እስራኤል ዞልፋካር በተሰኘ ተምዛግዛጊ ሚሳኤል ተመታች
በኢራን የሚደገፈው የየመኑ ሃውቲ ታጣቂ ቡድን የሚያደርስባት ዙሪያ መለስ ጥቃት ያንገሸገሻት ኢስራኤል፣ አሁን ይባስ ብሎ የየመን መንገስት ጥቃት ስለባ ሆናለች እየተባለ ነው፡፡
በዚህም የየመን መንግስት ጦር በቴል አቪቭ ከባድ የባላስቲክ ሚሳኤል ጥቃት መፈጸሙ እየሩሳለምን ክው አድርጓታል፡፡
የየመን ጦር ሃይል ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጄኔራል ያህያ ሳሬ እንደተናገሩት፣ የየመን ጦር የእስራኤል መንግስት መከላከያ ሚኒስቴር ግቢን፣ ዞልፋካር በተሰኘ ተምዛግዛጊ ሚሳኤል መምታቱን እስታውቀዋል፡፡
የየመን ጦር ሃይል ቃል አቀባይ ባወጣው መግለጫ እንዳመላከቱት፣ “በቴላቪቭ የሚገኘውን የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር፣ በሚሳኤል ጥቃት ኢላማ አድርገናል” ብለዋል።
ኦፕሬሽኑ የተካሄደው 'ዞልፋካር' በተሰኘ ባላስቲክ ሚሳኤል ሲሆን፣ ጥቃቱ በጥንቃቄ የተፈጸመ እና ግቡን የመታ ትክክለኛ ድብደባ ነው ሲሉም አክለዋል፡፡
የጠላት መከላከያ ስርአቶች ሊመከቱት ያልቻሉትን፣ ከባድ ጥቃት ፈጽመናል ሲሉ ቃል አቀባዩ ፎክረዋል።
@Addis_Reporter