Addis Ababa Education Bureau


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


ልምድ ልውውጡን ለማድረግ ከጋሞ ዞን ትምህርት መምሪያ የመጡ የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተማሪዎችን ውጤትና ስነ ምግባር ለማሻሻል እየተሰራ የሚገኘው ስራ ለሌሎች ተሞክሮ እንደሚሆን ጠቁመው ከቢሮው አመራሮች ጀምሮ በየደረጃው በቅንጅት መሰራቱ ተቋሙን ውጤታማ እንዲሆን ያበረከተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ማረጋገጣቸውን አስታውቀዋል።


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

Imo: - https://s.channelcom.tech/vlWdNr?from=TG
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com


ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ትምህርት መምሪያ የመጡ የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የልምድ ልውውጥ አካሄዱ።

(ህዳር 16/2017 ዓ.ም) ልምድ ልውውጡ በዋናነት በከተማ አስተዳደሩ ስላለው አጠቃላይ የመማር ማ ስተማር ሂደትን መሰረት አድርጎ የተካሄደ ሲሆን የቢሮው የማኔጅመንት እና የአጠቃላይ ካውንስል አባላት ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች ማብራሪያ እና ገለጻ ተሰቷል።

ከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ሴክተሩ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት መነሻ በትምህርት ቤቶች ተግባራዊ የሆነው የተማሪዎች ምገባ እና ዩኒፎርምን ጨምሮ በነጻ እየቀረቡ የሚገኙ የመማሪያ ቁሳቁሶች በተማሪዎች ውጤት ላይ ከፍተኛ መሻሻል እንዲመዘገብ ያበረከተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር ጠቁመው በሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ከ3ኛ ክፍል ጀምሮ የብዝሀ ቋንቋ ተግባራዊ መሆኑንም አመላክተዋል።

የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር ለማሻሻል አዲስ መመሪያ በማዘጋጀት የርዕሳነ መምህራን ሪፎርም በማካሄድ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በቅንጅት ስልጠና እንዲወስዱ መደረጉን ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ ከማል ጠቁመው የተማሪዎችን የሒሳብና እንግሊዘኛ ውጤት ለማሻሻል ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ በመደረግ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።


የሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡

(ህዳር 16/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ዳይሬክተር አቶ አብዱልበር መሐመድ ልጅን በማሳደግ ሂደት ውስጥ የወላጆች ሚና ምን መሆን እንደሚገባዉ የሚገልጽ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በመድረኩ ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ልጅን በማሳደግ ሂደት ውስጥ የወላጆች ሚና ከፍተኛ መሆኑን በመግለጽ የቀረበዉ ሰነድ ይህንን በደንብ የሚዳስስ በመሆኑ ሰራተኞች ከዚህ ብዙ ቁምነገር መጨበጥ እንደሚችሉ አመላክተዋል፡፡


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

Imo: - https://s.channelcom.tech/vlWdNr?from=TG
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication


በተያያዘም በ1ኛ ሩብ ዓመት በመደበኛ ስራው በሁሉም ትምህርት ቤቶች እየተሰሩ የነበሩ የሱፐርቪዥን ሥራዎች ግኝቶች ላይ የታዩ ክፍተቶችን ገምግሞ መረጃዎችን አደራጅቶ በማቅረብ በሁለተኛው ሩብ ዓመት የተሻለ የሱፐርቪዥን አፈፃፀም እንዲኖር ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል ::

የውይይት ሰነዶቹ በቢሮው የአማርኛና አፋን ኦሮሞ ቋንቋ ሱፐርቫይዘሮች የቀረቡ ሲሆን በውይይቱ ላይ የክፍለ ከተማ ሥራ አስተባባሪዎችና አፋን ኦሮሞ ሱፐርቪዥን አስተባባሪዎች ፣ የክፍለ ከተማና የቢሮ ሱፐርቫዘሮች እንዲሁም የቢሮው ዳይሬክተሮች ተሳታፊ ሆነዋል::

Sanadoota deeggarsaa qabxii gosa barnoota Ingiliffaa fi Herregaa foyyeessuu dandeessiisan shan irratti mariin gageeffame.

Biiroo barnoota bulchiinsa magaalaa finfinnetti daayirektoreti suppervizyini barnoota waliigalaa sanadoota deeggarsaa qabxii gosa barnoota Ingiliffaa fi Herregaa foyyeessuu dandeessiisan irratti qaamoota isaan ilaalatuu waliin mariin gaggeeffame jira.

Daawwannaa daree kilinikaalaa fi keessoo bu'aa qabeessa taasiisuuf, qabxii gosa barnoota Ingiliffaa fi Herregaa bu'aa qabeessa taasiisuuf gaheef gaafatamuummaa fi ittigaafatamuummaa hogansa barnootaa, sanada deeggarsa barnootaa, sanada gorsaa maatii baratootaa, barsiisotaa, ittigaafatamtooraa, barattootaa fi wiirtuulee kan jedhan sanadoota shan afaan amaariffaa fi afaan oromootiin dhihaatani hirmaattootaan mariin irratti gaggeefame jira.

Daayirektarri daayirektoreti suppervizyini barnoota waliigalaa obbo Abduulbar Mahaammad haasaa baniinsa taasiisaniin bu'aawwan qabxii gosa barnoota Ingiliffaa fi Herregaa galmaa'aa turan foyyeessuuf biiroon tarsiimoo qopheessee hojjechaa jiraachuu isaa yaadachuisani jiru. Qabxii gosa barnoota Ingiliffaa fi Herrega foyyeessuu fi bu'aa eeggamuu irra gahuuf gaheen suppervaayizerootaa guddaa ta'uu isaa duubbatani jiru.

Galmaan gahiinsa karoora tarsiimoo kanaaf suupparvaayizeronni gahee olanaa akka qaban kan ibsan daayirektarichii sanadoonni dhihaatan manneen barnootaan,aanaa fi kutaa magaalaatti suppervizyini gaggeeffaman adeemsa suppervizyini saayinsaawaa kan hordofan akka ta'an deeggaruu irraa darbeebarattoonni fi barsiisonni bu'aa qabeessuummaan akka itti fuufan deeggaruun hubannoo gahaa ni uumuu jedhani jiru. Dabalaniis akkaataa karoora tarsiimootiin bu'aa fiduuf sanadoota haala gaariin hubachuu fi hojii suppervizyini wal-simsiisani deemuun suppervaayizeroota fi ogeessa barnootaa hunda irraa kan eeggamuu ta'uu isaa ibsani jiru.

Kanuumaan wal-qabatee hojjiwwan manneen barnootaa, kutaa magaalaa fi wiirtuu kurmaana 1ffaa keessattii argaannoo suupparvizynii hanqinna jiru gamaagamuun ragaalee qindeessuun dhiyyessuun hojjiiwwan kurmaana 2ffaa cimsuun hundiinuu ittigafatamuummaa akka bahan huubachiisani jiru.

Sanadonni marii suupparvaayzyerota biiroo afaan oromoo fi afaan ammariiffaan kan dhiyyataan yoo ta'uu dursiitoota hojii kutaa magaalaa, qindeesiitoota afaan oromoo kutaa magaalaa, supparvaayizeroota biiroo fi kutaa magaalaa akkasumaas daayirekteroota biiroo hirmaataniiru.


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

Imo: - https://s.channelcom.tech/vlWdNr?from=TG
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- https://www.tiktok.

14k 0 11 5 83

የሂሳብና እንግሊዘኛ ትምህርቶች ውጤትን ለማጎልበት በሚያስችሉ ድጋፍ መስጫ ሰነዶች ላይ ውይይት ተካሄደ::

(ህዳር 15/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት የሂሳብና እንግሊዘኛ ትምህርት ውጤቶችን ለማጎልበት በሚያስችሉ የድጋፍ መስጫ ሰነዶች ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል::

በውይይቱ በክሊኒካልና በውስጥ ሱፐርቪዥን አገልግሎት አካሄድ ፣ በሂሳብና እንግሊዘኛ ትምህርቶችን ውጤታማ ለማድረግ የትምህርት አመራሩ ሚናና ተጠያቂነት ፣ የማጠናከሪያ ትምህርት መስጫ ሰነድ፣ የተማሪ መምህራንና ርእሳነ መምህራን ማማከሪያ እንዲሁም የክላስተር ማዕከላት ድጋፍ መስጫ የሚሉ አምስት ሰነዶች በአማርኛና አፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች ቀርበው በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎበታል ::

የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ዳይሬክተር አቶ አብዱልበር መሐመድ በውይይቱ መክፈቻ ባደረጉት ንግግር በሂሳብና እንግሊዘኛ ትምህርቶች ሲመዘገቡ የቆዩ ውጤቶችን ለማሻሻል ቢሮው ስትራቴጂክ እቅዶችን በማዘጋጀት ሥራዎች እየሰራ መሆኑን አስታውሰው የሂሳብና የእንግሊዘኛ ትምህርት ውጤቶችን ለማጎልበት እንዲቻል ለትምህርት ስራው ድጋፍ የሚያደርጉ ሱፐርቫይዘሮች ሚና ትልቅ መሆኑን ተናግረዋል::

ሱፐርቫይዘሮች ለስትራቴጂክ እቅዱ መሳካት ጉልህ ሚና እንዳላቸው የገለፁት ዳይሬክተሩ የሚቀርቡት ሰነዶች በትምህርት ቤቶች ፣ ወረዳና ክፍለከተሞች የሚደረጉ ሱፐርቪዥኖች ሳይንሳዊ የአሰራር መርሆችን የተከተሉ እንዲሆኑ ከማገዝ ባለፈ ተማሪዎችና መምህራን በውጤታማነት እንዲቀጥሉ በመደገፍ በቂ ግንዛቤ ያስጨብጣሉ ብለዋል:: አክለውም በስትራቴጂክ እቅዱ መሰረት ውጤት ለማምጣት ሰነዶቹን በተሻለ መረዳትና ከሱፐርቪዥን ስራው ጋር አጣጥሞ መሄድ ከሁሉም ባለሙያዎች የሚጠበቅ መሆኑን አብራርተዋል ::


tiktok.com/@aaeducationbureau
user3576024140337 on TikTok
@aaeducationbureau 7500 Followers, 9945 Following, 36.6k Likes - Watch awesome short videos created by user3576024140337

16k 0 1 11 54

ለብርሃን የአይነ ስውራን አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ  ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሕይወት ክህሎት ስልጠና ተሰጠ ::


(ህዳር 14/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ትግበራ ቡድን ለብርሃን የአይነ ስውራን አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ  ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሕይወት ክህሎት ስልጠና ሰጥቷል::


በስልጠናው በዋናነት ራስን ማወቅና ለራስ ክብር መስጠት ፣ ተግባቦትና ከሌሎች ጋር የመኖር ጥበብ ፣ ውሳኔ አሰጣጥ ፣ ግብ መጣልና ስሜትን መቆጣጠር በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰጥ መሆኑ ተገልፃል::


የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ትግበራ ቡድን መሪ አቶ ይልማ ተሾመ ስልጠናውን ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት መንግስት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ባስገነባው በዚህ አይነ ስውራን ትምህርት ቤት የሚገኙ ተማሪዎች ከአጠቃላይ ሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ እንደመሆኑ የተለያዩ ባህሎችና ቋንቋዎች ባለቤት በመሆናቸው ስልጠናው የራሳቸውን ባህል ቋንቋና ልማድ  ከሌሎች ጋር በማጣመር እንዴት አብሮ መኖር እንዳለባቸው ግንዛቤ እንደሚያስጨብጥ ተናግረዋል ::


አቶ ይልማ አክለውም ተማሪዎች ከስልጠናው በኃላ የሕይወት ክህሎታቸውን በማዳበር የሚገጥማቸውን ችግሮች በጋራ ለመፍታትና በመተሳሰብ እንዲኖሩ የሕይወት ክህሎት ጥበብ እንዲኖራቸው ያግዛል ብለዋል::


ስልጠናው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርዓተ ትምህርት ዝግጅት ባለሙያዎች  አቶ በላይ በለጠ ፣ ወ/ሮ ለዝና መንግስቴ እና አቶ ጌታሁን ጌታቸው አማካኝነት ተሰጥቷል::







10 last posts shown.