በሬክተር ስኬል 5.8 የደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ዛሬ ለሊት ተከሰተ
በኢትዮጵያ በሬክተር ስኬል 5.8 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ፤ ከለሊቱ 9:52 መድረሱን የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መስሪያ ቤት አስታወቀ። ሰሞኑን ሲከሰቱ ከነበሩት የመሬት መንቀጥቀጦች ዘለግ ላሉ ሰከንዶች የቆየው ርዕደ መሬት፤ ንዝረቱ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች ተሰምቷል።
የለሊቱ የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተው በአፋር ክልል መሆኑን የአውሮፓ ሜዲትራንያን ሴይስሞሎጂ ማዕከል (EMSC) ተቋም መረጃ ያሳያል። ርዕደ መሬቱ የተከሰተበት ቦታ ከአቦምሳ ከተማ 56 ኪሎ ሜትር እንዲሁም ከአዳማ ከተማ 146 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ መሆኑን የአሜሪካ እና የአውሮፓ ተቋማት ገልጸዋል።
የአውሮፓው የምርምር ማዕከል የለሊቱን የመሬት መንቀጥቀጥ የልኬት መጠን 5.6 እንደሆነ በመጀመሪያ ገልጾ የነበረ ቢሆንም ከቆይታ በኋላ ወደ 5.8 ከፍ አድርጎታል። የመሬት መንቀጥቀጡ መጠን ከሰሞኑ ከደረሱት ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።
ከዚህ ክስተት ስምንት ሰዓት አስቀድሞ በሬክተር ስኬል 5.5 የደረሰ ርዕደ መሬት ተከስቶ ነበር። አርብ አመሻሽ 11 ሰዓት ተኩል ገደማ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥም እንደዚሁ በሬክተር ስኬል ልኬት አምስትን የተሻገረ ነበር። በዚህ ጊዜ የተመዘገበው የርዕደ መሬት መጠን 5.2 ነው።
@Addis_Reporter