🇳🇬 በሰሜን ናይጄሪያ ነዳጅ ጫኝ ተሸከርካሪ ፈንድቶ ከ60 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተሰማ
በናይጄሪያ ኒጀር ግዛት የነዳጅ ጫኝ ታንከር ሹፌር ተሽከርካሪውን መቆጣጠር ባለመቻሉ መስቀለኛ መንገድ ላይ እንደተገለበጠ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ነዳጁ መንገዱ ላይ መፍሰሱን ተከትሎ በአካባቢው የነበሩ በርካታ ነዋሪዎች ነዳጁን ለመሰብሰብ ሲሞክሩ በድንገት ፍንዳታው ተከስቷል።
እንደ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ፤ እሳቱ በአቅራቢያ የነበሩ መኪኖች፣ ሞተር ሳይክሎች እና ሱቆችን በእሳት ነበልባል ገርፏል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር መሐመድ ኡማሩ ባጎ በክስተቱ ማዘናቸውን ገልፀው ለተጎጂ ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተዋል።
@Addis_Reporter