ተውሒድ የነብያት ጥሪ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


የአላህ መላክተኛ ሶለላህ አለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል:— ከተውሂድ ባለቤቶች የሆኑ ሰዎች በቂያማ ቀን የወንጀል ሚዛናቸው በመድፋቱ ሳቢያ በውስጧ (በጀሀነም ውስጥ) ከሰል እስከሚሆኑ ድረስ ይቀጣሉ። ከዚያም እዝነቷ (ከአላህ) ታገኛቸው እና ይወጣሉ ። ከዚያም ከጀነት በር ላይ ይጣላሉ የጀነት ነዋሪዎችም ውሀን ይረጩባቸዋል። ከዚያም የጎርፍ ደለል ላይ እንደሚበቅል ጎፋፊ ይበቅላሉ ። ከዚያም ጀነት ይገበሉ

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
في آخر الزمان يتحول الناس في اليوم بسبب شدة الفتن فكن حلس بيتك | للشيخ صالح الفوزان


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ماتقول فيمن يتمنى الموت بسبب كثرة الفتن ؟ - للشيخ د. سليمان الرحيلي


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


Forward from: MuhammedSirage M.Nur.
ከአላህ ውጭ ሌሎች አካላት (ነቢያቶች ፣ ወሊዮች እና ሌሎችም ፍጡራን ) እንዲመለኩ ጥሪ የሚያደርግ በሙሉ መሃይም ነው!

ቁርአን ን ፣ ሐዲስን ፊቅህን እና በርካታ የዱንያ ትምህርቶችን አብዝቶ ቢያውቅና ቢሸመድድም እንኳን ፍጡራንን የሚመልክ ሁሉ መሃይም ነው!

قُلْ أَفَغَيْرَ ٱللَّهِ تَأْمُرُوٓنِّىٓ أَعْبُدُ أَيُّهَا ٱلْجَٰهِلُونَ
«እናንተ መሃይማን ሆይ! ከአላህ ሌላን እንድግገዛ ታዙኛላችሁን?» በላቸው፡፡


“ወላሂ! ለዐቂዳ ለተውሒድ ዋጋ ካልሰጠን፣
ሺርክ ላይ ከወደቅን ፊቅሁም ይሁን ሌላ እውቀት ዋጋ የለውም፡፡
ያለተውሒድ የትኛውም እውቀት ፍፁም ፋይዳ የለውም፡፡
ለምን ቁርኣን አናፍዝም?
ለምን ሐዲሥ አንሸመድድም?
ለምን የፊቅህ ኪታቦችን አንሸመድድም?
ከሺርክ ጨለማዎች ውስጥ ከተዘፈቅን ምንም ዋጋ የለንም፡፡
በያዝነው እውቀትም አንጠቀምም!!”
#ሸይኽ_ረቢዕ_አል_መድኸሊይ


Forward from: قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )
♻️ተዉሒድ ♻️
〰〰〰〰〰
💎በተውሂድ የዱንያም ሆነ የአኸራ ስኬት ይገኛል።

🌐ሸይኽ ሙሀመድ ኢብኑ ሷሊህ አል ኡሰይሚን እንዲህ ይላሉ፦

♻️"በኛ ላይ ዋናው አሳሳቢው ነገር የተዉሂድ ቁንጮ የሆነዉን ተዉሂድ አል ኡሉሂያን(አላህን በአምልኮ መነጠል) በሰወች ነፍስ ዉስጥ ብቸኛ አላማ እስኪሆን ድረስ ማሰራጨት ነው።

✅አንድ ሰዉ በማንኛዉም ጉዳይ ላይ የአላህን ፊት እና የመጨረሻዉን ቀን የሚፈልግ እስኪሆን ድረስ!!

➻ በኢባዳዉ
➻ በስነ ምግባሩ
➻ በማህበራዊ ኑሮዉ
♻️የአላህን ፊት ፈልጎ መሆን አለበት ምክኒያቱም ዋናዉ አሳሳቢዉ ነገር ይህ ነዉና። ማለትም አንድ ሰው አላማዉ ተስፋዉ መመለሱ ወደ አላህ መሆን ማለት ነዉ ።
♻️በዚህ ተዉሂድ ማለትም በተዉሂድ አል ኡሉሂያህ አንድ ባሪያ የዱንያንም የአኼራንም ስኬት እድለኝነት ያገኛል።

📗[«مجموع رسائل فضيلة الشيخ ابن عثيمين» (٧/ ٣٥١)]


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ለህዝብ - ሙስሊሙ ያላቸውን ንቀት ለማሳየት አጋጣሚዎችን ሁሉ አያልፉም። በዚህ አገር በስንት ፈተና በተወጠረችበት ጊዜ አንዱ መስጂድ ካላፈረስኩ ይላል። ሌላው የሙስሊሙን የመቃብር ቦታ ካርታ አምክነናል ይላል። ክፋታቸውን ለማንፀባረቅ ሁነኛ ጊዜ እንኳ የማይመርጡ ለትልቅ ሃገራዊ ሃላፊነት ቀርቶ ለቀበሌ የማይመጥኑ ድኩማኖች ህዝብና መንግስትን ሆድና ጀርባ የሚያደረጉ ውሳኔዎችን ሲወስኑ ሃይ የሚላቸው የለም። አዲስ አበባ ውስጥ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በመንግስት የተሰጠው የማምለኪያ ቦታ ካለ በጣት የሚቆጠር ነው። በከተማው ውስጥ ያሉ መስጂዶች እንዳለ ሙስሊሙ በገንዘቡ የገዛቸው ወይም ከግለሰቦች ያገኛቸው ስጦታዎች ናቸው። እነዚህ ቦታዎች ላይ የተሰሩ መስጂዶች እውቅና ያገኙ ዘንድ የግድ ደም መፍሰስ አለበት። በአዲስ አበባ ደም ሳይፈስበት እውቅና ያገኘ መስጂድ በጣም ጥቂት ነው።
አዲሱ ስቴዲየም አጠገብ ያለው የጡሩ ሲና መስጂድ እንዲፈርስ የተፈለገበት ምክንያት ባቅራቢያው ካለው ቤተክርስቲያን እንዲርቅና የስቴዲየሙ ታዳሚ ዘንድ መስጂዱ እንዳይታይ ነው። አዎ መስጂድ አገሪቱን ማሳየት የሚሹበትን ገፅታ ያበላሻል። ሁሌ የማይሻሻል ትናንት ላይ የተቸነከረ ጭንቅላት። እነዚህ ህዝብ እንዲያገለግሉበት የተሰጣቸውን ወንበር ምን ታመጣላችሁ ንቀት የወለደው ውሳኔ እየወሰኑ ጠብ ያለሽ በዳቦ የሚሸልሉ አካላት ለከተማዋም፣ ለህዝቡም፣ ለዘመኑም የሚመጥኑ አይደሉም።
=
https://t.me/IbnuMunewor


በብዙ መስጂዶች ውስጥ የሴቶች መስገጃ አሰራር ቀድሞ የታሰበበትና የተጠና አይደለም። የኢማሙን ወይም የተከታዮችን ሁኔታ መመልከት ስለማይችሉ መከታተላቸው ላይ ችግር ሲፈጥር ያጋጥማል። ለምሳሌ እየተሰገደ እያለ መብራት ሲጠፋ ኢማሙ ምን ላይ እንዳለ እንኳ ማወቅ አይችሉም። ወይም ኢማሙ ተሳሳቶ የሆነ ነገር ቢቀይር ማወቅ አይችሉም። ለምሳሌ የመጀመሪያውን ተሸሁድ ረስቶ ቀጥ ብሎ ቢቆም የተቀመጠ መስሏቸው ተቀምጠው ሊጠብቁ ይችላሉ። ስለዚህ የመስጂድ አሰራር እንዲህ አይነት ችግሮችን ከግንዛቤ ያስገባ ሊሆን ይገባል።
ይህንን እንደ መነሻ ካነሳሁ በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ከሚገጥሙ ክስተቶች ውስጥ አንዱን አንስቼ ችግሩ ሲገጥም ምን ማድረግ እንደሚገባ ላስታውስ እወዳለሁ። እርሱም ሴቶች በሌላ ክፍል ውስጥ ሆነው የኢማሙን እንቅስቃሴ በማያዩበት ሁኔታ ኢማሙ ሱጁድ የሚወረድባቸው የቁርኣን አንቀፆችን ቢቀራና ሱጁድ የወረደ መስሏቸው ቢወርዱ እሱ ግን የወረደ ባይሆን፣ ወይም በተቃራኒው ሩኩዕ የወረደ መስሏቸው ሩኩዕ ላይ ሲጠብቁት እሱ ሱጁድ ወርዶ ኖሮ ቢመለስ ምን ማድረግ ነው ያለባቸው? ምላሹን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኙታል።

https://t.me/IbnuMunewor


Ⓜ️

የሸሪዓዉ ሙሉነትና የቢድዓ አደገኝነት ይፋ መሆን

Ⓜ️

በክቡር ሸይኽ ሙሐመድ ብን ሷሊህ አል’ዑሰይሚን ረሂመሁሏሁ ተዓላ

Ⓜ️

አዘጋጅ፡ ፈህድ ብን ናሲር ብን ኢብራሒም አስ’ሱለይማን

Ⓜ️

ትርጉም፡ አቡዓብዲልዓዚዝ / ዩሱፍ ብን አህመድ

Ⓜ️

#ክፍል_6


ዑመር ረድየላሁ አንሁ “ኒዕመቱል ቢድዓ ሀዚሂ” በማለት የፈለገው ከዚህ በፊት ተበታትኖ የነበረው ጀማዓ በአንድ ላይ በመሰባሰቡ መሆኑ ሊታወቅ ይገባዋል፡፡ ጀማዓው መሰባሰቡ ከዚህ በፊት ከነበረው የተበታተነ ጀማዓ የተለየ በመሆኑ ነው፡፡ በረመዷን የተራዊህ ሶላት በጀማዓ መሰገድ የተጀመረው በረሡል صلى الله عليه وسلمዘመን ነበር፡፡ ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ትክክለኛ ሐዲስ ዓኢሻ የሚከተለውን አስተላለፋለች፡-“የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلمለሶስት ሌሊቶች በሰዎች መካከል የተራዊህን ሶላት ሰገዱ፡፡ በአራተኛው ሌሊት ወደኋላ ቀሩ፡፡ ከዚያም የሚከተለውን ተናገሩ፡-
"إني خشيت أن تفرض عليكم فتعجزوا عنها"
“በእናንተ ላይ ፈርድ ይሆንባችሁና ያቅታችኋል ብየ ፈራሁ” (ቡኻሪ፡ 1129 ሙስሊም፡ 761)


በረመዷን የሌሊት ሶላትን በጀማዓ መቆም ከረሡል صلى الله عليه وسلمየተገኘ ሱና ነው፡፡ ዑመር ረድየላሁ አንሁ ቢድዓ ብሎ የጠራበት ምክንያት ረሡል صلى الله عليه وسلمየተራዊህን ሶላት ከቤት መስገድ ሲጀምሩ ሶሃቦች በመስጊድ ውስጥ ከፊሉ ብቻውን ፣ ከፊሎች ደግሞ ሁለት ሁለት እየሆኑ ተበታትነው ይሰግዱ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ የሙእሚኖች አሚር ዑመር ረድየላሁ አንሁ በረሡል صلى الله عليه وسلمዘመን ሲፈራ የነበረው ነገር በመወገዱ ሰዎችን በአንድ ኢማም ለመሰብሰብ አሰበ፡፡ ሶሃቦች የተራዊህን ሶላት በአንድ መሪ እንዲሰግዱ አደረገ፡፡ ከዚህ ቀደም ያልተሰባሰቡ ጀማዓዎች አሁን በአዲስ መልክ ስለተሰባሰቡ ይህችን ስብስባቸውን ቢድዓ በማለት ጠርቷታል፡፡ ይህች ቢድዓ ከመሰረቱ የተፈጠረች አዲስ ቢድዓ አይደለችም፡፡


ዑመር ረድየላሁ አንሁ የፈጠራት ቢድዓ አይደለችም፡፡ ምክንያቱም በረሡል صلى الله عليه وسلمዘመን ሲሰራ የነበረ ሱና ነው፡፡ ነገር ግን ረሡል صلى الله عليه وسلمፈርድ ይሆናል ብለው በመስጋት የተውትን ፣ ዑመር ረድየላሁ አንሁ በአዲስ መልኩ የጀመረው በመሆኑ ነው፡፡


በዚህ ህግ መሰረት የቢድዓ ሰዎች ቢድዓቸውን መልካም ለማድረግ ከዚህ የዑመር ረድየላሁ አንሁ ንግግር የሚያገኙት አንድም ክፍተት አይኖርም፡፡
አንድ ሰው የሚከተለውን ጥያቄ ሊያቀርብ ይችላል፡- በነብዩ صلى الله عليه وسلمዘመን የማይታወቁ ነገር ግን ሙስሊሙ ህብረተሰብ በስፋት እየሰራባቸው የሚገኙ አዳዲስ ነገሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ ፡- መድረሳ ፣ ኪታብ ማዘጋጀት እና የመሳሰሉ ነገሮች በረሡል صلى الله عليه وسلمዘመን አልነበሩም፡፡ እንደነዚህ ዓይነት ቢድዓዎችን ሙስሊሞች መልካም ብለው ተቀብለዋቸዋል ፤ እየሰሩባቸውም ይገኛል፡፡ ታዲያ ይህን ተግባርና “ኩሉ ቢድዓቲን ዶላላ” የሚለውን የረሡል صلى الله عليه وسلمንግግር እንዴት ማስታረቅ እንችላለን?

#መልስ፡- በተጨባጭ ካየነው ይህ ቢድዓ አይደለም፡፡ ይልቁንም ይህ ወደሸሪዓዊ ተግባራት የሚያዳርስ መልካም ተግባር ነው፡፡ ወደመልካም ነገር የሚያደርሱ ነገሮች ደግሞ እንደቦታውና እንደየዘመኑ ሊለያዩ ይችላሉ፡፡ በሸሪዓ የተረጋገጠው ህግና መርሆ ወደመልካም ግብ የሚያደርሱ ነገሮች የአላማውን ወይም የግቡን ብይን ይይዛሉ የሚል ነው፡፡ ህጋዊ የሆነ መዳረሻ እራሱ ህጋዊ ነው፡፡ ህጋዊ ያልሆኑ መዳረሻዎች ህጋዊ አይደሉም፡፡ ሀራም የሆነ መዳረሻም ሀራም ነው፡፡ መልካም ነገር ወደመጥፎ መዳረሻ የሚሆን ከሆነ እራሱ መጥፎ ይሆናል፡፡
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
“እነዚያንም ከአላህ ሌላ የሚገዙዋቸውን (ጣዖታትን) አትሳደቡ፡፡ ድንበርን በማለፍ ያለዕውቀት አላህን ይሰድባሉና፡፡” (አል አንዓም፡ 108)


አጋሪዎች የሚያመልኳቸውን ጣዖታት መሳደብ በቦታው ላይ ትክክለኛ ተግባር ነው፡፡ ነገር ግን እነርሱን በመሳደብ የአለማትን ጌታ የሚያሰድብ ከሆነ ጣዖቶችን መሳደብ ክልክል ነው፡፡ በዚህ ምክንያት የሙሽሪኮችን አማልክት መሳደቡ አላህን ወደመሳደብ የሚያደርስ ከሆነ ሀራም እና ክልክል ይሆናል ማለት ነው፡፡
መድረሳዎችም እንዲሁ ዒልም በኪታብ ጠርዞ ማዘጋጀት በነብዩ صلى الله عليه وسلمዘመን ያልነበረ አዲስ ነገር ቢሆንም ነገር ግን ወደመልካም የሚያደርስ ነው፡፡ ወደመልካም የሚያደርሱ ነገሮች ደግሞ የሚደረሱባቸውን አላማዎችና ግቦች ፍርድ ይሰጣሉ፡፡


በዚህ ምክንያት አንድ ሰው ሀራም ነገሮችን ለማስተማር መድረሳ እገነባለሁ ቢል የመድረሳው ግንባታ በራሱ ሀራም ይሆናል፡፡ አንድ ሰው ለሸሪዓዊ ትምህርት አላማ አድርጎ መድረሳ ቢገነባ ግንባታው መሽሩዕ ወይም ህጋዊ የሆነ ግንባታ ነው፡፡



ክፍል 7

ይቀጥላል

Ⓜ️
t.me/Abu_Reslann
t.me/Abu_Reslann
t.me/Abu_Reslann






🔺🔺መልስ🔺🔺
◾️ወሳኝ የዲን ጥያቄዎች
➖➖➖➖➖➖➖
🩸ክፍል አስር (10)
📖 አጠር ያለ መልስ ከተወሰነ ማብራሪያ ጋር አስቀምጡ
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
1️⃣✍️ "የላኢላሀ ኢለላህ" "لا إله إلا الله" ትክክለኛ ትርጉም ፃፋ⁉️
🔺መልስ
✅ ከአላህ ውጭ በሀቅ ሊገዙት የሚገባ አምላክ የለም ማለት ነው "لا معبود بحق إلا الله"
2️⃣✍️ የላኢላሀ ኢለላህ አርካኖች (ማእዘኖች) ስንት ናቸው⁉️ በዝርዝር ከነትርጉማቸው ጥቀሱ…
🔺መልስ
✅ የላኢላሀ ኢለላህ አርካኖች ሁለት ናቸው። እነሱም፦
①) ነፍይ "نفي" ነው። ይህም ማለት አምልኮትን ከአላህ ውጪ ካሉ አካላት ባጠቃላይ ውድቅ የምታደርግ ሲሆን
②) ኢስባት "اثبات"። የምንለው ነው። ይህም ማለት ኢባዳዎች በአጠቃላይ ለአላህ ማፅደቅን የሚያመላክት ነው።
3️⃣✍️ የላኢላሀ ኢለላህ ሸርጦች "شروط لا إله إلا الله" ስንት ናቸው⁉️ በዝርዝር አስቀምጡ……
🔺መልስ
✅ የላኢላሀኢለላህ ሸርጦች የተወሰኑ ኡለማዎች ሰባት መሆናቸውን ገልፀዋል ሌሎች ደሞ አንድ በመጨመር ስምንት አድርገዋቸዋል እነሱም፦
① العلم "እውቀት"
② الصدق "እውነተኝነት"
③ الإخلاص "ማጥራት"
④ الإقياد "ለትእዛዙ እጅና እግር መስጠት "
⑤ القبول "መቀበል"
⑥ المحبة "ውዴታ"
⑦ اليقين "እርግጠኝነት"
⑧ الكفر بما يعبد من دون الله "ከአላህ ውጪ በሚመለኩ ነገራቶች መካድ"
4️⃣✍️ ተውሂድ ማለት ምን ማለት ነው⁉️
🔺መልስ
✅ ትርጉሙ "افرد الله بالعبادة" "አላህን በአምልኮት መነጠል" ማለት ነው። አንዳንድ ኡለማዎች ከዚህ በተሻለ ሰፋ አድርገው ገልፀውታል إفراد الله بما يختص به من الربوبية" والألوهية والأسماء والصفات" አላህን ለሱ ብቻ በሆኑት ነገራቶች በጌትነት፣ በአምላክነቱና በስሞቹና በባህሪያቶቹ መነጠል ማለት ነው ብለዋል።
5️⃣✍️ የተውሂድ አይነቶች ስንት ናቸው⁉️ በዝርዝር አስቀምጡ………
🔺መልስ
✅ የተውሂድ አይነቶች ሶስት ናቸው። እነሱም
① توحيد الربوبية "በጌትነቱ ብቸኛ ማድረግ"
② توحيد الألوهية "በአምላክነቱ ብቸኛ ማድረግ"
③ توحيد الأسماء والصفات "በስሞቹና በባህሪዎቹ ብቸኛ ማድረግ"
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
↪️ ለተሳተፋችሁ በሙሉ አላህ ኸይር ምዳውን ይክፈላችሁ አላህ ጠቃሚውን እውቀት ይለግሳችሁ።
✅ መልሳችሁ በማስተያየት ስንት እንዳገኛችሁ እራሳችሁ በማረም ፃፋ!
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
➡️ የዛሬው መልእክቴ
💎ታላቁ ሰሀብይ አቡ ደርዳእ አላህ መልካም ስራው ይውደድለትና እንዲህ ብሏል።
✅ የዲን እውቀት ፈልጉ። ካልቻላችሁ የእውቀት ባለቤቶችን ውደዱ። እነሱን መውደድ ካልቻላችሁ ሌላው ቢቀር አትጥሉዋቸው።
📚(صفة الصفوة 240/1)


ሱፍያን አስ ሰውሪ ኑዛዜ ሲያደርጉ እንዲህ ይላሉ " የምተቀማመጠው ሰው በዱኒያ ጉዳይ ላይ እንድትብቃቃ ከማያስፈልግህ ነገር ችላ እንድትል የሚያደርግህ ይሁን በአኼራ ላይ ጉጉት እንዲኖርህ እነዚያን በተገናኙ ቁጥር ስለ ዱንያ ከሚያወሩ ሰዎች ጋር ከመቀማመጥ ተጠንቀቅ እነዚህ ሰዎች ዱንያህንም ቀልብህን ያበላሹብሀል ሞትን ማሰብን አብዛ ካለፈው ወንጀልህ ምህረት መጠየቅን አብዛ ለቀሪው እድሜህም የአላህን ጥበቃ ለምነው" ሂልየቱል አውሊያእ 7/82




Ⓜ️

የሸሪዓዉ ሙሉነትና የቢድዓ አደገኝነት ይፋ መሆን

Ⓜ️

በክቡር ሸይኽ ሙሐመድ ብን ሷሊህ አል’ዑሰይሚን ረሂመሁሏሁ ተዓላ

Ⓜ️

አዘጋጅ፡ ፈህድ ብን ናሲር ብን ኢብራሒም አስ’ሱለይማን

Ⓜ️

ትርጉም፡ አቡዓብዲልዓዚዝ / ዩሱፍ ብን አህመድ

Ⓜ️

#ክፍል_5


በአንድ ንግግር ላይ እነዚህ ሶስት ነገሮች - የተሟላ ታማኝነትና መልካም አላማ ፣ የተሟላ ማብራራትና በግልጽ መናገር ፣ የተሟላ እውቀት እና ግንዛቤ - ከተሟሉ የተነገረው ንግግር ትርጉሙን የሚጠቁም መሆኑን በትክክል ያስረዳል፡፡ ከዚህ አጠቃላይ ንግግር በኋላ ቢድዓን በሶስት መክፈል ይቻላልን? ወይም በአምስት መክፈል? በፍጹም ሊሆን አይችልም፡፡ መልካም ቢድዓ አለ ብለው የሚሞግቱት አንዳንድ ዑለሞች እንኳ ይህ አመለካከታቸው ከሁለት ነገር ያገለለ ሊሆን አይችልም፡-
1. ቢድዓ ሳይሆን ቢድዓ ነው ብለው መገመታቸው፡፡
2. የቢድዓን መጥፎነት ያለማወቅ፡፡


መልካም ቢድዓ ነው ብለው ለሚሞግቱለት ነገር ሁሉ መልሱ በዚህ ዓይነት ሊሆን ይገባል፡፡ በእጃችን “ኩሉ ቢድዓቲን ዶላለቲን” የሚል የተመዘዘ ሰይፍ አለ፡፡ ይህ ሰይፍ እያለ ለቢድዓ ባለቤቶች ቢድዓቸውን መልካም ለማድረግ ምንም አይነት እድል አይኖራቸውም፡፡
ይህ የተመዘዘ ሰይፍ የተሰራው በመልእክተኛው صلى الله عليه وسلمፋብሪካ ነው፡፡ የሰይፉን ማቴሪያል ያቀለጡት ረሡል صلى الله عليه وسلمናቸው፡፡ ይህን የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በቢድዓ መቃረን አይቻልም፡፡ ከዲን የሌለን ነገር መልካም ብሎ ሊለጥፍ አይችልም፡፡


በእርግጥ እውነታውን አላህ የገጠመው የሙእሚኖች አሚር ዑመር ኢብን አልኸጧብ ረድየላሁ አንሁ የተናገረውን ንግግር ስትሰሙ የሆነ ስሜት እንደሚሰማችሁ እገምታለሁ፡፡ በረመዷን የተራዊህ ሶላትን በጀማዓ እንዲያሰግዱ ዑበይ ብን ከዕብን እና ተሚም አድዳርይን አዘዘ፡፡ ሰዎች ኢማማቸውን ፊት ለፊት አድርገው ለጀማዓ ሶለት ወጡ ከዚያም ዑመር የሚከተለውን ንግግር ተናገረ፡-
"نعمت البدعة هذه والتي ينامون عنها أفضل من التي يقومون"
“ይህ ያማረ ቢድዓ ነው ከእርሷ (ከተራዊህ ሶላት) የተኙ ሰዎች ከሚቆሙት በላጭ ናቸውን?” (ቡኻሪ፡ 2010 ኢማሙ ማሊክ ፊ አል ሙወጦእ፡ 301)


ለዚህ ምላሹ ሁለት አይነት ነው፡
#አንደኛው፡- ማንኛውም ሰው የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلمየተናገሩትን ፣ ከነብዩ صلى الله عليه وسلمበኋላ በላጭ የሆነው አቡበክር ረድየላሁ አንሁ የተናገረውን ፣ ከነብዩ በኋላ በሁለተኛ ደረጃ በላጭ የሆነው ዑመር ረድየላሁ አንሁ የተናገረውን ፣ ከዚያም ከነብዩ በኋላ በሶስተኛ ደረጃ በላጭ የሆነው ዑስማን ረድየላሁ አንሁ የተናገረውን ፣ ከዚያም ከነብዩ በኋላ በአራተኛ ደረጃ በላጭ የሆነው ዓልይ ረድየላሁ አንሁ የተናገረውን በማንኛውም ሰው ንግግር መቃወም አይቻልም፡፡
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
“እነዚያም ትዕዛዙን የሚጥሱ መከራ እንዳትደርስባቸው ወይም አሳማሚ ቅጣት እንዳያገኛቸው ይጠንቀቁ፡፡” (አን ኑር፡ 63)


ኢማም አህመድ i የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
“ፊትና ማለት ምን እንደሆነ ታውቃለህ? ፊትና ማለት ሽርክ ነው፡፡ ምናልባት ከረሡል صلى الله عليه وسلمንግግር ከፊሉን ከመለሰ ከልቡ ውስጥ ጥመት ያርፍበትና ይጠፋል”
ኢብን ዓባስ ረድየላሁ አንሁማ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
"يوشك أن تنزل عليكم حجارة من السماء! أقول قال رسول الله صلى الله عليه
وسلم وتقولون قال أبو بكر وعمر"
“በእናንተ ላይ ከሰማይ ዲንጋይ ሊወርድ ይቀርባል፡፡ እኔ የአላህ መልእክተኛ ይህን ተናግረዋል እያልኩ እናንተ አቡበክር ዑመር ይህን ተናግረዋል ትላላችሁ፡፡” (አህመድ፡ 3121 ኢብኑ ተይሚያ ፊ መጅሙዕ፡20/215)

#ሁለተኛው፡- እኛ ፣ የሙእሚኖች አሚር የሆነው ዑመር ብን አልኸጧብ ረድየላሁ አንሁ ለአላህ ንግግር ፣ ለረሱል ንግግር ትልቅ ክብር የሚሰጥ መሆኑን በእርግጠኝነት እናውቃለን፡፡ ኡመር የአላህ ንግግር ሲነገረው ፈጥኖ ተመላሽ መሆኑን እናውቃለን፡፡


ታሪኩ ትክክል ከሆነ ዑመር ረድየላሁ አንሁ የመህር ገንዘብን በወሰነ ጊዜ አንዲት ሴት የዑመርን ውሳኔ በመቃወም የሚከተለውን የቁርኣን አንቀጽ እንዳነበበችና ዑመር ፈጥኖ ከነበረበት አቋም እንደተመለሰ ይታወቃል፡፡
“ከፊላችሁ ወደ ከፊሉ በእርግጥ የደረሰ ሲሆንና ከእናንተ ላይም (ሴቶች) የጠበቀ ኪዳንን የያዙባችሁ ሲሆኑ እንዴት ትወስዱታላችሁ!” (አን ኒሳእ፡ 21)


ዑመር ረድየላሁ አንሁ እንዲህ አይነት ባህሪ እያለው እንዴት የሰዎችን ሁሉ አለቃ ሙሀመድን صلى الله عليه وسلمንግግር ሊቃወም ይችላል? በፍጹም! ይህ ከእርሱ ባህሪ ጋር የሚሄድ አይደለም፡፡ “ኒዕመቱል ቢድዓ” ብሎ ሲናገር ይህ ቢድዓ “ኩሉ ቢድዓቲን ዶላላህ” (አዲስ ፈጠራ ሁሉ ጥመት ነው) በማለት ረሡል صلى الله عليه وسلمያወገዙትን ቢድዓ ፈልጎ እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ዑመር “ኒዕመቱል ቢድዓ “ በማለት የተናገረው “ኩሉ ቢድዓቲን ዶላላ” በሚለው የረሡል صلى الله عليه وسلمንግግር ውስጥ የሚካተት አይደለም፡፡

ክፍል 6

ይቀጥላል

Ⓜ️
t.me/Abu_Reslann
t.me/Abu_Reslann
t.me/Abu_Reslann


▶️ ጃይላኒ ማን ነው???

👆👆ዓጂብ ነው የሰለፍያ #ጠላት ነው ጀይላን።

ይደመጥ ይደመጥ! !!

የሼይኹን ንግግር ለመስማት 👇👇

https://t.me/abuUseyminabdurehman/2568

🎙 ትርጉም በአብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

https://t.me/abuUseyminabdurehman/2638


✅ ከሙብተዲእ ዘንዳ ኢልምን አትቅሰም
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
♻️ሸኽ ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ ብለዋል።
🔹ከስሜት ተከታይ
🔹ከሙብተዲእና
🔹አዲስ ፈጠራ ከሚያመጣ ሰው ጋር እውቀትን አትቅሰም።
💢ይልቁንስ መማር (እውቀትን መቅሰም) ያለብህ፦
🩸ከአህለሱናዎች
🩸ከሱና ኡለማዎችና
🩸ከትክክለኛ አቂዳ ባለቤቶች ነው።
💎ልክ መሀመድ ቢን ሲሪን አላህ ይዘንለትና እንዳለው፦
【ይህ እውቀት ዲን (ሀይማኖት) ነው። ስለዚህ ከማን መውሰድ እንዳለባችሁ ጠንቅቃችህ እወቁ】
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/1691
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/1691


Ⓜ️

የሸሪዓዉ ሙሉነትና የቢድዓ አደገኝነት ይፋ መሆን

Ⓜ️

በክቡር ሸይኽ ሙሐመድ ብን ሷሊህ አል’ዑሰይሚን ረሂመሁሏሁ ተዓላ

Ⓜ️

አዘጋጅ፡ ፈህድ ብን ናሲር ብን ኢብራሒም አስ’ሱለይማን

Ⓜ️

ትርጉም፡ አቡዓብዲልዓዚዝ / ዩሱፍ ብን አህመድ

Ⓜ️

#ክፍል_4

አስገራሚው ይህ ብቻ አይደለም ይህን አመለካከቱን የሚቃረንን ሰው ልክ አላህን ከፍጡራን ጋር እንደሚያመሳስል በመቁጠር ተለጣፊ ስም ማውጣቱ ነው፡፡


አንዳንድ ሰዎች ከአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلمጋር ምንም ግንኙነት የሌለውን አዲስ ፈጠራ በመፍጠር ልክ ረሡልን صلى الله عليه وسلمእንደሚወዱ፣ እርሳቸውን እንደሚያልቁ የሚሞግቱ ሰዎችም በጣም ያስገርማሉ! በዚህ ቢድዓቸው ሰዎች ካልተስማሟቸው ደግሞ ረሡልን صلى الله عليه وسلمእንደሚጠሉ አድርገው በማሰብ መጥፎ ስያሜዎችን የሚለጥፉ አሉ፡፡
በዲኑ ላይ አዳዲስ ፈጠራዎችን እየፈጠሩ “እኛ አላህንና ረሡልን صلى الله عليه وسلمአፍቃሪ ነን” የሚሉ ሰዎች ያለምንም ጥርጥር ከአላህና ከረሡል صلى الله عليه وسلمፊት እየተቀደሙ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡


አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
“እናንተ ያመናች ሆይ! በአላህና በመልክተኛው ፊት (ነፍሶቻችሁን) አታስቀድሙ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ሰሚ ዐዋቂ ነውና፡፡” (አል ሑጁራት፡ 1)


ወንድሞቸ ሆይ! እኔ በአላህ ስም እጠይቃችኋሁ! ለምጠይቃችሁ ጥያቄ ምላሻችሁ ከስሜታችሁ ፣ ከዝንባሌያችሁ ሳይሆን ከልባችሁ እንዲሆን እፈልጋለሁ፡፡ ከተጎታችነት ሳይሆን ፣ ከዲን ፍላጎት የመነጨ እንዲሆን እፈልጋለሁ፡፡


ከአላህ ዛት (አካል) ጋር የተያያዘም ይሁን ከአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلمጋር በዲን ላይ አዳዲስ ፈጠራዎችን እየፈጠሩ እኛ አላህን እያላቅን ረሡልን صلى الله عليه وسلمክብር እየሰጠን ነው በሚሉ ሰዎች ላይ ምንድን ነው የምትሉት? አላህን በማላቅ ፣ ረሡልን صلى الله عليه وسلمበማላቅ ላይ እነዚህ ሰዎች ተገቢዎች ናቸው ብላችሁ ታስባላችሁ? ወይስ እነዚያ የጣታቸውን ጫፍ ያክል ከአላህ ሸሪዓ የማያፈነግጡ ፣ በአላህ ሸሪዓ አምነናል ፣ እውነት ብለናል ፣ አላህ የነገረንን ሁሉ ተቀብለናል ፣ ሰምተናል ፣ ታዘናል ፣ የከለከለውን ተከልክለናል ፣ ከአላህና ከረሡል صلى الله عليه وسلمፊት መቀደምን ተከልክለናል ፣ በአላህ ዲን ውስጥ የሌለን ነገር የመጨመር መብት የለንም የሚሉት ናቸው አላህን በማላቅና በማክበር ተገቢዎቹ?! ከሁለቱ ለአላህና ለረሡል صلى الله عليه وسلمወዳጅ ፣ ለአላህ እና ለረሡል صلى الله عليه وسلمክብር የሚሰጡ የትኞቹ ናቸው?!
እኛ አምነናል ፣ በተነገረን ሁሉ እውነተ ብለናል ፣ ሰምተናል ፣ በታዘዝነው ሁሉ ታዘናል ፣ ባልታዘዝንበት ደግሞ ተቆጥበናል ተከልክለናል ፣ በሸሪዓ ምንም የሌለውን ነገር ከመጨመር ወይም በአላህ ዲን ላይ ምንም የሌለውን ነገር ከመጨመር ተከልክለናል የሚሉ ሰዎች የነፍሳቸውን ማንነት የተገነዘቡ ፣ የፈጣሪያቸውን መብት ያወቁ ፣ የአላህንም የረሡልንም صلى الله عليه وسلمክብርና ልቅና ያወቁ ፣ ለአላህና ለረሡል صلى الله عليه وسلم ያላቸውን ፍቅር ይፋ ያደረጉ መሆናቸው ምንም የሚያጠራጥር አይደለም፡፡


በአላህ ዲን ላይ በዓቂዳም ይሁን በንግግር ወይም በተግባር የሌለ ነገር የፈጠሩ የቢድዓ ሰዎች አላህን እና ረሡልን صلى الله عليه وسلمፍፁም አክባሪ ሊሆኑ አይችሉም፡፡
የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلمየሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-
"إياكم ومحدثات الأمور فإن كل محدثة بدعة، وكل بدعة ضلالة، وكل ضلالة في النار"
“እናንተንም አዳዲስ ፈጠራዎችንም አስጠነቅቃችኃለሁ ፤ ማንኛውም አዲስ ፈሊጥ ፈጠራ ነው፡፡ አዲስ ፈሊጥ ደግሞ ጥመት ነው ፤ ማንኛውም ጥመት ደግሞ የእሳት ነው፡፡” (አህመድ፡ 17144 አቡዳውድ፡ 4607 ቲርሚዚይ፡ 2676 ኢብኑ ማጀህ፡ 46 አድ ዳሪሚይ፡ 96)


“ኩሉ ቢድዓቲን” ባለው ቃል ውስጥ የምትገኘውን “ኩል” ሁሉን የምታጠቃልል ቃል መሆኗን ያውቃሉ፡፡ ይህን ቃል የተናገሩት ደግሞ የዓረብኛን ቃል አጣርተው የሚያውቁ ፣ ለህብረተሰቡ ታማኝና መካሪ የሆኑት የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلمናቸው፡፡
ስለዚህ ነብዩ “ صلى الله عليه وسلمኩሉ ቢድዓቲን ዶላላህ” (ሁሉም አዲስ ፈሊጥ ጥመት ነው) ብለው ሲናገሩ የሚሉትን ያውቃሉ፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ንግግሩ የመነጨው ህዝብን በታማኝነት እና በተሟላ ሁኔታ መካሪ ከሆኑት የአላህ መልእክተኛ ነው፡፡

ክፍል 5

ይቀጥላል

Ⓜ️
t.me/Abu_Reslann
t.me/Abu_Reslann
t.me/Abu_Reslann
Ⓜ️


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የፈጅር (የሱብሕ) ሶላት ትሩፋቶች እና ፈጅርን አለመስገድ ያለው አደጋ
~~~ ~~~ ~~~~ ~~~ ~
1. ፈጅርን ስገድና በአላህ ጥበቃ ስር ሁን፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ሱብሕን የሰገደ በአላህ ጥበቃ ስር ነው” ብለዋል፡፡ [ሙስሊም]
2. ፈጅርን ስገድ ሌሊቱን በሶላት እንደቆምክ ይቆጠርልሃልና፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ዒሻእን በጀማዐህ የሰገደ ግማሽ ሌሊትን በሶላት እንደቆመ ነው፡፡ ሱብሕን በጀማዐህ የሰገደ ደግሞ ሌሊቱን በሙሉ እንደቆመ ነው” ይላሉ፡፡ [ሙስሊም]
3. ሱብሕን ስገድ እራስህን ከሙናፊቆች መገለጫ አፅዳ፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “በሙናፊቆች ላይ እንደፈጀር እና ዒሻእ ሶላት የሚከብድ የለም” ይላሉ፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
4. ፈጅርን ስገድ ለጭንቅ ቀን ብርሃን ይሆንሃልና፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “በጨለማዎች ወደ መስጂዶች የሚጓዙትን በቂያማህ ቀን ሙሉ በሆነ ብርሃን አብስራቸው” ይላሉ፡፡ [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 570]
5. ሱብሕን ስገድ መላእክት ይመሰክሩልሃል፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡- “በናንተ ውስጥ የሌሊት መላእክትና የቀን መላእክት ይተካካሉ፡፡ በፈጅር ሶላት እና በዐስር ሶላት ላይ ይሰባሰባሉ፡፡ ከዚያም እነዚያ በናንተ ዘንድ ያደሩት (ወደ ሰማይ) ይወጣሉ፡፡ ይህኔም ጌታቸው በነሱ ሁኔታ አዋቂ ሆኖ ሳለ “ባሪያዎቼን በምን ሁኔታ ላይ ተዋቸኋቸው?” ሲል ይጠይቃቸዋል፡፡ “እነሱ እየሰገዱ ነው የተውናቸው፡፡ እየሰገዱም ነው የመጣናቸው” ይላሉ፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
6. ሱብሕን ስገድ ሙሉ የሐጅና የዑምራን አጅር እፈስ፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “የማለዳን ሶላት በጀማዐ የሰገደ ከዚያም ፀሀይ እስከሚወጣ ድረስ አላህን እያወሳ የተቀመጠ እና ከዚያም ሁለት ረከዐ ሶላት የሰገደ ልክ እንደ ሐጅና ዑምራ አጅር አለው፡፡ ሙሉ! ሙሉ ! ሙሉ!” ይላሉ፡፡ [አስሶሒሐህ፡ 3403]
7. ፈጅርን ስገድ በአለም ላይ ካሉ ፀጋዎች ሁሉ በላጭ የሆነ ፀጋ የምትጎናፀፍበት እድል ታገኛለህና፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “የፈጅር ሱንናህ (ከፈርዱ በፊት የምትሰገደዋ ትርፍ 2 ረከዐ ሶላት) ከዱንያ እና በውስጧ ካለ ሁሉ በላጭ ነች” ይላሉ፡፡ [ሙስሊም]
8. ፈጅርን ስገድ ከጀሀነም መትረፊያ ጀነትን መጎናፀፊያ ብስራትን ታገኛለህና፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ፀሀይ ከመውጣቷ እና ከመግባቷ በፊት የሰገደ አንድም ሰው እሳት አይገባም” ይላሉ፡፡[ሙስሊም] እነዚህ ሶላቶች ፈጅርና ዐስር ናቸው፡፡ በሌላም ሐዲሥ “ሁለት ብርዳማ ሶላቶችን የሰገደ ጀነትን ይገባል” ብለዋል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
9. ፈጅርን ስገድ ከፀጋዎች ሁሉ በላጭ ፀጋ የሆነውን የላቀውን ጌታ መመልከትን ትታደላለህና፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “እናንተ ይህን ጨረቃ እንደምታዩት ጌታችሁን ታያላችሁ፡፡ እሱን በማየትም አትቸጋገሩም፡፡ ፀሀይ ከመውጣቷና ከመግባቷ በፊት ባለ ሶላት አለመረታት ከቻላችሁ አድርጉት (ስገዱ)” ይላሉ፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
10. ፈጅርን ስገድ ጥሩ ነፍስ ይዘህ አንግተህ ንቁ ሆነህ ትውላለህ፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
ተጠንቀቅ!
1. የፈጅርን ሶላት ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ ከፈጅር ሶላት መሳነፍ አደገኛ የሆነ የሙናፊቆች ምልክት ነውና!! [ቡኻሪና ሙስሊም]
2. የፈጅርን ሶላት ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ የሸይጣን መፀዳጃ አትሁን፡፡ በአንድ ወቅት ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ እስከሚነጋ ድረስ ሌሊቱን ስለሚተኛ ሰው ተወራ፡፡ ይህኔ እሳቸው እንዲህ አሉ፡- “ያ በጆሮዎቹ ውስጥ ሸይጣን ሽንቱን የሸናበት ሰው ነው!” አሉ፡፡ አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል፡፡ [ሶሒሑትተርጊብ ወትተርሂብ፡ 644]
3. የፈጅርን ሶላት ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ ያለበለዚያ የሸይጣን ወጥመድ ሲሳይ ትሆናለህ፡፡ ቀንህን ሙሉ ድብርት ይጫጫንሃል፣ ንቃት ይቀልሃል፡፡ ፈጅር ላይ ተነስቶ ውዱእ አድርጎ ያልሰገደ ሰው ቆሻሻ ነፍስ ይዞ እንደሚያነጋና ስንፍና እንደሚጫጫነው ተናግረዋል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
4. ፈጅርን ስገድ ያለበለዚያ በቀብርህ ውስጥ እስከ እለተ ቂያማ የሚዘልቅ ዘግናኝ ስቃይ ትሰቃያላህ፡፡ ከነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንደተላለፈው አንድ ሰው ተንጋሎ ሌላው ካጠገቡ ቋጥኝ ይዞ በመቆም እራሱን ይደቁሰዋል፡፡ ድንጋዩ ተንከባሎ ሲሄድም እሱን አምጥቶ እስከሚመለስ ድረስ እራሱ እንደነበር ይመለሳል፡፡ ከዚያም እንደ መጀመሪያው ይሰራበታል፡፡ ቂያማ እስከሚቆም ድረስም በዚሁ መልኩ ይቀጥላል፡፡ ይህን በዚህ መልኩ የሚሰቃየውን ሰውየ ምንነት ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጂብሪል ሲጠይቁት “ይሄ ቁርኣንን ይዞ ፊት የሚነሳው ከግዴታ ሶላትም የሚተኛ ነው” አላቸው፡፡

ወንድሜ ሆይ! ከፈጅር ሶላት አትዘናጋ፡፡ ወቅቱን ጠብቀህ እንድትሰግድ የሚያግዝህን ብልሃትም ተጠቀም፡፡
1. በጊዜ ተኛ፡፡ የምሽት ወሬ ይቅር፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከዒሻ በፊት እንቅልፍ፣ (ከዒሻ) በኋላ ደግሞ ወሬ ይጠሉ ነበር፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
2. ቀኑን በወንጀል ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ ወንጀል ከኸይር ስራ ያቅባል፡፡ በሌላ በኩል ለኸይር ስራ ትጋ፡፡ ኢስላማዊ የመኝታ ስርኣቱን ጠብቅ፡፡ የኸይር ስራ አንድ ሽልማቱ ለሌላ ኸይር ስራ መታደል ነውና፡፡
3. ማታ ከመተኛትህ በፊት ለፈጅር ለመነሳት ቁርጠኛ ውሳኔ አድርግ፡፡ ረጅም ጉዞ ወይም አሳሳቢ ጉዳይ ቢኖርብህ ያለ ማንም አጋዥ ምናልባትም ያለአላርም እየነቃህ ለሶላት ሲሆን መዘናጋትህ ስለእውነት ከባድ የሞራል ልሽቀት ነው፡፡
4. ማንቂያ ደወል (አላርም) ተጠቀም፡፡ ምናልባት ሳይታወቅህ አጥፍቶ የመተኛት አጉል ባህሪ ካለብህ ትንሽ ራቅ አድርገህ አስቀምጠው፡፡
5. በሰአቱ ነቅተህ ከተጫጫነህ “ትንሽ ተኛ” ለሚሉ ሸይጣን እና ነፍስያ ሸንጋይ ጉትጎታ እድል አትስጥ፡፡ መነሳትህ ያለውን ዋጋ፣ መተኛትህ ያለውን አደጋ ላፍታ አስብ፡፡ ብትነሳ 50 ዶላር ይሰጣል ቢባል የሚኖርህን ንቃት ቃኝና እራስህን ታዘብ፡፡ ፈርዱ ቀርቶ ትርፍ የሆነችዋ የፈጅር 2 ረከዐ እንኳን ከዱንያ ፀጋ ሁሉ በላጭ እንደሆነች እራስህን አስታውስ፡፡
6. በመልካም የሚያግዝ ጓደኛ ወይም የህይወት አጋር ካለህም እሰየው፣ ተጠቀምበት፡፡

(ኢብኑ ሙነወር፣ ሃምሌ 21/2007)
https://t.me/IbnuMunewor


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፦
"صَدَقَتُكَ عَلَى المِسْكِينِ صَدَقَةٌ، وَعَلَى ذِي الرَّحِمِ صَدَقَةٌ وَصِلَةٌ"

"ለምስኪን ሶደቃ መስጠትህ ሶደቃ ነው። ለዘመድ ሲሆን ግን ሶደቃ እና ዝምድና መቀጠል ነው።"
📓 [መጀመዑል ፈታዋ፡ 13/43]
.
.
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor

20 last posts shown.

429

subscribers
Channel statistics