የ1997 የኮንዶሚኒየም ቤት ተመዝጋቢዎች አቤቱታ በ15 ቀናት ውስጥ መፍትሔ ካልተሰጠው ለፓርላማ እንደሚቀርብ ተገለጸ
የጋራ መኖሪያ (ኮንዶሚኒየም) ቤት ለማግኝት ተመዝግበው ገንዝብ በባንክ ሲቆጥቡ የነበሩና እስካሁን ቤቱን ያላገኙ የ1997 ዓ.ም. ተመዝጋቢዎች አቤቱታ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምላሽ ካልሰጠበት፣ በ15 ቀናት ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚያቀርበው የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አስታወቀ፡፡
ለሃያ ዓመታት ያህል ቤት ይደርሰናል ብለው እየጠበቁ ቢሆንም፣ መንግሥት ምላሽ አልሰጠንም ያሉ ቢያንስ 67 ሰዎችን አቤቱታ ተቀብሎ እየመረመረ መሆኑን የገለጹት፣ የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የሕግና አስተዳደር በደል ምርመራ መሪ ሥራ አፈጻሚ አቶ መንግሥቱ ቀና ናቸው፡፡
‹‹የቀረበውን አቤቱታ ተቀብለን የከተማ አስተዳደሩን ማብራሪያ ጠይቀናል፡፡ ምላሽ ካልመጣ ተቋሙ የሚወስደው ዕርምጃ ይኖራል፤›› ያሉት ኃላፊው፣ ‹‹በ1997 ዓ.ም. ተመዝግበን ቤት ሳይደርሰን ለሌሎች ተሰጥቷል፤›› በሚል ተደራጅተው ጠይቀዋል፣ ‹‹እኛም ጥያቄ አቅርበናል፡፡ ነገር ግን የከተማ አስተዳደሩ እስካሁን መልስ አልሰጠንም፤›› ብለዋል፡፡
የከተማ አስተዳድሩ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በቅርቡ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ተወካዮች ጋር በነበረ ውይይት ባደረጉት ንግግር፣ ከዚህ በፊት በ2015 ዓ.ም. በተላለፉት ቤቶች የ1997 ዓ.ም. ቆጣቢዎች ሁሉም ዕጣ እንዲወጣላቸው መደረጉንና ለተመዘገቡት ሁሉ ቤት ተሰጥቶ መጠናቀቁን ገልጸው ነበር፡፡
ይሁን እንጂ የሕዝብ ዋና ዕንባ ጠባቂ ተቋም ግን በዚህ ሁኔታ ከከተማ አስተዳደሩ የደረሰው ምላሽ እንደሌለ የገለጹት አቶ መንግሥቱ፣ ለረዥም ጊዜ ጠብቀው ምላሽ ያልተሰጣቸውን ሰዎች አቤቱታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማቅረብ የመጨረሻ ዕልባት እንዲያገኝ ይደረጋል ብለዋል፡፡
በ1997 ዓ.ም. የቤት ምዝገባ በርካቶች ተመዝግበው ለሃያ ዓመታት ሲቆጥቡ መቆየታቸውን በመግለጽ፣ መንግሥት የተሠሩትን ቤቶችን ለአርሶ አደር ልጆች፣ ለፖለቲካ ሹመኞችና ለተለያዩ ግለሰቦች እየሰጠ ነው በማለት ቅሬታ ሲያቀርቡ ነበር፡፡
ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባና በሸገር ከተማ ቤታቸው የፈረሰባቸው ነዋሪዎች ባቀረቡት አቤቱታ ካሳና ተለዋጭ ቦታ እንዲሰጥ በተደጋጋሚ ጥያቄ ሲያቀርብ እንደነበር መረጃ የደረሰው ዕንባ ጠባቂ ተቋም፣ አሁን በመሀል አዲስ አበባ ከሚከናወነው የኮሪደር ልማት ጋር በተገናኘ የደረሰው የሕዝብ አቤቱታ የለም ሲሉ አቶ መንግሥቱ አስረድተዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ወደ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በብዛት እየቀረቡ ያሉ አቤቱታዎች የሥራ ስንብት፣ የመሬት አገልግሎት፣ የጡረታ መብትና የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን የተመለከቱ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
Via : wasu mohammed
@Addis_Reporter