከሺርክ የሚያስጠነቅቁ ተቆርቋሪዎችን እንደ ጠላት እየቆጠርክና ጧት ማታ እያጠለሸህ ሶሐቦችን የሚያወግዙ፣ ቁርኣንን የሚያረክሱ ሺዐዎችን ታወድሳለህ። አልተማርክማ! እንዲሁ "ሲሉ ሰማሁ ብየ እላለሁ ነብዬ" ብቻ!
• ተውሒድ ካልተማርክ ለቶንሲል ህመም "አር ማረኝ" እያልክ በአይነ ምድር ታሻርካለህ፣ (ሰው እንዴት ካካውን ይማፀናል?) ወላሂ ከእንዲህ አይነቱ የሰው ዝቃጭ ካካውን የሚያቦካ የአእምሮ በሽተኛ ሺ ጊዜ ይሻላል።
ጎንበስ ብለህ ተውሒድህን ተማር። አካዳሚ ትምህርት ከሺርክ አያወጣህም። ስንት እንጨት፣ ላም፣ ድንጋይ፣ ሰው፣… የሚያመልኩ፣ ጠንቋይ ለጠንቋይ የሚርመጠመጡ ዶክተሮችና ፕሮፌሰሮች አሉ መሰለህ?
\=\

የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የውይይት ጥሪ ለአሕባሾች
~
① ጠሪ: –

አቡ ዒምራን ሙሐመድ ሲራጅ
እና
ኢብኑ ሙነወር

② የጥሪው አድማስ:–

ለሁሉም አሕባሾች። ሰሞኑን "እንወያይ" ሲሉ የነበሩትን ሀቢብ እና ወሂድን ጨምሮ እስከነ ዑመር "ኮምቦልቻ" … ባጭሩ ለሁሉም።
(ማሳሰቢያ:- ንፅፅር ላይ የሚሰራው ወሒድ ዑመር አይደለም።)

③ የውይይት ርእስ:–

"አላህ ከዐርሹ በላይ ነው" የሚሉ ሙስሊሞችን እያከፈራችሁ ስለሆነ የምንጀምረው በዚህ የ"ኢስቲዋእ" ርእስ ነው። ይህንን ለመቋጨት ከበቃን እንደ "ኢስቲጋሣህ" ባሉ ሌሎች ወሳኝ ርእሶች እንቀጥላለን።

④ የውይይት መስፈርት: –

✅ ማስረጃዎች ከቁርኣን፣ ከሐዲሥ እና ነቢዩ ﷺ ምርጥነታቸውን ከመሰከሩላቸው ቀደምት ትውልዶች ንግግር ብቻ‼
✅ ይሄ ከጠበበባችሁስ?! በዚህ ምክንያት እንድትሸሹ አንፈልግም። እኛ:–

👉🏾 በሰለፎች አካሄድ ተገድባችሁ መሟገት አትችሉም ብለን ስለምናምን፣
👉🏾 በዚህ ምክንያት ከውይይቱ እንድትሸሹም ስለማንፈልግ፣
👉🏾 "እንከተላቸዋለን" ከምትሏቸው አቡል ሐሰን አልአሽዐሪ ፈፅሞ እንደማትገናኙ ማጋለጥም ስለምንሻ
እስከ አቡል ሐሰን ዘመነ–ህልፈት #ድረስ ያሉ ዓሊሞችን #ብቻ እንድታጣቅሱ እንስማማለን። ከዚያ በኋላ #ፈፅሞ አይሆንም።

✅ በዚህ ዘመን የምንገድብበት ምክንያት:–

1⃣ ውይይቱ ልጓም የለሽ ሆኖ እንዳይለጠጥ ለመወሰን፣
2⃣ እምነታችሁ ከጊዜ በኋላ የመጣ እንጂ የዚያ ምርጥ ዘመን ትውልድ እምነት እንዳልሆነ ለማሳየት፣
3⃣ ዐቂዳችሁ "ኢማማችን" የምትሉት አቡል ሐሰንም እምነት እንዳልሆነ ለማሳየት፣
4⃣ "አላህ ከዐርሽ በላይ ነው" የሚለው ዐቂዳ "የወሃቢዮች ዐቂዳ ነው" በማለት መጤ አስተሳሰብ በማስመሰል ነጭ ውሸት በመንዛት ህዝብ እያደናገራችሁ ስለሆነ

በተቃራኒው ይህ "አላህ ከዐርሹ በላይ ነው" የሚለው እምነት በቁርኣንና በሐዲሥ የፀና፣ እነዚያ ምርጥ ትውልዶች የተጓዙበት፣ እንዲሁም የነ አቡል ሐሰን አልአሽዐሪ ጭምር ዐቂዳህ እንደሆነ ለማሳየት ርእሱን መገደብ ግድ ብሏል።

⑤ የውይይቱ ቦታ:–

ቴሌግራም ላይ በዚህ ግሩፕ ይሆናል:–
👇🏾
https://t.me/IbnuMuneworsb

🔊 መልእክቱን አዳርሱልን። ምናልባት ፈቃደኛ ሆኖ የሚቀርብ ሊኖር ይችላልና።


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ድንቁርናው ምን ያክል ቢደርስ ነው በዚህ የግፍ ውሳኔ ላይ ምንም ሳያፍር ስምና ፊርማውን የሚያሰፍረው?
እንዲህ አይነት በደል ባደባባይ የሚፈፀምበት ሃገር ነው የመቻቻል ተምሳሌት እየተባለ የሚዘመርለት!!
ይሄ እንግዲህ አደባባይ የወጣው ነው። ህዝብ የማያየው ስንትና ስንት ግፍ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ ይደርሳል?


Forward from: ኢቅራ የቂራት ማእከል
«መንሃጅ» ማለት ምን ማለት ነው⁉️


✍️በቋንቋ ደረጃ:

«መንሃጅ» ማለት (ግልጽ የሆነ) «መንገድ» እንደ ማለት ነው።



አላህ በቁርአን ላይ እንዲህ ይላል፦
{لِكُلٍّ جَعَلْنا مِنْكُمْ شِرْعَةً وَمِنْهاجاً}"
"ከናንተ ለሁሉም ሕግንና መንገድን አደረግን:.."
((አል ማኢዳህ፡ 48))
*
ኢማሙ ጦበሪይ በተፍሲራቸው ላይ እንዲህ ይላሉ፥

"وأما"المنهاج"، فإنّ أصله: الطريقُ البيِّنُ الواضح، ... ثم يُستعمل في كل شيءٍ كان بيِّنًا واضحًا سهلاً"
"ሚንሃጅ የሚለውማ፦ መሰረቱ ግልጽና የተብራራ የሆነው መንገድ ነው።
ከዚያም በሁሉም ነገር ላይ ይተገበራል፤
ግልጽ፣ የተብራራና ቀላል ሆነ።"

((ተፍሲሩ ጥጦበሪይ፡ 10/384))
*
ገጣሚውም እንዲህ ይላል፤
مَــنْ يـكُ فِـي شَـكٍّ فَهـذَا فَلْـجُ
مَـــاءٌ رَوَاءٌ وَطَـــرِيقٌ نَهْــجُ
*
በእንግሊዝኛው "Methodology", "Syllabus", "Curriculum" የሚሉት ቃላት ይተኩታል።
በአጠቃላይ የሚለውን ቃል መንገድ፣ ፈለግ፣ ፋና፣ ትውፊት፣ አካሄድ የሚሉት ቃላቶች እንደየ አገባቡ ይተኩታል።
*
✍️በሸሪዓዊ ደረጃ ደግሞ፤
````
እውቀታዊና ተግባራዊ በሆኑ የአምልኮ ተግባራቶች እንዲሁም
በሰዎች መካከል ስላለ መስተጋብር ሁሉ የአላህ ህግ (ሸሪዓዊ ብይን) የሚገለጽበት መንገድ ማለት ነው።
الطريق الذي يبين به أحكام الله في العبادات العلمية والعملية وفي المعاملة بين الناس .

*
👉ታዲያ በቃላዊ ደረጃ የተለያዩ መንሃጆች (መንገዶች) አሉ።

ለምሳሌ፦
የፈላስፎች መንገድ (መንሃጁል ፈላስፋ)፣
የሰለፎች መንገድ (መንሃጀ ስሰለፍ)፣
የሙስሊሞች መንገድ (ሚንሃጁል ሙስሊም) ወዘተ ይባላል።
*
✍️ነገር ግን እንደ አጠቃላይ እንደ ሙስሊም እኛ መከተል ያለብንና አርአያ አድርገን መያዝ ያለብን የመልካም ቀደምቶችን የሰለፎችን መንገድ ነው።
እርሱም "መንሃጁ ስ-ሰለፍነ ሷሊሕ" ይባላል።

ይህ መንሃጅ (መንገድ)፡
ነብያችንን ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በመልካም የተከተሉ ሶሐቦች፣
ሶሐቦችን በመልካም የተከተሉ ታቢዒዮች፣
ታቢዒዮችን በመልካም የተከተሉ አትባዑ ታቢዒዮችንና ከዚያም በኋላ ያሉትን መልካም ቀደምቶች ያቀፈ ነው።

✍️ለምሳሌ፦
ሶሐቦች እንዳሉ ሆነው እነ ኢማም አቡ ሐኒፋ፣ ኢማሙ ማሊክ፣ ኢማሙ ሻፊዒይ፣ ኢማሙ አሕመድ፣ ቡኻሪ፣ ሙስሊም፣ ነሳኢይ፣ ኢብኑ ማጃህ፣ አቡ ዳውድ፣ ቲርሚዚይ፣ ሸይኹል ኢስላም ኢቡ ተይሚይያህ፣ ኢብኑ ቁዳማህ፣ ኢብኑ ዓብዱልበር፣ ኢብኑ አቢ ዱኒያ፣ ኢብኑል ቀይዩም፣ ኢብኑል ጀውዚይ፣ ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዓብዱል ወሃብ እና ሌሎችም።

✍️ከዘመናችን ታላላቅ እንቁዎች ውስጥ ደግሞ፥
ኢማም ኢብኑ ባዝ፣ ኢብኑ ዑሠይሚን፣ ኢማም አልባኒ፣ ሸይኽ ሙቅቢል፣ ሸይኽ ሙሐመድ አማን አልጃሚ፣ ሸይኽ ሰዕዲይ እና ሌሎችም።

✍️አሁን ላይ በህይወት ካሉት ውስጥ ደግሞ፥
ሸይኽ ዶ/ር ሷሊሕ ፈውዛን፣ ሸይኽ ረቢዕ አል መድኸሊይ፣ ሸይኽ ዶ/ር ሙሐመድ ሰዒድ ረስላን፣ ሸይኽ ዶር ፕሮፌሰር ሱለይማን አር-ሩሐይሊ፣ ሸይኽ ዶ/ር ፕሮፌሰር ዓብዱረዛቅ አልዐባድ፣ ሸይኽ ሱሐይሚይ፣ ሸይኽ አሊ አደም፣ አል-ሸይኽ እና ሌሎችም።



*
✍️እነዚህ ከዋክብቶች በመንሃጀ ስሰለፍ (በቀደምቶች ትውፊት፣ ፋና) ላይ ያሉ ናቸው።
ቁርአንና ሐዲሥንም እነዚያ ቀደምቶች በተረዱትና ተግብረውት በነበረው ነገር ይረዳሉ፣ ይተገብራሉ።
አስተምህሯቸውም ከነርሱ ያፈነገጠ አይደለም።
በዚህም የተነሳ አህሉ ሱንና ወልጀመዓ ይሰኛሉ።
ሱንናን አጥብቀው በመያዝ በሐቅ ላይ የተሰባሰቡ ናቸውና።



*
👉ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ በእስልምና ሽፋን የተለያዩ የጥመት አንጃወች እንደ አሸን ፈልተዋል።
ከቀደምት ሰለፎች መንሃጅ ውስጥ የሌለን አካሄድ በመሄድ፣
የራሳቸውን መንገድ ቀይሰው እየሄዱ ነው።
ከነዚህ ከተፈለፈሉ መንሃጆች ውስጥ

ለምሳሌ:
~~~~~~~
የሺዓ መንሃጅ፣ የአሕባሽ መንሀጅ፣ የሱፍያ መንሃጅ፣ የኢኽዋን መንሃጅ፣ የተብሊግ መንሃጅ፣ የሐዳድያ መንሃጅ፣ የጀህምያ መንሃጅ፣ የአሻዒራ መንሃጅ፣ የሙዕተዚላ መንሃጅ፣ የኸዋሪጅ መንሃጅ፣ የተክፊር መንሃጅ ወዘተ የመሳሰሉት፣
ሁሉም ከአህለ ሱንና ወል ጀመዓ ያፈነገጡና ከሰባ ሁለቱ ጠፊ ቡድኖች ውስጥ የሚካተቱ ናቸው።

እነዚህ በውጭ ሃገር ብቻ የሚገኙ አይደሉም።
በሃገራችንም ውስጥ አሉ።

✍️ለምሳሌ፦
ኢኽዋን የሚባሉት ቡድኖች
አንድን ህዝብ በመሪህ ላይ አምጸህ ውጣ ብለው ለከፋ ችግር ሲዳርጉት በየሃገሩ ይስተዋላል።
በሰላማዊ ሰልፍ፣ ከዲን ይልቅ በስልጣን ጥማት የተነሳ የፖለቲካ ፍትጊያ መገለጫቸው ነው።
አብዛኛውን ጊዜ ሚዲያ ያገነናቸውና በሰፊው የዋህ ህዝብ ዘንድ ታዋቂነት ያላቸው ሰዎች በብዛት ይገኙበታል።


*
✍️አህለ ሱንና ወል ጀመዓዎች የተለያዩ መጠሪያዎች አሏቸው።
ለምሳሌ፥
በቀደምቶች ትውፊት ላይ የሚጓዙ ስለሆነ ሰለፍዮች ይባላሉ።
ከእሳት የምትድነዋ አንዷ ብቻ ስለሆኑ ይባላሉ።
"ጧኢፈቱ መንሱራም" ይባላሉ።
ሁሉም መልካም ገለጻዎች ስለሚገልጿቸው ነው።



*
*
✍️ስለዚህ ከእኛ የሚጠበቀው፣
ሁሉንም ከሱንና ያፈነገጡ፣ የሰለፎችን መንሃጅ (መንገድ፣ ትውፊት) የሳቱ ቡድኖችንና ግለሰቦችን በመራቅ፤
በትክክለኛው የቀደምቶች (የሰለፎች) መንሃጅ ላይ ጸንቶ መጓዝ ነው።
ቁርአንና ሐዲሥንም እነርሱ ተረድተው በኖሩበት መንገድ መኖር ነው።

መርሃችን «ቁርአንና ሐዲሥን በመልካም ሰለፎች አረዳድ መረዳት መሆን አለበት።»
መንሃጃችንም የሰለፎች መንሃጅ ይሰኛል።
ለነርሱ የበቃው ይበቃናል።

ወደ ሰለፎች በተግባሩና በንግግሩ የተጠጋም "ሰለፍይ" ይባላል።
አንድ ሰው "ሰለፍይ ነኝ!" ሲል "ሙስሊም አይደለሁም!" ማለቱ አይደለም።
እንዳውም ለሙስሊምነቱ ምንም ጥርጥር የለውም።

"እያንዳንዱ ሰለፍይ ሙስሊም ነው።
እያንዳንዱ ሙስሊም ነኝ ባይ ግን "ሰለፍይ" ሊሆን አይችልም።"
አንዳንዶች ሲባሉ ይደነግጣሉ።
ሰለፍያ ማለት ግን የሰለፎች (ማለትም የሶሐቦችና የታቢዒዮች) መንገድ ነው።
ለሌሎች ሼር ያርጉ ጆይን አይዘንጉ !!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://telegram.me/tewihd

20 last posts shown.

55

subscribers
Channel statistics